Friday, October 11, 2013

የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች አዲስ በተከራዩት ቢሮ ውስጥ ተደበደቡ፡፡

112233
ሰማያዊ ፓርቲ ግንፍሌ አካባቢ ከሚገኘው ቢሮው የካቲት 12(መነን) አካባቢ አዲስ ፅ/ቤት ለመክፈት ከቤቱ ባለቤቶች ጋር ለ2 ዓመት የሚቆይ ውል የተዋዋለ ሲሆን በውሉ እንደተገለፀውም ከዛሬ ጥቅምት 1/2006 ዓ.ም ጀምሮ ቤቱ የሰማያዊ ፓርቲ በመሆኑ ቤቱን ለመረከብ በሄዱበት ወቀት ቤቱን እኛም ተከራይተንዋል በሚሉ ግለሰቦች ድብደባ ተፈፅሞባቸዋል፡፡

የቤቱ ተከራይ ነኝ የሚለው ግለሰብ አቶ በላቸውየተባለ ግለሰብ ሲሆን በዛው በመነን አካባቢ ወሄነት ባርና ሬስቶራንት የሚል ምግብ ቤት ከፍቶ የሚነግድ ሲሆን ምግብ ቤቱም የወረዳው የኢህአዴግ ካድሬዎች የሚውሉበትና የሚያመሹበት ቤት እንደሆነና በወረዳው ለሚዘጋጁ የኢህአዴግ የተሃድሶ ፕሮግራሞች ላይም የመጠጥ አቅርቦት በነፃ በስጦታ እንደሚያቀርብ ያገኘንው መረጃ ያመለክታል፡፡
ከታማኝ ምንጮች የተገኘ መረጃ እንደሚያመለክተው ሰማያዊ ፓርቲ ቢሮውን ለመከራየት ውል ከተዋዋለ በኋላ የወረዳው ካድሬዎች አቶ በላቸው ቤቱን እንዲከራየው እንዳዘዙትና ለቤቱ የ1 ወር ክፍያ 15000 (አስራ አምስት ሺ )ብርም ከወረዳው ጥቃቅንና አነስተኛ ቢሮ እንደተሰጠው ተረጋግጧል፡፡በዛሬው እለትም ቤቱን ከባለቤቶቹ ለመረከብ ወደ ግቢው የገቡትን አመራሮች ወሄነት ፔንሲዮን በቅርብ ቀን ስራ ይጀምራል የሚል ባነር በሩ ላይ ለጥፎ ይጠባበቃቸው የነበረው ተከራይ ነኝ ባይ ግለሰብ ይህ የኔ ቤት ነው ውጡ በማለት በግቢው ውስጥ ከነበሩ ግብረ አበሮቹ ጋር በፓርቲው 5 አመራሮች ላይ ድብደባ የፈፀመ ሲሆን ፖሊስ በመጥራት አመራሮቹ ወደ ፖሊስ ጣቢያ እንዲሄዱ ተደርጓል፡፡የፓርቲው አመራሮችም ቤቱን በህጋዊ መንገድ እንደተከራዩትና ከዛሬ ጀምሮ የቤቱ ባለመብቶች እንደሆኑ ለፖሊስ ያስረዱ ሲሆን ፖሊስ ለከሰአት 8 ሰአት የቀጠራቸው ሲሆን ግለሰቡን ግን ወደግቢው ገብቶ እንዲቀመጥ ፖለሶች ፈቅደውለት ከግብረ አበሮቹ ጋር በግቢው ውስት ይገኛል፡፡
Minilik Salsawi

No comments:

Post a Comment