ሰማያዊ ፓርቲ በባህር ዳር ከተማ የከፈተው ቢሮው በአከራይ ላይ በተፈጸመ ከፍተኛ ወከባና ማስፈራሪያ ምክንያት እንደተዘጋበት በስፍራው የፓርቲው አስተባባሪ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጸ፡፡
በባህር ዳር የፓርቲው አስተባባሪ አቶ አዲሱ ጌታነህ እንደገለጹት ቅርንጫፍ ቢሮው ከትናንት ጀምሮ የፓርቲው ንብረቶች ውስጥ እንዳሉ ተቆልፏል፡፡ አቶ አዲሱ ቢሮውን ያከራዩት ሰው በተደጋጋሚ ከፖሊስ፣ ከኢህአዴግ ካድሬዎችና ከደህንነት ሰዎች ዛቻና ማስፈራሪያ እየደረሰባቸው እንደሆነ በመግለጽ ቤቱን እንዲለቁላቸው ሲነግሯቸው እንደነበር አስታውሶ፣ ሆኖም ግን ፓርቲው የአንድ አመት ውል ስላለው መልቀቁን እንዳልፈለገ ገልጹዋል፡፡
አከራዩዋ ‹‹ቀሪ ብራችሁን እመልሳለሁ፡፡ የሚደርስብኝን ጫና መቋቋም አልቻልኩምና ውጡልኝ፡፡ ሰዎቹ በዱርየዎች እንደሚያስደበድቡኝ መዛታቸውን ስለሰማሁ ቢሯችሁን ቆልፌዋለሁ›› ማለታቸውን የጠቀሰው አቶ አዲሱ፣ በተለይ በከተማዋ የበላይ ዘለቀ ቀበሌ የጸጥታ ዘርፍ አስተባባሪ አቶ ጌታቸው ግዛቸው አላስፈላጊ ወከባውን በማስተባበር ላይ መሆኑን አስረድቷል፡፡
ፓርቲው ጉዳዩን ወደ ህግ እንደሚወስደውም አቶ አዲስ ጨምሮ ገልጹዋል፡፡
ፓርቲው ጉዳዩን ወደ ህግ እንደሚወስደውም አቶ አዲስ ጨምሮ ገልጹዋል፡፡
No comments:
Post a Comment