Thursday, December 24, 2015

ኦቦ በቀለ ገርባ ታሰሩ

(ዘ-ሐበሻ) በኦሮሚያ የተለያዩ ከተሞች የተነሳውን የሕዝብ ቁጣ ተከትሎ በርካታ ወጣቶችን እያሰረ የሚገኘው ሕወሓት መራሹ መንግስት ባለፈው ማርች 2015 ከ እስር የተፈቱትን አቶ በቀለ ገርባን እንደገና አሰረ::
ዘ-ሐበሻ ከአዲስ አበባ ምንጮቿ እንዳገኘቸው የኦሮሞ ፌዴራሊስት ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ምክትል ሊቀመንበር የሆኑት ኦቦ በቀለ ገርባ ዛሬ የታሰሩት በኦሮሚያ የተለያዩ ከተሞች ከተከሰተው የሕዝብ ቁጣ ጋር ተያይዞ እንደሆነ ይገመታል::
ኦቦ በቀለ ከቤታቸው ሲወሰዱ በርካታ የደህንነት ሃይሎች እና ፖሊሶች እንደነበሩ ጨምሮ የደረሰን መረጃ ያስረዳል::

Monday, December 21, 2015

የትግራይ ሽፍቶች ለምን ወንድሞቻቸውን ይገድላሉ? – ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም

አፄ ምኒልክ ጦራቸውን ሰብስበው በእግርና በበቅሎ ከደቡብ ተነስተው ትግራይ እስቲደርሱ ኤርትራና ትግራይ ምን አድርገው ጠበቁዋቸው? የኢጣልያ ጦር ትግራይን ሰንጥቆ አምባ አላጌ እስቲደርስ ማን ሊያቆመምው ሞከረ? የኢጣሊያ ጦር መቀሌ ገብቶ ሲመሽግ ማን ተከላከለው? ስብሓት እስከዛሬ ሳይገለጥለት ቀርቶ ከሆነ የኢጣልያንን ጦር ከአምባ አላጌ ያስወጣው የምኒልክ ጦር ነው፡፡ ከመቀሌም ምሽግ ያስወጣው የጣይቱ ዘዴና የምኒልክ ጦር ነው፡፡ በኢትዮጵያዊ ይሉኝታ ተሸፋፍኖ የቆየውን እናፍረጥርጠው ከተባለ ለማን አሳፋሪ እንደሚሆን ግልጽ ነው፡፡

በቅርቡ የምንሰማው ዜና በጥምር ተቀናጅተው ኦነግ እና አርበኞች ግንቦት 7 ኢትዮጵያን ነጻ ለማውጣት ወደፊት እየገሰገሱ ወያኔን መቆሚያ እያሳጡት ነው የሚለው ይሆናል።

ምከረው ምከረው እንቢ ካለ መከራ ይምክረው እንደሚሉት አበው 25 ዓመት ሙሉ ሲመከር ሲለመን ሲዘከር ምክርን እንደ ስድብ ልመናን እንደ ፍራቻ ዝክርን እንደ ማታለል አድርጎ በመቁጠር ዝም በሉ ዝም ካላላችሁ ዝም አደርጋችሃለሁ ረግጫችሁ እገዛችኋል አማራና ኦሮሞን አጋጭቶ በመሃል እኔ ስልጣኔን እያደላደልኩኝ 100 ዓመት እገዛለሁ ብሎ የቀየሰው ስልት ዛሬ በእርግጠኝነት መናገር ወደሚቻልበት ትግል የኢትዮጵያ ህዝብ  በመግባቱ ታውቋል። ኦነግና  አርበኞች ግንቦት 7 የተቀናጀ ድምጽ አሰምተውን ኦነግ በአሶሳ ፤በሀረር ፤በቦረና ወያኔን እየደመሰሰ ወደ ፊት እየመጣ ነው። አርበኞች ግንቦት 7 በጎንደር፤ በጎጃም ፤በደቦብ በድሬደዋና በመላው ኢትዮጵያ ብሎም በአዲስ አበባ ትግሉን በማቀጣጠል ወያኔን መቆሚያና መቀመጫ እያሳጡት ነው የሚለውን ዜና እንሰማለን።

ዳር ድንበራችን በአገር ከሃዲዎች አይሸጥም!

የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ Ethiopian Border Affairs Committee P. O. Box 9536 Columbus, Ohio 43209 USA E-mail: ethiopianborders@gmail.com
 ዳር ድንበራችን በአገር ከሃዲዎች አይሸጥም!
 ከኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ ታህሳስ 7 ቀን 2008 ዓ/ም ( December 17, 2015 ) በቅርቡ የወያኔ ጠቅላይ ሚኒስቴር አቶ ኃ/ማርያም ደሳለኝ የሱዳንን ምክትል ፕሬዚዳንት ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት በሰጡት መግለጫ በያዝነው ወር ውስጥ የኢትዮጵያና ሱዳን ድንበር በመሬት ላይ የመካለሉ ሥራ እንደሚጀመር በድፍረት የሰጡት ቃል የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴን ጨምሮ መላው የኢትዮጵያን ሕዝብ በእጅጉ ያሳዘነና ያሳፈረ ከፍተኛ የአገር ክህደት ወንጀል ነው።

ፍልስፍና አልባ የሆነ አገዛዝና የፖለቲካ ትግል ዘዴ የአንድን ህብረተሰብ አስተሳሰብ ያዘበራርቃል - የመጨረሻ መጨረሻም አገርን ያወድማል!

 ፍልስፍና አልባ የሆነ አገዛዝና የፖለቲካ ትግል ዘዴ የአንድን ህብረተሰብ አስተሳሰብ ያዘበራርቃል - የመጨረሻ መጨረሻም አገርን ያወድማል! ፈቃዱ በቀለ፣ ዶ/ር 
 ከረዥም ጊዜ ጀምሮ በብዙ አፍሪካ አገሮች የሚታየው የአስተዳደር ብልሹነት፣ የህዝቦች ኑሮ መዘበራረቅና ዓላማ-ቢስ መሆን፣ እንዲያም ሲል በአንድ አገር ውስጥ የሚኖር ህዝብ በሃይማኖትና በጎሳ አሳቦ ርስ በርሱ እንዲጠላላ ማድረግና፣ የመጨረሻ መጨረሻም ወደ ርስ በርስ መተላለቅ እንዲያመራ መንገዱን ማዘጋጀት፣ በተራ አነጋገር ከመልካም አስተዳደር እጦት፣ ከአምባገነናዊ አስተዳደር መስፈንና ከዲሞክራሲ አለመኖር ጋር ሲያያዝ ይታያል። አንዳንዶች እንዲያውም እንደዚህ ዐይነቱን ዓላማ-ቢስ የህብረተሰብ ጉዞ የአፍሪካ መሪዎች ወይም የጥቁር ህዝብ ችግር አድርገው የሚመለከቱ አሉ። በእርግጥ ለአንድ አገር ስርዓት ባለው መልክ መተዳደርና፣ ህብረተሰቡም በዕቅድና በዓላማ እንዲመራ ከተፈለገ በዚያ የሰፈነው አገዛዝ ህብረተሰቡን በማደራጀት ረገድ የሚጫወተው ሚና አለ።

የዲሞክራሲ መብት መሳሳት ጭምር ነው!!!

 ግርማ ሠይፉ ማሩ 
girmaseifu32@yahoo.com
 ሰሞኑን በሀገራቸን ያሇው ትኩሳት በኦሮሚያ ክሌሌ የተከሰተው በአብዛኛው ተማሪውን ያሳተፈው “እንቢ የተቀናጀ ማስተር ፕሊን” በሚሌ የተነሳው ንቅናቄ ነው፡፡ ሇዚህ ንቅናቂ መንሰዔ ናቸው በሚሌ የኦሮሚያ ክሌሌ እና የፌዳራሌ መንግስቱ ከፍተኛ የኦህዳዴ ሾሞች መግሇጫ እየሰጡ ይገኛሌ፡፡ በእነሱ መግሇጫ መሰረት ዯግሞ ጥያቄው ከዚህም አሌፎ የመሌካም አሰተዲዯር ጭምር መሆኑን አምነዋሌ፡፡ ሁሊችንም እንዯምናሰተውሇው ኦህዳዴ ውስጥ የሚታየው ከፍተኛ የተማረ የሰው ኃይሌ እጥረት ከተወሰኑ ሰዎች ውጭ ሇማየት እዴሌ አሌሰጠንም፡፡ ይህ ባጠቃሊይ በኢህአዳግ ውስጥ ያሇ ችግር ነው፡፡ የዚህ ችግር ምንጭ ገዢው ፓርቲ የሚከተሇው መስመር ሇተማረ ቀርቶ ሇሚያመዛዝን ሰው እንኳን ምቾት የሚሰጥ አሇመሆኑ ነው፡፡ ኤርሚያ ሇገሠ የሚባሇው የቀዴሞ ኢሕዳግ ሹም ሂሣብ ተምረህ እንዳት ኢህአዳግ ሆንክ? የሚሌ ጥያቄ እንዯቀረበሇት ሰምቻሇሁ፡፡