Friday, October 11, 2013

ስለ ተስፋየ ገ /አብና ተያያዥ ጉዳዮች (አንበሳው ይብራ )

እኛ ኢትዮጵያውያን እንኳን ተወልዶባት ፤ አድጎባት ፤ ማእረግ አይቶባት ይቅርና ለሃገራችን ለኢትዮጵያ ቅንጣት ታክል ፍቅርና ክብር ላሳያት የማንኛውም ሃገር ዜጋ ልዩ ፍቅርና እንክብካቤ እናደርጋለን። አገራችን ዜጋዋ ብለን በቆጠርነው ሰው ክህደት ሲፈፀምባት ይህ የመጀመሪያው አይደለም ። ከቅኝ ገዢ ወራሪዎች ጋር ህዝባችን ሲፋለም በኢጣሊያ ሊሬ ተደልሎ ሃገሩን የከዳውን ሁሉ የባንዳ ቤት ታሪክ ይቁጠረው ። ይህን የተስፋየ ገ /አብ ክህደት ልዩ የሚያደርገው ፤ እንዲህ በራሳችን ቋንቋ በስነ – ጽሁፍ አድጎና ተመንድጎ ፣ በእያንዳንዳችን ልብ ውስጥ ትንሽ ትንሽ ስፍራ የሰጠነው ግለሰብ ፤ ከዚህ በፊት የፈፀመውን አንዱን ህዝባችንን ከሌላው ህዝባችን የማጋጨት ተግባር ይቅር ብለን ፤ እንደገና ፍቅርና ሙቀት ብንሰጠው ዳግም ከታሪካዊ ጠላቶቿ ጋር ከጀርባችን ሳንጃ ሲሰካብን ስላገኘነው ነው ።

No comments:

Post a Comment