Saturday, November 30, 2013

በባህሬን በቤት ሠራተኝነት ተቀጥራ ትሠራ የነበረች ኢትዮጵያዊት በሶስት ወንዶች ተጠልፉ መደፈሯንና በሴተኛ አዳሪነት እንድትሰራ መገደዷን በመግለፅ ክስ መሰረተች

እስራኤል ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ 60ሺህ አፍሪካውያንን አስወጣለሁ አለች

ከ120 በላይ ኢትዮጵያውያን ከሊቢያ ይመለሳሉ
እስራኤል ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ 60ሺህ የሚጠጉ አፍሪካውያን ስደተኞችን ከሃገሯ እንደምታስወጣ ያስታወቀች ሲሆን በህገወጥ መንገድ በሊቢያ የሚኖሩ ከ120 በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ደግሞ ወደ ሃገራቸው ይመለሳሉ ተብሏል፡፡ የእስራኤል ካቢኔ ባለፈው እሁድ ስደተኞቹን የሚያስወጣ አዲስ ህግ ካፀደቀ በኋላ የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያዊን ኔትያሁ፣ ህገወጥ ስደተኞቹን ከሀገራቸው እንደሚያስወጡ አስታውቀዋል፡፡

የ132 ድርጅቶችን ማህተም በመጠቀም ሃሰተኛ ሰነድ ሲያዘጋጅ የነበረው ተከሰሰ

የዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ እና የኢ/ር ሃይሉ ሻውል ቲተርና የፓርቲያቸው ማህተም 
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን ጨምሮ የበርካታ ሚኒስቴር መ/ቤቶች ማህተም 
የኦነግና የኢሜሬት ኢምባሲ ማህተሞች ተገኝተዋል
የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ጨምሮ የ132 መንግስታዊና የግል ድርጅቶችን ማህተም እንዲሁም የፖሊስ ኮሚሽነሮችን እና  የተለያዩ ግለሠቦችን ቲተር በህገወጥ መንገድ በመያዝ ለግለሠቦች ሃሠተኛ ማስረጃዎችን ሲሠራ ነበር የተባለው ተጠርጣሪ ላይ በፀረ ሙስና ኮሚሽን አቃቤ ህግ የቀረበው ክስ እንዲሻሻል ፍ/ቤት ብይን ሰጠ፡፡

የኔትዎርክ መቆራረጥ እንጂ የደንበኞች መቆራረጥ አልገጠመኝም” - ኢትዮ ቴሌኮም

ኢህአዴግም ያልተሰደደው ሥልጣን ላይ ስለሆነ ነው!
የደከመው ባለስልጣን ማረፍ እንጂ አምባሳደር መሆን የለበትም! 

በአሁኑ ጊዜ የቱንም ያህል “ልማታዊ” ለመሆን ቢሞክሩ ፈፅሞ ያልተሳካላቸው የመንግስት ተቋማት ቢኖሩ በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሱት የኢትዮጵያ መብራት ኃይል ኮርፖሬሽንና ኢትዮ ቴሌኮም ናቸው፡፡ (ልማታዊ ያልሆነ ሁሉ ኪራይ ሰብሳቢ ነው ማለት ግን አይደለም!) መብራት ሃይል መብራት እምቢ ሲለው፣ ቴሌኮምም ኔትዎርክ (በቴክኖሎጂ ግንኙነትን ማቀላጠፍ) አልሆንልህ ብሎታል (ምኑን ኖሩት ታዲያ?!) 

ከ“ፎርጅድ” ፖለቲከኞች፣ባለሥልጣናት፣ ፓርቲዎች፣ … ይጠብቀን!

“የመለስን ራዕይ እናስፈጽማለን” እያሉ ተጐልቶ መዋል ምንድነው?
ሰሞኑን ፖሊስ በቁጥጥር ሥር የዋለውን የፎርጅድ “ስፔሻሊስት” ጉድ ሰምታችሁልኛል? የመቶ ምናምን መስሪያ ቤቶችን ማህተም፣ ቲተር፣ ወዘተ… በመቅረፅ ሃሰተኛ የትምህርት ማስረጃ (ሳይማሩ ድግሪ እኮ ነው!)፣ መንጃ ፈቃድ፣ የጋብቻ ሰርተፊኬት፤ ውክልና፣ ሊብሬና ሌሎች ሰነዶችን “ሲያመርት” መክረሙን የሰማሁት ከኢቴቪ የፖሊስ ፕሮግራም ነው፡፡ (ፎርጅድ በፎርጅድ ሆነናላ!) ይሄኛውን የፎርጅድ “ስፔሻሊስት” ከቀድሞዎቹ ልዩ የሚያደርገው ምን መሰላችሁ? ያልደፈረው የመንግስት መስሪያ ቤትና የግል ተቋማት የለም፡፡ (አይዞህ ያለው ማነው?) የውጭ ጉዳይ ሚ/ር፣ የፖሊስ ኮሚሽነሮች፣ የግል ክሊኒኮች፣ የመንግስትና የግል ዩኒቨርስቲዎች፣ ወዘተ (የማን ቀረ ታዲያ!) ማህተሞችን … ፎርጅድ እየሰራ የተለያዩ ማስረጃዎችን ያቀርባል ወይም ይቸበችባል፡፡ (ፎርጅድ ፈላጊው “በሽ” ነው ማለት እኮ ነው!) 

Friday, November 29, 2013

አላማ በወጣትነት ሲቀጭ

ደረሰባት የመኪና አደጋ ህይወቷ የተቀየረው እና የአልጋ ቁራኛ የሆነችው የሺወርቅ ምህረቴ
አንዳንዶች ጥሩ ገቢ አግኝተው ህይወታቸውን ለመቀየር ወደ ባህር ማዶ ተጉዘው ባዶ እጃቸውን ወደ ሀገራቸው ይመለሳሉ። ሌሎች በህመም ወይም በአደጋ ህልማቸውን ዕውን ከማድረግ ይሰናከላሉ። በዚህ ክስተት እነሱ ብቻ ሳይሆኑ የሚረዱት ቤተሰባቸውም ጭምር ችግር ይገጥመዋል። የዛሬው የወጣቶች ዓለም ዝግጅት « አላማ በወጣትነት ሲቀጭ» ይሰኛል።

ማን ነው የተዋረደው? (ይሄይስ አእምሮ፣ ከአዲስ አበባ)

ይሄይስ አእምሮ
ከጥቂት ሣምንታት ወዲህ በተለይ የኢትዮጵያን የወያኔ መንግሥት በሚቃወሙ የሚዲያ ማዕከላት ዘንድ ዋና መነጋገሪያ ሆኖ የሚገኘው በሳዑዲ የኢትዮጵያውያን መንገላታትና መሰቃየት እንዲሁም ከኢሰብኣዊነትም በወረደ ሁኔታ በግፍ መጨፍጨፍ ነው፡፡ ዜጎቻችን በአካፑልኮ ቤይ የመዝናኛ ሥፍራ ሲንሸራሸሩ ከርመው የመጡ ይመስል ይህ ምስል በኢትዮጵያው የወያኔ ሚዲያ በአስደሳች መልክ እየቀረበ ቢሆንም ትክክለኛውን መረጃ ከአማራጭ የዜና ምንጮች እንደወረደ እንደምንከታተለው ከሆነ ግን ከሀገርና ከሕዝብ ኅልውና አኳያ ነገሩ እጅግ አሳሳቢ ነው፡፡ ከአንድ ጨለማ ውስጥ ብርሃን እንደሚጸነስ ሁሉ ከዚህ አስከፊ ገጠመኝ ውስጥ የፈነጠቀው የሕዝብ አንድነት ግን በሌላ ወገን ተስፋችን እንዲያንሠራራ አድርጓል፡፡

የአውሮፓ ህብረት ተወካዮች ከተቃዋሚዎችን ጋር ተወያዩ

ለአውሮፓ፣ ኤዥያ፣ ካሪቢያን፣ፓስፊክና አፍሪካ ጉባኤ አዲስ አበባ የተገኙት የአውሮፓ ህብረት ተወካዮች በቢሮአቸው ከተቃዋሚዎች ጋር ተወያዩ፡፡ ከስፔን፣ ፖርቱጋል፣ ማልታ፣ ፈረንሳይና እንግሊዝ የተወከሉ ልኡካን በኢትዮጵያ ስላላው አጠቃላይ ሁኔታ ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡ ከተቃዋሚዎች በኩል ከመድረክ ዶ/ር መረራ ጉዲና፣ ከአንድነት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳና አቶ አስራት ጣሴ፣ ከመኢአድ አቶ አበባው መሀሪ፣ ከሰማያዊ ፓርቲ አቶ ይልቃል ጌትነት እንዲሁም ከኢዴፓ አቶ ልደቱ አያሌውና የፓርቲው ፀሀፊ ተገኝተዋል፡፡ ከተወካዮቹ በኩል የተነሱት ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው፡- 

የወያኔ በዲሞክራሲ ቁማር እስከመቼ?

በአሸናፊ ንጋቱ
በስልጣን ላይ ያለው የወያኔ መንግስት የዛሬ 22 ዓመት አንግቦት የነበረውን የዲሞክራሲ መፈክር በማየት ዲሞክራሲ የጠማው የኢትዮጵያ ህዝብ የደስታ ጮቤ በመርገጥ ነበር የተቀበለው፡፡ ነገር ግን ይህ መፈክር ድራማ መሆኑ እየዋል እያደረ ነበር እየተጋለጠ የመጣው። ጮቤ እየረገጠ፤ ትግሉን ተቀላቅሎ መስዋት የከፈለውን ህዝብ የቁልቁል ወደ ባሰ የመከራ ማጥ ከቶታል።
ወያኔ እራሱ ህግ አውጥቶ እራሱ የማፍረስና በህጉ ያለመገዛት አባዜ የተጠናዎተው አንባገነን ስርአት መሆኑ በሃያ ሁለት አመታት የስልጣን ጉዞው አስመስክሯል፡፡ በትክክል እንደ ህገ-መንግስቱ ቢሆን ኖሮ ህገ-መንግስት የህጎች ሁለ የበላይ ህግ ነው፡፡ነግር ግን ወያኔ ያለምንም ከልካይ እንዳሻው ያለ ህዝብ ተሳትፎ ለስልጣናቸው እርዝማኔ ይመች ዘንድ ሲዘርዙትና ሲደልዙት ይስተዋላል፡፡

የህዝባችን መከራ የወያኔ የፖለቲካ መጠቀሚያ አይሆንም! (ግንቦት 7)

Ginbot 7 weekly editorialበሳውዲ አረቢያ ውስጥ እጅግ ብዙ ኢትዮጵያውያን አሁንም መከራና ስቃይ ላይ ናቸው። የደረጃ ጉዳይ ነው እንጂ ችግሩ በመካከለኛው ምስራቅ ሀገሮች በሚኖሩ ወገኖቻችን ላይ የተንሰራፋ ነው። በመላው አለም ተበትኖ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ካለማቋረጥ ያደረገው ወገንና ሀገር አኩሪ ጩኸትና አቤቱታ ችግሩ በአለም ዙሪያ ትኩረት እንዲያገኝ ባያደረግ ኖሮ የወገኖቻችን መከራ ከዚህም በከፋ መልክ ይቀጥል እንደነበር ጥርጥር የለውም። አንድ ቀን እንኳን ለሚገዛው ህዝብ ሀላፊነትና ተጠያቂነት ተሰምቶት የማያውቀው የወያኔ ጉጅሌ መንግስት እግሩን እየጎተተ ቢሆንም ወደ ችግሩ አቅጣጫ እንዲመለከት የተገደደው በዚሁ የወገን ጩኸት መሆኑ ግልጽ ነው።

Another a Heart touching News from Beirut, Lebanon (ከቤሩት የተሰማ አሰቃቂ መረጃ)

ከቤሩት የተሰማ አሰቃቂ መረጃ (ይህን ቪድዮ ከ18 ዓመት በታች የሆኑ እንዲያዩት አይመከርም)
ወደ ዘ-ሐበሻ ዝግጅት ክፍል በፌስቡክ የግል መልዕክት አንድ እህት ብታነጋግሩኝ አሳዛኝና ማንም ያልዘገበው መረጃ ቤሩት ውስጥ የተፈጸመ አቀብላችኋለሁ አለችን። ፈቃዳችንን ገልጸን ስልኳን ተቀብለን ወደ ቤሩት ደወልንላት። አነጋግርናት። ሌሎችንም እንዲሁ አንጋገርን። ከዚያም የሚከተለው አሳዛኝ መረጃ እንዲህ ተቀናበረ።

Thursday, November 28, 2013

በጅጅጋ የብሄር ብሄረሰቦችን ቀን ለማድመቅ የተቀረጸው የመለስ ዜናዊ ሃውልት ፈረሰ

ህዳር ፲፰(አስ ስምንት )ቀን ፳፻፮ / ኢሳት ዜና :-የሶማሌ ክልል 8ኛውን የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ታከብራለች መባሉን ተከትሎ የክልሉን ዋና መቀመጫ ጅጅጋን  አርቲስቶች እና የመንግስት ባለስልጣናት በየጊዜው እየጎበኙዋት ነው።
ለበዓሉ ዝግጅት የተመደበለትን 31 ሚልዩን ብር ከዝግጅቱ በፊት ቀድሞ ያጠናቀቀው የሶማሌ ክልል መንግስትን ለበአሉ ማክበሪያ እና ማድመቂያ በማለት ተጨማሪ 14 ሚሊዮን ብር ጠይቋል።
ለበዓሉ ማስተናገጃ የሚሆን ስቴዲየም በመገንባት ላይ የተጠመደው ክልሉ ፤ በገጠመው የበጀት እጥረት የተነሳ በጅምር ባለ ስታዲየም በዓሉን ያከናውናል፡፡ የፌድሬሺን ምክር ቤት ባካሄደው ግምገማ ከ10 ሚልየን ብር በላይ ገንዘብ ያለ አግባብ የባከነ መሆኑን አረጋግጦዋል፡፡ በተመደበው በጀት ዘወትር ከስራ ስዓት ውጭ የከስዓት ጊዜን በመጠቀም የክልሉ ባለስልጣናት ገንዘቡን ጫት ቅመውበታል ሲል ምክር ቤቱ ትችት አቅርቧል።

ሰማያዊ ፓርቲ አፄ ምኒልክ የሞቱበትን አንድ መቶኛ ዓመት በዓል ሊያከብር ነው።

ሰማያዊ ፓርቲ አፄ ምኒልክ የሞቱበትን አንድ መቶኛ ዓመት በዓል እንደሚያከብር የፓርቲው የሕዝብ ግንኙነት አስታውቋል። አፄ ምኒልክ የሞቱበት ዕለት ታህሳስ 3 ቀን በመሆኑ ዕለቱን የፓናል ውይይት፣ ጉብኝትና ኤግዚቪሽኖች በማዘጋጀት በአሉን በልዩ ልዩ ፕሮግራሞች ለማክበር እየተዘጋጁ መሆኑን አስታውቋል።  በዕለቱ በተመሳሳይ ቀን ያለፉት ፊታውራሪ ኃብተጊዮርጊስ ዲነግዴ አብረው የሚታሰቡ መሆኑን የፓርቲው አስታውቋል። ፓርቲው ወደፊትም “የታላቋ ኢትዮጵያ ቀን” በሚል በየሶስት ወሩ ቋሚ ፕሮግራም እንደሚያዘጋጅ ጨምሮ አስታውቋል።

በደላላ ሃገር ሰትመራ!

ታደለ መኩሪያ
በትግራይ ሕዝብ ነፃነት ግንባር ሽፋን፤ ዛሬ ይህቺን ጥንታዊት ሃገር ኢትዮጵያን እየመራት ያለው ወያኔ የሚባል ቡድን ነው። ይህ የጭንጋፍ ስብስብ  በትግራይ ሕዝብ ልባስ የኢትዮጵያን ለም መሬትና ቡቃቅላ  ልጆቿን በደላላነት ለሳውዲ አረቢያ ሲያቀርብ መቆየቱን ዓለም ያወቀው ፀሐይ የሞቀው ሐቅ ነው። የዚህ ቡድን የጥቅማጥቅም ተቋዳሾችና አልጠብባዮች ጋር በመተባበር ቤሔራዊ ኩራታችንን አደጋ ላይ ጥለውታል።እነዚህ የዕንግዴ ልጆች  ሆድ አደሮች ፤ትውልድም፣ የገዛ ልጆቻቸው የሚያፍሩባቸው ናቸው። ይህቺን በደምና አጥንት የቆመች ሃገር በአደባባይ እንድትዋረድ አደርገዋታል፤የቤሔራዊ ውርደት እንድንከናነብ አድርገውናል፤ በአባቶቻችን መሰዕዋትነት ለዘመናት  አንገታችንን  ቀና እንደላደረግን ዛሬ በውርደታችን አፍረን አቀርቀረናል።

በሪያድ የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች በወገኖቻችን ስም በእጅ አዙር ገንዘብ ማሰባሰብ መጀመራቸው እየተነገረ ነው ።

በሪያድ መለዝ አካባቢ የሚገኝ፡አሚራ ኑራ ዩንቨርስቲ ግቢ ሜዳ ላይ ያለዳስ ብርድ እና ጸሃይ የሚፈራረቅባቸው ከ 7 ሺሕ የሚበልጡ ወገኖቻችን በመግብ ወሃ እና የመጸዳጃ ቦታ እጦት እየተሰቃዩ ነው ። የተጠቀሰው መጠለያ ውስጥ ያሉት ወገኖቻችን አብዛኛዎቹ ሴቶች ህጻናት እና አረጋውያን እንደሆኑ መረጃዎች ያመለክታሉ።
* በሪያድ የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች በወገኖቻችን ስም በእጅ አዙር ገንዘብ ማሰባሰብ መጀመራቸው እየተነገረ ነው ።

‹‹ሰው ለሰው›› የቴሌቪዥን ተከታታይ ድራማ በወ/ሮ አዜብ መስፍን ትእዛዝ ስክሪፕቱን እንዲቀይር ተገደደ፡፡

ኢሳት ዜና :-በኢትዩጵያ የቴሌቪዥን ድራማ ታሪክ በረዥምነቱ ቀዳሚውን ቦታ በመያዝ የሚታውቀው ሰው ለ ሰው ተከታታይ ድራማ 109 ክፍሎች ያህል ከተላለፈ በኃላ፣ ሰዎች በማህበራዊ ድህረ ገጾች የድራማው ተዋንያን የሆነውን በትወና ስሙ አስናቀ የተባለውን  ከቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ባለቤት ከወ/ሮ አዜብ መስፍን ጋር  በማመሳስል ገጸባህሪውና ወ/ሮ አዜብ መስፍን ባለስልጣናትን በገንዘብ ይገዛሉ ፤ ፍትህን ይረግጣሉ ፤ በሰው ህይዎት ይነግዳሉ፡ ፤ ሰው ያስገድላሉ፤ ህዝብን ያስለቅሳሉ ፤ በወንጀል ይነግዳሉ፤ ሰው በላ እና ነፍሰ ገዳይ አምባገነን ናቸው ሲሉ እንደሚተቹዋቸው ይታወቃል፡፡

Wednesday, November 27, 2013

የሳዑዲ ጉዳይ የዛሬ አዳዲስ መረጃዎች – በነብዩ ሲራክ (ጋዜጠኛ)

ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ከ40 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ ሃገራቸው ገብተዋል ይሉናል፤ የሳዑዲ ባለስልጣናት ደግሞ 28 ሺህ ኢትዮጵያውያንን ነው ወደ ሃገራቸው የላክነው ይላሉ። ዶ/ር ቴዎድሮስ 13 ሺህ ሰው ከየት ሸቅበው ነው?… ለማንኛውም ሳዑዲ አረቢያ የሚገኘው ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ የሚሰጠንን አዳዲስ መረጃዎች ይመልከቱ…
ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ በፌስቡክ ገጹ እነዚህን አዳዲስ ነገሮች አካፍሎናል፦
* ጅዳ …. ትናንት ከጅዳ ቆንስል አካባቢ ወደ ሽሜሲ ማቆያ እስር ቤት ከሌሊት እስከ ምሽት የሔዱት ወገኖች ቁጥር 1.500 እንደሆነ ታውቋል። መሔዳቸውን ተከትሎ በርካታ የተጨበጡና ያልተጨበጡ መረጃዎች እየተሰራጩ ነው ።

የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ 3ኛ ዓመት ተማሪዎች ሲጮኹ ዋሉ፤ ዲኑ ተማሪዎቹን “በዩኒቨርሲቲው በቀን ሦስቴ እየበላችሁ ጠገባችሁ” አሉ

የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ 3ኛ ዓመት ተማሪዎች ሲጮኹ ዋሉ፤ ዲኑ ተማሪዎቹን “በዩኒቨርሲቲው በቀን ሦስቴ እየበላችሁ ጠገባችሁ” አሉ
NOV 27,2013
በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ 3ኛ ዓመት ተማሪ የሆኑ ተማሪዎች ከውጤት አሰጣጥ ጋር ከዩኒቨርሲቲው አመራሮች ጋር በፈጠሩት አለመግባባት ሲጮኹ መዋላቸውን የዘ-ሐበሻ የባህርዳር ዘጋቢዎች ከስፍራው ዘግበዋል። እንደ ዘጋቢዎቻችን ገለጻ የ3ኛ ዓመት ተማሪዎቹ ጩኸታቸውን ሲያሰሙ ከዋሉ በኋላ የዩኒቨሲቲው ዲን ዶ/ር ባየልኝ ዳምጤ ሰብስበው ያነጋግሯቸው ቢሆንም፤ ዶ/ሩ ችግሩን ከማብረድ ይልቅ እሳት ለኩሰውበት ሄደዋል ሲሉ ተማሪዎቹ ለዘ-ሐበሻ ዘጋቢ ነግረውታል።

ኢትዮጵያን ልትሸጥ ?

ይቺ ኢትዮጵያ የምትባል ሃገራችን ፈርዶባት በየቀኑ፤ በየሰአቱ፤ በየደቂቃው፤ በየሴኮንዱ አዳዲስ ችግርና መከራ እያፈጠጠባት ለስቃይ የተሰራች ሃገር እየሆነች ነው፡፡ ሀገራችን ብለን በፍቅር የምንጠራትና፤ ከክፉ ነገር እንድትጠበቅ፤ የምንጸልይላትና አቅማችን በፈቀደልን መጠን የምንጠብቃት በርካታ ልጆች ብንኖርም፤ በየደቂቃውና በየሴኮንዱ ክፉ የሚያስቡላት፤ መከራዋን የሚመኙላት፤ ዜማ ጭፈራቸው ጥፋቷን የሚመኝላት፤ ጥቂት፤ ከራሳቸውም፤ ከዜግነታቸውም፤ ከሰብአዊነታቸውም፤ ከተፈጥሯቸውም ተጣልተው፤ ከሆዳቸው ጋር ብቻ ተፋቅረውና ተግባብተው የሚኖሩ ኢምንት አርጉም የእንግዴ ልጆችም አሏት፡፡

በታላቁ ሩጫ ሕዝቡ በሳዑዲ ላይ ተቃውሞውን ሲያሰማ ነበር፤ ሕዝቡ “አዝኗል ሀገሬ” እያለ ዘፍኗል – ሪፖርተር

ሥራ አጥነት የስደት አበሳ ማብቂያው ቅርብ ላለመሆኑ ማስረጃ” በሚል ርዕስ ሪፖርተር ጋዜጣ ባስነበበው ዜና ትንታኔ “ታላቁ ሩጫ እሑድ ኅዳር 15 ቀን 2006 ዓ.ም. በጃንሜዳ ሲካሄድ ተሳታፊው ሁለት ስሜቶችን እኩል ለማስተናገድ ሲታገል ተስተውሏል፡፡ አንዴ የሐዘን ደግሞ ወዲያው የደስታ ስሜቱን ሲያስተጋባ ታይቷል፡፡” ብሏል።
የሪፖርተር (የብርሃኑ ፈቃደ 0 ዘገባ እንደወረደ፦
የተቃውሞ ድምፁን በሳዑዲ ዓረቢያ መንግሥት ላይ ሲያሰማ ተደምጧል፡፡ የተቃውሞ ድምፁ የወቅቱን የኢትዮጵያን ስደተኞች እንግልት ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡ በተቃወመበት አፍታ ደግሞ ዋልያዎቹን እያወደሰ ይደሰታል፡፡ መንግሥትንም በአሽሙር ይሸነቁጣል፡፡ የአርቲስት ስለሺ ደምሴ (ጋሽ አበራ ሞላ) አዲሱ ‹‹ኧረ ያምራል አገሬ›› ዘፈን፣ በሯጩ ሕዝብ ‹‹ኧረ አዝኗል አገሬ›› ተብሎ ተዘፍኗል፡፡

EU Member of Parliament Ana Gomes in Addis Ababa

Serious talk! EU Member of Parliament Ana Gomes, known for publicly criticisingEthiopia following the 2005 government crackdown, which claimed over 200 lives, in a seemingly serious discussion during lunch break with Ethiopian MP and Speaker of the House Abadulla Gemeda in Addis Ababa, November 25, 2013. ANDUALEM SISAY | NATION MEDIA GROUP
The 26th European Union (EU) and African Caribbean Pacific (ACP) Joint Parliamentary Assembly (JPA) opened in Addis Ababa, Ethiopia Monday morning.

ዶክተር ሀይሉ የተቃዋሚዎችን ድክመት በድፍረት ተናገሩ

የዛሬዋ ኢትዮ ምህዳር ስለ ተቃዋሚዎች ውህደትና ህብረት ሰፊ ሀተታ ይዛ ወጥታለች፡፡ በተለይ ዶክተር ሀይሉ አራዕያ ስለ ተቃዋሚዎች ውህደት ያነሱት ሀሳብ ወቅታዊና አንገብጋቢ ሆኖ አግኝቸዋለሁ፡፡
ዶክተር ሀይሉ የተቃዋሚዎችን ድክመት በድፍረት ጽፈዋል፡፡ ዶክተሩ ተቃዋሚዎች ካልተዋሃዱ፣ ካልተባበሩ በስተቀር ምርጫ ሊያሸንፉና ለውጥ ሊያመጡ እንደማይችሉ አስረግጠው ነግረዋቸዋል፡፡ ዶክተሩ የሚሉት ለስልጣን ሳይሆን ለህዝብ ተዋሃዱ፣ ካለፈው ስህተት፣ ከሌሎች አገራትም ተማሩ፣ ህዝብን አታስገዙ፣ ጥቂት ተስፋ ሰጥታችው ዋናውን ተስፋውን አትንጠቁ ነው፡፡

[አሳዛኝ ዜና]በአሜሪካ ቴክሳስ ግዛት ውስጥ ዳናይት ኪዳነ የተባለች ልጁን በጩቤ ወግቶ ከገደለ በኃላ እራሱን በእሳት ለኩሶ ሲያቃጥል ፖሊስ ደርሶ ወደ ሆስፒታል ወሰደው

[አሳዛኝ ዜና] በአሜሪካ ቴክሳስ ክፍለ ግዛት ውስጥ አቶ ሙሉጌታ ተረፈ የተባለ አባት ዳናይት ኪዳነ የተባለች ልጁን ቤቱ ውስጥ በጩቤ ወግቶ ከገደለ በኃላ ከአካባቢ በመሰወር መኪና ውስጥ እራሱን በእሳት ለኩሶ 98% ሰውነቱን ካቃጠለ በኃላ ፖሊስ ደርሶ ወደ ሆስፒታል ወስዶታል:: ዝርዝሩን ከዚህ ቭዲዮ ያግኙ::
CORPUS CHRISTI 
The Nueces County Medical Examiner’s Office has confirmed the identity of the woman who died after she was stabbed multiple times Monday night in Flour Bluff.

ኮንዶሚንየም ቤቶች የዝሙት መናሀሪያ ሆነዋል

መንግስት በተለምዶ ኮንደሚንየም ብሎ አንደነገሩ ገነባብቶ ቀብቶ ከሰራቸው እና ለህዝብ ካደላቸው በኣዲስ ኣበባ በየቦታው ባሉ የባለኣራት ፎቅ ኣፓርትመንት የጋራ የመኖሪያ ቤቶች ኣካባቢ የዝሙት፥ የመጠጥ እና የኣደንዛዥ እጽ መናሀሪያዎች ሆነዋል ሲሉ ነዋሪዎች ተናገሩ::
የድሮ ስንቅ እና ትጥቅ በኣሁኑ “ጎተራ” በሚባለው ኮንዶሚንየም ሳይት ውስጥ ያለውን ሁኔታ ከኣካባቢው ነዋሪዎች ኣንዱ እንዲህ ስል ይገልጸዋል፥፥
መደበኛ ስራው የቤት ደላላ የነበረ ሲሆን ኣሁን ግን በኮንዶሚንየም ለሚገኙ ሴተኛ ኣዳሪዎች ማምሻውን ደንበኛ በማፈላለግ ይሰራል፥፥ኣካባቢው ሃያ ኣራት ሰኣት ክፍት ነው:: በስፍራው የቁጥራቸው ትንሽ የማይባል የመጠጥ ፥የጫት ቤቶች : ራቁት መደነሻዎች ጭምር ከ ምድር እስከ ላይ ሶስተኛ እና ኣራተኛ ፎቆች ላይ ይገኛሉ ይለን እና ለ ዝሙት ንግድ የሚሆኑ ክፍሎች ይገኛሉ ይላል::

Tuesday, November 26, 2013

ኢትዮጵያዊ ዋጋው ስንት ነው?

(ተመስገን ደሳለኝ)
የዚህ ፅሁፍ ማጠንጠኛ የፖለቲካ አመለካከትን መተቸት አይደለም፤ ከዋና ዋና ሀገራዊ አጀንዳዎች ወረድ ያሉ የጉልበታሙን ስርዓት የሥራ አፈፃፀሞችን ማብጠልጠልም አይደለም፤ የተቀናቃኝ ፓርቲዎችን ስንክሳር መንቀስም… አይደለም፡፡ ኢትዮጵያዊ (አል-ሀበሽ) መሆን ለፈተና፣ ለመከራ፣ ለሰቆቃ… መዳረጉ የወለደው ብሶት እንጂ፤ መመረር-ማምረር ነው፡፡ …ይህ የእኛ ዕጣ ፈንታ የሆነበትን ምስጢር መመርመር ነው፡፡
ሰሞኑን የሳውዲ አረቢያ መንግስት ታጣቂዎች እና በድጎማ የሚያድሩ የሀገሬው ተወላጆች በመሰረቱት የጥፋት ግንባር ጉልበታቸውን ገብረው፣ በላብ በወዛቸው በሚያድሩ ስደተኛ ወገኖቻችን ላይ የተፈፀመው አረመኔያዊ ወንጀል፣ የሁሉንም ኢትዮጵያዊ ልብ በከባድ ሀዘን የሰበረ፣ በቁጭት ያንገበገበ አሳዛኝ ፍፃሜ ሆኗል፡፡

ከአቶ ታምራት ላይኔ ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ (ከአንድ ጉዳይ በቀር በርካታ ቁምነገሮች አለው)

(ዳዊት ከበደ ወየሳ) – ከአቶ ታምራት ላይኔ ጋር የተደረገው ቃለ ምልልስ አስገራሚ ነው። በአውስትራልያ የ-SBS አማርኛ ፕሮግራም ነው ይህንን ያስደመጠን – ምስጋና ይገባቸዋል። በቃለምልልሱ ውስጥ የምናውቃቸውና የማናውቃቸውን፤ በወሬ የሰማናቸውንም ሆነ በታሪክ ያየናቸውን ጉዳዮች ተካተዋል። ከራሳቸው የግል ህይወት አስተዳደግ እና አስተሳሰብ በመነሳት ስለ ትጥቅ ትግሉ ታሪክ ብዙ ብዙ ነገሮችን ብለዋል። ኢህዴን የተባለው ድርጅት ከጎንደር አካባቢ ተነስቶ ወደ ትግራይ ክልል ከመሄዱ በፊት፤ ከህወሃት ጋር የርስ በርስ ንግግር የተደረገ መሆኑን፤ ያንጊዜ ወደ ትግራይ እንዲገቡ ባይፈቅዱላቸው የርስ በርስ ግጭት ሊኖር ይችል እንደነበር ወይም ወደ ሱዳን ተመልሰው ሃይል አጠናክረው ትግራይ መግባታቸው የማይቀር መሆኑን ያብራራሉ። ከዚህም በተጨማሪ ኢህዴን በኤርትራ ላይ የነበረው አቋም ምን እንደነበረና በኋላም ከህወሃት ጋር ተቀላቅሎ “ኢህአዴግ” የተባለ ግንባር መመስረቱን፤ ከዚያም ይህ ድርጅት ከብሄራዊ ድርጅትነት ወደ ብሄር ድርጅትነት ወርዶ “ብአዴን” ስለመባሉ ይገልጻሉ። ነገር ግን ወደ ዝርዝር ማብራሪያ አልሰጡበትም። “ብዙ ነገር አለ” ብለው ያልፉታል።

የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባርና የጋምቤላ ሕዝብ ነፃነት ንቅናቄ ሰራዊት በጋራ ወታደራዊ ጥቃት ፈፀሙ

የጋራ ትግል አስፈላጊ መሆኑን በፅኑ የሚያምኑት የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር /ኢሕአግ/

Ethiopian freedom fighters
የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባርና የጋምቤላ ሕዝብ ነፃነት ንቅናቄ /ጋሕነን/ በሕዳር 13/2006 ዓ.ም በሁመራ ሉግዲ ከቀኑ 10፡00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 1፡00 ለሶስት ሰዓት ያህል በወሰደው ውጊያ የወያኔው 24ኛ ክፍለ ጦር ድባቅ ተመቷል።
ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በ24ኛው ክፈለ/ ጦር ላይ በተመሳሳይ ሥፍራ  ከፍተኛ ድል መቀዳጀቱ ይታወሳል።
በሕዳር 13/2006 ዓ.ም የኢሕአግና የጋህነን ሰራዊት በወሰዱት ድንገተኛ ወታደራዊ ጥቃት 66 /ስልሳ ስድስት/ ገድለው 113 /አንድ መቶ አስራ ሶስት/ በማቁሰል እንዲሁም ቁጥራቸው የበዛ የጦር መሳሪያዎችን ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ማርከዋል።

በሽብርተንነት ስም የህዝብ መብቶችን ማፈን ይቁም!

ከቅዱስ ዬሃንስ
ፀረ -ሽብርተኝነት ለአምባገነኖች ሁለት ጥቅም ያስገኝላቸዋል፡፡ አንደኛ በፀረ- ሽብርተኝነት ስም ከምዕራባውያን ኃያላን ጎን በአጋርነት በመቆማቸው በጥሬ ገንዘብም ሆነ በዓይነት (ለምሳሌ በመሣሪያ፣ በፖለቲካ ድጋፍ) ዳጎስ ያለ ጥቅም ያገኛሉ፡፡ ሁለተኛ ሽብርተኝነትን በመዋጋት ስም የሚያወጡት ሕግ የውስጥ የሥልጣን ተቀናቃኞቻቸውን ለማጥቃት የሚያስችላቸውን ሕጋዊ ሽፋን ይሰጣቸዋል፡፡ ስለዚህ ነው ፀረ -ሽብርተኝነት ለአምባገነኖች ከሰማይ የወረደ የተቀናቃኝ ማጥቂያ መሣሪያ ነው የሚባለው፡፡ ይህንን ያልኩበት አብይ ጉዳይ ዛሬ ሃገራችንንና ህዝቧን እያስጨነቀ ያለው የወያኔ አገዛዝ የፀረ ሽብርተኝነት ህግን ከለላ በማድረግ በሰላማዊ ህዝብ ላይ እያደረሰ ያለው የመብት ረገጣ፤ እጅግ የከፋ ደረጃ በመድረሱ ነው።

ተዋርደን አንቀርም!! ኢ/ር ይልቃል ጌትነት (የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር)

ሳውዲ አረቢያ በዜጎቻችን ላይ እያደረሰች ያለውን ግፍና በደል በሰላማዊ ሰልፍ ለመቃወም ፓርቲያችን በወሰነው መሰረት ለሚመለከተው ክፍል አሳውቀን ነበር፡፡መቸም ህዝባችን በጭቆና ውስጥ ስለኖረ በመብቱና በግዴታው መሀል ያለውን ድንበር በውል ካለመረዳቱ የተነሳ ሰልፉ እንዲደረግ ስለመፈቀዱ በተደጋጋሚ ስንጠየቅ ነበር፡፡ህጉ የሚለው ግን ማስፈቀድ ሳይሆን ማሳወቅ ብቻ ነው፡፡በተቃራኒው መንግስት በተለያዩ ጉዳዮች ሳቢያ በእለቱ ለሰላማዊ ሰልፉ የደህንነት ከለላ መስጠት የማይችልበት ሁኔታ ከገጠመው ሰልፉን ለጠራው አካል ችግሩን ገልጾ ቀኑ እንዲተላለፍለት ይጠይቃል፡፡በመሆኑም ይህን መሰል ጥያቄ ከሚመለከተው መስሪያ ቤት ለፓርቲያችን ባለመቅረቡ በሙሉ ልብ ቅድመ-ዝግጅት ማድረጉን ተያያዝን፡፡

ህወኃት ወያኔ በሳዉዲ ዜጎቻችን ብቸኛ ተጠያቂ ነዉ

Author Roba Pawlos
ሮባ ጳዉሎስ
ኢትዮጵያ የህዝቦችዋ መኖርያና ሀገሪቷ ለህዝቦችዋ መሆንያለባትን እንዳትሆን ላለፉት ፪፪ አመታት ሲወጠን እና ሲደረግ የነበረ የኢሰብአዊና አረመኔያዊ የህወኃት ወያኔ የገማ የዘር ፓለቲካ ዉጤት መልስ ነዉ በሳዉዲ አረቢያ በዜጎቻችን ላይ የተፈፀመዉ መታረድና መደፈር።
እኩልነት መቻቻል ሰላም ፍትህና ነፃነት ዜጎችን በመከልከል በሀይማኖት በዘርና በጎሣ በመከፋፈል እየነጠለ በመምታት እንዲሁም ለይቶና ረግጦ መግዛት የማይችልባቸዉን ቦታዎች በኢንቨስትመንት ስም ለዉጪ ወራሪዎች በመስጠት ዜጎችን በዘመናዊ ባርነት ስር በመጣል ከገዛ መሬታቸዉ በማፈናቀልና በማሳፈን ሀገሪቷ ላይ ያለዉን የስራ እድል ለዉጭ ወራሪዎች እና ለገዳዮቻችን የሳውዲ ዜጎች ጭምር በመስጠት ወጣቱን ገሎ አስሮ አሰድዶ አዋርዶናል።

“ኦሮሞዎች ኢትዮጵያውያን አይደለንም”የሚለውን መፈክር ማሰማት- ምን ማለት ነው?

“እኛ ኦሮሞዎች ኢትዮጵያውያን አይደለንም”የሚሉ ኦሮሞዎች እንዳሉ አውቃለሁ። ይህን አቋም የሚያራምዱት ከአጠቃላይ የኦሮሞ ህዝብ ውስጥ ምን ያህል ፐርሰንቱን እንደሚወክሉ
ግን መረጃው የለኝም። በፖለቲካ ፓርቲ ደረጃ አንድኛው የኦነግ ክንፍ ከኢትዮጵያ የተለየችን ኦሮሚያ የመፍጠር ዓለማ ሰንቆ ሲንቀሳቀስ፤ ሌለኛው ደግሞ “መፍትሔው ሁላችንም በእኩልነትና በፍትህ የምንኖርባትን ኢትዮጵያ እውን ማድረግ ነው” ብሎ ማወጁን ከሁለት ዓመት በፊት ሰምቻለሁ። ይህ ብቻ ሳይሆን በነ ፕሮፌሰር መረራ የሚመራው ኦብኮ( ልብ በሉ ኦብኮ በ 1997ቱ ምርጫ ወቅት ከቅንጂት ቀጥሎ በተናጠል በርካታ የፓርላማ መቀመጫዎችን ያሸነፈና በኦሮሞ ህዝብ ንድ ተቀባይነቱን ያስመሰከረ ፓርቲ ነው) ፣ በአቶ ቡልቻ ደመቅሳ የተመሰረተው ኦፌዲንና ሌሎችም የኦሮሞ ፓርቲዎች- ከነባሩ ኦነግ የተለየ አቋም እንደሚያራምዱ እና ዲሞክራሲ፣ ፍትህና እኩልነት በሰፈነባት ኢትዮጵያ ውስጥ የ ኦሮሞን ህዝብ መብትና ጥቅም ከማረጋገጥ ውጪ ሌላ የተሻለ አማራጭ እንደሌለ አውጀው እየተንቀሳቀሱ ነው።

ህወሃት በጄነራል ሓየሎም አርአያ እንዴት ጨከነች? Asgede g/selasi

‹‹ዳግመ አሉላ ››የሚል መጠሪያ የተሰጠው ግለ ታሪክ መጽሐፍ በመቀሌ በቅርቡ ተመርቋል፡፡መጽሐፉ በመጠጥ ቤት ውስጥ በተነሳ አንባጓሮ ህይወቱን ስላጣው የቀድሞው የህወሃት/ኢህአዴግ የጦር አመራር ሜጀር ጄኔራል ሐየሎም አርአያ የሚተርክ ነው፡፡ጸሐፊው በቅን ልቦና በመነሳሳት ‹‹ጀግና››በማለት የሚጠሩትን ተጋዳላይ ታሪክ የሚዘክር መጽሐፍ ለማዘጋጀት ገና ሲነሳሱ ሐሳባቸው በዋናነት በህወሃት ሰዎችና በሃየሎም የቅርብ ሰዎች አንቱታን እንደሚያገኝ ተስፋ ሰንቀው የነበረ ቢሆንም ደጃቸውን የረገጡባቸው የህወሃት አመራሮችና የሐየሎም ጓዶች የሚያውቁትን መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል፡፡

“አንዱዓለም አራጌ በትግራይ ሕዝብ የሚወደድ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ነው” አብርሃ ደስታ

ከመቀሌ ኢትዮጵያ በየጊዜው በፌስቡክ እና በተለያዩ ድረገጾች ወቅታዊ መረጃዎችን በማድረስ የሚታወቀው አብርሃ ደስታ አንዷአለም አራጌ በትግራይ ሕዝብ የሚወደድ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ነው አለ።
በአሁኑ ወቅት የ ዕድሜ ልክ እስራት ተፈርዶበት በማረሚያ ቤት የሚገኘውና በዚህ አመት የዘ-ሐበሻ እና የኢሳት ተከታዮች የዓመቱ ምርጥ ሰው በሚል ሽልማት ያገኘው አንዷለም አራጌ በትግራይ ሕዝብ ዘንድም ከፍተኛ አክብሮት የተሰጠው ፖለቲከኛ መሆኑን አብርሃ ደስታ ገልጿል።
“ከትግራይ ሰዎች ባሰባሰብኩት መረጃ መሰረት ባሁኑ ሰዓት ክብርና አድናቆት የተቸረው የተቃዋሚ ፖለቲካ መሪ አንዱአለም አራጌ ነው” ሲል በፌስቡክ ገጹ የገለጸው ሌሎች ዝርዝር መረጃዎችን አላስቀመጠም።

የ ታላቁ ሩጫ ተሳታፊዎች ተቃዉሟቸዉን አሰሙ!!!

ቁጥራቸዉ ቀላል የማይባል ወገኖች ዛሬ በተካሄደዉ የ ታላቁ ሩጫ ላይ በሳዑዲ ስለሚሞቱና ስለሚንገላቱ ኢትዮጵያዊያን ድምፃቸዉን ሲያሰሙና በመንግስትም ላይ ወቀሳቸዉን በመፈክር እዲዲሁም በዜማ አሰምተዋል፡፡ መንግሰት በዚህ ሩጫ ላይ ህብረተሰቡ የሰማያዊ ፓርቲን ጥሪ እዳይቀበል በአዘጋጀቹ በኩል ቢያሳስብም(ጥቁር ሪቫን እንዳይደረግ) የሀገር ፍቅር ያቃጠላቸዉና የወገኖቻቸዉ ጥቃት ያተሰማቸዉተሳታፊዎች ከፍተኛ የፖሊስና የደህንነት ቁጥጥር ከቁብ ሳይቆጥሩ “በሳዑዲ ነገር እንነጋገር የሳዑዲን ነገር ” ሲሉ አርፍደዋል፡፡ ገና ከመግቢያዉ ጀምሮ ከፍተኛ ፍተሻ ሲደረግ የነበረ ቢሆንም አብዛኞቹ ተሳታፊዎች ሪቫኑን ትተዉ በጥቁር ኮፍያና ሱሪዎች ሩጫዉን መካፈል ችለዋል(በተቃዉሞዉ የተሳተፉቱ)፡፡

ከአቶ ኃይለማሪያም መጠበቃችን ስህተት ነበር – ግርማ ካሳ

በሕገ መንግስቱ መሰረት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥና የሚኒስቴሮች ምክር ቤት ሰብሳቢ ናቸዉ። የጦር ኃይሎች ኤታ ማጆር ሹምን፣ ተቀዳሚ ጠቅላይ ሚኒስትርን፣ የሚኒስቴር ካቢኔዎችን፣ የፌደራል ፖሊስ አዛዦችን … የመሾምና የመሻር ሙሉ ስልጣን አላቸው። ፓርላማዉን በትነው አዲስ ምርጫ መጥራትም ይችላሉ። ፓርላማው በፈለገ ጊዜ ጠቅላይ ሚኒስቴሩን አዉርዶ፣ ሌላ መሾም ይችላል። ጠቅላይ ሚኒስትሩም ተጠሪነታቸው ለፓርላማዉ ብቻ ነዉ።
የፓርላማ አባላት፣ በፓርቲያቸው ለእጩነት ቢቀርቡም፣ በሕዝብ የተመረጡ፣ ተጠሪነታቸው ለፓርቲዉ አመራር አባላት ሳይሆን፣ ለመረጣቸው ሕዝብ ብቻ ነዉ። በፓርላማዉ ካሉ 547 መቀመጫዎች ደግሞ፣ የሕውሃት አባል የሆኑት 38ቱ ብቻ ናቸው (6.9 በመቶ ብቻ)።

ጠጉረ ልውጦች ከአራት ኪሎ እንጅ ከሶማሊያ ወይንም ከኢራቅ ይመጡ ይሆን?

ጠጉረ ልውጡ ‹‹መንግስት››
………
ሰሞኑን በኢቲቪና በሬዲዮ፣ እንዲሁም ህዝቡን እየሰበሰቡ ‹‹ጠጉረ ልውጥ ሰው ካያችሁ ጠቁሙን!›› ሲሉ ሰንብተዋል፡፡
ጠጉረ ልውጥ ማለት አገሪቱን አሊያም ህዝቡን የማያውቅ ማለት አይደለም፡፡ እሱማ ፈልጎም ሆነ አፈላልጎ ወደዛው ደርሷል፡፡ ጠጉረ ልውጥ የሚገኝባት አገርም ሆነ ህዝብ በውል የማያውቁት በዕድ ማለት ነው፡፡
አሁን ወደ ጥቆማው እንግባ፡፡ በእርግጠኝነት ጠቁሙ የተባልነው የውጭ አገር ዜጎችን አይደለም፡፡ እንደዛ ከሆነማ ቻይናዎቹንም አናውቃቸውም፡፡ የሶማሊያ ስደተኞችንስ ስናሳስር ልንውል ነው እንዴ? እኔ እንደሚመስለኝ እነሱ ጠጉረ ልውጥ ብለው ያተኮሩት ከ90 ሚሊዮኑ ህዝብ መካከል ነው፡፡ ስለሆነም ማተኮር የፈለኩት እዚሁ አገር ውስጥ ነው፡፡

Sunday, November 24, 2013

ሰበር ዜና ሪያድ-በኢትዮጵያውያን እና በሳውዲ ፖሊሶች መሃከል በተነሳ ግጭት አንዲት ነፍሰጡር ኢትዮጵያዊት በአውቶብስ ተገጭታ ህይወቷ አለፈ።

ሪያድ አሚራ ኑራ ዩንቨርስቲ ውስጥ፡ግዜያዊ መጠለያ ሜዳል ላይ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና በሳውዲ ፖሊሶች መሃከል በተነሳ ግጭት አንዲት ነፍሰጡር ኢትዮጵያዊት በአውቶብስ ተገጭታ ህይወቷ አለፈ።
ሪያድ መንፉሃ እየተባለ ከሚጠራ አካባቢ ሰሞኑንን በውሳዲ ፖሊሶች ታፍሰው ከከተማይቱ 120 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ወደ ምትገኝ፡ በተለምዶ ሚንዛህሚያ እየተባለ የሚጠራ እስርቤት ተወስደው ከነበሩ 10 ሺህ ኢትዮጵያውያን መሃከል ግማሽ፡ያህሉ በ 17 አውቶብስ ተጭነው ማምሻውን ሪያድ ከተማ አሚራ ኑራ እየተባለ የሚጠራ ዩኒቨርስቲ ሜዳ ላይ መጣላቸውን ተከትሎ ከባድ ሁከት መቀስቀሱን ከሪያድ የሚደርሱ መረጃዎች ያመለክታሉ ።

በጎንደር ዩንቨርስቲ ውጥረቱ እንደቀጠለ ነው .አንድ ተማሪ በታጣቂዎች ተገድሏል

ነገሩ የተፈፀመው የተማራቂ ተማሪዎች “ጌት
ተጌዘር” አዘጋጅተው ያንን ፖሮግራም ጨርሰው ከምሽቱ ሁለት ሰአት ተኩል አካባቢ ወይም ከዛ ረፈድ ብሎ በቁጥር ወደ
ሀምሳ የሚሆኑ ተማሪዋች ወደ ዩኒቨርስቲው በር አካባቢ ሲደርሱ ሞች እና በወቅቱ ከሟች ጋር አብራ የነበረች ተማሪ ቀድመው
ወደ ጥበቃ በመድረሳቸው ጥበቃው እንዲቆሙ በሚያዛቸው ወቅት ሟች የለም ከግቢው በር ውጭ ልታስቆመን መብቱ የለህም እንደውም መታወቂያህን አሳየኝ በማለት በመባባል ነገሩ እንደተጀመረ እና በወቅቱ ተማሪዎቹ መጠጥ መቀማመሳቸውን፣ ሟችም በስካር መንፈስ ሆኖ ግብግብ መፈጠሩን ጥበቀውም ከሟች ጋር የነበረችውን ምንዋን እንደመቱዋት ባልታወቀ ሁኔታ እራሱዋን መሳትዋን

ለዜጎቹ የማይቆረቆርና ጥብቅና የማይቆም መንግስት (ከአስገደ ገ/ስላሴ ወ/ሚኬኤል)

saudi and ethiopians
በዚሁ ባለንበት ዘመን ያለፉት ስርአቶች ወደኃላ ተመልሰን ስናስታውስና አሁን ያለውን የህ.ወ.ሓ.ት መንግስት ስንመለከት ኢትዮጵያውያንን  ለስድት የሚዳርጓቸዉ ችግሮች ነበሩ።
በዘመነ ዘውዳዊ አገዛዝ ስርአቱ ለዘውዳዊ ንጉሳዊ ቤተሰብ ለተቀማጠለ ኑሮ ቅድሚያ ስለሚሰጥ በወቅቱ ያጋጥሙ  ለነበሩ እንደ ድርቅ ያርሶ አደሩ ሰብል በተባይ ሲጠቃ ህ/ሰቡ ስለሚራብና ስለሚቸገር ዘውዳዊ ስርአቱ ደግሞ መሰረታዊ የፖለቲካ ፣ የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊ ችግሮች መፍትሄ የማይሰጥ ስለነበረ ብዙ ያልተማረ ህዝብ ወደ ስደት እየፈለሰ የመከራ ኑሮ ይገፋ ነበር።

ከሳኡዲ የተመለሱ ኢትዮጵያውያን ሰቆቃ

ሰሞኑን በህገወጥ መንገድ ሳኡዲ አረቢያ ከገቡ ብዙ ሺ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች መካከል ዓለም አቀፍ የስደተኞ ተቋም ከ350 በላይ የሚሆኑትን ወደ አገራቸው መልሷቸዋል፡፡ ጋዜጠኛ አበባየሁ ገበያው በተቋሙ መጠለያ ጣቢያ ያገኘቻቸውን ሦስት ተመላሾች አነጋግራለች፡፡
“ሳኡዲ ወርቅ እየዘነበ ነው ቢሉኝ አልሰማም” አብዱ እንድሪስ
“ኢትዮጵያውያን በእስር ቤት እየተሰቃዩ ናቸው” እንድሪስ መሃመድ
“አበሻ ለእነሱ ርካሽ እቃ ማለት ነው” እንድሪስ የሱፍ

“እኔ ራሴ ስድስት ያበዱ ሴቶችን ይዤ መጥቻለሁ..” ራውዳ ጀማል – ከሳዑዲ ተመላሽ ኢትዮጵያዊት (ቃለ ምልልስ)

በሃገር ቤት እየታተመ የሚወጣው አዲስ አድማስ ጋዜጣ ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሃገራቸው ከተመለሱ ኢትዮጵያውያን ጋር ቃለ ምልልስ አድርጓል። ቃለ ምልልሱ ዘ-ሐበሻ ከዚህ ቀደም ትዘግባቸው የነበሩ የሳዑዲ ሕይወቶችን የሚያጠናክሩ በመሆናቸው ጋዜጠኛ አበባየሁ ገበያው ያደረገችውን ቃለምልልስ ለአንባቢዎቻችን እንደወረደ ይኸው፦
ራውዳ ጀማል ትባላለች፡፡ የሃያ ዓመት ወጣት ናት፡፡ ስለራስዋም ሆነ በሳኡዲ ስላሉ ኢትዮጵያውያን ወቅታዊ ሁኔታ ስታወራ እያለቀሰችና እየተወራጨች ነው፡፡ ለማነጋገር ስቀርባት “ወንድ ከሆናችሁ ጋዜጠኞች ነን፣ የህዝብ አፍ ነን ካላችሁ፤ እዚህ ተቀምጣችሁ፣ “ሁለት ሰው ሞተ” እያላችሁ ከምታቅራሩ ሳኡዲ ሂዱና በየቀኑ ሁለት ሶስት ሰው የሚሞትበትን እልቂት ተመልከቱ፣ “ሰዎቹን ምን እየሰራችሁ ነው?” ብላችሁም ጠይቁልን” አለችኝ። መቅረፀ ድምፄን ሶስት አራት ጊዜ ያስጠፋችኝ ቢሆንም በመጨረሻ ግን ለቃለ ምልልስ ፈቃደኛ ሆነችልኝ፡፡

Saturday, November 23, 2013

The Great Ethiopian Run (Nationalism)

by Tedla Asfaw
In less than 24 hours some 37,000 will participate on the 13th Great Ethiopian Run (GER) in Addis Ababa, Ethiopia. Out of which there are 500 elite runners from Ethiopia and another 500 from overseas. As always this platform will be used for denouncing the ruling regime for its crimes.Great Ethiopian Run 2002
Tomorrow’s run which I rename it as The Great Ethiopian Rise (GER) is “historical” because it is on the weekend where the Ethiopian Diaspora staged in more than 35 cities all over the world protest rallies denouncing Saudi Arabia for killing, raping, beating and jailing Ethiopians close to the number that are now participating on the 13th GER.

ኢትዮጵያ፣ በህዳርና በ… ሁልጊዜ አስታውሳለሁ!! (ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገ/ማርያም)

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገ/ማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
የህዳር ወር በኢትዮጵያውያን በአሰቃቂነቱ ሁልጊዜ ሲታወስ ይኖራል፡፡
እ.ኤ.አ ኖቬምበር 2013 ሳውዲ አረቢያ ውስጥ በቃላት ለመግለጽ በሚዘገንን መልኩ በኢትዮጵያውያን/ት ላይ ሰቆቃ የተፈጸመበት ወር ነው፡፡ ላለፉት ጥቂት ዓመታት በሳውዲ አረቢያ በሚኖሩ፣ በሚሰሩና የፖለቲካ ጥገኝነት ለመጠየቅ ጥረት በማድረግ ላይ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን/ት ላይ ስልታዊ የሆነ ጥቃት ሲሰነዘር ቆይቷል፡፡ እንዲያውም በግል በሚኖሩበት ቤት እምነታቸውን በማራመዳቸው ብቻ ኢትዮጵያውያኑ/ቱ ዜጎች ላይ የወንጀል ድርጊት ተፈጽሞባቸዋል፣ እንዲጋዙም ተደርጓል፡፡

ኢትዮጵያ፣ በህዳርና በ… ሁልጊዜ አስታውሳለሁ!! (ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገ/ማርያም)

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገ/ማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
የህዳር ወር በኢትዮጵያውያን በአሰቃቂነቱ ሁልጊዜ ሲታወስ ይኖራል፡፡
እ.ኤ.አ ኖቬምበር 2013 ሳውዲ አረቢያ ውስጥ በቃላት ለመግለጽ በሚዘገንን መልኩ በኢትዮጵያውያን/ት ላይ ሰቆቃ የተፈጸመበት ወር ነው፡፡ ላለፉት ጥቂት ዓመታት በሳውዲ አረቢያ በሚኖሩ፣ በሚሰሩና የፖለቲካ ጥገኝነት ለመጠየቅ ጥረት በማድረግ ላይ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን/ት ላይ ስልታዊ የሆነ ጥቃት ሲሰነዘር ቆይቷል፡፡ እንዲያውም በግል በሚኖሩበት ቤት እምነታቸውን በማራመዳቸው ብቻ ኢትዮጵያውያኑ/ቱ ዜጎች ላይ የወንጀል ድርጊት ተፈጽሞባቸዋል፣ እንዲጋዙም ተደርጓል፡፡

ኢትዮጵያ፣ በህዳርና በ… ሁልጊዜ አስታውሳለሁ!! (ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገ/ማርያም)

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገ/ማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
የህዳር ወር በኢትዮጵያውያን በአሰቃቂነቱ ሁልጊዜ ሲታወስ ይኖራል፡፡
እ.ኤ.አ ኖቬምበር 2013 ሳውዲ አረቢያ ውስጥ በቃላት ለመግለጽ በሚዘገንን መልኩ በኢትዮጵያውያን/ት ላይ ሰቆቃ የተፈጸመበት ወር ነው፡፡ ላለፉት ጥቂት ዓመታት በሳውዲ አረቢያ በሚኖሩ፣ በሚሰሩና የፖለቲካ ጥገኝነት ለመጠየቅ ጥረት በማድረግ ላይ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን/ት ላይ ስልታዊ የሆነ ጥቃት ሲሰነዘር ቆይቷል፡፡ እንዲያውም በግል በሚኖሩበት ቤት እምነታቸውን በማራመዳቸው ብቻ ኢትዮጵያውያኑ/ቱ ዜጎች ላይ የወንጀል ድርጊት ተፈጽሞባቸዋል፣ እንዲጋዙም ተደርጓል፡፡

ኢትዮጵያ፣ በህዳርና በ… ሁልጊዜ አስታውሳለሁ!! (ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገ/ማርያም)

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገ/ማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
የህዳር ወር በኢትዮጵያውያን በአሰቃቂነቱ ሁልጊዜ ሲታወስ ይኖራል፡፡
እ.ኤ.አ ኖቬምበር 2013 ሳውዲ አረቢያ ውስጥ በቃላት ለመግለጽ በሚዘገንን መልኩ በኢትዮጵያውያን/ት ላይ ሰቆቃ የተፈጸመበት ወር ነው፡፡ ላለፉት ጥቂት ዓመታት በሳውዲ አረቢያ በሚኖሩ፣ በሚሰሩና የፖለቲካ ጥገኝነት ለመጠየቅ ጥረት በማድረግ ላይ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን/ት ላይ ስልታዊ የሆነ ጥቃት ሲሰነዘር ቆይቷል፡፡ እንዲያውም በግል በሚኖሩበት ቤት እምነታቸውን በማራመዳቸው ብቻ ኢትዮጵያውያኑ/ቱ ዜጎች ላይ የወንጀል ድርጊት ተፈጽሞባቸዋል፣ እንዲጋዙም ተደርጓል፡፡

ኢትዮጵያ፣ በህዳርና በ… ሁልጊዜ አስታውሳለሁ!! (ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገ/ማርያም)

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገ/ማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
የህዳር ወር በኢትዮጵያውያን በአሰቃቂነቱ ሁልጊዜ ሲታወስ ይኖራል፡፡
እ.ኤ.አ ኖቬምበር 2013 ሳውዲ አረቢያ ውስጥ በቃላት ለመግለጽ በሚዘገንን መልኩ በኢትዮጵያውያን/ት ላይ ሰቆቃ የተፈጸመበት ወር ነው፡፡ ላለፉት ጥቂት ዓመታት በሳውዲ አረቢያ በሚኖሩ፣ በሚሰሩና የፖለቲካ ጥገኝነት ለመጠየቅ ጥረት በማድረግ ላይ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን/ት ላይ ስልታዊ የሆነ ጥቃት ሲሰነዘር ቆይቷል፡፡ እንዲያውም በግል በሚኖሩበት ቤት እምነታቸውን በማራመዳቸው ብቻ ኢትዮጵያውያኑ/ቱ ዜጎች ላይ የወንጀል ድርጊት ተፈጽሞባቸዋል፣ እንዲጋዙም ተደርጓል፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ፣ የዜጎችን ሰቆቃ እና በደል ችላ ማለት ከግፈኞች ጋር እንደመተባበበር ይቆጠራል!!

ሰማያዊ ፓርቲ በሳውዲ አረቢያ የሚገኙ ዜጎቻችን ላይ የሳውዲ መንግስት እያደረሰ ያለውን እስራት፣ ስቃይ እና ግድያ በመቃወም እና ህይወታቸው ላለፈ፣ ለተደበደቡ እንዲሁም የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ህዝቡ ሃዘኑን እንዲገልጽ በመጪው እሁድ በሚደረገው ታላቁ ሩጫ ላይ የሚሮጡ ተሳታፊዎች ጥቁር ሪቫን አድርገው እንዲሮጡ ጥሪ ማስተላለፉ የሚታወቅ ነው፡፡
ይሁን እንጂ የታላቁ ሩጫ አስተባባሪዎች ይህንን ጥሪ እንደሚቃወሙት እና በፕሮግራሙም ላይ ጥቁር ሪቫን ያሰረ ተሳታፊን እንደተሳታፊ እንደማይቆጥሩ መናገራቸው ፓርቲያችንን እጅግ አሳዝኖታል፡፡

ወደ ተግባር

ከአንተነህ መርዕድ እምሩ
ኖቬምበር 20 ቀን 2013
ኢትዮጵያውያን እንደ አሁኑ ተገፍተን ገደል ጠርዝ የቆምንበት ጊዜ ያለ አይመስለኝም። እስከ አሁን ትንንሽ መሸሻ ስለነበረን ፍርሃታችንን እንኳን ከሰው ከራሳችንም ደብቀን ስናፈገፍግ ኖረናል። ፈሪነታችንን ባባቶቻችን ጀግንነት፣ ውርደታችንን ባባቶቻችን ኩራት እያለበስነው መጓዝ የማያዛልቅ ለመሆኑ ከሰሞኑ የበለጠ ምስክር ምን አለና።
ያጋጠመን ብሄራዊ ውርደት ከፊሎቻችንን ከእንቅልፋችን ገና ሲያባንነን ብዙዎቻችንን አጥንታችን ድረስ ገብቶ ተሰምቶናል። አባቶቻችን “ሞት ሲዘገይ የቀረ ይመስላል” እንዳሉት ባንዳንዶች ላይ የደረሰው ውድቀት እኛን ስላልነካን የሚቀር መስሎን ነበር። በገዥዎቻችን በየለቱ በምትወረወረዋ ከፋፋይ የቤት ስራ ተጠምደን ግዙፉ ህልውናችን አዳጋ ላይ መሆኑን እንኳ ማየት ተስኖን ነበር።

“የኢትዮጵያ ህዝብ ለውጥ ፈልጓል፤ ግን ለውጡን የሚሸከምለት ፓርቲ ይፈልጋል”

መላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) በቅርቡ
ከአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ጋር ውህደት፣ ከሌሎች 10 ፓርቲዎች ጋር ቅንጅት ለመፍጠር እየተንቀሳቀሰ ሲሆን ፓርቲው ከረጅም አመታት በኋላ
የፕሬዚዳንት ለውጥም አድርጓል፡፡
ከአዲሱ ፕሬዚዳንት አቶ አበባው መሃሪ ጋር ፓርቲው ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር እየፈጠረ ስላለው ውህደት እና ቅንጅት እንዲሁም በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ የአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ አለማየሁ አንበሴ፤ በፓርቲው ጽ/ቤት ተገኝቶ አነጋግሯቸዋል፡፡
ከ“መድረክ” ጋር ያለው ጥያቄ “አንድነት” ሊፈታው የሚገባው ነው
ፓርቲያችን ግራ የተጋባ አይደለም
መኢአድ በሀገሪቱ ካሉ ፓርቲዎች ጠንካራው ነው
ህዝቡ እውነተኛውንና ውሸታሙን መለየት አለበት

ኦባንግ – ከዓለምአቀፍ ተቋማት ጋር እየሠራሁ ነው አሉ. የሳዑዲ ልዑል አንጋቾቻቸውን አወደሱ

በሳዑዲ አረቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰውንና እየደረሰ ያለውን ፈር የለቀቀ አስነዋሪ ግፍ ዓለምአቀፍ ይዘት እንዲኖረው ለማድረግ ከሰብዓዊ መብት ተሟጋች እና ሌሎች ዓለምአቀፋዊ ድርጅቶች ጋር እየሠሩ መሆናቸውን አቶ ኦባንግ ሜቶ በተለይ ለጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ ተናገሩ፡፡ የሳዑዲ ልዑል ሰብዓዊነት የረገፈበትንና በግፍ የተሞላ የወሮበላ ተግባር የሚፈጸምበትን አሰቃቂ ተግባር የሚከናውኑትን አንጋቾች አሞካሹ፡፡

ሰበር ዜና፡- በአሜሪካ፣ ሜሪላንድ ክፍለ ግዛት፣ በዛሬው እለት ኢትዮጵያዊ አሜሪካዊው ቢኒያም አሰፋ እና ባለቤቱ፣ የ3 ወር ህፃን ልጃቸውም በጥይት መሞታቸው ተዘገበ፤

ሰበር ዜና፡- በአሜሪካ፣ ሜሪላንድ ክፍለ ግዛት፣ በዛሬው እለት ኢትዮጵያዊ አሜሪካዊው ቢኒያም አሰፋ እና ባለቤቱ፣ የ3 ወር ህፃን ልጃቸውም በጥይት መሞታቸው ተዘገበ፤ ባልና ሚስቱ ራሳቸውን ያጥፉ ወይም ይገዳደሉ አልታወቀም። ይሄ ሁሉ ሲካሄድ የ5 አመት ልጃቸው ወደ ጎረቤት አምልጣ ተርፋለች። ሙሉ ዜናው እነሆ!

የሰማያዊ ፓርቲ የምክር ቤት አባልና በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የቴክኖሎጂ ፋኩልቲ መጨረሻ አመት ተማሪ ዮናስ ከድር በደህንነቶች ድብደባ ደረሰበት

“ፓርቲዉንና በዩኒቨርስቲ ያለዉን እንቅሰቅሴ ሰልልን”
8፡00 ሰዓት ላይ በላንቻ ፖሊስ ጣቢያ ረዳት ኢንስፔክትር ሀይለማሪያም ታረቀኝ በአርቡ ሰልፍ ላይ ለምርመራ ትፈለገላህ ተብሎ ይጠራል፡፡ በፖሊስ ጣቢያዉ ሲደርስም ወደ ቢሯቸው እንዲገባ ከተደረገ በኋላ ሁለት ደህንነቶች ተከትለዉ ሲገቡ ረዳት ኢንስፔክተሩ ቢሯቸዉን ትተዉ ይወጣሉ፡፡

የወያኔ የግድያ እቅድ መክሸፍ ለሁመራና ወለወቃይት ጸገዴ ወጣቶች ችግር ፈጠረ

ፋሽስት ወያኔ ‘ወያኔ ኦ ሚሊኒየም’ ብሎ ሰይሞት የነበረውና በአቶ አንዳርጋቸው ፅጌና የግንቦት 7 ሕዝባዊ ሃይል አመራሮች ላይ የተጠነሰሰ የግድያ እቅድ ከከሸፈ ወዲህ ህዝባዊ ሃይሉ ይገኝበታል ተብለው በተጠረጠሩት አጎራባች ወረዳዎች በሚገኙ ወጣቶች ላይ የተጠናከረ አሰሳ በማድረግ ወጣቶችን በማሰር ላይ መሆኑን ከቦታው የደረሰን መረጃ ይጠቁማል። ፋሽስት ወያኔ ልክ እንደቆሰለ አንበሳ እዚህም እዚያም በፍርሃት በመንደርደር በሁመራና በወልቃይት ጸገዴ የሚገኙ ወጣቶችን እያሰረ ይገኛል።

Friday, November 22, 2013

የህወሓት እኩይ ተግባር እያደረ ይገለጣል!! (ኢንጂኔር አብደልውሀብ ቡሽራ – መቀሌ)

 ከሁለት ሳምንታት በፊት ወደ ሽሬ ለመሄድ ወደ መቀሌ አውቶብስ ተራ ሄድኩና በሰላም ባስ አውቶብስ ተሳፍሬ ጉዞየን ጀመርኩ:: እየተጓዝን እያለን በተቀመጥኩበት ወንበር አጠገብ ሁለት ሰዎች ነበሩ:: ሰዎቹ ከዛ በፊት አይቻቸው አላውቅም:: ሁለቱም አካል ጉዳተኞች ናቸው:: በመንገዳችን እየተጓዝን እያለን ሁለቱ ሰዎች የድሮ ትዝታቸው እያነሱ እያወሩ ነበሩና እኔም የነሱ ወሬ አዳምጥ ነበርኩ:: እንደዛ ቆየሁና ወሬያቸው ታሪካዊና የድሮ ትዝታቸው ስለጣመኝ በመሃላቸው ገባሁና ተዋወቅኩዋቸው:: እነዛ ሰዎች ሁለቱም የቀድሞ የህወሓት ታጋዮች የነበሩና በትግሉ ጊዜ አካላቸው የተጎዱ መሆናቸው አወቅኩ::

የኢትዮ-ኤርትራ ችግር መፍትሄ፣ ድንበር ማስመር ሳይሆን ድንበር ማፍረስ ነው

Eritrean–Ethiopian War Map 1998.png

 
ኤርትራ ራሷን እያወደመች ነው የኢትዮጵያ ትምህርት ችግሮች ቋንቋና ያለ እቅደ መስፋፋት ናቸውፕሮፌሰር ተከስተ ነጋሽ በስዊድን አገር በኡፕስላ ዩኒቨርሲቲ የዘመናዊ ታሪክ ፕሮፌሰር ናቸው፡፡ ፕሮፌሰሩ በኢትዮጵያ ትምህርት ላይ ከፍተኛ ምርምሮችን ያደረጉ፣ በመስኩም የታወቁ ምሁር ሲሆኑ ከከዓምናው ጀምሮ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ ትምህርት ክፍል ተጋባዥ ፕሮፌሰር ሆነው በማገልገል ላይ ይገኛሉ፡፡ እ.ኤ.አ በ1947 በአስመራ ከተማ ተወልደው የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአስመራ፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በጅማ ተከታትለዋል፡፡

ኦባንግ – ከዓለምአቀፍ ተቋማት ጋር እየሠራሁ ነው አሉ. የሳዑዲ ልዑል አንጋቾቻቸውን አወደሱ

በሳዑዲ አረቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰውንና እየደረሰ ያለውን ፈር የለቀቀ አስነዋሪ ግፍ ዓለምአቀፍ ይዘት እንዲኖረው ለማድረግ ከሰብዓዊ መብት ተሟጋች እና ሌሎች ዓለምአቀፋዊ ድርጅቶች ጋር እየሠሩ መሆናቸውን አቶ ኦባንግ ሜቶ በተለይ ለጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ ተናገሩ፡፡ የሳዑዲ ልዑል ሰብዓዊነት የረገፈበትንና በግፍ የተሞላ የወሮበላ ተግባር የሚፈጸምበትን አሰቃቂ ተግባር የሚከናውኑትን አንጋቾች አሞካሹ፡፡

Thursday, November 21, 2013

የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር ኃይል በሰሜን አሜሪካ፣ ነፃነት ያለ ደም …. ክብርስ ያለ መስዋዕትነት እንዴት ሊገኝ ይችላል?

ነፃነት ያለ ደም …. ክብርስ ያለ መስዋዕትነት እንዴት ሊገኝ ይችላል?

የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር ኃይል በሰሜን አሜሪካ
በሳውዲት አረቢያ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ላይ እየተካሄደ ያለውን አሰቃቂ ግድያና ሰቆቃ አጥብቆ ያወግዛል !
አድዋ ላይ የፈሰሰው ደም ፣ በማይጨው የተከሰከሰው አጥንት ፣ በመተማ ግንባር ላይ የተቀላው አንገት ፣ በዶጋሊ በደም የተፃፈው ጀግንነት …… ለግል ታሪክ ማዳመቂያ ሳይሆን እኛ ኢትዮጵያኖች በገዛ አገራችን በባርነት ቀንበር ስር እንዳንማቅቅና በነፃነት ተከብረንና ኰርተን እንድንኖር አድርጐናል ።

ወደ ተግባር (ከአንተነህ መርዕድ እምሩ)

ከአንተነህ መርዕድ እምሩ
ኢትዮጵያውያን እንደ አሁኑ ተገፍተን ገደል ጠርዝ የቆምንበት ጊዜ ያለ አይመስለኝም። እስከ አሁን ትንንሽ መሸሻ ስለነበረን ፍርሃታችንን እንኳን ከሰው ከራሳችንም ደብቀን ስናፈገፍግ ኖረናል። ፈሪነታችንን ባባቶቻችን ጀግንነት፣ ውርደታችንን ባባቶቻችን ኩራት እያለበስነው መጓዝ የማያዛልቅ ለመሆኑ ከሰሞኑ የበለጠ ምስክር ምን አለና።
ያጋጠመን ብሄራዊ ውርደት ከፊሎቻችንን ከእንቅልፋችን ገና ሲያባንነን ብዙዎቻችንን አጥንታችን ድረስ ገብቶ ተሰምቶናል። አባቶቻችን “ሞት ሲዘገይ የቀረ ይመስላል” እንዳሉት ባንዳንዶች ላይ የደረሰው ውድቀት እኛን ስላልነካን የሚቀር መስሎን ነበር። በገዥዎቻችን በየለቱ በምትወረወረዋ ከፋፋይ የቤት ስራ ተጠምደን ግዙፉ ህልውናችን አዳጋ ላይ መሆኑን እንኳ ማየት ተስኖን ነበር።

በህገወጥነት ሽፋን ለወገኖቻችን መጭፍጨፍ ግባር ቀደም ተጠያቂው በሪያድ የኢትዮጵያ ኤንባሲ እና አለቆቻቸው ናቸው !

በሪያድ የኢትዮጵያ ኤንባሲ ዛሬ በተለምዶ መንፉሃ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በተቀሰቀሰ ሁከት ቁጥራቸው በውል ለማይታወቁ ወገኖቻችን አስቃቂ ግድያ እና በ10 ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በሳውዲ አረቢያ እየደረሰባቸው ላለው ስቃይ እና መከራ ግንባር ቀደም ተጠያቂ የሚያደርገው የተዝረከረከ አሰራሩ ሲቃኝ። ይህ ጽሁፍ ሜይ 23 2013 የሳውዲ አረቢያ መንግስት የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው የውጭ፡ሃገር ዜጎች የመኖሪያ ፈቃዶቻቸውን እንዲያስተካክሉ የ 7 ወር የምህረት አዎጅ በሰጠበት ወቅት በሪያድ የኢትዮጵያ ኤንባሲ እንደ ዜጋ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ከህገወጥነት ለመታደግ የፓስፖርት እድሳትን ጨምሮ ዜጎቻችን ህጋዊ ለመሆን የሚያስችሎቸውን መሰል ተዛማጅ መረጃዎች በወቅቱ አንባሳድር መሃመድ ሃሰን እና ዲፕሎማቱ ሲደናበሩ የነበረበት የተዝረከረከ አሰራር….. ……

ቪኦኤ የሣዑዲን ተመላሾች አዲስ አበባ ላይ አነጋገረ

ኢትዮጵያዊያን በየአቅጣጫው እየተንቀሣቀሱ ነው፡፡
ከራሣቸው ይልቅ እስካሁን ወደ ሀገራቸው ያልገቡት ዜጎች ጉዳይ እንደሚያሳስባቸው ከሳዑዲ አረቢያ ወደ አዲስ አበባ እየገቡ ያሉ ኢትዮጵያዊያን አስታወቁ።
እዚያ ያለው ሁኔታ አሣዛኝ መሆኑን የገለፁት ተመላሾች ሁላችንም ወደ ሀገራችን እንድናስብ ያደረገ ነው ብለዋል።
ዘጋቢያችን እስክንድር ፍሬው ቦሌ አይሮፕላን ጣቢያ ተገኝቶ አንዳንዶቹን አነጋግሯል፡፡

Open Letter to Ethiopian Foreign Minister

Open Letter to Ethiopian Foreign Minister

Center for the Rights of Ethiopian Women
crew_logo
Center for the Rights of Ethiopian Women (CREW) is concerned about the recent abuse of Ethiopian migrant workers in Saudi Arabia, especially the reported torture, abuse and rape of Ethiopian women. CREW is a non-government, non-profit, non-partisan, human rights and peace organization established to promote the social, economic and legal rights of Ethiopian women in Ethiopia and worldwide. One of the objectives of the organization is to assist and represent abused Ethiopian women living and working abroad.

በሳዑዲ አረቢያ የደረሰው ግፍና መሠረታዊ ችግራችን (ከአንዱ ዓለም ተፈራ፤ የእስከመቼ አዘጋጅ)

ethio saudi 11
ዘግናኙ የስደተኛ ኢትዮጵያዊያን ግፍ በሳዑዲ አረቢያዊያን እጅ፤ ከፊታችን ተደቅኗል። ሁላችን በያለንበት፤ “ለምን? ምን አደረግን? መጨረሻው ምንድን ነው? መቼ ነው ይኼ ሁሉ የሚያበቃው?” እያልን እርስ በርሳችን እየተጠያየቅን ነው። እኛ ወደ የምንፈልገው መንገድ ካልገባን፤ ሌላ ሊይስገባን የሚችል ኃይል የትም የለም። በሳዑዲ አረቢያ የተደረገውን ኢሰብዓዊ ድርጊት፤ ሁላችን ኢትዮጵያዊያን በግል በራሷና በራሱ እንደተደረገ በደል አድርገን ወሰደነዋል። ተገቢም ነው።

የኢትዮጵያን መንግስት ለፍርድ ለማቅረብ ከተነሱት ስዊድናዊ ጠበቃ ጋር ውይይት ተደረገ

stellan-yarde
ቅዳሜ ኖቬምበር 2 ቀን 2013 ዓ.ም የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ መድረክ በስዊድን የወያኔን መንግስት በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ለማቅረብ የተጀመረውን ክስ መነሻ በማድረግ የክሱን ሂደት ከሚመሩት ከስዊድናዊው ጠበቃ ከስቴላ ያርዴና ከሌሎች እንግዶች ጋር በርካታ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት ወይይት አደረገ።
million
ም/ኢኒስፔክተር ሚሊዮን ብሩ
ውይይቱ ከቀኑ 14፡00 ሰዓት የተጀመረ ሲሆን ውይይቱን የከፈቱት የመድረኩ ሊቀ መንበር ም/ኢኒስፔክተር ሚሊዮን ብሩ ናቸው። ኢኒስፔክተር ሚሊዮን በንግግራቸው መክፈቻ ጥሪ የተደረገላቸውን እንግዶችና ተሰብሳቢውን ህዝብ አመስግነው መድረኩ የተቋቋመበት ዓላማ በሀገር ውስጥና በውጪ የሚደረገውን የነጻነት ትግል የተደራጀ መልክ ይዞ የሚጓዝበት መንገድ ለማመቻቸትና በየጊዜውም ይህንን መሰል ውይይት በማድረግ ትግሉን ለመርዳት መሆኑን ገልጸው የዛሬውንም ስብሰባ የዚህ መነሻ እንደሆነ አስታውቀዋል።

ማስታወሻ በቸግራችን ለደረሳችሁልን ኢትዮጵያውያን በሙሉ

በሣዑዲ ዓረቢያ የምንኖር ወገኖቻችሁ
በሳዑዲ ዓረቢያ ከግማሽ ሚለዮን በላይ የምንቆጠር ኢትዮጵያውያን በተለያዩ የስራ መስኮች ተሰማርተን እንገኛለን፡፡ ከሃገር ያስወጣንን ድህነት ለማሸነፍ ብዙውን ግዜ ከአቅም በላይ የሆኑ የጉልበት ስራዎችን እና ስነልቦና የሚጎዱ በጣም ዝቅተኛ ደረጃ በሆኑ የስራ መስኮች ተሰማርተን እስከአሁኑ ግዜ ደርሰናል፡፡ በሺዎች የምንቆጠር ደግሞ ባለንበት ሃገር ቤተሰብ መስርተን እና ሃብት ንብረት አፍርተንና ለአመታት በአንፃራዊ ሰላም ስንኖር ቆይተናል፡፡

የስዊድን የጦር ፍርድ-ቤት አቃቢ-ህግ በኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ላይ ምርመራ እንዲካሄድ ወሰነ፡፡

ኢሳት ዜና :-የጦር ፍርድ ቤቱ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው በቅርቡ በኦጋዴን የተፈጸመውን የሰብአዊ መብት ጥሰት በተመለከተ፣ የክልሉ የወጣቶች ሊቀመንበርና የፕሬዚዳንቱ የግል ዌብሳት ማኔጀር እና አማካሪ የነበረው ወጣት አብዱላሂ ሁሴን በኦጋዴን የጦር ወንጀልና የሰብአዊ መብቶች ጥሰት መፈጸሙን የሚያሳይ ማስረጃ ለፍርድ ቤቱ አቃቢ ህግ ማቅረቡን ተከትሎ ነው።

በ1997ቱ የኢትዮጵያ ምርጫ ታዛቢ የነበሩት አና ጐሜዝ አዲስ አበባ ሊመጡ ነው

በ1997 ዓ.ም. በኢትዮጵያ በተካሄደው አገር አቀፍ ምርጫና ምርጫውን ተከትሎ ተከስቶ በነበረው የፖለቲካ ውዝግብ አካል የነበሩት የአውሮፓ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ አና ጐሜዝ ወደ ኢትዮጵያ ሊመጡ ነው፡፡
በኢትዮጵያ በ1997 ዓ.ም. ተካሂዶ የነበረውን ምርጫ በአውሮፓ ኅብረት ተወክለው ምርጫውን በዋና ታዛቢነት የመሩትና የአውሮፓ ኅብረት ፓርላማ አባል የሆኑት አና ጐሜዝ፣ ምርጫውን አስመልክቶ ባወጡት ሪፖርት ኢሕአዴግ ከሚመራው መንግሥት ጋር ጥልቅ የሆነ ግጭት ውስጥ ገብተው ነበር፡፡

Wednesday, November 20, 2013

ዋና ጠላታችን የትግሬ ነፃ አውጪ ወያኔ ነው!

’ ወዴት ነው የምንሄደው ለማን ነው የምንነግረው መንግስት ረስቶናል ኤንባሲው አላቃችሁም …ብሏል ነገ እኔ እህትህን ወይ ተደፍሬ ወይ ሞቼ ወይ አብጄ ነው የምታገኘኝ’’ አንዲት በሳውዲ ተደብቃ ያለች እህታችን ያስተላለፈችው መልዕክት አቦይ ስብሃት ከጉልምስና እስክ ሽምግልና የታገልክለት ኢትዮጽያና ኢትዮጽያዊነት የማዋረድ አላማህ ከሃገር አልፎ በአለም ሁሉ ሆኖዓልና እንኳን ደስ ያለህ አዜብ መስፍን የባልሽ እረፍት የለሹ እስከ መቃብር ያለመታከት የቆመለት አላማ ትቶት ያለፈው ራዕይ የአገዛዝ ውጤቱ ይህው ኢትዮጽያውያንን አንገት የማስደፋት ተሳክቶ እዚህ በመድረሱ የሃዘንሽ መጽናኛ ከሆነልኝ እንኳን ደስ አለሽ፤

በግብታዊነት የተደራጀ የልማት ሰራዊት ውጤቱ ጥፋት ነው -ከአስገደ ገ/ስላሴ ወ/ሚካኤል መቐለ

ህ.ወ.ሃ.ት ትግራይን በመልካም አስተዳደር ፣ በፍትህ፣ በነፃነት፣ በልማት፣ በግብር አሰባሰብ ፣ በባለሃብቶች ፍሰት የኢንቨስትመንት ግበአት፣ በከተማ ልማት በጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት እድገት በእርሻ እድገት በአርሶ አደሩ ሞዴልነት በኢንዱስትሪ በጤና ፣ በትምህርት፣ ጥራት፣ በማህበራት ኣደራጃጀት በሁሉም አይነት ዲሞክራሲ መብት አጠባበቅ ሞዴል፤ ለሁሉም ክልሎች እንደሰርቶ ማሳያ ተደርጎ ነዉ የሚቀርበው የህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች ሲደሰኩሩበት የቆዩና ያሉት ። ሃቁ ግን በሚከተሉት ፅሁፍ አንቀፅ በአንቀፅ ላስቀምጣቸዉ እሞክራለሁ።

“አንድ አንዳርጋቸውን መግደል የነፃነቱን ትግል ማስቆም አይቻልም” – ግንቦት 7

ህወሃቶች የንጹሃን ዜጎችን ደም በከንቱ ሲያፈሱ የኖሩ ነብሰ ገዳዮች እንደሆኑ የሚታወቅ ነው። አሁንም ክብሬንና ነፃነቴን የሚሉ ዜጎችን ይዘው ደብዛቸውን ለማጥፋት ብዙ ዓይንና ብዙ ጆሮዎችን በየቦታው አቁመናል እያሉ ያቅራራሉ። ይሄን ሁሉ ዓይንና ጆሮ ይዘንስ የሚያሸንፈን ማን ነው ? ሲሉም ይደመጣሉ። እነርሱ እንደሚሉት ዓይኖቻቸው ማየት፤ጆሮዎቻቸውም መስማት የሚችሉ አይደሉም።

ማስታወሻ በቸግራችን ለደረሳችሁልን ኢትዮጵያውያን በሙሉ

በሣዑዲ ዓረቢያ የምንኖር ወገኖቻችሁ
በሳዑዲ ዓረቢያ ከግማሽ ሚለዮን በላይ የምንቆጠር ኢትዮጵያውያን በተለያዩ የስራ መስኮች ተሰማርተን እንገኛለን፡፡ ከሃገር ያስወጣንን ድህነት ለማሸነፍ ብዙውን ግዜ ከአቅም በላይ የሆኑ የጉልበት ስራዎችን እና ስነልቦና የሚጎዱ በጣም ዝቅተኛ ደረጃ በሆኑ የስራ መስኮች ተሰማርተን እስከአሁኑ ግዜ ደርሰናል፡፡ በሺዎች የምንቆጠር ደግሞ ባለንበት ሃገር ቤተሰብ መስርተን እና ሃብት ንብረት አፍርተንና ለአመታት በአንፃራዊ ሰላም ስንኖር ቆይተናል፡፡ የሃገሪቱ መንግስት ህገ ወጦች ናችሁ በሚል ሰብአዊ መብትን በጣሰ መንገድ በዜጎቻችን ላይ የሚፈፅመው አሳዛኝ ድርጊት እስከተፈጠረበት ግዜ ድረስም በሃገራችን ያጣነውን የስራ ዕድል ሳዑዲ ዓረቢያ ላይ ተፈጥሮልን በሃበሻነታችን ተፈልገን የምንሰራ እንጂ ሃበሻ በመሆናችን እንድንሸማቀቅ የተደረግንበት አጋጣሚ የጎላ አልነበረም፡፡

በዶ/ር መረራ ጉዲና መፅሐፍ ላይ ሊደረግ የነበረው ውይይት ተሰረዘ

በዘሪሁን ሙሉጌታ

በቅርቡ ለሕትመት የበቃው “የኢትዮጵያ ፖለቲካ ምስቅልቅል ጉዞ እና የህይወቴ ትዝታዎች” በሚል ርዕስ ለሕትመት በበቃው መፅሐፍ ባለፈው አርብ ሕዳር 6 ቀን 2006 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ራስ መኮንን አዳራሽ ስድስት ኪሎ ካምፓስ ሊካሄድ የነበረው ውይይት ተሰዘረ።
ውይይቱ ተዘጋጅቶ የነበረው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና የጀርመን ተቋም የሆነው የፍሬዲሪክ ኤቨርት ፋውንዴሽን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ ዲፓርትመንት ጋር በመተባበር ነው። ተቋሙ ከዚህ በፊት የንባብ ባህልን በማበረታታት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በተለያዩ የሀገሪቱ ምሁራን በታተሙ መፅሐፎች ላይ ሕዝባዊና ምሁራዊ ውይይት ሲያካሂድ ቆይቷል።