Thursday, October 17, 2013

32ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ጉባኤ በጥሩ መንፈስ እየተካሄ ነው ተባለ

:-በስብሰባው ላይ የተሳተፉ አባቶች ለኢሳት እንደገለጹት በዛሬው ስብሰባ የልማት ኮሚሽኑ ሪፖርት ሰፊ ሽፋን የተሰጠው ሲሆን፣ መንግስት በቤተክርስቲያኑዋ ገቢ ላይ እየተጠቀመ መሆኑ ተነግሯል።የኮሚሽኑ መሪ ” በጭንቅ ውስጥ ነው እየሰራን ያለነው ፣ በመኖርና ባለመኖር ውስጥ እንገኛለን ያሉ” ሲሆን፣ ስሜታቸውን በድፍረት ሲናገሩ ከዋሉት ጳጳሳት መካከል ብጹዕ አቡነ ቄርሊዎስ ” ዛሬ ጀመርነው፣ እስካሁን የለንም ነበር፣ ዛሬ ስለቤተክርስቲያን መናገር ጀመርን” በማለት በመዝሙር ሚስጢር ማቅረባቸውን ጉባኤውን የተሳተፉት ገልጸዋል።

በቤተክርስቲያኑዋ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ መነቃቃት በዚህ ጉባኤ ላይ መታየቱን የገለጹት ተሳታፊዎች፣ ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ከውድቀት ለመታደግ ይቻላል ብለዋል።
ብጹዓን አባቶች ያሰሙት ተቃውሞ በአገር ቤትም በውጭም ከፍተኛ የመነጋገሪያ አጀንዳ ሆኗል።

ጥቅምት (ሰባት)ቀን ፳፻፮ / ኢሳት ዜና 

No comments:

Post a Comment