Tuesday, March 31, 2015

በኢትዮጵያ ዝሆኖችም “ተሸብረዋል” ባለፉት 30ዓመታት 90በመቶ ዝሆኖች አልቀዋል

ivory
የዝሆኖችን ግድያ ለማስቆም በሚል የብአዴኑ ደመቀ መኮንን ከዝሆን ጥርስ የተሰራ ስድስት ቶን የሚመዝን ጌጣጌጥ እንዲቃጠል እሣቱን በለኮሱበት ጊዜ ኢህአዴግ በአገዛዝ በቆየበት 25 ዓመታት ውስጥ የኢትዮጵያ ዝሆኖች ቁጥር ከ90በመቶ በላይ ለምን ሊቀንስ እንደቻለ የተናገሩት ነገር የለም፡፡

ኢህአዴግ ከቻይና ጋር ከተፋቀረበት ጊዜ ጀምሮ የዝሆን ቀንድ ንግድ እየተጧጧፈ እንደሄደ የሚናገሩ ጥቂቶች አይደሉም፡፡ በዚህም “ጮማ” ንግድ ውስጥ ቢጂንግን፣ ሲንጋፖርን፣ ታይላንድን፣ … መመላለሻቸው ያደረጉ ቱባ ባለሥልጣናትና ደላሎቻቸው ይጠረጠራሉ፡፡ የቡድሃ ሃይማኖት እጅግ በተስፋፋባቸው በሩቅ ምስራቅ አገራት የዝሆን ጥርስ እጅግ ተፈላጊ ሲሆን ዋንኞቹ አስተላላፊዎች ደግሞ የዘመኑ የቻይና ቱጃሮች ናቸው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ  የዝሆን ጥርስ ለሩዝ መብያ ስንጥር (chopsticks)፣ ለተለያዩ ዓይነት ጌጣጌጥ፣ ለቤት ውስጥ ዕቃ፣ ወዘተ ተፈላጊነት አለው፡፡
ivory 2ቻይና በዝሆን ጥርስ ገቢ ንግድ ላይ የአንድ ዓመት ማዕቀብ ጥያለው ብትልም በአፍሪካ ያሰማራቻቸው ባለሃብቶቿ ከየአገሩ ባለሥልጣናት ጋር በመሆን ንግዱን እንደተቆጣጠሩት የእንስሳት መብት ተከራካሪዎች ይናገራሉ፤ ወደ አፍሪካ በሚያስገቡት ኮንቴይነር የአፍሪካን ሃብት ጭነው እንደሚልኩ በስፋት የሚነገር ነው፡፡ ይህም የቻይና አካሄድ በዚሁ ከቀጠለ በአፍሪካ የዝሆን ዝርያ የማይኖርበት ደረጃ ላይ እንደሚደርስ ይገመታል፡፡
በአንዳንድ ኤክስፐርቶች ግምት ሁኔታው ካልተሻሻለ እኤአ በ2025 አፍሪካ ዝሆን አልባ ትሆናለች ይላሉ፡፡ በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ ደግሞ መሻሻል ካልተደረገበት የኢትዮጵያ ዝሆኖች እስከዚያ ስለ መዝለቃቸው ግምት መስጠት አይቻልም፡፡ ኢህአዴግ በአገዛዝ በቆየባቸው 25ዓመታት ውስጥ 90በመቶው ዝሆኖች ካለቁ የቀሩት 10 በመቶው አሉ የተባለው “ምርጫው” እስኪያልፍ ነው በማለት አንዳንዶች ተሳልቀዋል፡፡ (የመግቢያው ፎቶ AFP: Zacharias Abubeker)

No comments:

Post a Comment