በቅርቡ ተጠቅላይ ሚንስትሩ ሃይለማሪያም ደስ አለኝ ዓረብ ሐገር ያዩትን ወገንና አዉሮፓ መጥተዉ ያዩትን የወገን ችግር፣በምፀት ሲገልፁ- ብዙ እንቶ ፈንቶ ተናግረዉ ነበር ፈረንጆቹ bla -bla ይሉታል ፣ ከዛ ዉስጥ ግን አንድ አነጋገራቸዉ ቀልቤን ስባ ሌላም ነገር አስታወሰችኝና ትንሽ ልበል ብዬ እኔም ብዕሬን አነሳዉ ።
ምን ሆነዉ ነው እንደዚህ በሰዉ ሐገር እሚሰቃዩት -ሐገራቸዉ ቢሆኑ ጠግበዉ መብላት እንደሚችሉ, ስደተኛዉን ኢትዮጵያዊም ሆነ ያገሪቷን ክብር በወረደ ቃላት ሲዘባበቱበት ከራሳቸዉ አንደበት ሰማሁና ፣ ታዲያ ይሔን ግዜ ምን አሰብኩ እኝህን ጠቅላይ ሚንስትር በዙሪያቸዉ ያሉ የድሮ ማርክሲስት ኤሊትሶች ይህን እንዲናገሩ እና እንዴት ከጨወታ እያስወጡዋቸዉ እንደሆነና መጨረሻቸዉም ከግዜሩም ከሰይጣኑም እንዳይሆኑ ተደርጎ የስርዓቱ የተሞላ አሻንጉሊት ሲሆኑ ማየቱ እንደዜጋም እንደሰዉም ስላሳዘንኝም ነዉ ።
ባንድ ዎቅት በፈረንሳይ ዓብዮት የፈረንሳይ የተራቡ ጭሰኞች በ፩፯፯፭ 1775 በፈረንጆቹ አቆጣጠር ባነሱት የዳቦ ጥያቄ ልዕልቲቷን ማሪይ አንቶይነት Marie Antointte ዳቦ ከሌለ ለምን ኬክ አይበሉም ዎይንም ደግሞ ኬክ ይብሉ ብላ የተናገረችዉን በወቅቱ የነበረዉ ምሁር ዓብዮተኛ የልዕልቲቷን አባባል በሁለት መንገድ ሰንጥቆ የህዝብ ቁጣ public plight መቀስቀሻ ተደርጎ በወቅቱ የነበረዉን የቡርዥዋ የመደብ አርስቶክራሲ aristocracy ችግር በማሣየትና እና የልዕልቲቷን ኦስትሪያዊነት ከፈረንሳይ ሞናርኪ ሉዊስ ፩፮ኛLouis XVI. ለመገንጠል የርስዋን አባባል ለፖለቲካ ትርፍ ተጠቅመዉበታል ።(ላንባቢያን- እንደማስታወሻ እንደምርቃትም ትሆነን ዘንዳ በዚች ዙሪያ ትንሽ ብናክል)-በነገራችን ላይ እዚህ ጋር አንባቢያን ስለዚህ አባባል በተለያዩ የታሪክ ፅሁፎች ዉስጥ ለምን ኬክ አይበሉም ያለችዉ ማሪያ ተረዝ Maria Therese ትባል የነበረች የፈረንሳዩ የሉዊስ ፩፬ኛ XIV ሚስት የነበረችዉን እንደሆነም ይነገራል ይህንንም የፃፈዉ ለመጀመሪያ ግዜ ዤን ዣኹዊዝ Jean -Jacques Rousseau ይባል የነበረ የፖለቲካ ፈላስፋ ‘ኑዛዜ’ ዎይንም ‘ኮንፌሽን confession ‘ብሎ ባሳተመዉ መፅሐፉ ዉስጥ እንዳሰፈረ የተለያዩ መጣጥፎች ይናገራሉ በዚ ጉዳይ እስካሁን ብዙ የታሪክ ፀሐፍት ለሁለት እንደተከፈሉ ነዉ ፤አንደኛዉ ወገን Marie Antoinette የማሪዬ አንቶይነት አባባል ሲል ሌላኛዉ ደግሞ የማሪያ ተሬዝ Maria Thereseነዉ እንዳለ ነዉ ። Louis XVIIሉዊስ ፩፰ኛም በራሱ ብዕር በ፩፯፱፩ (1791) አጠናቅሮ እንደፃፈና ኣባባሉም የማርያ ተረዝ መሆኑን የፃፈዉ ማስረጃም እንዳለ እሚተርኩ አሉ )
እናም ታዲያ ወደተነሳሁበት ርዕስ ስመለስ የኙ ጠቅላይ ሚንስትር ሐይለማሪያም ደስ አለኝ የጀርመን German ጉብኝት ወገን በመጠለያ ካምፕ ዉስጥ ባዶ ዱቄት ሲበላ አይተዉ የተናገሩት የማሪዬን Marie A.ዎይንም ማሪያ ተረዝ Maria Therese አባባል ስላስታወሰኝ እና መጨረሻቸዉም ስላሳዘነኝም ነዉ። ዱቄት ለምን ይበላሉ ዶሮ እያለ ከሆነ አባባላቸዉ ለኛ ሐገሩ ሐይለ ማሪዬ Marie የዘመናችን ያበሻ አባባል phrase ሆና እንዳትቀር ያስፈራል ፤ ከሆነ እንግዴ ሳንወድ በግድ ከ ማሪዬ Marie .A እና ከ ማሪያ Maria Therese ጎን ሌላ ያበሻ ሃይለ ማርዬ Marie ልንጨምር ግድ ይላል ማለት ነዉ- አጃኢብ ነዉ ። ለኛ ሐገርም ራሳቸዉን ለለዩ የመደብ ማርኪሲስት aristocrats መካከልና በቅዠት እሚኖረዉን የምንዱባን ህይዎት ባጠቃላይ ባያሳይልንም በከፊል ግን የሳቸዉ አባባል ያለዉን የመንግስትና የህዝብ ክፍተት ፍንትዉ አድርጎ ያሳያል – ልብ ያለዉ ልብ ይበል።
ብዙዉን ግዜ ያንድ ሐገር ጠቅላይ ሚንስትር ባገር ጉዳይ ስራ ላይ በሚሆንበት ግዜ የራሱ ያነጋገር ዘይቤዎች፣ የሚናገራቸዉ የሚጠቀማቸዉ ቃላትና አባባሎች ዕጅግ ጥንቃቔ ይደረግባቸዋል ፤ያም እሚሆነዉ የባለስልጣኑ አነጋገርና አካሔድም ሆነ አቀማመጥ ፕሮቶኮል የመላዉን ህዝብ እና ሐገር ስለሚወክል ነዉ ። ስለዚህ የራሱ የሆኑትን ልማዶችና ዕምነቶች በህዝብ ፊት ዎይንም በማንኛዉም የሚዲያ መገልገያ አዉታሮች ላይ ዕንዳይጠቀም የስራዉ ሃላፊነትና የስልጣኑ ደረጃ ባያስገድደዉም ፣ነገር ግን ብያንስ ግድ ይሏል። ይሔም ማለት በቀላል አገላለፅ ክብርንና ደረጃን ሐገርንና ህዝብን በሚመጥን መልኩ ማለት ነዉ፤ ፕሮቶኮል ጠባቂ ዎይንም ደምብ ጠባቂ ሹሙ ቢቻል ቀድሞ ይቀርፀዋል፤ ካልሆነም ቀድሞ ምክር ይሰጣል ። የዶሮ ወጥ ይዞ ስለመጉዋዝና ስለግርድና ስራ፣ ስለ ወገን ሰደተኝነት ማብጠልጠልና ተራ አነጋገርና ቃላትን መጠቀም ትርፉ ራስንና አገርን ማዋረድ ካልሆነ በቀር ሌላ የፖለቲካ ትርፍ አለዉ ቢባል ጅልነት ነዉ።
ለዛዉም ደግሞ ሲደተኞቹ የጦር ምርከኞች ሳይሆኑ ጥገኝነት ጠያቂዎች ሆነው የጀርመን መንግስትም ወስዶ ማስጎብኘቱ ሌላዉ ልብ ያላሉት እና ያልተዘጋጁበት ይመስላል ፤ ይህም ቢሆን ባዉሮፓ የስደተኞች አያያዝ ህግ መሰረት ለጀርመን መንግስትም ቢሆን የፖለቲካ ኪሳራ ነዉ ፤የታደጉዋቸዉን ሰደተኞች ለገዳያቸዉ ዎይ ደግሞ አሳዶ ላስወጣቸዉ መልሰዉ ካስጎበኙም የሚያሳዝን ነዉ። ይልቅ የዶሮ ወጡን ይዘዉ የመጡት ለዘመዶችዎ ከሆነ እና እዛዉ ጣቢያ ዉስጥ በስደተኛ ስም ለልዩ ስራ የተመደቡ ከሆነ ዕርግጥ ነዉ እነዚያ ሰዎች ምን ጎሎአቸዉ እና ምን አጥተዉ አንደሆነ እኛም አናውቅም እርሶንም ያ ከሆነ ያንገበገቦ ሚስኪኑን ትክክለኛ ስደተኛ ሳይደርቡ ለይተዉ ቢነግሩን ጥሩ ነበር።
በጀርመናዉያንም ጓደኞቻቸዉ ‘ኸይም’ heim (መጠለያ) ትርጉሙ ተነግሮአቸዉ’ እተዘጋጀ የስደተኞች ጣቢያ ተኪዶ ወገንን -ያንድ ሐገር ጠቅላይ ሚኒስትር ቆሞ ሲያሾፍና ሲዘባበት ያንን በህዝብ የመገናኛ ጣቢያ እንደ ትልቅ የፖለቲካ ትርፍ ወሰደዉ መደስኮሩ ፣ ፖለቲካ ሳይሆን ተራነትንና መደዴነትም ነዉ። ያገር ክብር የህዝብ ክብርን ከምንም በላይ ተምሳሌት ሆኖ እሚገለፀዉ በመሪዉ ነዉ ይሔን ክብር ነዉ ፈረንጆቹም DIGNITYዲግኒቲ እሚሉት ሐገር ህዝቡ ቢደኸይም በምንም ዓይነት ግን የራስ ክብርን dignityዲግኒቲ አሳልፎ አንድ ያገር ጠቅላይ ሚኒስትር እራሱንና ህዝቡን ባደባባይ አያዋርድም ። በጠቅላይ ሚኒስትሩ የክርስቲያን ሃይማኖት መፅሐፍ ቅዱስ ዉስጥም ሙሴ ያንን በባርነት ስር የነበረዉን ወገኑን አዝኖ አከበረው እንጂ አላዋረደዉም ፤ ክብር ለሰዉ በሰዉነቱ ፣ክብር ለህዝብ በማንነቱ፣ ክብር ለወገን በወገንነቱ ፣መስጠት ልማታዊ ባያረግም ነገር ግን ስልጡን ያረጋል ሙሉ ስብዕናንም ያላብሳል።
ጉብኝቱን የፈቀደልዎት የጀርመን መንግስት ዘመዶችዎ በመጠለያ ጣቢያዉ እንደነበሩ አሳዉቀዉ ከሆነ ፣ይኼም ቢሆን ለራስዎ የፖለቲካም ሆነ የሞራል ኪሳራ ሲሆን ለመላዉ ኢትዮጵያዊ ግን ዉርደት ነው። የጀርመን መንግስት ለርስዎ ጣቢያዉን ማስጎበኘቱም ባለም አቀፍ የስደተኞች አያያዝና የደህንነት ህግ አንቀፅ ጥሰት ሊያስጠይቀዉ እንደሚችል ሊያዉቁትም በተገባ ነበር ፤ ይሔንንም ባደባባይ ሲያወሩ ባዶ አማኝና ባዶ ፖለቲከኛ መሆንዎን ነው የሚያሳየዉ ።ለዚህም ነዉ የፕርቶኮል አስፈላጊነት በመሪ ደረጃ እንዲህ ያሉ ተቀጣጣይ የሆኑ አነጋገሮችን ቀድሞ እሚያርመዉ፤ ያለበለዚያ ራስንም አገርንም ተኩሶ እንደመምታት ነዉ ። ጠቅላይ ሚኒስትራችን የፊንላንድ finish ተማሪም ሆነዉ ኸይም heim ምን ማለት እንደሆነ አለማወቆን በሚድያ መናገርም በዉነት የፖሊቲካ አሽሙርም (political sarcasm) አለያም ደግሞ መሞዳሞድ( humor) ሊሆን አይችልም፤ ይልቅ ትዝብት ዉስጥ ነዉ የጣሎት።ጠቅላይ ሚኒስትራችን በፊኒሽ Finish ምድር የዉሃ ጥናት ትምህርቶን ሲወስዱ master ማስተር አድርገዉ የወጡት በዉሃ ላይ መንሳፈፍን ብቻ ይመስላል ለዚህም ነዉ በፖለቲካዉም ከሞራሉም አኳያ ራስዎን ሳይሆኑ እንደብርቅዬዋ የፊንላንድ ዳክዬ ተንሳፈዉ የሚታዩት the whooper swan ።
ለዚህ ርዕስ መነሻ የሆነን የሰሞኑ ትኩስ የመነጋገሪያ ኣጀንዳ የሆነዉ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንጝግር ነዉ። ዋናዉ መልክታችን የሰዉየዉ የራሳቸዉን ህዝብ ማሳነሱና መዝለፉ ላይ ሳይሆን ሰዎቹ የተዘለፉበትን ምክንያቶች ላይ ትንሽ ለማለትና ምናልባትም ጠቅላይሚኒስትሩ ራሳቸዉንና ሰርዓታቸዉን ዞር ብለዉ ቢያዩበት ከሚል ነዉ።
ዛሬ በኢትዮጵያ ስለሚታየዉ የወጣት ሰቶች፣ ወጣት ዎንዶች ፣ የባለሙያ ምሁራን ስደት ዋናዉና ትልቁ ምክንያቱ የኢኮኖሚ ምኪንያት ሳይሆን ባገሪቱ ያለዉ የሰርዓት ኣልበኝነትና ስርአቱ ባመጣዉ የፖለቲካ ጫና ነዉ ።
ዛሬ ያለዉ የገዢዉ ሥርዓት በሰዉ ፍልሰት ንግድ በግልፅ በመሰማራቱና ባሰማራቸዉና ስርዓቱ በዘረጋዉ ዘመናዊ የሰዉ ንግድ ቀለበት ዉስጥ አንዲገቡ በተደረጉ ዜጎችና በተለይ ድግሞ ሆን ተብሎ በዘዴ የመሬት ንጥቂያና ዝርፊያዉ ባልተማሩና ምንም አይነት የስራ ሙያ ትምህርትና ልምድ በሌላቸዉ ሚስኪን የገበሬ ልጆች ከብቶቻቸዉን እና ያላቸዉን ጥሪት በዘዴ እንዲሸጡ እየተደረገ ገበሬዉን ያለዓምራች ሃይል እንዲሆን በማድረግና ያገሪቱን መሬት እና አንጡራ ሃብት ለዉጭ ባለሃብቶች አየተሰጠ በዛሬይቱ ኢትዮጵያ ዉስጥ ስዉም መሬቱም እኩል እየተሸጠ እንዲሰደድ በማስገደድና የመኖሪያ ቦታ በማሳጣትም ጭምር ነዉ።
እንዲሁም ዜጋዉን መሬት አልባና አገር አልባ በማድረግ ስደተኛ የሚል ተቀፅላ ስም ዎይንም መጠሪያ እንዲሸከም በመደረጉ ነዉ። ሰደተኛ በሚያደርገዉ የሥርዓቱ ዉጤት የዜጎች ስቃይና ያለፍላጎት የተሸከሙት ስደተኛ የሚለዉን ስም ነዉ ።
ዛሬ ያንድ ኢትዮጵያዊ የስደት ጉዞዉን እና አገር ለቆ የሚወጣበትን ሚክንያቶች በቅጡ ለተገነዘበ ሰዉ ኢትዮጵያዉያኖች ባገራቸዉ ያለዉን ከባድ ስራ ንቀዉ ሳይሆን ባገራቸዉ ያለዉን ከባድ የፖለቲካ ጫና፣ አፈና፣ ግድያ፣ እስር፣ የስራ ዕጦት፣ የምግብ ርሃብ፣ እና የነፃነት ርሃብና ፣ የቁም ቅዠት የሆነዉን የኑሮ ልዩነት ሽሽት የፍትሕ አለመኖር መሆኑ ግልፅና የማያከራክር ነዉ ።
እዚም በረንጆቹ አገር ዛሬ ያበሻን ስደተኛ በለበጣ ለተሻለ ሕይዎት ስደትን የሚመርጥ የስደት ገበያተኛ የሚል ቅፅል ስም አስከማዉጣት ተደርሶአል ፤በዚሁ አገር አባባል እንደወረደ አሲል ሾፐርስ asyl kjopers ፡ በንግሊዝኛዉ አሳይለም ሾፐር ASYLUM SHOPER ማለት ነዉ ። የዚን ወገን ህዝብ እመራለሁ የሚሉ ያገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሐይለማሪያም ደሳለኝ የዶሮ ዎጥ ይዘዉ መምጣታቸዉ ካዉሮፓ ዱቄት ሰፋሪዎች ጋር ሆነዉ የራስ ወገንን ችግር እያዩ ማላገጡ የሚያስከብር ሳይሆን ራስን እሚያዋርድና ራስንም መስደብ መሆኑን ልብ ሊሉት ይገባል ።ዱቔት ሲያቦኩ እና የሰዉ መኪና ተደግፈዉ ፎቶ እሚልኩ ያልዋቸዉ ወገኖች ናቸዉ በያረብ ሃገር ፣ባዉሮፓ፣ ባሜርካ ፣ኤሲያ ሌት ተቀን እየሰሩ ባገራችን ያለዉን የዘመናት ድህነት ለመቀንስና ቢያንስ የየራሱን ቤተሰብ በመደጎም ዙሪያ በዉጭ ያለዉ ኢትዮጵያዊ ስደተኛ ነዉ ትልቁን የለት ተዕለት ኑሮን በመሸፈን ላይ ያለዉ እንጂ መንግስት አደለም ዜጎቹን እየደጎመና እያኖረ ያለዉ ፣ መንግስት ይልቅ በተቃራኒዉ ህዝቡን ኣዋርዶ በያገሩ እየሔዱ ልመናን ስራዬ ብሎ ተያይዞታል ።
ባሁንዋ ኢትዮጵያ ዉስጥ መሬቱንና ልጁን በዘዴ ከተቀማዉ ያብዛኛዉ ማህበረሰብ ክፍል የሚገኘዉ ወጣት ስደተኛ ሴትም ሆነ ዎንድ በዓረብ ሐገራት ተበትኖ በግርድናም ይሁን በሞያ ስራ ላይ የተሰማራዉ ወገን ፡ በያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ቤተሰብና ማህረሰብ ከዛም አልፎ በዚያች አገር በተለይም የኢኮኖሚዉ ግንባታና የለት ተዕለት የህብረተሰቡ ኑሮ ዉስጥ ከፍተኛዉን ድጋፍና ተሳትፎ አያረገ ያለዉ ይኸዉ ባረብ ሐገራትና በሌላዉ ዓለም የተበተነዉ ሰደተኛ የተባለዉ ኢትዮጵያዊ ወገን ነዉ ።ይህ ደግሞ ሊያስመሰግነዉና ተበረታቶ ትክክለኛዉን የዜግነት ክብሩንና መብቱን ሊከበርለትና ዋስትና ሊኖረዉ ሲገባ ፤አሁን ያለዉ መንግስት በራስ ወገን ስቃይና ደም ፡ንግድ ዉስጥ ተገብቶ በራስ ዙሪያና ለራስ ብቻ እየተኖረ ወገንን ፡አገር አልባ አድርጎ የተበላሸ የዶሮ ወጥ ባዉሮፓና ባረብ አገር ይዞ መዞሩ ከሙቀቱ ወደ በረዶ – ከበረዶዉ ወደ ሙቀቱ ወጡን ይዘዉ ቢያጉዋጉዙ ትርፉ የዶሮ ወጡን ብቻ ሳይሆን ጠቅላይ ሚንስትራችንንም ሆነ ፖለቲካቸዉን እጅ እጅ እንዲሉ አድርጎዋቸዋል ።
ጠቅላይ ሚንስትሩ ስርዓታቸዉ ጠቅልሎ ባመጣዉ ችግር መልሰዉ ራሳቸዉ በራስ ወገን እና ዜጋ ላይ ማላገጥ አዋቂነት ሳይሆን ራስንና አገርን ማዋረድ ነው ። በጀርመን ሐገር የሚገኘዉን ‘ኸይም ‘ Heim መጠለያ ጣቢያ ሂደዉ፣ ዱቔት ሲፈጩ ባዩት ከማላገጥ የሰሩትን ዶሮ ወጥ በትኩሱ ባገር ቤት ጠርተው የበተኑትን ወገን ሊያበሉት ቢሞክሩ ምንኛ በመጠናቸዉ ፣ዶሮ ወጥ ሰርተዉ ባገሪቱ ጎዳና በየቦታዉ ለወደቁ ህፃናትና አረጋዊያን ቢያበሉ ምንኛ በመጠናቸዉ ፣የሰሩበትን ያመታት ጥሪት በገዛ አገራቸዉ በጉምሩክ ፈታሽና በግዜዉ ባለስልጣኖች የተዘረፉት ሴት እህቶቻችን በየመንገዱ ቀን ለቀን ባዶአቸዉን ግራ ገብቷቸዉ ያሉትን ፣እንደገና ዳግም ለመከራ ስደት መንገድ ላይ ያሉትን -በሰዉ ሐገር ያለዉን ከሚጎበኙ በገዛ አገሩ ሰደት ዉስጥ ያለዉን ቢጎበኙ ምንኛ መልካም ነበር።
እርግጥ ነዉ በዚ ልማታዊ መንግስት ዛሬ ኢትዮጵያ ዉስጥ የፈረንሳይ የታሸገ የመአድን የተጣራ ዉሃ french evian mineral water ገዝቶ የሚጠጣ ባለግዜ የደሃ ሃገር ቡርዥዋ እንዳለ ሁሉ ከቆሻሻ ገንዳ ከዉሻ ጋር እየተጋፋ በተራቡ እና በደከሙ ጣቶች የቁሻሻ ገንዳ ዉስጥ ሲቆፍሩ የሚዉሉም አሉ ፤ይኼንን ሃይማኖተኛዉና ፖለቲከኛዉ ጠቅላይ ሚንስትራችን ምናልባት ከየትኛዉ የስራ ዘርፍ ዉስጥ እንደመደቡት ባናውቅም ዛሬ ያ ሚስኪን ወገን ወስፋቱን መዝጊያ ለማግኘት ፡ከጠዋት እስከማታ ከተራቡ ዉሾች ጋር መከራዉን ሲቆፍረዉ እየኖረዉ ነው ፣ ጠቅላይ ሚንስትራችን ሰደተኛዉን ባገሪቱ ዉስጥ ያለዉን ከባድ ስራ ሸሸተዉ የወጡ ብለዉናል ፤ እንዴት አይሸሽ ከባዱስ ስራ የትኛዉ ይሆን?? ለጠቅላይ ሚንስትራችን ፣ ሰዉ ተሰልፎ በቁሙ ለጉርሻ ትርፍራፊ ምግብ ባደባባይ ሲሰለፍ ፣ ህፃናት በጎዳናና በመማሪያ ክፍል መሃል ከተማ ዉስጥ እየተራቡ ፣ ወገን በቁሙ በየበረሃው በቁሙ እየተበለተ፣ ወገን በየሃይቁ እንደሳርዲን ታጭቆ ፡ በመጨረሻም እንደ ጉማሬ ተነፍተዉ ዉሃ አንሳፎ እየተፋቸዉ በመላዉ ዓለም እየታየ፣ እንደዕባብ በሰዉ አገር እየተቀጠቀጡ ፣ እንደዓሳ በዘይት ፊታቸዉ እየተጠበሰ ፣ በጠራራ ፀሃይ መህል ከተማ ዉስጥ ወጣት ሴት ልጅ በግፍ ተድፍራ ስትገደል ሴቶች እንዴት ሸሽተዉ አይሰደዱ ?? ተነግሮ የማያልቀዉን መከራና ስቃይ ሲጋት እሚኖረዉ በዝቶ እያለ፣ጠቅላይ ሚንስትራችን ይሔን የማህበራዊና የኢኮኖሚ የፖለቲካ ቀዉስ ስደተኛዉ ላይ ደፍድፈዉ በራስ ጥጋብና ምርጫ ህዝቡ እንዳመጣዉ ተደርጎ መዘባበት ትናንት እንደተባለዉ ከርስዎ በፊት በነበሩት ጠቅላይ ሚንስትር ስለድርጀቶ የተነገረዉን መንቀዝና የፖለቲካ የመጨረሻዉ ብስባሴ ባንድ ዎቅት አሰምተዉን ነበር አሁን ማን ይንገረን ? ?
ከሞራልም አኳያ ቢሆን በየትኛዉም የዕምነት መፅሐፍ ቅዱስ ዉስጥ እንዲህ አይነቱን ስብዕናና ክፋት – በሀይማኖት የቅዱስ መፅሐፎቻቸዉ መገሠጭያውንም ማስተማሪያዉንም ከትበዉ ይዘዋል ፤ያን ላንባቢያን እንደምርጫቸዉ ስንተወዉ ለሞራልና ለግብረግብ እንዲሁም ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የዕምነት አባቶች ግን የሳቸዉን አነጋገርና ትዕቢት ክፍተቱን ከሞራልና ከክርስትና አኳያ እንዴት እንደሚሞሉት በማስተዋል እንጠብቃለን ፣ሰማይ አይታረስ ንጉስ አይከሰስ ከሆነም ከነማብራሪያቸዉ እንጠብቃለን።
ጠቅላይ ሚኒስትራችን እንዴት እንደሚረዱትና እንደሚያዩት ባናውቅም ዛሬ ያለዉ ሃበሻ ኢትዮጵያዊ ባሜሪካም ሆነ ባዉሮፓ ያለዉ ሂስፓኒክ አደለም ፣ዛሬ ባረብ አገር ያለዉ ሃበሻ- ኢትዮጵያዊ ፡ ይሁዲ አዶለም ይሔንን እሳቸዉ ተምረዉ ባደጉበት የፖለቲካም ሆነ የሃይማኖት ትምህርት የህዝብ የራስ ወገንን ክፍተኛ ፍልሰት exodus ለያይተዉ ማየት አለመቻላቸዉ ምናልባትም ያገዛዙ ዋና ኤሊትሶች ፈረንጆቹ horse hood ሆርሰ ሁድ የሚሉትን ለሳቸዉም ባንገታቸዉ አጥልቀዉላቸዉ ይሆን ? እንዲህ ግራ ቀኙን እንዳያዩ አድርገዉ እሚጋልቧቸዉ? ፣እጅ- እጅ ብሎ እጅ- እጅ ካለ የዶሮ ዎጥ ጋር ዝም ብሎ መጋለብ ፣ አሳፋሪም አስነዋሪም ነዉ።
ተፃፈ – ስለ- ክብር፤ ለመላዉ ስደተኛ ኢትዮጵያዊ ሁሉ እንዲሁም በህይዎት ለሌሉ እና ባገራቸዉም ካገራቸዉ ዉጭ በግፍ ላለቁ ሁሉ።
No comments:
Post a Comment