Thursday, October 10, 2013

***ሀገር አቀፍ የሆነ አንድነትንና ሰላምን ማግኘት ነው የሕዝብ ፍላጎት***

***ሀገር አቀፍ የሆነ አንድነትንና ሰላምን ማግኘት ነው የሕዝብ ፍላጎት***

ከሰብኣዊ

ህውሃት የሕዝቡን ሰላምና መረጋጋት ለማግኘት፤ በሀገር ፀጥታና በብሔሮች ነፃ መውጣት ስም አምታትቶ፤ ዴሞክራሲያዊ መብቶችን በመንፈግና የመሪዎችን ኪስ በማሳበጥ፤ የውሸት ሀገራዊ ዕድገትን ለመሸፋፈን መሞከሩ የትም አላደረሰውም። ይልቁንም በሕዝቡ የኑሮ ሁኔታ ቁማር መጫወቱ ራሱን ዞሮ መቶታል። መሠረታዊ የሆነውን የመንግሥት ተልዕኮ ስቷል።

በዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መንግሥት ማለት፤ የሕዝብ ተወካይ ማለት ነው። 
መንግሥት ማለት በሕዝብ ፍላጎት የቆመ ማለት ነው።
መንግሥት ማለት በሕዝቡ መካከል እኩልነትን የሚጠብቅና የሚያሰጠብቅ ማለት ነው። 
መንግሥት ማለት ለሕዝብ ደኅንነት፣ ለሰላምና ለሀገር ዕድገት የቆም ማለት ነው። 
መንግሥት ማለት የሕዝብ አገልጋይ ማለት ነው። 
ህውሃት ከላይ የዘረዘርኳቸውን አንዳቸውንም አላሟላም።
የደርግን መንግሥት የኢትዮጵያ ሕዝብ የጠላበት ምክንያት፤ በአረመኔነቱ፣ ያለሕግ የፈለገዉን በማድረጉ፣ የግለሰቡ ኢትዮጵያዊ ዴሞክራሲያዊ መብቶች ባለመከበራቸው፣ በየትኛውም የኢትዮጵያ ክልል ሠርቶ የማደርና የመበልፀግ በሩ በመዘጋቱ፣ የባለሥልጣኖች ወገን የሆኑ የሁሉም ነገር ፈላጭ ቆራጭ በመሆናቸው ነበር።

ታዲያ ህውሃት ግንባር መጥቶ የቀየረው ነገር ቢኖር፤ በደርግና በኢሠፓ ቦታ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መሪዎችና ፓርቲ መተካታቸውን ብቻ ነው። ግድያው፣እስራቱና የሀገር ሀብት ዝርፊያው ብሷል። ጥቂቶቹ በሃብት መጨማለቃቸውና አብዛኛው በድኅነት መማቀቁ የዕለት እውነታ ሆኗል።
ህውሃት መሪዎችና ሀብት ነጣቂ አባሪዎቻቸው፤ የሕዝቡን የነፃነት ፍላጎትና ሠርቶ የማደር ጉጉት በስግብግብ የግል ጥቅም ማካበት ሩጫቸው አመድ አስጋጡት። ሀገሪቱን በጣጠቋት። ደንበሯን ሸጡት። ለሙን መሬት ከባለቤቱ ነጥቀው ለራሳቸውና ለውጭ ከበርቴዎች በርካሽ ቸበቸቡት። ይህ የሕዝቡን ቁጣ አስነስቶ መቃብራቸውን እንዲቆፍር ገፍቶታል። ለሥልጣናቸው በር መክፈቻ የተዋቀረው የክልል ግዛት፤ እንዳቋቋመው ፌዴራላዊ ግዛት ውስጡ በስብሶ ንቅዘቱ ሕዝቡን ቀስቅሶታል። 
ይህን ማስተካከል አሁን የሕዝቡ ኃላፊነት ነው።
የአንድ ቡድን ወይንም ፓርቲ ግዴታና ውዴታ አይደለም። በአንድነት መስራት የሁላችን ነው። 
ህውሃት በሌላ አንድ ፓርቲ ባሁኡ ሰዓት ለመለወጥ የኢትዮጵያ ሕዝብ ፍላጎት አይደለም።
ሀገር አቀፍ የሆነ አንድነትንና ሰላምን ማግኘት ነው የሕዝብ ፍላጎት። 
ከሰብኣዊ

No comments:

Post a Comment