የኢትዮጵያ ህዝበ የተለያዩ የሰላማዊ ትግል ዘዴዎችን በመጠቀምም ለመብቱ መከበር የሚያደርገውን ጥረት ቀጥሏል፤ ወጣቶች ብሶቶቻቸውን በብር ኖቶች ላይ ጽፈው ገበያው እንዲያዘዋውራቸው እያደረጉ ነው። ይህም “የወረቀት ገንዘብን ለተሠራበት ዓላማ ብቻ ተጠቀሙ” የሚለውን ህግ በመጣስ ለቅስቀሳ ሥራ መጠቀም በመሆኑ የሕዝባዊ እምቢተኝነት አካል ነው። በሚቀጥሉት ጥቂት ወራት ውስጥ በርካታ የወረቀት ገንዘቦች በምሬት መግለጫነት ይውላሉ ተብሎ ይገመታል። ምስሎቹ በማህበራዊ መድረኮች በከፍተኛ ሁኔታ እየተሰራጩ ነው።
No comments:
Post a Comment