የአንድነት ፓርቲ አስቸኳይ የብሄራዊ ምክር ቤት ስብሰባ ውሎ አራት አጀንዳዎች ምክር ቤቱ በመጀመሪያ መረጃዎችን ተለዋውጧል። በዚህም መሰረት በቅርቡ ጠ/ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተወያይተዋል።
ጠ/ሚኒስትሩ ፓርቲው በጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ በሰጡት ማብራሪያ ሁለት የማይታገሰው ነገር እንዳለ ምክር ቤቱ አምኗል። የመጀመሪያው ጠ/ሚኒስትሩ ፓርቲውን ከሌሎች ኃይሎች ትዕዛዝ የሚቀበል አድርገው ለማሳየት የሞከሩበት አግባብ ነው። ምክር ቤቱ አንድነት የራሱ የሆነ አጀንዳ በአጭርና ረዥም ጊዜ ቀርፆ የሚንቀሳቀስ መሆኑን አስምሮበታል።
እንደ አብነትም ጠ/ሚኒስትሩ የፓርቲውን የአምስት አመት ዕቅድና የስትራቴጂ ፓላን አግኝተው ቢሆን እንደዚህ እንደማይሉ አክሏል። በዚህ ላይ በተለይ የሻዕቢያ ተላላኪነት ማዕረግ የምኒልክ ቤተ መንግስት ለመሸጉት እንጂ ለአንድነት እንደማይገጥም አብራርተዋል። በመቀጠል ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ ህገ መንግስታዊ መብት ሆኖ ሳለ በፓርቲዎች መብዛት ለሁሉም ጥበቃ ማድረግ እንደማይችሉ፣ ሁለትም መንግስት አቋም የያዘባቸውን አጀንዳዎች ሲለሚያነሱ ከንግድህ ለይፈቀድ ይችላል ማለታቸው ግልፅ የሆነ ህገ መንግስታዊ ጥሰት በመሆኑ እንደሚከሳቸው ገልጸል። ሚሊየን ጊዜ ሰላማዊ ሰልፍ የመውጣት መብትም እንዳላቸው ተናግሯል። በመሆኑም ስራ አስፈፃሚው አስቸኳይ መግለጫ እንዲያወጣ ምክር ቤቱ ጠይቋል።
ሁለተኛው አጀንዳ አይ ሲ ሲን (I C C) የሚመለከት ነበር። ምክር ቤቱ የአፍሪካ መሪዎች በተቋሙ ላይ የያዙትን አቋም አውግዟል። ውሳኔው የአፍሪካ መሪዎች ህዝቡን እንደፈለግን እናድርግ ማለታቸውን የሚያሳይ ከመሆኑም በላይ ለዚያ እውቅና ይሠጠን ማለታቸው መሆኑን ምክር ቤቱ ፌዝ ነው ብሎታል። ነገር ግን የሀይማኖት መሪ የሆኑት የኖቤል ተሸላሚ ዴዝሞን ቱቱ የጀመሩትን ከተቋሙ ያለመውጣት ዘመቻ አንድነት እንደሚደግፈው ገልጧል። በተጨማሪም በሚቻለው ሁሉ እንደሚደግፈው ምክር ቤቱ አረጋግጧል። ሶስተኛ ጉዳይ ምክር ቤቱ ራሱን እንዲገመግም የሚያዝ ነበር። በዚህም ሶስት ሰዎች ያሉበት ኮሚቴ ተቋቁሟል። ዋነኛ ስራውም ከዚህ ግምገማ በሚገኝ ውጤት ቀጣዩን ምክር ቤት ለማጠናከር እንዲረዳ ነው። አራተኛው ከሌሎች ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ያለው ግንኙነት በቂ እንዳልሆነ ያየበት ነው።
ስለዚህ በስትራቴጅክ ፕላኑና የአምስት አመት ዕቅድ መሰረት የውህደት አመቻች ኮሞቴው 2 ተጨማሪ ሰዎችን አክሎ በደንብ እንድንቀሳቀስ አዟል። በተጨማሪም ከፓርቲው ቀጣይ ጠቅላላ ጉባኤ ምን ይጠበቃል ሲል ተወያይቷል።
No comments:
Post a Comment