የቢቢሲው ሌራቶ ምቤሌ ዘገባውን ሲጀምር በተዘዋወርንባቸው የአዲስ አበባ መንገዶች ሁሉ ካሜራችንን ስናወጣና ፎቶ ልናነሳ ስንሞክር ጠጋ ብለው ምን እንርዳችሁ የሚሉ ኢትዮጵያዊያንን ብዙ አግኝተናል ይላል.ይሁን እንጂ ስለአንዳንድ ነገሮች እንጠይቃችሁ ብለን ስንጠጋ ግን ይገጥመን የነበረው ዝምታ ነው የሚለው ዘጋቢው ኢትዮጵያዊያን ሀሳባቸውን በውስጣቸው ማስቀረት እንደሚመርጡ ይናገራል.
በቅርብ አመታት በሀገሪቱ ስለመጡ ለውጦች የሚያትት ዘገባ ለመስራት በአዲስ አበባ ቀረጻ አድርገን ወደ ደቡብ አፍሪካ ሳመራ ከአንዲት ኢትዮጵያዊት ሴት ወ / ሮ ጋር ተገናኘሁ የሚለው ዘጋቢው በጉዞአቸው ስላወሯቸው አንዳንድ የሀገሪቱን ሁኔታዎች ስለተመለከቱ ጉዳዮች ይተርክልናል. ደግ ሲል ያሞገሳቸውን ሴት ወ / ሮ ጋዜጠኛው ስለናይጄሪያው የቅርብ ጊዜ ምስጉን ምርጫ አንስቶ እንዳጫወታቸው እሱን አስታኮም በመጪው ግንቦት በሚካሄደው የኢትዮጵያ ምርጫ ላይም ስኬታማ የምርጫ አፈጻጸም ይኖራል ብሎ ተስፋ እንደሚያደርግ ለጥያቄ የሚጋብዝ ሀሳብ እንዳነሳላቸው ይናገራል.
ሴትየዋ ለዚህ አስተያየቱ የምርጫው ውጤት ከወዲሁ የተበላ እቁብ እንደሆነ ሹክ እንዳሉት የሚገልጸው ጋዜጠኛው ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ በሀገሪቱ ፈጣን እድገት እንዲመዘገብ ማድረጉን በማስታወስ ህዝቡም በዚህ የተነሳ እርሱን ሊመርጥ እንደሚችል ሀሳብ መሰንዘሩን ይናገራል. ለዚህ ሀሳቡ ግን ከሴትየዋ የቱ እድገት የሚል አይነት የፌዝ ምላሽ ማግኘቱን ሚናገረው ይኸው ጋዜጠኛ ሌላ ጊዜ ኢትዮጵያን ሲጎበኝ አይኑን በደንብ ከፍቶ ማይት መቻል እንዳለበት እንደተመከረ ይነግረንና በዚህ መነሻነትም ስለሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ ለውጥ የበለጠ ለማወቅ መረጃዎችን በሰፊው መጎርጎር እንደጀመረ ይተርክልናል.
የሀገሪቱ ኢኮኖሚ በሁለት ዲጂት አሀዝ እያደገ እንደሆነ መረጃዎች ቢያሳዩም ይሁን እንጂ ከድህነት ወለል በታች በሆነ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚኖረው ህዝብ 40 ከመቶ መሆኑን አሀዞች ይናገራሉ የሚለው ዘጋቢው የእድገቱ ጉራማይሌነት ከየት እንደመጣ ለማወቅ ለሴትየዋ በርካታ ጥያቄዎችን ሲያቀርብላቸው እንደተጓዘ ይናገራል. እጅግ ያማሩና የተንደላቀቁ ፎቆችና አፓርትመንቶች ብቻ ሳይሆን የከተማ ባቡር ፕሮጀክትም በአዲስ አበባ በፈጣን ሁኔታ እየተገነቡ እንዳለ ይህንንም ለሚሰራው ዘገባ ሲቀርጽ መክረሙን ሚገልጸው ዘጋቢው በተገላቢጦሹ ግን ቤት አልባ የሆኑ ደሀ ዜጎች በከተማዋ በሰፊው እንደሚኖሩ ይናገራል.
አናገርኳቸው ያላቸው ሴት ወ / ሮም ቢሆን ይህን በተመለከተ ብዙሀኑ የሀገሬው ዜጋ እነዚህን ህንጻዎች ሊኖርባቸው የማይችል መሆኑንና በአብዛኛው ባዶ የኮንክሪት ግንቦች መሆናቸውን በመንገር የሀገሪቱን እድገት እንዳጣጣሉበት ነው የሚዘረዝረው. የዚህን ዘገባ ሙሉ እኛ ጋር ያገኙታል.
No comments:
Post a Comment