Friday, October 18, 2013

የአሲምባ ፍቅር

ደራሲ- ካህሳይ አብርሀ (አማኑኤል)
ትችት-(ሐተታ)- ሽፈራው
“ማን ያውራ የነበረ” እንዲሉ
“ለቀባሪ አረዱት” እንዳይሆን፤
ለስራ ጉዳይ ወደ ኮሎራዶ (ዴንቨር) በሄድኩበት ጊዜ አማኑኤል ማንጁስ ዴንቨር መኖሩን ሰምቼ ስለነበር ስልክ ደወልኩለት። በአንድ የኢትዮጵያ ሬስቶራንት ተቀጣጥረን ለመጀመሪያ ጊዜ ከ30 አመት በኃላ መሆኑ ነው አማኑኤል ጋር ተገንኘን። ለረጅም ጊዜ በዝምታ ከተያየን በኃላ አማኑኤል ሽፈራው አልተቀየርክም አለና እንደገና እቅፎ ሳመኝ። አይ አንተስ ብዙ ተቀይረሀል ማንጁስ አይደለህም? ይህ ውፍረት ይህ ቁመት ከየት መጣ አልኩት።
አማኑኤል ብዙ መናገር ሳይፈልግ እንባው ጠብ ጠብ ማለት ሲጀምር እኔም ለምን ታለቅሳለህ? ብዙ መከራ ስቃይ ወጥተን በህይወት ለመገናኘት በመብቃታችን የሚያስደስት ነው። ለአምላካችን ምስጋና የሚገባው ነው ብዬ ለማጽናናት ሞከርኩ። [ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]

No comments:

Post a Comment