Saturday, March 14, 2015

የሀገርና የቤተክርስቲያን ታሪክ ጠላት ስውሩ ተኩላ ዳንኤል ክብረት! – ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
የዓለም መድኃኒት የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል ሰሞን የዘንድሮውን (2007ዓ.ም) ማለቴነው አንድ ወንድሜ በሙያው የህክምና ዶክተር (ሠራየ ሕማም) ይደውልና ሊያገኘን እንደሚፈልግ ይነግረኛል፡፡ ተቀጣጥረን ተገናኘን፡፡ በእጁ ሁለት መጻሕፍት ይዟል፡፡ በመጽሐፈ ገጽ (ፌስ ቡክ) ላይ በኢቴቪ (ኢቢሲ) የገና በዓል ዝግጅት ዲ/ን ዳንኤል ክብረትና አቶ ውብእሸት ወርቅ አለማሁ ከአገዛዙ የተሰጣቸውን ተልእኮ ለመወጣት ዲ/ን ዳንኤል እኛ ኢትዮጵያዊያን ብንበላው የማንጨርሰው ሀብት ያለን ስለሆነ በፍጹም መሰደድ እንደሌለብን አቶ ውብሸት ደግሞ ኢኮኖሚያችን እንዳደገ ግንባታ በግንባታ እንደሆንን የተናገሩት ነገር አስቆጥቶኝ የጻፉኳትን አጭር መልእክት “ዲ/ን ዳንኤል ክብረት እውነት ብለሀል በልተን የማንጨርሰው ሀብት ነበረን ነገር ግን ወገን የሚሰደደው ይሄ ጠፍቶት አይደለም፡፡
ጸሐፊ ሆነህ እንዴት ይሄ ይጠፋሀል? ነው ወይስ እንደሚባለው…..ዜጎች መራራ ሞትን እየተጋፈጡ አስቀድመው በዚያ መንገድ ስደት የወጡት በበረሀ እንደረገፉ በባሕር እንደሰጠሙ የሰማይ አሞራ የአራዊትና የዓሣ ሲሳይ ሆነው እንደቀሩ እያወቁ ግን ሳይፈሩ ለምን በዚያው መንገድ ሞትን ተጋፍጠው እንደሚሰደዱ ልንገርህ? በገዛ ሀገራቸው ካልወየናቹህ በስተቀር ሠርታቹህ መብላት፣ ትምህርት መማር፣ የመሰላቸውን ኅሊናቸው ያመነበትን አስተሳሰብ አመለካከት ይዘው በነጻነት መኖር ፈጽሞ አትችሉም ስለተባሉ፣ አማራ በመሆናቸው ብቻ እንደ በደል ተቆጥሮባቸው በሀገራቸው መኖር ስላልቻሉ ነፍሳቸውን ለማትረፍ፣ ሀገሪቱ የአንድ ጎሳ ብቻ እንድትሆን ስለተደረገ እንደ ዜጋ ሠርቶ የመብላት ዕድል ስለሌለ፣ ባጠቃላይ ዜጎች ምንም ነገር የማድረግ ዕድል ስላጡ በገዛ በሀገራቸው ሕይዎት ጭንቅ ጥብ ስለሆነችባቸው ነው እሽ? ከዚህ የማይሻል የለም ብለው የሚሰደዱት፡፡ ይሄ ላንተ ይጠፋሀል ብየ አይደለም ልታምታታው የፈለከውንና የምታደናቁረውን ሕዝብ ያለበትን ችግር የሕዝቡን ሕይዎት የማያውቁ የሩቅ ሰዎች ካሉ እውነቱን ለነሱ ለመግለጽ እንጂ፡፡ ዜጎች በእነዚህ ችግሮች ምክንያት የሚሰደዱ ከሆነ መፍትሔው ምን እንደሆነ ይጠፋሀል ብየ አላስብም ልታደርጉት ስለማትሹ እንጅ፡፡
ነጭ ልብስ መልበስን ከምሥራቃውያን እንደተዋስን አድርገህ ያወራኸውም የተሳሳተ ነው፡፡ እንዲህ ዓይነት ብዙ የተሳሳቱ ነገሮችን በግምት እያወራህ ብዙ እያሳሳትክ ነው፡፡ እኛ ነጭ ልብስ የምንለብሰው ከምሥራቃዊያን ተውሰን ሳይሆን ከጥንት ጀምሮ ከጥጥ የሚሠራው ሸማችን በተፈጥሮው ነጭ ስለሆነ ከዚያ የመጣ ነው እሽ ዲ/ን ዳንኤል? በአጋጣሚ ደግሞ ከሃይማኖታዊ አስተምህሮ ጋራ ተጣጣመልን፡፡ ይሄው እንደምንታየውም እናምርበታለን እንደምቅበታለን፡፡
አቶ ውብሸትም የእርስዎ ኢኮኖሚ አድጎ ከሆነ ይንገሩን ሕዝቡ ግን ሁለቴ እንኳን መመገብ አቅቶት በቀን አንዴ ለመመገብ ተገዷል ድህነት እየጠናበት ሄዷል ይሄም ሆኖ በውስኪ የሚታጠቡ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር አንጻር ሲታዩ ከ1% በታች የሆኑ ወገኖች እንዳሉ ግልጽ ነው፡፡ የእነሱ ስኬትና እድገት ግን የሀገር ወይም የሕዝብ አይደለም፡፡ እኔም እርስዎም ሁሉም ሰው የሚያውቀው የሚሠራው የጥራት ደረጃው ብላሽ የሆነ መንገድም ሆነ ሌላ ሥራ በእርዳታና በብድር ገንዘብ የሚሠራ መሆኑን፣ የሚሠሩት ሰማይጠቀስ ሕንፃዎች በሙሰኛ ባለሥልጣናትና በአጋር ተሟሳኝ ባለሀብቶች ከሀገርና ሕዝብ እየተዘረፈ የተሠራ መሆኑን ነው እንጅ በዚህ አገዛዝ የሚመራው ጥቂቶችን ብቻ ተጠቃሚ የሚያደርገው የምጣኔ ሀብት እንቅስቃሴ ባመነጨው ሀብት አይደለም፡፡ ይሄ የሀገር ውድቀት እንጅ የሀገር እድገት አይደለም እሽ አቶ ውብሸት? ምናልባት የእነሱ ብቻ እድገት ማለት ይቻል ይሆናል፡፡ እርስዎም ይሄ የሚጠፋዎት አይመስለኝም አፍዎን የጥቅም ተጋሪነት ስለሸበበው እንጅ፡፡ ለመሆኑ መቸ ነው ይሄንን ትዕዛዝ የተቀበላቹህት? አቶ ውብሸት ሀገሪቱ እንደለማች እንዲያወሩ ዲ/ን ዳንኤልም ሀገራችን የሞላት የተረፋት ስለሆነች መሰደድ እንደማይገባ ሕዝቡን እንድትሰብኩ እንድትደልሉ? እርግጠኛ ነኝ ነገ ደግሞ በግልጽ በካድሬነት የምታወሩት ብዙ ነገር ይኖራል፡፡ በቅርቡ ወያኔ ባወጣው ሰነድ ላይ ከሕዝቡ ጋር መግባባትን ለመፍጠር እናንተን አሁን እያወራቹህት ያለውን ነገር እንድታወሩ ማድረግ አንዱ አቅዱ እንደ ሆነ በነጻው የብዙኃን መገናኛ ስሰማ እውነት መሆኑን ለማመን ተቸግሬ ነበር እናንተ ግን ቀድሞ ተወርቶም እንኳን ተነቅቶብናል ብላቹህ ሳታፍሩ ይሄው አድርጋቹህት ሳይ ገረመኝ በጣም ያሳዝናል! ምንደኛ ሁላ”
የምትል ነበረች እሷን አንሥቶ ስንጫወት ቆየንና ወደፈለገኝ ጉዳይ ገባ፡፡ ከሁለቱ መጻሕፍት አንዱን አነሣና ይሄንን መጽሐፍ አንብበኸዋል? ሲል ጠየቀኝ እንዳላነበብኩት ነገርኩት የማን እንደሆነም ጠየኩት የዳንኤል ክብረት እንደሆነ ነገረኝ ርእሱ “ስማቹህ የለም ይላል” መጽሐፉን ገለጠና “የሌለውን ፍለጋ” በሚል ርእስ የተጻፈውን አውጥቶ እንዳነበው ጋበዘኝ፡፡ እኔ ዳንኤል ከጥፋት ኃይሎች ጋር ተሰልፎ ሽ ጊዜ የጥፋት ዓላማ ቢኖረው የዚህን ያህል ጥፋት ይሠራል ብየ ለመገመት በጣም እቸገራለሁ፡፡ ጭራሽ በመጽሐፍ ደረጃ ፀረ ኢትዮጵያና ቤተክርስቲያን የሆነ ጽሑፍ ይጽፋል ብየ አልገምትም ነበር፡፡ ብቻ ከላይ ከአቶ ውብሸት ጋር ሆነው እንዳሉት ዓይነት ነገሮችን እየተናገረ እየጻፈ አገዛዙን ያገለግላል፤ ባይሆን በስውር ግን በደንብ ያገለግላቸው ይሆናል ብየ አስባለሁ እንጅ እንደዚህ ዓይን ባወጣና ድፍረት የተሞላበት ተግባር ይፈጽማል ብየ በጭራሽ አላስብም ነበር፡፡ እጅግ እየገረመኝ አነበብኩት፡፡ ወዳጀም የተፈጠሩበትን ጥያቄዎች እያነሣ ድፍረቱ እንደገረመውና ጉዳዩ በእርግጥስ እሱ (ዳንኤል) እንዳለው ነው ወይ? እያለ ጠየቀኝ ብዙ አወራንና ተለያየን፡፡
እኔ ዳንኤልን የማውቀው የማኅበረ ቅዱሳን ንቁ አገልጋይ በነበረበት ጊዜ ነው፡፡ ሲያገለግል ቆይቶ ከዓመታት በፊት ጥሎ ወጣና እስከአሁንም ድረስ በግሉ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ አሁንም ጥቂት ከማይባሉ ዓመታት ወዲህ ጀምሮ ጥቂት በጥቂት ሲል ቆይቶ አሁን እንዲህ ራሱን በደንብ እስከገለጠበት ጊዜ ድረስ ማንነቱን ሲገልጽ ቆይቷል፡፡ ይህ ከዓመታት ወዲህ የያዘው ማንነቱ ከቀድሞ ጀምሮ እንዳልነበረ በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል፡፡ ጊዜው በትክክል በማይታወቅ ወቅት ባለፈው ጊዜ “በአይሁዶች መርዘኛ ጥርስ የገባች ሀገር ኢትዮጵያ!” በሚል ርእስ በጻፍኩት ጽሑፍ ላይ እንደገለጽኩት የሚፈልጓቸውን ሰዎች ማንነታቸውን በማጥናት እያደኑ የጎሰኝነትንና የጸረ አማራ የጥላቻ መርዘኛ መርፌ የሚወጋው ክፍል መርዘኛውን መርፌ ወግቶት ከልቡ ውስጥ የነበረውን ሃይማኖት አጥፍቶ ወደ መርዘኛ ተኩላነት ለውጦት ዐረፈው ወያኔም ሆነ፡፡ እንደ ወያኔነቱም ባገኛቸውና በተመቻቸለት መድረኮች ሁሉ አገዛዙን የሚጠቅሙ ነገሮችን በመናገር በመጻፍ በመሥራት ወያኔን እያገለገለ ይገኛል፡፡ ወያኔን የሚቃወሙ ጎላ ጎላ ያሉ አካላትንና ግለሰቦችን ብቻ እየመረጠ አድፍጦ እንደውሻ በመንከስ ያቆስላል፡፡ ተናክሶ ዞር ይላል እንጅ ለመወያየት የሐሳብ ፍጭት ለማድረግ ፈጽሞ አይፈልግም፡፡ ዓላማውም እሱ አይደለምና፡፡ የጻፏቸውን የወያኔን ግፍና ወንጀል የሚያጋልጡ መጻሕፍቶቻቸውንም በሕዝብ ዘንድ ተአማኒነት እንዳያገኙ እንደ ምንም ብሎ ይጠጋና የጻፉት ሐሰትና የፈጠራ እንደሆነ ይናገራል፡፡ ለምሳሌ ኤርሚያስ ለገሰ፣ ተስፋየ ገብረአብ የመሳሰሉት፡፡ ተስፋዬ ገብረአብ ስለ አኖሌ የጻፈው የፈጠራና ሰይጣናዊ ዓላማ ያለው እንደሆነ ማንም ያውቃል ስለ ወያኔ የጻፈው ግን እንዲያውም የሚገባውን ያህል እንዳልጻፈ መረዳት ይቻላል፡፡ ዳንኤል አኖሌን ወይም ስለ አቡነ ተክለሃይማኖት የጻፈውን ብሎ ነጥሎ ቢጠራ በተስማማኝ እሱ ግን በጥቅሉ ነው መጽሐፎቻቸውን ውሸትና ፈጠራ ነው የሚለው፡፡
በዳንኤል ከተነከሱ ሰዎች አንዱ ፕሮፌሰር መስፍን አንዱ ናቸው “መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ” የሚል መጽሐፋቸውን እንዳሳተሙ በርእስ የተገለጸውን የመጽሐፉን ማጠንጠኛ ሐሳብ ከአውድ ውጪ በመውሰድ ቆንጽሎ አውጥቶ ታሪክ አይከሽፍም በማለት ፕሮፌሰርን ለመተቸት ለመንቀፍ ሞከረ፡፡ ዓላማው ግን እንደ ወያኔ ቅጥረኛነቱ ጥቃት በተነጣጠረባቸው ሰዎች ላይ ጥቃት መፈጸም እንጅ መማርና ሊያስተምረው የሚችለው ነገር ካለም ማስተማር አይደለምና ቦጭቆ ዞር አለና “ተወያይ ተነጋገር ሐሳብህን አጋራ ያልገባህን ትረዳለህ የተገለጸልህ ካለ ደግሞ ታጋራለህ” ቢባል ጉድጓድ ውስጥ እንደገባች አይጥ እራሱን ሰወረ ትንፍሽ አልልም አለ፡፡ የገረመኝ ነገር ይሄ በሆነበት ሰሞን በኢቴቪ ከምሽት 2 ሰዓት ዜና በኋላ በቀረበ በአንድ ዝግጅት በታሪክ ጉዳይ ላይ ጠይቀውት ሲመልስ ምን አለ? “እኔ እንዲያው ታሪክን ኤዲት ማድረግ ቢቻል ይሄ ዘመነ መሳፍንት የሚባለውን መጥፎ የታሪካችን ክፍል ቆርጨ ከታሪካችን አወጣው ነበር” አለና ዐረፈው፡፡ አየ ዳንኤል! ፕሮፌሰርስ ታዲያ ምን አሉ?
የዳንኤልን ጽሑፎች የሚያነቡ ሰዎች እንደሚሉት እስከ ዛሬ ድረስ ለአንድም ጊዜ እንኳን ቢሆን ጸሐፊ ነኝ እንደማለቱ በወያኔ ከሰብአዊ መብት ገፈፋ እስከ የዘር ማጥፋት ከሙስና በዜጎች ላይ እስከሚፈጸሙ ኢሰብአዊ ጥቃቶች ከአሥተዳደር በደሎች እስከ ሐሳብን በነጻ የመግለጽ መብት መነፈግና ያለ ጣልቃ ገብነት እምነትን በነጻ የማራመድ መብትን እስከማጣት በታመሰች ሀገር ውስጥ ሆኖ እንደጸሐፊ አይደለም እንደዜጋ እንኳን በእነዚህ ነገሮች ላይ አንድም ነገር ተናግሮ ተንፍሶ አያውቅም፡፡ እዚህ ላይ ግን ጌቶቹ ማለት ወያኔ ስሕተት ሠርቷል እንዳይጠረጠርበት ለማድረግ ለማስመሰል እንኳን በአንዳንድ ነገሮች ላይ እየተቃወመ እንዲጽፍ ለምን ማድረግ እንዳልፈለገ ይገርመኛል፡፡
እኔ ዳንኤል መመረዙን ለመጀመሪያ ጊዜ የተረዳሁት የላይፍ መጽሔት በቅጽ 7 ቁጥር 102 መጋቢት 2005ዓ.ም. ከእሱ ጋር ያደረገውን ቃለመጠይቅ ባነበብኩ ጊዜ ነበር፡፡ ይመስለኛል እኔ የዳንኤልን ጽሑፎች ስላላነበብኩ እንጅ እርግጠኛ ነኝ ከዚያም በፊት ከዚያም በኋላ ባሉ ጽሑፎቹና ቃለ መጠይቆቹ ሌሎች ተመሳሳይ ነውረኛና መሠሪ ድርጊቶቹን ሊገልጡ የሚችሉ ጽሑፎችም ሆኑ ንግግሮች ይኖራሉ፡፡ በጠቀስኩት ወቅት ከላይፍ መጽሔት ጋር አድርጎት የነበረው ቃለ መጠይቅ ግን የልጁን ማንነት (የልጁን አልኩኝ? የስንት ጊዜ ታላቄን) ቁልጭ አድርጎ ያሳየ ነበር፡፡ እንዳነበብኩት ሰው መስሎ አልታይህ ነበር ያለኝ፡፡ ከሱ ያልጠበኩት ቆሻሻና እርኩስ አረማዊ ማንነቱ ኅሊናየን እጅግ እረበሸው፡፡ ፎቶዎቹን ሳይ ዲያብሎስን ያየሁ ያህል ይቀፈኝ ጀመር፡፡ ግን ለምን እያልኩ እራሴን ደጋግሜ ጠየኩ በወቅቱ ጥቅም በልጦበት ተራ ጥቅም ፍለጋ ወይም ደግሞ ሚስቱ ትግሬ ስለሆነች ሚስቱን ለማስደሰት መስሎኝ ነበር፡፡ ነገሩ እየጠራ ሲመጣ ግን ከተራ ጥቅም ፍለጋና ሚስቱን ከማስደሰትም በላይ የከበደ ሆኖ አገኘሁት፡፡
በዚያ መጽሔት ላይ ዳንኤል በቃለ መጠይቁ የተናገራቸው ነገሮችንና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን በሚቀጥለው ጊዜ እመለስበታለሁ አሁን “በስማቹህ የለምና ሌሎች” በሚል ርእስ ባሳተመው መጽሐፍ ውስጥ “የሌለውን ፍለጋ” በሚል ርእስ ወደ ጻፈው ጽሑፉ ልለፍ፡-
ተኩላው “ስማቹህ የለም” በሚል ርእስ ባሳተመው መጽሐፉ ላይ እጅግ በጣም በሚገርም ድፍረት የወያኔነቱን ተልእኮ ከውኗል፡፡ በዚያ መጽሐፍ ውስጥ “የሌለውን ፍለጋ” በሚል ርእስ በጻፈው ጽሑፍ ላይ የአቡነ ተክለሃይማኖትን ገድልና ክብረ ነገሥት የሚባለውን የሀገርና የቤተክርስቲያን ታላቅ ታሪክ ተራኪ ሀብትና ቅርስ ተአማኒነት ለማሳጣት ከፍተኛ ጥረት አድርጓል፡፡ ተኩላው በክብረ ነገሥት ላይ ሰፊ ሽፋን ተሰጥቶት የሚተረከውን በዓለማዊያኑ የታሪክ ጸሐፍት ዘንድ “ሰሎሞናዊ” በቤተክርስቲያን ደግሞ “የዳዊት መንግሥት” እየተባለ የሚጠራውን ሥርዎ መንግሥት በሀገራችን አልነበረም በማለት ክብረ ነገርትንና ይሄንን የክብረ ነገሥትን ታሪካዊ ትረካ የሚጠቅሱና የሚያረጋግጡ ከገድላት እስከ ድርሳናት ከተአምራት እስከ ፍካሬያት ከሊቃውንት እስከ ትርጓሜያት ያሉትን የቤተክርስቲያን መጻሕፍትን ሐሰተኛ አድርጓቸዋል፡፡
ተኩላው ከእነኝህ ክብረ ነገሥት የሚተርከውን የዳዊት (ሰሎሞናዊ) ሥርዎ መንግሥት ትረካ በተለያየ መንገድ ከሚያረጋግጡት ከሚተርኩት የቤተክርስቲያን መጻሕፍት አንዱ የሆነውን የአቡነ ተክለሃይማኖትን ገድል ይወስድና አቡነ ተክለ ሃይማኖት የኢትዮጵያ የመንግሥት ሥልጣን በመሀል ከገቡት ከዛጉዌ ሥርዎ መንግሥት ተመልሶ ወደ ዳዊት ሥርዎ መንግሥት እንዲመለስ ስለማድረጋቸውና ከይኩኖ አምላክም ለቤተክርስቲያን ሲሦ ድርሻ ስለማሰጠታቸው የሚተርከውን የገድላቸውን ክፍል እንዲህ የሚል ነገር በአቡነ ተክለሃይማኖት ገድል ላይ ፈጽሞ የለም ሲል ወያኔያዊ ክህደቱን በሀገርና በቤተክርስቲያን ታሪክ ላይ ፈጽሟል፡፡ ጤነኝነቱን ሁሉ በእጅጉ እንድንጠራጠር የሚያደርግ ድፍረት በቤተክርስቲያንና በሀገር ላይ በደል ፈጽሟል፡፡
እኔ እጅግ የገረመኝ ነገር ቢኖር ድፍረቱ ልክ ያጣ መሆን ነው፡፡ ግድ የለም ሊቃውንተ ቤተክርስቲያንንስ እንደሌሉ ቆጥሮ ታሪክን ትውፊትን ነገር ሃይማኖትን እያሳከረ በሚያሳትማቸው የቤተክርስቲያን መጻሕፍት ላይ መሐመድን (የእልምናን መሥራች) “ነቢዩ መሐመድ” እያለ ቤተክርስቲያን የመሐመድን ነቢይነት የምታምን የምትቀበል አስመስሎ እንደፈለገ ሲጽፍ አልተናገሩትምና እነሱንስ አይፍራ፡፡ ይሄንን ታላቅ የቤተክርስቲያንና የሀገር ታሪክ እየሰማ ያደገ ሰው ሁሉ ተኩላው እንደቀላል ነገር ሲደመስስ ገንድሶ ሲጥል ተረት ተረት ነው ሲል ማንም ምንም እንደማይለው ማሰቡ እግጅ አስገርሞኛል፡፡ እኔ “ነቢዩ መሐመድ” እያለ በሚያሳትማቸው የቤተክርስቲያን መጻሕፍት ላይ መጻፉን እንዲተው ስልክ ደውየ ለሱ የተናገርኩበት ጊዜ ሁሉ ነበር፡፡ አይሰማም ሲያጠፋ እንዳጠፋ እንደተሳሳተ እያወቀ ለመታረም ዝግጁ አይደለም፡፡ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ሊያርሙት የሚፈልጉት ሰው ዓይነት አለውና ለዚያ የማይበቃ ሆኖባቸው ንቀው ዝም ሲሉት ጊዜ ዐዋቂ ነው የተባለ መስሎት እራሱን አንቱ አለ በትዕቢት ወጠረ፡፡ የትዕቢቱ ትዕቢት ባለ ንስር ዐይን ነኝ እስከማለት ደረሰ፡፡ ይታያቹህ ድፍረቱ! ስንት አራት ዐይና ሊቃውንት እራሳቸውን እንደ ዐላዋቂ ቆጥረው እንዳሉ እንኳን በማይታወቅባት ቤተክርስቲያን በአብነት ትምህርት ቤቶች በአንድ ጉባዔ እንኳን ወንበር ይዞ አንድ የቤተክርስቲያንን ትምህርት ሳይማር ምሥጢር ሳይጠነቅቅ ባለ ንስር ዐይን ነኝ ብሎ ቁጭ አለ፡፡ አይገርምም? ድንቄም ባለ ንስር ዐይን! በዚህ መንገድ ባለማለፉ ምሥጢር ባለመጠንቀቁ ነው በመጻሕፍቱ ላይ የሚታዩት ስሕተቶች በርክተው ሊታዩበት የቻለው፡፡ ድፍረቱና ትዕቢቱም የመጣው ከዚህ የተነሣ ነው፡፡
ይሄንን የክብረ ነገሥትን ትረካ በተመለከተ ተኩላው የሚለው “መንግሥት ወደ ጎንደር ከተዛወረ በኋላ በ17ኛው መቶ ክ/ዘ በተጻፈው ብዕለ ነገሥት በሚል መጽሐፍ ላይ ነው የጻፉት እንጅ በአቡነ ተክለሃይማኖት ገድል ላይ እንዲህ የሚል ነገር የለም” ሲል ሸምጥጦ የካደውን የአቡነ ተክለሃይማኖት የገድል ክፍል የደብረ ሊባኖስ ገዳም ያሳተመውን “ገድለ አቡነ ተክለሃይማኖት” የሚለውን መጽሐፍ ገልጦ ምዕራፍ 26ን እና 27ን ቢያነብ ይሄ ተኩላ ያለአንዳች ፍርሐትና ሐፍረት በድንቁርና ድፍረት የለም ሲል የካደውን ታሪክ እንዳለ ሊያረጋግጥ ይችላል፡፡ ተኩላው በጠቀሳቸውና ባልጠቀሳቸው ታላላቅ ገዳማት ያሉ የአቡነ ተክለሃይማኖት ገድላት ላይም ይሄ ታሪክ በሚገባ አለ፡፡ ተኩላው የለም የሚለው የሌለ መስሎት ወይም እንዳለ ሳያውቅ ቀርቶ እንዳይመስላቹህ በጎሳና ጸረ አማራ መርዘኛ መርፌ ተወግቶ ከተመረዘ በኋላ በወያኔነቱ መሥራት ካለበት ሥራዎችና ከተሰጠው ተልእኮ እንዱና ዋነኛው በመሆኑ እንጅ፡፡ እኛ ስናውቀው ተኩላው አማራ ነበር ማንነቱን አጥንተው መርዘኛውን የጎሳና የጸረ አማራ በርፌ ከወጉት በኋላ ግን አገው ነኝ ባይ ሆኗል፡፡ ይሄንን የክብረ ነገሥትንና የአቡነ ተክለሃይማኖት ገድልን ታሪክ ውሸት ነው ተረት ተረት ነው ፈጠራ ነው ሲል በሱ ቤት ዛጉዌዎች (አገዎች) ወገኖቹ ስለሆኑና የዳዊት (ሰሎሞናዊው) ደግሞ የአማራ ስለሆነ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ካላቸው ቅድስናና በአኃት አብያተክርስቲያናት ዘንድ ካላቸው ዓለማቀፋዊ ተቀባይነት አንጻር በእሳቸው ገድል ላይ ይሄ ነገር ሰፍሮ መገኘቱ የታሪኩን እውነተኛነት ስለሚያረጋግጥ ለእሱና እሱን ለመሰሉት ደግሞ እንዲህ መሆኑ ስለማይመቻቸው ስለማይወዱት ስለማይፈልጉት ነው በገድላቸው የለም ሲል ዐይን ባወጣ የጅል ድፍረት ሸምጥጦ ሊክድ የቻለው፡፡
ደግነቱ ብራናው ወይም መጽሐፉ በእሱና በቡድኑ እጅ ብቻ ያለ አለመሆኑ ነው፡፡ ይሄም ቢሆን ተኩላውና በወያኔ የተደራጀው ከእሱ ጋር የሚሠራው ቡድኑ እንዲህ ዓይነት ደፋር የጥፋት ዓላማና አቋም ካላቸውና መንቀሳቀስ ከጀመሩ በጥቂት ገዳማቶች እጅ ያሉትን ተኩሎችን የማያስደስቱ እውነተኛ ታሪኮችን የያዙ ጥንታዊ የብራና መጻሕፍት በጣት የሚቆጠሩ ብቻ ከመሆናቸው አንጻር የወያኔንና ወያኔ የሚያሽከረክረውን ሲኖዶስ ጡንቻ በመጠቀም ለቃቅመው ሊያጠፏቸው የሚችሏቸው መሆናቸውን ሳስብ ሐዘኔ ጥልቅ ነው፡፡ ይሄ ተኩላና መሰሎቹ የዚያ ቡድን አባላት ደግሞ ቀድሞ ደኅና በነበሩ ጊዜ ያላሰሱት ገዳማትና አድባራት ካለመኖሩ የተነሣ ምን ቦታ ምን ዓይነት ቅርስና ጥንታዊ የብራና መጻሕፍት እንዳሉ በማወቃቸው እነኝህ ቅርሶችና መረጃዎች ምናልባት እስከአሁን ሳይበረዙ ሳይከለሱ ወይም ሳይሰረቁ ተጠብቀው ካሉ ለምን ዓይነት ከባድ አደጋ እንደተጋለጡ በግልጽ ማየት ይቻላል፡፡
ተኩላው “አራቱ ኃያላን” የሚለውን መጽሐፍ ያዘጋጀበት ምክንያትም ይሄው ነው፡፡ የአማራ ነገሥታትን ስም ለማጥፋት ከማሰብ የተነሣ በግነት አጡዞ አቀረበው እንጅ የቅዱሳኑን ገድል እንዲዘከር ከማሰብ አይደለም፡፡ አሁን ላይ ተኩላው ሃይማኖት ያለውና እግዚአብሔርንም የሚፈራ ሰው አይደለም፡፡ ለሃይማኖታዊ ሕግጋት ይቅርና ለሞራል (ለቅስም) ድንጋጌዎች እንኳን ዋጋ አይሰጥም እንደጌቶቹ ሁሉ ምን ይሉኝ! አይልም ነውር ለሚባሉ ነገሮች ግድ የለውም ወያኔን ለማገልገል ንጹሐንን በሚያጠቃበት ጊዜ ፈጥሮ ሲያወራ ነጭ ውሸት ዋሽቶ ስማቸውን ሲያጠለሽ ሰባኬ ወንጌልነቱ ይቅርና እንደ “ተራ” ክርስቲያን እንኳን ትንሽ አይሰቀጥጠውም፡፡ እንኳን ክርስቲያን የሆነ ክርስቲያን የነበረ እንኳን አይመስልም፡፡ እናም ተኩላው ሃይማኖት የለውም ሃይማኖት አለው ከተባለም እንደማንኛውም ወያኔ ሁሉ አምላኩ መለስ ሃይማኖቱም ወያኔነት ነው፡፡ የሚገርመው እንዲህ ዓይነት ሰው ሆኖ አሁንም እሰብካለሁ እያለ በየጉባኤው መቆሙ ነው፡፡ አይ! ሞኝ ሆንኩ መሰለኝ ዋናው ሥራ የሚሠራው የት ሆነና? ተኩላው አሁን የኢትዮጵያን ቤተክርስቲያን እየተጠቀመባት ያለው ለጥፋት ዓላማው ምቹ ሜዳው ስለሆነችና ዒላማውም ስለሆነች ነው፡፡ መቸም ቤተክርስቲያንን በእንዲህ ዓይነት ድፍረት አዋርዶ ተዳፍሮና ክብሯን ገፎ መጻሕፍቶቿንም አስተኃቅሮ የልብ ወለድ ድርሰቶት ቋት ተደርጋ እንድትቆጠር አድርጎ አሁንም የቤተክርስቲያን ልጅ ነው ብሎ የሚያስበው ሰው ካለ የመጨረሻ የዋህ ነው ወይም የዓላማው ተጋሪ ነው፡፡ ቤተክርስቲያን ካሏት መጻሕፍት ተኩላው ውሸት ነው ያለውን ታሪክ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ እውቅና ከሚሰጡት ከሚጠቅሱትና ከሚያረጋግጡት ይልቅ በይዘታቸው ምክንያት የማይጠቅሱት በጣም ጥቂቶች ናቸው፡፡ እነኝህን ሁሉ ነው ተኩላው ተረትና የውሸት ያደረጋቸው፡፡
በጣም የሚገርመኝ ደግሞ ተኩላው የክብረ ነገሥትን ታሪካዊ መረጃ ውሸት ነው ካለ በኋላ ታቦተ ሙሴ ኢትዮጵያ ውስጥ መኖሯን አፉን ሞልቶ ሲናገር በምን መረጃ አምኖና አረጋግጦ ሊያምን እንደቻለ ነው? እስከ ቅርብ ጊዜ እዚህ ኢትዮጵያ ውስጥ የነበሩት ትውልደ እስራኤላዊያን ነን የሚሉ አይሁዶች እዚህ እንደነበሩ ሲናገርስ በማን ዘመን በምን ሁኔታ መጡ ብሎ አምኖ እንደሚናገር ነው? ነው ወይስ በመጽሐፍ ቅዱስ በመጽሐፈ ነገሥትና ዜና መዋዕል ላይ የሰፈረው የንግሥተ ሳባን ታሪክም ተረት ተረት ነው ብሎ ነው የሚያምነው? ምክንያቱም ክብረ ነገሥትም የታሪኩ መሠረት የሚያደርገው ይሄንን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ነውና፡፡ ነው ወይስ እንደ አንዳንዶቹ የታሪክ ጸሐፍትና ተመራማሪ ተብየዎች ሳባ የደቡብ አረቢያ ንግሥት እንጅ የኢትዮጵያ ንግሥት ናት ብሎ አያምንም? እንዲህ ብለው ለሚያምኑ ሰዎች የምለው ነገር ቢኖር አንድ መጽሐፍ ቅዱስን የመረጃ ምንጩ ያደረገ በሳል መርማሪ ሰው ንግሥተ ሳባ ኢትዮጵያዊት መሆኗን ሳያቅማማ በቀላሉ ሊረዳ ሊያረጋግጥ የሚችል መሆኑን ነው፡፡ በእርግጥ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደተጠቀሱት እንደሌሎች ታላላቅ ኢትዮጵያውያን ኢትዮጵያዊ ተብሎ እንደተጻፈው ሁሉ ሳባንም ኢትዮጵያዊት ብሎ አልጠራም በአንጻሩም የመናዊት ወይም ዓረባዊትም አላለም፡፡ እነኚህን ባይልም ዜግነቷን ወይም አገሯን በቀላሉ ልንለይ የምንችልበት ቀላል መንገድ ግን አለ፡፡
እንደሚታወቀው እንደመጽሐፍ ቅዱሱ ቅድመ ልደተ ክርስቶስ በሀገርና በሕዝብ በመንግሥትም ደረጃ እግዚአብሔርን የሚያመልኩ ወይም የሚያውቁ እሱም የሚያውቃቸውና ሕዝቤ ልጆቼ የሚላቸው ሕዝቦች ወይም ሀገሮች ሁለት ብቻ ናቸው፡፡ እነርሱም ኢትዮጵያና እስራኤል ከእነዚህ ውጪ ማንም አልነበረም፡፡ ሌሎች ሀገሮች ከተነሱም በስደስ ሔደው ምኩራባቸውንም በዚያ ሠርተው እግዚአብሔርን ያመልኩ ከነበሩት አይሁዳውያን የተነሣ ካልሆነ በቀር፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ከእስራኤል ልጆችና ከኢትዮጵያ ልጆች ውጪ እግዚአብሔርን ያመልካሉ ተብሎ የተጻፈለት ሕዝብ አልነበረም፡፡ በት.አሞ.፱፣፯ ላይ እማ እንዲያውም በኩራት ናቸው ከሚባሉት እስራኤላዊያንም ይልቅ እኛ ኢትዮጵያዊያኑ ከብረን እንታያለን፡፡ ቃሉ እንደሚለው “የእስራኤል ልጆች ሆይ እናንተ ለእኔ እንደኢትዮጵያ ልጆች አይደላችሁምን? ይላል እግዚአብሔር”፡፡ እግዚአብሔር የእስራኤል ልጆችን እንደእኛ የኢትዮጵያጵያ ልጆች አድርጐ እንደሚያያቸው ከእኛ አሳንሶ እንደማያያቸው የእስራኤል ልጆችን በማጽናናትና በማረጋጋት የተናገረበት ጊዜ ነበር፡፡
እንግዲህ ቁልፉ ነገር ያለው እዚህ ላይ ነው፡፡ ሳባ በእግዚአብሔር የምታምን እንደነበረች ከተናገረችው ቃል መረዳት ይቻላል፡፡ አንደኛ ነገሥት 10፤1-13 ሁለተኛ ዜና መዋዕል 9፤1-12 ላይ ታሪኩ ተጽፎ እንደሚገኘው ሳባ ሰሎሞንን “አንተን የወደደ በእስራኤልም ዙፋን ያስቀመጠ አምላክህ እግዚአብሔር የተባረከ ይሁን፡፡ እግዚአብሔር እስራኤልን ለዘለዓለሙ ወዶታልና፡፡ ስለዚህ ጽድቅና ፍርድን ታደርግ ዘንድ ንጉሥ አድርጐ አስነሣህ” ብላዋለች፡፡ በንግግሯ እግዚአብሔር የጽድቅና የፍርድ አምላክ መሆኑን ከነበራት እምነት ተነሥታ መስክራለች፡፡ የተባረከ ይሁን ብላም ፈጣሪዋን አመስግናለች፡፡ ይህንን ንግግር ለመናገር ስለእግዚአብሔር ጥልቅ የሆነ እውቀትና እምነት ጊዜ የወሰደ ትውውቅ ሊኖራት ግድ ይላል፡፡ ከእስራኤላዊያን ውጪም ይህንን ሊያደርጉ የሚችሉ ሌላ ሕዝብና መንግሥት ካለም ቀደም ሲል በቀረበው ማብራሪያ ወይም በመጽሐፍ ቅዱሱ መሠረት ኢትዮጵያዊያን ብቻ ናቸው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን ስናነብ ከሳባም በፊት ኢትዮጵያ እግዚአብሔርን የምታመልክ ሀገር መሆኗን የሚያረጋግጡ ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ መረጃዎች አሉ፡፡ እስራኤላዊያን ከሌላ ከማንም ወገን ጋር እንዳይጋቡ በእግዚአብሔር ተከልክለው በነበሩበት ወቅት ጭራሽ ሊቀነቢያት ሙሴ ግን ያገባው ኢትዮጵያዊቷን የካህንኑ የራጉኤልን ልጅ ሲፓራን ነበር፡፡ ይህንን በማድረጉም ከእግዚአብሔር ዘንድ አንዳችም ተግሳጽ አልደረሰበትም፡፡ ይልቁንም ሙሴ ኢትዮጵያዊቷን በማግባቱ ያጉረመረሙት ወንድሙ አሮንና እኅቱ ማርያም እግዚአብሔር በባሪያዬ በሙሴ ላይ አጉረምርማችኋል በማለት ቁጣውን አወረደባቸው ማርያምንም በለምጽ ቀጣት እንጂ፡፡ ዘኁ.፲፪፣፩-፲፭ ዘጸ.፪፣፲፮-፳፪ ይህም የሆነበት ምክንያት ሌሎች ነቢያት ወደኋላ ግልጽ እንዳደረጉት የኢትዮጵያ ሕዝብ እግዚአብሔርን አምላኪና ሕዝበ እግዚአብሔር በመሆኑ ነው፡፡ ክብረ ነገሥት የሳባ አባቶች ዘንዶ አምላኪ እንደነበሩ ይናገራል ይሄ ማለት ግን እግዚአብሔርን ጨርሶ አያውቁትም ነበር ማለት አይደለም፡፡ እስራኤላውያንም ከእግዚአብሔር ዘንድ ያ ሁሉ ተአምራት እየተደረገላቸውና እያወቁት ለጣኦት ያልሰገዱበትና ጣኦት ያላመለኩበት ዘመን አልነበረምና፡፡ ከነገሥታቶቻቸውም ከዳዊት በስተቀር ለጣኦት ያልሰገደ አልነበረምና፡፡
እናም ዳንኤልንና መሰሎቹን በመርዛማ መርፌ ስለተወጉ በዓላማ ነውና ታሪክን የሚያዛቡትና የሚክዱት ምንም ልላቸው አልችልም፡፡ ለሌሎቹ ተታለው ተወናብደው ጥልቅና ጠንቃቃ ንባብና መረዳትም ከማጣት የተነሣ ክብረ ነገሥትን የፈጠራና የተረት መጽሐፍ አድርገው ለሚያዩ እንዲታይም ለሚጥሩ ግለሰቦች ግን ከላይ መጽሐፍ ቅዱስን መሠረት በማድረግ ለመግለጽ ከሞከርኩት መረዳት እንደሚቻለው ሁሉ ክብረ ነገሥት ንግሥተ ሳባን ኢትዮጵያዊት መሆኗን አረጋግጦ ታሪኳን ሲተነትን ፈጥሮ አይደለምና ተረት ፈጠራ አለመሆኑን ሊያውቁ ይገባል፡፡ ናይጄሪያ ቢሔዱ የንግሥተ ሳባን አፈ ታሪክ ሊሰሙ ይችላሉ ግዛቷ እንደነበረም ሊነግሯቸው ይችላሉ፡፡ ከሀገሯ ስትመጣ የመጣችበት ነው የሚሉትን የዋሻ መንገድም ሊያሳዩዋቸው ይችላሉ፡፡ የመኖች ንግሥተ ሳባን የኛ ንግሥት ናት የሚሉበት ምክንያትና የግእዝ አሻራዎችም እዛ የመገኘታቸው ምክንያት ከጥንት ዘመን ጀምሮ እኛ ከፋርሶች ጋር በመፈራረቅ ሳውዲ ዓረቢያንና የመንን ለረጅም ጊዜ ስንገዛው ስለነበረ ነው እንጅ ሳባ ዓረብ ስለነበረች አይደለም፡፡ ኢትዮጵያ የመንን እንደገዛች ደግሞ እራሳቸው የመኖችም የሚያረጋግጡት ነገር ነው፡፡
እርግጥ ነው ጥቂት የማይባሉ የክብረ ነገሥት መረጃዎችና መቸቶች የምዕራባዊያኑን መረጃዎች መሠረት በማድረግ ክብረ ነገርሥትን ተረት ነው የሚሉ ግለሰቦች ትክክል ነው ብለው ከሚቀበሉት የታሪክ መረጃዎች ጋር ስለማይጣጣምላቸው ለምን እንደሆነ ካለመረዳት የተነሣ የመጽሐፉን ተአማኒነት ለማሳጣት ጥረት ሲያደርጉ ይስተዋላሉ፡፡ ክብረ በገሥት ሆን ተብቶ በተፈጸሙ የመቸት ስሕተቶች ባለው መልኩ የተጻፈበት ምክንያት መጽሐፍ ቅዱስን ጨምሮ እንደሌሎቹ የቤተክርስቲያን የታሪክና የሃይማኖት መጻሕፍት ሁሉ የሀገርንና የቤተክርስቲያንን ቅርሶች ሀብቶች ከመጭው ወይም አሁን ካለው የዐመፃ ትውልድ ክፋት የተነሣ ከዚህ የዐመፃ ትውልድ ጥቃት የቤተክርስቲያንና የሀገርን ሀብት ለመጠበቅ ሲባል ጠቃሚና ዋና ዋና መረጃዎችን ሰውሯል፡፡ የክብረ ነገሥትን መረጃዎች በመከተል ወደ እነዚያ የቤተክርስቲያንና የሀገር ሀብቶች የሚወስዱ መንገዶችን አምታትቷል፡፡ ከላይ እንዳልኩት ይህ የተደረገው ሆን ተብሎ ነው፡፡ አጥኚዎች ይሄንን ለመረዳት ባለመቻል የመጻሕፍቱን አብዛኛ ክፍል እንደ ሐሰትና የፈጠራ ድርሰቶች አድርገው ይመለከቷቸዋል፡፡ አልገባቸውም እንጅ የመጻሕፍቱ በዚህ ዘይቤ መጻፍ ግብም ይሄው ነው ቀበኞችን ማምታታት፡፡ ለአማኞች ደግሞ እነኝህ ሀብቶች እንዳሉን ሊረዱ በሚችሉት ምሥጢራዊ አገላለጽ ማስረዳት፡፡ እነኝህ መጻሕፍት በዚህ መልኩ ባይጻፉ ኖሮ አንድም የቤተክርስቲያንና የሀገር ቅርስ ባልቀረልንም ነበር፡፡ ይህ የጥፋት ትውልድ እየለቃቀመ በቸበቸባቸው ነበር፡፡ ምሳሌ ጽላተ ሙሴን (ጽዮንን) መጥቀስ ይቻላል፡፡ የክብረ ነገሥትንም ሆነ ሌሎች ግልጽ የወጡ የመጻሕፍት መረጃዎችን በመከተል ታቦተ ሙሴን ለማግኘት ብትሞክሩ ደክማቹህ ትቀራላቹህ እንጅ አታገኗትም፡፡ በእነዚህ መጻሕፍት መረጃዎች በመመራት ብዙዎቹ ቅጥረኞች “ከፓትርያርክ” እስከ ምእመን ከመንግሥት ባለሥልጣናት እስከ ተራ ታጋይ አሳልፈው ለመስጠት ፈልገው ፈልገው ማግኘት ሳይችሉ ደክመው ቀርተዋል፡፡ በቃ የመጻሕፍቱ መረጃዎቹን ሆን ብለው የሚያዛቡበት ምክንያትና ዓላማ ይሄው ነው እንጅ እውነቱን ስለማያውቁ እነዳንኤል እንደሚሉት የፈጠራ ድርሰቶች ሆነው አይደለም፡፡
መጻሕፍቱ በዚህ ቅኝት በመጻፋቸውም መንፈሳዊነታቸውን ወይም ያላቸውን የመንፈስ ቅዱስ ጸጋቸውን የሚያሳጣ ቅንጣት ነገር የለም፡፡ አዲስ ነገርም አይደለም መጽሐፍ ቅዱስም የነጻፈው በዚሁ ዘይቤና ቅኝት ነውና “መጽሐፍ ቅዱስ ምሥጢርን እንጅ ዘይቤን አይጠነቅቅም” የሚባለውም ከዚህ የተነሣ ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን ስታነቡ ታቦተ ሙሴ እስከማን ዘመን ድረስ እንደነበረች ይናገራል እንጅ ከዚያ በኋላ የት እንደደረሰች ማን እንደወሰዳት አይናገርም፡፡ ነቢያቱና ሐዋርያቱ ያልተናገሩት ስለማያውቁ ይመስላቹሀል? ከክፉው ከዐመፀኛው ትውልድ እጅ ለመሰወር ሲባል የተደረገ ነው፡፡ ጠልቀው መመርመርና መረዳት የማይችሉ ታሪክ ተመራማሪዎችና ጸሐፍት ነን ባዮች ግን ይሄንን መረዳት ስለማይችሉ ቶሎ የሚቀናቸው መጻሕፍቱን መንቀፍ ማጣጣል መተቸት ማዋረድ ነው፡፡ ዳንኤልንም ሆነ መሰሎቹ የገድለ አቡተ ተክለሃይማኖትን መጽሐፍ እውነተኛነትና መንፈሳዊነት ማረጋገጥ ከፈለጉ ወደ ደብረ ሊባኖስ ይውረዱና ገድል ቤት ወይም ጸበል ቦታ የሚሠራውን ተአምራት ይመልከቱ፡፡ በአጋንንት ቁራኛ የሚሰቃዩ፣ ሽባዎች ወይም ልምሹዎች፣ ዐይነ ስውራን፣ በዘመናዊ ሕክምና ፈውስ ከሌላቸው ብዙ ዓይነት በሽታዎች ሕሙማን ሲፈወሱ በዐይናቹህ በብረቱ ትመለከታላቹህ፡፡ በዚህ የቀናና የአባታችንን ገድል ተአማኒነት ለማሳጣት የሚጥረውን ያደረባቹህን የሰይጣንንም ሆነ የአጋንንትን መንፈስም እዛው ተገላግላቹህት ትመጣላቹህ፡፡ እንድትሔዱ ምክሬን እለግሳለሁ፡፡
ሌላው ሳልጠቅሰው ማለፍ የማልፈልገው ጉዳይ ቢኖር ተኩላውና ቡድኑ ሰሞኑን በመጽሐፈ ግጽ (ፌስ ቡክ) “አክራሪ እስልምና የኢትዮጵያ ክርስትና አስቸጋሪ ፈተና” በሚል ርእስ ጥናታዊ ጽሑፍ የተባለውን ጽሑፍ ተኩላው ካቀረበው ከዓመታት በኋላ ከሞላ ጎደል በወያኔ ሴራ እየተቀመረና እየተሴረ በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያንና በምዕመናን ላይ የተፈጸመውን ያንን ሁሉ ግፍና ጉድ በራሳቸው በእስላሞች ተነሣሽነት የተፈጸመና አገዛዙ የታደገን አስመስሎ በማቅረብ ከዓመታት በኋላ ያንን እንደገና አስታውሰው በዚህ ወቅት በድረ ገጾች ለመናኘት የሚያበቃ ከተለምዷዊው ውጪ አንዳችም ቀስቃሽ ድርጊት በሌለበት ሁኔታ ለሕዝብ በመናኘት ሕዝቡ ጭንቅ ጥብ ውስጥ እንዲገባ እንዲሸበር ያደረጉበት ምክንያትም ከወያኔ የተሰጣቸውን ተልዕኮ ለመፈጸም ነው፡፡ ወያኔ ከሕዝብ ዐመፅ ይቀሰቀስብኛል ብሎ ሲያስብ በህልውናው ላይ ደስ የማይል ሥጋት ባደረበት ቁጥር የሚያደርጋቸው የተለመዱ ዘዴዎች አሉት፡፡ የሆኑ የሆኑ ቦታዎች ላይ የሃይማኖት ወይም የዘር ግጭቶችን ይቀሰቅስና ሕዝቡን እርስ በእርሱ እንዲፋጠጥ ያደርገዋል፡፡ በዚህ ወቅት ሕዝቡ እርስ በእርሱ ከመፈራራቱና የከፋ የእርስ በእርስ መተላለቅን ከመፍራቱ የተነሣ ለደኅንነቱ ሲል አገዛዙ መኖሩን አስፈላጊ አድርጎ እንዲያስብ ያደርገውና በአገዛዙ ላይ ለማመፅ የነበረውን ሐሳብ እንዲተው ያደርጋል፡፡ በዚህ መልኩ ወያኔ ሥጋቱ ባደረበት ቁጥር እንዲህ እያደረገ እድሜውን ሲያራዝም ቆይቷል፡፡ ተኩላውና ቡድኑ በዚህ ወቅት ይሄንን ጥናት የለቀቁበት ምክንያትም ይሄው ነው፡፡ ወያኔ አሁን ሥጋት ላይ ስለሆነ ይሄንን ከፊት ለፊቱ ያፈጠጠበትን ሥጋትና አደጋ ለማለፍ የተለመደውን ዘዴ ለመጠቀም ስለፈለገ ነው ሕዝበ ክርስቲያኑን በማሸበር በመስጨነቅ ለደኅንነቱ ሲል የእሱን መኖር አስፈላጊ አድርጎ እንዲያስብና ዐመፁን እንዲተው ለማድረግ ሲባል ነው የተኩላው አሸባሪ ጥናት አሁን ላይ የተለቀቀው፡፡ እኔ እስላሞች ሁሉም ባይሆኑ ከፊሉ በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያንና ምእመናን ላይ እንዲህ ዓይነት ዓላማ የላቸውም አልልም እንዳላቸው በሚገባ አውቃለሁና፡፡ ይህ ችግር ስላለም ነው ወያኔ ለራሱ እንዲመች አድርጎ እየተጠቀመበት ያለው፡፡ እኔ እያልኩ ያለሁት እስላሞች እንዲህ ዓይነት የጥፋት ሐሳብ ቢኖራቸውም እየሆነ ያለው ነገር ሁሉ ግን እነሱ ሊያደርጉት ከሚፈልጉት ምቹ ጊዜ ነው ብለው ከሚያስቡት ውጪ በወያኔ ገፋፊነትና ሴራ ነው እየሆነ ያለው ነገር እየሆነ ያለው ነው እያልኩ ያለሁት፡፡
ለዚህች ሀገርና ለባለውለታዋ እናት ቤተክርስቲያን ታሪክና አጠቃላይ እሴቶች ህልውናና ደኅንነት የምትቆጩ የምትቆረቆሩ የሚገዳቹህ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ ማስተላለፍ የምፈልገው መልእክት ቢኖር ይህ ተኩላው ያለበት የወያኔን ጥቅም ለማስጠበቅ ታጥቆ እየሠራ ያለው የጥፋትና የዐመፃ ቡድን ከምትገምቱት በላይ የተቀናጀና ከብዙኃን መገናኛዎች እስከ ማኅበራት ከመንግሥት ተቋማት እስከ የግል ድርጅቶች ድረስ ትስስር ፈጥሮ በመናበብ እየተንቀሳቀሰ ያለ ቡድን ነው፡፡ የሌሉበት ቦታ የለም በተቀናጀ አሠራር ስለሚሠሩ በርካታ ሕዝቡ ያላየውና ያልደረሰበት ጥፋት ማድረስ ችለዋል እያደረሱም ይገኛሉ፡፡ ስለ እግዚአብሔር ብላቹህ ንቁ! ተከላከሉ፣ ጠብቁ፣ የጥፋት ሥራዎቻቸውን አጋልጡ፣ ከሁሉም በላይ የጎሳና የጥላቻ መርዘኛና አጥፊ አመለካከትና አስተሳሰባቸውን ተዋጉ ለሀገርም ለሕዝብም ለቤተክርስቲያንም ለማንም አይጠቅምምና፡፡ ይህንን ማድረግ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ የዜግነት ግዴታው ነው፡፡ ለክርስቲያኑ ደግሞ ሃይማኖታዊ ግዴታው እንደሆነ ሊያውቅ ይገባል፡፡ እኛ አንቀላፍተኛል ተኝተናል ጠላት በነፍሳችን እንዳሻው እየተጫወተ ነው፡፡ በላያችን ላይ ምን እየተሠራ እንደሆነ ምንም የምናውቀው ነገር የለም፡፡ የጥፋት ኃይሎች የማጥፋት ስልት እንዳንነቃና ምን እያደረጉ እንደሆነ ምንም እንዳናውቅ አድርጎናል፡፡ ማንነታችን ጨርሶ እየጠፋ ነው፡፡ እንዲህ ያፈጠጡ የሚታዩ ድፍረትና ንቀት የተሞላባቸው የጥፋት ሥራዎች ሲሠሩ ካልነቃንና ካላወገዝን ካልተቃወምን በግልም በቡድንም በማኅበርም ማድረግ ያለብንን ካላደረግን ለኢትዮጵያዊነታችን ለሃይማኖታችን ኢምንት እንኳን ክብርና ፍቅር እንደሌለን ልናውቅ ይገባል፡፡ ማኅበረ ቅዱሳንም እንደማኅበር ከተመሠረተበትና ከሚያራምደው አቋምና ዓላማ በተፃራሪ አባልነት ባላቸውና ስማቸው ከማኅበሩ ጋር በተሳሰረ ግለሰቦች እንዲህ ዓይነት የጥፋት ሥራዎች ሲሠሩ በዝብታ መመልከቱን ትቶ መውሰድ ያለበትን እርምጃ እንዲወስድ ማሳሰብ እወዳለሁ፡፡
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
- See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/39677#sthash.ozZFkmw8.dpuf

No comments:

Post a Comment