ኢትዮጵያውያን ለውጥ እንፈልጋለን:: ለውጥ እንፈልጋለን ብለን ለትግል ስንነሳ መንገድ ሁሉ አልጋ በአልጋ ይሆንልናል ማለት አይደለም::በትግሉ ውስጥ የሚከሰቱ እሾህ እና አሜኬላዎች እንቅፋት ሆነው ከስንዴው እኩል እንደ እሸት የሚያብቡ እንክርዳዶች እየሰረጉ በመግባት ትግሉን ለማኮላሸት አሊያም ደሞ ተያይዘው ለመጥፋት በሚያሴሩት ደባ የህዝብ ልጆች በሚያደርጉት ተጋድሎ እነዚህን እንቅፋቶች ማስወገድ እና በጥንካሬ ጋሬጣውን ማለፍ የሚጠበቅበት ወቅታዊ አጋጣሚዎች ሳንዘናጋ ልንጠቀምበት ይገባል:: በትግል ጊዜ የሚከሰቱ እንቅፋቶች ለነገ ትልቅ ትምህርት የሚሆኑ ወርቃማ ጊዜያት አድርገን ልንማርባቸው ይገባል::
ኢትዮጵያውያን ላለፉት 24 አመታት በጫንቃችን ላይ የተቀመጠውን አምባገነን ስርአት ለማስወገድ በተገኘው መንገድ ታግለን በወያኔ መቃብር ላይ ነጻነታችንን ለማረጋገጥ ሁላችንም በተለያዩ የትግል ስልቶች ደፋ ቀና እያልን የምንገኝበት ወቅት ላይ መከሰታችን እሙን ነው:: ይህ ትግል ለለውጥ እና ለነጻነት መደረጉ እና የጋራ ጠላት የሆንው ወያኔ ላይ ማተኮሩ ደሞ ሕዝባዊ አንድነቶች እንዲጎለብቱ አስታውጾ ሲያበረክት ያልበሰሉ እና የፖለቲካ እውቀቱ የሚያንሳቸው በትግሉ ዙሪያ ሰበብ በማብዛት ዋጋ ባሌላቸው ነገሮች ላይ በማተኮር እንዲሁም በሌላው ዘርፍ ለሆዳቸው ተገዢ በመሆን ሌላውን አሳልፎ በመስጠት አንድም ከሃገር በመውጣት አልያም ኑሯቸውን በሃገር ውስጥ በማደላደል ትግሉን ለራስ ጥቅም ብሎም ሌላውን ለመጥለፍ ሲጠቀሙበት ማየት የሚያም ጉዳይ መሆኑ የዚህን ሰሞን ጡዘቶች ያሳያሉ::
ወቅቱ ትግሎች ተፋፍመው ሕዝባዊ ድሎች በሚገኙበት በአሁን ወቅት የሃገር ቤት ትግሎችን እና በዳር ሃገር ያሉ ትግሎችን በማስተባበር አንድ ወጥ የሆነ የትግል ስትራቴጂ በሚቀጣጠልበት ጊዜ ላይ በትግል ውስጥ በሚከሰቱ እንቅፋቶች ራሳችንን ሳናዘናጋ አሊያም እንቅፋቶችን ሌላውን ለመጥለፍ እና ለማደፍረስ ሳንጠቀምበት በሰለጠነ መልኩ ከተከሰቱ ችግሮች ተምረን ለአዳዲስ ስልቶች ጥንካሬያችንን ማደስ ይገባናል::በትግል ውስጥ የሚከሰቱ አሜኬላዎች/አረሞችን ነቅሎ ለመጣል ዋናው እና መጀመሪያ የሚያስፈልገው የኛ እና የኛ ጥንካሬ ነው::አንዳንድ ጊዜ በሚደርሱ እንቅፋቶች ሳንዘናጋ እና ሳንገዳገድ በራስ መተማመን እና የትግል ጽናትን በውስጣችን በማስረጽ ለተሻለ ድል መገስገስ አንዱ የትግል ስልት ሊሆን ይገባል::ጥንካሬ ከራስ መተማመን እና ከጽናት እንደሚፈጠር እና ብረት ሆኖ መገኘት እንዲሁን ራስን በየጊዜው እያዳበሩ መታገል ከዝገትነት ይከላከላል::ዛሬ ላይ ለሚገጥሙ እንቅፋቶች ለመሸፋፈን ከመሮጥ በጊዜው ተመካክሮ እና ተወያይቶ ችግሮን በመፍታት ለነገ ትግል ሂደት መንገድ መጥረግ የሚጠበቀው ክኛ ሆኖ ሳለ እንቅፋቶችን/ችግሮችን በጊዜው ካላስወገድን እና ከሸፋፈንን የተገላለጠ እና የፈነዳ እለት ትልቅ ጉዳት እና ተአማኒነት ሊያሳጣ ይችላል::
በትግል ውስጥ ሊከሰቱ የሚችሉ እንቅፋቶችን በጥንካሬ ልናልፋቸው የሚገባው እንግዲህ ከዚህ አኳያ ነው::ጥንካሬያችን ነገ ለሚፈጥረው ትውልድ ትልቅ ትምህርት እና የነጻነት ባለቤት ስለሚያደርገው የሃገራዊ እና የህዝባዊ የትግል ሃላፊነቶችን ተሸክመን በድን አደባባይ ለማስቀመጥ እና ታላቅ የሆነ የለውጥ አብዮት አቀናጅተን በመፍጠር ሳንዘናጋ የትልቅ ህዝባዊ ድል ባለቤት ለመሆን በአንድነት እንጠንክር::

No comments:
Post a Comment