ስንታየሁ ከሚኒሶታ
በቅርቡ በጀርመን ሃገር የሙዚቃ ኮንሰርት አዘጋጅቶ በሕወሓት መንግስት ደጋፊነቱ የተነሳ ቦይኮት የተጠራበትና በኪሳራ የተመለሰው ድምፃዊ ማዲንጎ አፈወርቅ በቅርቡ ስላወጣው አልበም ቴዲ አፍሮ በኢትዮጵያ በሚተላለፍ አንድ ራድዮ በመቅረብ ስለድምፃዊው ዘፈን ጥሩ በማውራት ፍቅር አስተማረው::
ወ/ሮ አዚብ ትመራው በነበረው ሜጋ ኪነጥበባት ማዕከል ውስጥ ሠራተኛ የነበረው ማዲንጎ የሕወሓት መንግስት አፍቃሪ ከመሆኑ የተነሳ በተለይ ከመንግስት ጋር የማይተባበሩ አርቲስቶችን ልክ እንደ ሰራዊት ፍቅሬ “አቃጣሪ” በመሆን በመንግስት በማስጠመድ እና ሥራዎቻቸው በመንግስት ሚዲያዎች እንዳይተላለፍ ሲያስደርግ ቆይቷል:: ድምፃዊው በሕወሓት መንግስት ደጋፊነቱ በመመጻደቅ ወያኔ የሰሜን አሜሪካውን አመታዊ ስፖርት ፌስቲቫል ለሁለት በሰነጠቀበትና ተለጣፊ ባዘጋጀበት ወቅት በተለጣፊው ቡድን ውስጥ ሆኖ ዋሽንግተን ዲሲ በመምጣት ለከፍተኛ ኪሳራ ተጋልጦ ነበር::
ማዲንጎ በተለይ ቴዲ አፍሮ ታስሮ በነበረበትም ወቅት ሆነ ከተፈታ በኋላ በሰራው ጥቁር ሰው አልበም ዙሪያ ከሕወሓት ባለስልጣናት ጋር በመሆን የማጣጣል ተግባር ሲፈጽም የቆየ ቢሆንም ፍቅር ያሸንፋል የሚለው ድምፃዊ ቴዲ አፍሮ ስለ ማዲንጎ አፈወርቅ አልበም አስተያየት ስጥ ሲባል ስለአልበሙ መልካም ነገር ከመናገሩም በላይ በተለይም ጎዳናው የሚለው ዘፈን መልካም እንደሆነ በራድዮ ቀርቦ በመናገር ለድምፃዊው ፍቅር ምን እንደሆነ አስተምሮታል::
ጎንደር ተወልዶ ያደገው ማዲንጎ የሕወሓት መንግስት ደጋፊ በመሆኑ የሚመጻደቅ ከመሆኑም በላይ ኢትዮጵያ ከኢሕ አዴግ በላይ ማንንም መልካም መሪ አታገኝም ሲል ገንጣዩን መንግስት የሚደግፍ አርቲስት ነው::
No comments:
Post a Comment