የኢትዮጵያ መንግስትን በጦር ሀይል ለመጣል ሚታገሉት “የኢትዮጵያ የተባበሩት አርበኞች ግንባር” በደቡብ ሱዳን ግጭት ውስጥ ከፕሬዘዳንት ሳልቫኪር ሀይል ጎን ተሰልፎ የተቃዋሚውን የሪክ ማቻርን ሀይሎች ይወጋል በሚል የቀረበባቸውን ክስ ውድቅ አደረጉ.
በሪክ ማቻር የሚመሩት የደቡብ ሱዳን ተቃዋሚዎች በቅርቡ እንዳስታወቁት ከሆነ በምእራብ ኢትዮጵያ ጋምቤላ ክልል ሚንቀሳቀሰውና በቀድሞው የአካባቢው አስተዳዳሪ በሆኑት በቶዋት ፓልቻይ የሚመራው የኢትዮጵያ አርበኞች ግንባር ኢትዮጵያን ለመውጋት በደቡብ ሱዳን መን ግስት ስልጠና ይሰጠዋል የመሳሪያና የቴክኒክ ድጋፍ ይደረግለታል የሚል ክስ ሲያቀርቡበት ቆይተዋል.
ቡድኑ ከዚህ በተጨማሪም በደቡብ ሱዳን ግጭት ውስጥ ራሱን አስገብቶ ከሳልቫኪር ሀይል ጋር በመወገን እኛን በጦር ይወጋል ሲሉም አማጺያኑ ጨምረው ይከሳሉ.
ይህን ተከትሎ ከኢትዮጵያ መንግስት በኩል የተሰጠ አስተያየት አለመኖሩን የገለጸው ሱዳን ትሪብዩን የወሬ ምንጭ የአርበኞች ግንባሩ ሀላፊ ቶዋት ፓልቻይ በሰጡት ምላሽ የተባለው ክስ መሰረተ ቢስ እንደሆነ ተናግረዋል ሲል ዘግቧል.
ቶዋት ፓልቻይ ለሱዳን ትሪብዩን በላኩት ደብዳቤ እንዳረጋገጡት ከሆነ ቡድናቸው በተጠለለበት ሀገር የውስጥ ጉዳይ ምንም አይነት ጣልቃ ገብነት እንደማያደርግና የተባለው በሙሉ ተራ ፕሮፓጋንዳ መሆኑን ነው የተናገሩት
No comments:
Post a Comment