Friday, October 18, 2013

በፖለቲካ ቋሚ ጠላትና ቋሚ ወዳጅ የለም!!!

ከዘካሪያስ አሳዬ

ብሶት የወለደው ብሎ ነው ወያኔም ሲታገል የነበረው ብሶት ታዲያ ወያኔን ብቻ አይደለም ወልዶ መአን የሆነው ብሶት እስካለ ድረስ አመፅ አለ።
የግንቦት 7 ዋና ፀሀፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በተናገሩት ንግግር በአለም ላይ መወያያና መነጋገሪያ ሆኖ ነበር እንዲሁም ጠቅላይ ሚኒስተሩ ጨምሮ በኢቲቪ መስኮት ከተናገሩት ንግግር አንዱ የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል ትግል ነበር።ግንቦት 7ና የኤርትራ ጉዳይ አነጋጋሪ ሆኖ የተለያዩ ሰዎች ፁሁፎች ይፅፋሉ አንዳንድ ድርጅቶችም መግለጫ  እያወጡ ትክክል አይደለም ከጠላት ጋር አብሮ መውጋት ነው እያሉ መግለጫ ያወጣሉ።አንዳንድ ሰዎች አስተያየት የሚሰጡት ከወዳጅነት የተነሳ ሲሆን አንዳንዶቹ ደግሞ አላማቸው አይታወቅም። ስለ ኢሳያስ አፈወርቄ የሰጡት አስተያየት አላስፈላጊ ነው ከሚል ይነሳል ምክንያቱም በ principle ደረጃ በኤርትራ በኩል የሚመጣ ማንኛውም ለውጥ ለኢትዮጵያ አደገኛ ነው በሚል አቋም ያላቸው ድርጅቶች አሉ።

ለምን የሚል አስተያየተ የለኝም ግን ስጋቱ ለምን መጣ የሚለውን ማየት ይኖርብናል።ፀረ_ሻቢያ ፕሮፓጋንዳ ላለፉት 17 ዓመት ስለ አሰብ ጉዳይ የተለያዩ ሰዎች ሀሳባቸውን ሲናገሩ ቆይተዋል።ቀጥሎም በባድመ ጉዳይ ህውሃት/ወያኔም ቀጥሎበት ነበር።በህዝቡ ውስጥ ሻቢያና ህውሃት በኢትዮጵያ ህዝብ አንድነትና በግዛቷ ልዋላዊነት ላይ የመጣውን አደጋ የሚረሳ አይደለም በዚህ ሂደት ውስጥ ኤርትራ የምትባል አሁን አገር እንደሆነች የሚረሱ ሰዎች አሉ።ኤርትራ ከኢትዮጵያ ተገንጥላለች።
ኤርትራን በማስገንጠል በኩል የኤርትራ ነፃ አውጪ ግንባር ታግለዋል።አነሳሳቸውና ትግላቸው ፀረ_ኢትዮጵያ የሆነ ትግል ሳይሆን የብሔራዊ ዲሞክራሲያዊ ጥያቄ ነው ተብሎ ከተማሪ እንቅስቃሴ ጀምሮ የሚታወቅ ነው።በኋላ ግን አፈታቱ ላይ ከቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ ጀምሮ በኋላም ደርግም በወሰደው የኃይል እርምጃ ነገሩ ስር እየሰደደ ለወያኔ መፈጠር ፣ለወያኔ መጎልበት ትልቅ አስተዋፅዎ አደረገ።አሁን አገራችን ኢትዮጵያ ስለደረሰችበት ሂደት ደረጃ ከፍተኛ አስተዋፅዎ ያደረገ ነው።
      በተለይም ሻእቢያ አጅቦ ቤተ_መንግስት ድረስ በማድረስና በማስገባት በተወሰነ ግዜ በነበራቸው ማሊሙ የኢትዮጵያን ህዝብ የሚረሳው ነገር አይደለም።ብዙ ሀብትና ንብረት ተዘርፏል፣በአንድ ወቅት ኤርትራዊያኖች የቡና ላኪ እስከሚሆኑ ድረስ ከፍተኛ ደረጃ ደርሰው ነበር።እነኒህ ነገሮች እንዳሉ ሆነው ግን ዛሬ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የኢኮኖሚ ፣የፖለቲካ ፣የማህበራዊ አፈናና የሰብኣዊ ጥሰት በሚመለከት ህዝቡ እየታገለ መሆኑን መርሳት አያስፈልግም።
ህዝቡ ደግሞ የሚታገለው በዲዛይን አይደለም፣በድርጅትም አይደለም ብሶት የወለደው ብሎ ነው ወያኔም ሲታገል የነበረው ብሶት ታዲያ ወያኔን ብቻ አይደለም ወልዶ መአን የሆነው ብሶት እስካለ ድረስ አመፅ አለ።የኢትዮጵያ ህዝብ በሰላማዊና ህጋዊ መንገድ የሚታገሉ ህዝቦች አሉ።በሰላማዊና ህጋዊ መንገድ ታግለው ስላቃታቸው የሞት ፍርድና ዕድሜ ልክ የተፈረደባቸው ሀይሎች ደግሞ በሌላ መልክ ትግል ያደርጋሉ።በዚህ ጉዳይ ላይ አቋም በመውሰድ የሚያስፈልገውን ትግል በየት በኩል ይምጣ ፣የቱ ጋር ይደራጅ የሚለው የድርጅቱ ጉዳይ ነው የሚሆነው።
ዛሬ ባለው ሁናቴ ላይ የአቶ አንዳርጋቸው ንግግር በጣም BOLD ሆኖ መውጣት ምንአልባት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ባህል ውስጥ ያልተለመደና ትንሽ አስቸጋሪ ቢሆንም አሁን ግን እውነታው መድረክ ላይ ስለመጣ የኢትዮጵያ ጂኦፖለቲካ ስንመለከት ዛሬ ለትጥቅ ትግል አመቺ የሆነ የጎረቤት አገሮች ብዙም የሉም ምንአልባት ወያኔ ሲታገል የነበረበት ጊዜ ሻእቢያ በተደራጀበት ሁናቴ የሱዳን፣የሱማሌ ወይም የሌሎች አረብ አገሮች እርዳታ የለም ዘመን ተቀይሯል፣ጂኦፖለቲካ ተቀይሯል ።
አሁን እውነታው ግን ለጊዜው በሻእቢያና በወያኔ መካከል የተፈጠረ ግጭት አለ።አንዳንድ ሰዎች አሁንም ወያኔና ሻእቢያ አንድ ናቸው የሚል የደረቀ ክርክር አለ።
በፖለቲካ ቋሚ ጠላትና ቋሚ ወዳጅ የለም።ኤርትራ አሁን አገር ናት ኤርትራን እንደ አገር ካየን እንደ ሱዳን እንደነ ኬንያ ነው የምናየው።ስለዚህ የኤርትራ መንግስት ለራሱ አጀንዳ ሊሆን ይችላል ወይም በተለይ ለነኒ ብሶት ለወለዳቸው ታጋዮች የሚለውን የድርጅቱ መልስ ነው።ለምን ግን ግንቦት 7 ላይ ትኩረት እንደተደረገ አላውቅም እንጂ ከዛ በፊት ጫካ የገቡ የአርበኞች ግንባር፣የ T P D F እነኒ ላይ ትኩረት ተደርጎ ሲተች ሰምቼ አላውቅም ዛሬ ለምንድን ነው ግንቦት 7 ላይ ትኩረት እንደተደረገ ግን አይገባኝም።ግንቦት 7 ዛሬ ጫፍ ላይ ያለ ነው ለትግሉ በኤርትራ መንግስት እርዳታ ልናገኝ እንችላለን ጥሩ green light አለ እንዲሁም ያለው እርዳታ በአቶ አንዳርጋቸው አባባል እንዳሉት በአሜሪካ ስብሰባቸው ላይ ከአራተኛ ኮከብ ሆቴልና ከአምስተኛ ኮከብ ሆቴል ያላነሰ እርዳታ ነው የምናገኘው ከምንጠብቀው በላይ ነው ከዚህ በላይም ከኤርትራ መንግስት መጠበቅ የለብንም እዛ ተደራጅተን ትግላችንን በአገራችን ውስጥ እናደርጋለን ነው የሚሉት ይኽንን ደግሞ እሳቸው ጫካ ወርደው 4 አመት ቆይተው አይተው ያሉትን ሲናገሩ እኔ አልቀበልም የሚል የሞራል ድፍረትም የለኝም እዛ ብዙ የታጠቁ ሀይሎች አሉ እዛ ታጥቀው የፖለቲካ leadership and training የሚያስፈልጋቸው ሀይሎች አሉ ለእነሱ leadership የሚያደርግ የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል ተፈጥሯል ስለዚህ ይህ ግንቦት 7 ሻእቢያ አያንቀሳቅሰውም የሚባል ክስ አለ በአንድ በኩል ደግሞ በሻእቢያ በኩል የሚመጣው ውጤት አስቸጋሪ ነው የሚባል ነገር አለ በዚህ በኩል የሚመጣ ነገር ሌላ ወያኔ ነው የሚመጣው የሚል ክስ ነው።አንዳንዶቹ ደግሞ የግል ጠብ በግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል ላይ ያለ ይመስላል።አገራዊ ጥቅምና አጀንዳ የጎደላቸው ትችቶች ናቸው የሚቀርቡት በዚህ አስተያየቶች በግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል ይቆማል ወይ ነው ትልቁ ጥያቄ? መሆን ያለበት ዛሬ ይህ ትግል ሊቆም አይችልም።
ዛሬ በኢትዮጵያ ያሉት  የሰላማዊ ተቃዋሚ ታጋዮችን torture እያደረገ ነው ያለው የወያኔ መንግስት ጠቅላይ ሚኒስተሩ ሀይለማሪያም ደሳለኝ በሰጡት መግለጫ 99 የተለያዩ ፓርቲዎች አሉ በየሳምንቱ ሰላማዊ ሰልፍ እየወጣቹ ከምጨውብን ተደራጅታቹ ወጣቹ ብጮሁ ይሻላል ነው ያሉት ዛሬ በሰላማዊ  ፓርቲ  ውስጥ ያሉት አመራሮች አንበርክኮ በመግረፍ እና ሰላማዊ ሰልፍ አትወጡም በማለት የተለያዩ በደል ሲፈፅምባቸው እያየን ምንድነው የሚጠበቀው።
በግል ጥላቻ የተነሳ የተለያዩ አስተያየት ይሰጣል።አንዳንዱ ግንቦት 7 አመፅ እንዲመጣ ይፈልጋል እያሉ ሟርት የሚናገሩ ሰዎች አሉ ለዚህ ሁላ ተጠያቂው ወያኔ ነው ምክንያቱም የኢትዮጵያ ህዝብ በሰላም፣በፍትህ፣በዲሞክራሲ፣በህግ ህገ መንግስቱን አንተርሶ ጥያቄዎችን እያቀረበ መልስ ሳይሰጠው በየአደባባዩ በጥይት መደብደብ ፣መታሰር ፣መሰደድ ሆኗል መልሱ ስለዚህ አላፊነቱን መውሰድ ያለበት ወያኔ እንጂ ግንቦት 7 አይደለም።
ታዲያ ግንቦት 7 ብረት አንስቶ ቢታገል ምንም አይገርምም በተለይ ለውጥ ፈላጊ ነን የሚሉ ድርጅቶች ይህን የትግል አጋር መሆን ሲገባ ትችቱ ከየት የመጣ ነው ? ወያኔ አምባገነን ስርዓት ነው እያሉ ትግል ደግሞ አያስፈልግም ማለት ከሀሳባቸው ጋር የሚጣረስ ስለሆነ እራሳቸውን ዞር ብለው ቢመለከቱ መልካም ነው።
ሰርቶ ማሳየት ነው እንጂ ተቃዋሚ ሆኖ መግለጫ ማውጣ ህዝብን ማደናገር ይብቃ።አንዳንድ ተቃዋሚ እንዴት መታግል እንዳለባቸው የገባቸው አይመስለም::ትግል ምን እንደሆነም የሚያውቁአይደሉም::ማነን ነው የምታሰተባብሩት ለሚለው ጥያቅም መልስ የላቸውም::በአንድ ቦታ ተሽጉጠው መግለጫ ማውጣት ብቻ ነው ስራቸው::መግለጫ ማውጣት የትግል ውጤት አይደለም::የሚጨበጥና የሚታይ ነገር ይዞ ብቅ ማለት ይሻላል::ታግሎ ውጤት ማምጣት ከአልተቻለ ቦታውን ለሚታገሉ ድርጅቶች በስላምና በቅንነት መልቀቅ እራሱ አገርን እንደመርዳት ይቆጠራል::ከፈረሱ ጋሪው ይቀድማል ብሎ ማስብ ዓይነት ትግል ከመታገል በሚመጥናቸው ቦታ መስማራት ይገባል:: ለትግል የሚሆን ድርጅት አይደለም::የሚሰራውን ድርጅት ከመተቸት አለን የምትሉ ከሆነ አቅርቡት እንይላችሁ::
ኢትዮጰያ፣ ኢትዮጵያማለት ብቻውን ጉንጭን ማልፋት ነው፤ የወገን ፍቅር ይኑረንያንንም በተግባርና ለማስመሰል ሣይሆን ከእውነት እናሳይ፤ አናቱን የሚያሳክከውን እግሩን ብናክለት ኅሊናችንም ታካኪውም ይታዘቡናልና በአፋጣኝ እንለወጥ፤ በሞተ ሕዝብ ላይ ለመንገሥ ከምንራወጥ የሚሞተውን ሕዝብ ጠላቶቻችን ናቸው ብለን ከፈረጅናቸው ወገኖች ጋርም ቢሆንተመሳጥረንእናድነው፤ ከወገን ጋር ተባብሮና ተመሳጥሮ ሕዝብን ከመግደል ይልቅ ከጠላት ጋር ተባብሮ ሕዝብን ማዳን በፈጣሪም በታሪክም ታላቅ ዋጋ አለውና አሁን ለአቃቂርና ለወሬ ስለቃ ጊዜ እንዲኖረን ፈቃዳችን አይሁን፡፡ ለዚህ የተቀደሰ ተግባር ደግሞ ሁሉም ወገን መተባበር አለበት፡፡ ወገን እየተሰቃዬ፣ እየተሰደደ፣ አካሉ እየተቆራረጠና ለመለዋወጫነት እየተሸጠባለበት የሚዘገንን ሁኔታ በድሎትና በቅንጦት መኖር፣ ገንዘብንም በአልባሌ ሥፍራና ለአልባሌ ተግባር ማዋል በእግዚአብሔር ዘንድ በኃጢኣተኝነት ባይሆንም እንኳን በነውረኝነት ሳያስፈርጅ የሚቀር አይመስለኝም፡፡ እናም ከዚህ አንጻር ብዙዎቻችን ብዙ መሥራት፣ ራሳችንንም በጥሞናና በተመስጦ መፈተሸ ይጠበቅብናል፡፡ በተለይም እዬዬም ሲደላ ነውና ሕዝባችን ላይ የተሰኩትን እሾሆች ለመንቀል ምንም ጥረት ሳናደርግና ፈቃደኝነት ሳይኖረን እርስ በርስ በነገር ጦር ብንጠዛጠዝ ታሪክ ምሮ አይምረንም።
ከዘካሪያስ አሳዬ

edenasaye@yahoo.com



No comments:

Post a Comment