Monday, October 14, 2013

ከሶስት ሚልየን በላይ ዜጎች ለወባ ወረርሽኝ ተጋልጠዋል

የክረምቱን መውጣት ተከትሎ ወባ በሚያጠቃቸው ወረዳዎች ወረርሺኙ መከሰቱን የደረሰን መረጃ አመልክቷል።በገዳይነቱ  ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ደረጃ  የሚይዘው የወባ በሺታ በአሁኑ ስዓት በአርሶ አደሩ ህይዎት ውስጥ ፈታኝ መሆኑን ከሁሉም ክልሎች ለፌድራል ጤና ጥበቃ ሚኒስትር የተላለፈው መረጃ ያመለክታል፡፡

በበሺታው ፈውስ አጥተናል የሚሉት ኗሪዎች ከገበያ እንደ ሸቀጥ እቃ የሚገዙዋቸው መዳህኒቶች የማዳን አቅም የላቸውም ይላሉ፡፡በኢትዩጵያ የረጅ ድርጁቶች እጅ በመሰብሰቡ ምክንት በ2005 ዓ.ም ምንም ዓይነት የአጎበር ስርጭት ያልተከናወነ ሲሆን በአለም ጤና ደርጅት ለጤና እክል ይሆናል ሲባል የታገደውን ዲዲቲ ኬሚካል ርጭት 4.6 ሚልየን ቤቶች ላይ ተከናውኗል፡፡ ይህም የመተንፈሻ ችግር እያስከተለ እንደሆነ ባለሙያዎች ተናግረዋል፡፡

ጥቅምት (አራት)ቀን ፳፻፮ / ኢሳት ዜና :-

No comments:

Post a Comment