የዘር ፖለቲካ ቡድነኝነት ነው:: በግለሰቦች ነጻነት ሞት ላይ የቆመ የጋርዮሽ ፖለቲካ ነው:: አንዱም ከመንጋው ክፉን ቢያስተውል በግሉ እንዳይናገር የጋርዮሽ ፖለቲካው መብቱን ይነፍገዋል:: መለስ "በማእከላዊው ኮሚቴ እንጂ በራሴ ፍላጎት ስልጣኔን መልቀቅ አልችልም" ሲል የተጋነነ ቢሆንም በባህሪው ግን እውነት ነው:: በፓርላማ ተቃውመህ እጅህን ብታወጣ ከመንጋው እንደተለየህ እወቅ::
ወደ ቁምነገሩ ልመለስ!!
"ተስፋዬ ገ/አብ (ገዳ ገ/አብን) የነካ እኛን እንደነካ ይወቀው" ብለው ነበር በሞጋሳ ስርአት የኦሮሞን ማንነት ሲቀበል:: ጥልቅ ፍልስፍናውን ባላገኝውም ሊብራል ነኝ ብዬ አምናለሁ.... እናም ከት ብዬ ሳኩ (ትዝ ይለኛል የሰማሁ ለት የሳኩት ሳቅ) ተስፋዬ ሲነካ ምን?? ወይ የጋርዮሽ ፖለቲካ... ይህ ሊብራል ለሆነ ዜጋምን ማለት ነው? አንድን ግለሰብ በመናገር ማህበረሰብን መናገር ነው ብሎ የመናገር/የመውቀስ ነጻነቱ ላይ መደራደር??

ቀናት አልፈው ከሁለትና ሶስት ጽሁፎቹ ቀጥሎ አሳፋሪ መልእክት ያለው ታሪክ ይዞ ብቅ አለ:: ጭብጡ ኦሮሞው አማራ ፍቅረኛውን በፖለቲካ አቅዋሙ ምክኒያት እንዳላገባት እናም ትክክለኛ የሚለውን ውሳኔ እንደወሰነ:: ይህንን ሰብረው በፍቅር የኖሩ:እየኖሩ ያሉ: ትዳር የመሰረቱ: ልጆች የወለዱ: የሌላ ብሄር አባል (ብሄር አልባም ትሆናለች/ይሆናል) ፍቅረኛ ያላቸው... ያ ሁሉ በጋርዮሹ ፖለቲካ ውል ምክኒያት በግል የመናገርና የመጻፍ መብቱን ተጠቅሞ አልወቀሰውም.... ወይንም እኔ አላየሁም:: እጅግ አሳፋሪና ሊወገዝ የሚገባው ቢሆንም ወጥቶ የተናገረው የለም::
ይሄ ሁሉ ዳርዳርታ እንዴት ጃዋር
"የኦሮሞ ቤተክርስቲያንና መስኪድ እንዲሁም እድር መሰራት አለባቸው:: የአበሻ ቤተክርስቲያን ሄደን የምናስቀድስበት የሃበሻ መስኪድ ሄደን የምንሰግድበት ምክኒያት የለም..በአበሻ ቤተክርስቲያንና መስኪድ አትሂዱ"
ብሎ ሲያስተምር ዝም ብላችሁ ከረማችሁ? ሙስሊሙስ/ ክርስቲያኑስ እንዴት ዝም አለ?... እንዴት ያለ ቆሻሻ ትምህርት ነው!!!!

አብሮ መጸለይ: መስገድ እንዲሁም በማህበራዊው ኑሮ እድር: እቁብ መሰብሰቡን የሚያወግዝ ባለጌን እንዴት ዝም እንላለን?... ኦሮሞዎችም ብትሆኑ ሌሎችም ብትሆኑ... የዘር ፖለቲካ ተከታዮች ያው እንዲህ ያለውን ውርደት ለመቀበል ሊብራል መብቶቻችሁን አሳልፋችሁ ሰጥታችሁዋል... ሌሎቻችሁ ማን እንዳይከፋው ነው ዝም ማለታችሁ?... ይሄ እኮ አብሮ በመኖር ላይ በቀጥታ የተሰነዘረ በትር ነው!!
የኢህአዲግ ባለስልጣናት ምን የተለየ ሰሩ? እነሱ እኮ የመሰደብ ሱስ ስላለባቸው አይደለም ቀን በቀን የሚጠጡት!! የፖለቲካ ስልጣናቸውን ተጠቅመው ስላሳዘኑን እንጂ!! እንደ ጃዋር ያሉት ደግሞ ተደማጭነታቸውንና መንጋ ተከታዮቻቸውን
No comments:
Post a Comment