“መንግስት በሊቢያ በዜጎቻችን ላይ የተፈጸመው አሰቃቂ ድርጊት ከተሰማበት ጊዜ ጀምሮ ሰፋፊ ሰራዎችን ለመስራት በመንቀሳቀስ ላይ መሆኑን የጠቀሱት ዶ/ር ቴድሮስ በቤንጋዚ ያሉ ኢትዮጵያውያን በግብጽ መንግሰት በኩል፣ ትሪፖሊ ያሉትን ደግሞ ከሱዳን መንግሰት ጋር በመተባበር ከሊቢያ ለማውጣት ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።” የሚል በዶር ቴድሮስ አዳኖም ፌስ ቡክ ገጽ ላይ አነበብኩ። የዝግጅቱን ዝርዝር ባላውቅም ዝግጅቶች እየተደረጉ ሊሆኑ እንደሚችኑ ማንበቤ ትንሽም ቢሆን ደስታ ሰጥቶኛል።
በሊቢያ ከአሥራ አምስት በላይ የሚሆኑ ኃይላት አሉ። እነዚህ ኃይላት እርስ በርስ እየተቀናጁ በዋናነት ሦስት ቡድኖች ተፈጥረዋል። እነርሱም፡
መቀመጫዉን ቱብሩክ (ወደ ግብጽ ድንብር የተጠጋች ከተማ) ያደረገው በጀነራል ካሊፋ ሃፍተር የሚመራው ስብስብ ነው። ይህ ስብስብ ደርና ከምትባለዋና አይሰስ ከሚቆጣጠራት ከተማ በስተቀር፣ አብዛኛዉ ቤንጋዚ ጨምሮ፣ እስከ ግብጽ ድንበር ድረስ ያሉትን ግዛቶች ይቆጣጠራል። ይህ ስብስብ በአለም አቀፍ ማህበረሰብ እንደ ሕጋዊ የሊቢያ መንግስት የሚቆጠር ሲሆን ከግብጽ መንግስት ጋር የቀረበ ግንኙነት አለው።
መቀመጫው ሚስራታ የሆነውና ትሪፖሊን የሚቆጣጠረው፣ Libyan Dawn (የሊቢያ ጎህ) የሚባለው ስብስብ ነው። ይህ ስብስብ በዋናነት አይሰስን ሳይጨመር፣ ከሙስሊም ብራዘር ሁድ ጋር ግንኙነት ያላቸውን በርካታ እስላማዊ የሆኑ ድርጅቶችን ያሰባሰበ ነው። እንድ ቱርክ፣ ካታር ያሉ አገሮች በዚህ ስብስብ ላይ ተጽእኖ ማሳደር እንደሚችሉ ይነገራል:
ሶስተኛው አሸባሪው የአይሰስ ቡድን ነው። በሚስራታና በቤንጋዚ መካከል የምትገኘው የሲርት ከተማን እና አካባቢዉ ይቆጣጠራል። በቤንጋዚ እና በቱብሩክ መካከልም ያለቿን የደርና ከተማ ዉስጥም አለ። በዚሁ በደርና ከተማም ነው የግብጽ ክርስቲያኖችችን አይሰስ አንገታቸውን ያቀላው። በተጨማሪ በደቡብ ሊቢያም በቻድና በኒጄር ድንበር አካባቢም እንደሚንቀሳቀስ ይነገራል።
በሊቢያ ያለው የኃይል አሰላለፍ ይህ ሆን እንዳለ፣ ኢትዮጵያዉያንን ለማስወጣት የግደታ ከጀነራል ቡድን እንዲሁም ከሊቢያ ዶዉን ባለስልጣናት ጋር መነጋገር ያስፈልጋል።
የኢትዮጵያ መንግስት ዝግጅት፣ ትሪፖሊ ያሉትንን በሱዳን በኩል፣ ቤንጋዝዚ ያሉትን ደግሞ በግብጽ በኩል በማስወጣት ላይ ያጠነጠነ ሳይሆን እንዳልቀረ አስባለሁ። በዚህ ጉዳይ ላይ ትልቅ ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገባ በጣም አንገብጋቢ ጉዳዮችን እንዳነሣ ይፈቀድልልን።
ኢትዮጵያዉያን በቤንጋዚ፣ በሚስራታና በትሪፖሊ በብዛት አሉ። በመሆኑምም ከጀነራል ካሊፋ ሃፍተር ካሊፋ ሃፍተር እንዲሁም ከሊቢያ ዶውን ባለስልጣናት ጋር በተናጥል በመነጋገር፣ ከቻያና፣ ወይም ግርሪክ፣ አሊያም ጣሊያን ትላልቅ ቻርተር መርከቦችን በመከራየት ከሶስቱ ወደቦች በመሰብሰብ ወደ ግብጽ እንዲገቡ ማድረጉ በጣም የተሻለ አማራጭ ነው።
በባስ ጭኖ ለማስወጣት ከታሰበ ደግሞ፣ ቤንጋዚ ያሉትን ወደ ግብጽ ለማምጣት የታሰበው መልካም ሐሳብ ነው። ሆኖም መጠነኛም ቢሆን፣ ደርና አካባቢ አይሰሶች ሊኖሩ ስለሚችሉ፣ በደርና በኩል ሳይሆን በአጅዳቢያ በኩል መሆን ይኖርበታል።
ከትሪፖሊ ወደ ሱዳን ወገኖቻችንን ለማስወጣት የታስበው ፈጽሞ ሊሆን የሚገባው አይደለም። ይህ ከግምት ዉስጥ መግባቱ ራሱ አስደንጋጭ ነው: አንደኛ ከትሪፖሊ ሱዳን ድንበር ቢያንስ 1920 ኪሎሜትር ረቅት ነው ያለው። ሁለተኛ እልም ያለ በረሃ ነው። ሶስተኛ ቢያንስ 4 እስከ 5 ቀን ይፈጃል። ሕጻናትት አሉ። ሴቶችን፣ ነፍሰ ጡሮች አሉ። አራተኛና ትልቁ ነጥብ ደግሞ አይሰስ በዚያ መንገድ ላይ የመንቀሳቀሱ እድል በጣም ከፍ ያለ መሆኑ ነው። በቅርቡ የተገደሉት ወገኖቻችን ከሱዳን ወደ ትሪፖሊ ሲሄዱ አይሰስ ይዟቸው ነው።
በሱዳን በኩል ወገኖቻችችንን ለማስወጣት ማቀድ፣ እንደገና ወገኖቻችን ለአደጋ ማጋለጥ ነው። ይሄንን እቅድ የኢትዮጵያ መንግስትት መሠረዝ አለበት የሚል አቋም ነው ያለኝ። የመሠረዝ ፍላጎት ከሌለው፣ ኢትዮጵያዉን በአገር ዉስጥና ከአለም ዙሪያ ሁሉ ጠንካራ ተቃዋሞ ማሰማት ይኖርብናል። እንደገና ወገኖቻችን አይሰስ ሊንቀሳቀስባቸው ወደ ሚችልባቸው ቦታዎች መወሰድ የለባቸውም።
የሚሻለው፣ የኢትዮጵያ መንግስት ከሱዳን ጋር ሳይሆን ከቱኒዚያ መንግስት ጋር በመነጋገር፣ ከሚስራታና ትሪፖሊ ያሉ ወገኖቻችን በቀጥታ ሳብራታና ዙዋራ በሚባሉ ከተሞች አልፎ፣ መዲኒን ወደ ተባለችዋ የቱኒዚያ ከተማ እንዲሄዱ ማድረግ ነው። ርቀቱ 800 ኪሎሜተር ብቻ ሲሆን በ3 ሰዓት ዉስጥ ይገባል፡
No comments:
Post a Comment