Monday, April 28, 2014

ሠማያዊ ፓርቲ የነፃነት ትግልና የሃበሻ ጀብዱ

ዳኛቸው ቢያድግልኝ
በቅርቡ የሴቶችን ቀን አስመልክቶ በተደረገ የሩጫ ዝግጅት ወቅት የሚኒሊክና የጣይቱ ልጆችነ ነን ያሉ የሰማያዊ ፓርቲ ወጣት ሴቶች “አትለያዩን! አትከፋፍሉን! ነፃነት እንሻለን! ለድሃው ይታሰብለት! ኑሮ ከበደን! ውሃ ጠማን! መብራት ናፈቀን!” በማለት በጣም ሰብዓዊና እናታዊ ጥሪ ጮክ ብለው አሰምተው ነበር። ይህም መልካም ድርጊታቸው ለፍትህና ለአንድነት የሚደረግ ህዝባዊ ጥሪ በሚያስበርግጋቸው የወያኔ ባለስልጣናት ሁከት ፈጠራ ተብሎ ተወነጀሉ። ፕሮፌሰር አልማርያም በተቆጣው ብዕራቸው
… ያገሬ ወይዛዝርቶች በምህረት አልባ ጨካኞች ሲንገላቱና ሲወገሩ ከዳር ቆሜ ማየትን ህሊናዬ ፈጽሞ አይፈቅድልኝም። ይልቁንም የእንግልታቸው ምክንያት ሰብዓዊ በሆነው መብታቸው ድምፃቸውን ስላሰሙ በመሆኑ የነሱና የመሰሎቻቸውን ጥሪ በዚህም ሳቢያ የሚደርስባቸውን አበሳ ሁሉ ለአለም አሳውቅ ዘንድ ድምጼን ከፍ አድርጌ እጮሃለሁ… ብለው ነበር።

Sunday, April 27, 2014

ከኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ(ኢጋመ) የተሰጠ መግለጫ፣ የጋዜጠኞቹና የአክቲቪስቶቹ እስር አሳሳቢ ነው

ትላንት ሚያዝያ 17 2006 አመሻሽ ላይ ዞን 9 በተሰኘ ድረ ገጽ (ብሎግ) ላይ በሳል ፖለቲካዊና ማህበራዊ ትችቶችን በማቅረብ ከሚታወቁት ፀኀፍት መሀከል 7 ቱ (ማህሌት ፋንታሁን በፍቃዱ ሀይሉ Ethiopians journalists forumናትናኤል ፈለቀ ዘላለም ክብረት አጥናፍ ብርሀነ አቤል ዋበላ ኤዶም ካሳዬ) እና የአዲስ ነገር ባልደረባ የነበረው ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች በቁጥጥር ስር መዋላቸዉ ይታወቃል፡፡ ግለሰቦቹ በተለያየ ቦታ በየስራ ገበታቸዉ ላይ እያሉ ሁሉም በተመሳሳይ ሰዓት በፀጥታ ሀይሎች ተይዘዉ ማዕከላዊ ምርመራ ማዕከል ታስረዉ የሚገኙ ሲሆን፤ የተለያዩ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት እስሩ በደንብ የታሰበበት ነበር፡፡

Ethiopia detains bloggers and journalist

Security forces arrest six bloggers and a journalist in latest crackdown on opposition voices.
The Ethiopian government has arrested six independent bloggers and a journalist in what human rights group Amnesty International has called a "suffocating grip on freedom of expression".
Six members of independent blogger and activist group ‘Zone 9’ and a prominent Ethiopian journalist were arrested on Friday in the capital Addis Ababa.
These arrests appear to be yet another alarming round up of opposition or independent voices
Claire Beston, Amnesty International

Wednesday, April 23, 2014

ምክር ለሰማያዊ ፓርቲ

በክፍያለው ገብረመድኅን
የተነጠቁ መብቶቻችን እናስመልስ” በሚል መሪ ዓላማ ስማያዊ ፓርቲ ያደረገው ጥሪ የተከበረ ግብ ቢሆንም፤ ውጥንቅጥና ውስብስብ በሆነው፡ ሕወሃት በፈንጂ ባጠረው የተግል ጎዳና የሰማያዊ ፓርቲ ብቸኛ ጉዞ መምረጡን በክፍተኛ ኃዘንና ቅሬታ እንድመለከተው ተገድጃለሁ።demonstration in Addis Ababa

ጥያቄው ሰማያዊ ፓርቲን የመቀበልና አለመቀበል ጉዳይ መደረግ የለበትም። መግለጽም ካስፈለገ፡ ለሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አድናቆት አለኝ። ይህንንም በተደጋጋሚ በዚህ ድህረ ገጽ ላይ አስረግጬ መስክሪያለሁ።

የሚታደስ ቃል ኪዳን (ጸጋዬ ገብረ መድኅን አርአያ)

ጸጋዬ ገብረ መድኅን አርአያ
“ መኳንንቶቼ፣ ልጆቼና ሕዝቦቼ ሆይ! እኔ ስለ እናቴ ኢትዮጵያ ሕይወቴን ልሰዋላት ሙሉ ፈቃድ አለኝ። በእኔ ልብ ያለው አሳብ በትክክል በእናንተም ልብ በመታሰቡ በጣም ደስ ብሎኛል።
“ እንግዲህ አሳባችን አንድ ከሆነ ጠንክሩ እንጂ አትፍሩ። ለዘመቻውም አዋጅ አናግራለሁና አይዞአችሁ አትፍሩ!
“ አገሬ ሆይ ስሚ! መኳንንቶቼ፣ ወታደሮቼ፣ ሕዝቦቼ ስሙ…..ወደፊት ገስግሱ እንጂ ወደኋላ አትቅሩ!
“ የኢትዮጵያ ልጅ ሆይ! ልብ አድርገህ ተመልከት ኢትዮጵያ የተባለችው አንደኛ እናትህ ናት! ሁለተኛ ዘውድህ ናት! ሦስተኛ ሚስትህ ናት! አራተኛ ልጅህ ናት! አምስተኛ መቃብርህ ናት! እንግዲህ የእናት ፍቅር፣ የዘውድ ክብር፣ የሚስት ደግነት፣ የልጅ ደስታ፣ የመቃብር ከባቲነት እንደዚህ መሆኑን አውቀኸው ተነሳ!”

ከሰማያዊ ፓርቲ የሰላማዊ ሰልፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ለንግዱ ማህበረሰብ የተላለፈ ጥሪ!

በንግዱ ዓለም ለተሰማራችሁት ኢትዮጵያውያን በሙሉ፤
በአሁኑ ወቅት ስልጣን ላይ ያለው ፓርቲ ሁሉንም የኢኮኖሚ መስክ ጠቅልሎ በመያዙ በአገሪቱ ኢኮኖሚ የሚገባችሁን አስተዋጽኦ እያደረጋችሁ እንዳልሆነ እንረዳለን፡፡ ለይስሙላ ብቻ ነጻ ገበያን ‹‹ፈቅጃለሁ!›› የሚለው ገዥው ፓርቲ ኢኮኖሚውን በራሱ ድርጅቶች ተቆጣጥሮ ለስልጣን መቆያ መሳሪያ አድርጎታል፡፡ የመንግስት ድርጅት የሚባሉትም ቢሆኑ ኢኮኖሚው ጠቅልለው ለተመሳሳይ አላማ መሳሪያ በመሆን ላይ ናቸው፡፡ ይህን ተከትሎም አገራችን ነጻ ገበያና የግል ባለሃብቶች የተዳከሙባት ግንባር ቀደም አገር ሆናለች፡፡

የወያኔዎች አስቂኝ መመሪያዎችና ዐዋጆች

ነፃነት ዘለቀ (ከአዲስ አበባ)
በመጀመሪያ የክርስትና እምነት ተከታይ አንባቢዎች እንኳን ለ2006ዓ.ም የትንሣኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፡፡
ሕወሓት ወደ ሥልጣን መጥቶ በዓይነቱ የተለዬ የጥቁር አፓርታይድ ሥርዓትን በዓለማችን ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ ካቆመ ወዲህ እጅግ ብዙና ለመቁጠርም የሚያዳግቱ መመሪያዎችንና ዐዋጆችን ቀርፆአል፡፡ አንዳንዶቹን በዘፈቀደና በነሲብ እየቸከቸከ በፈለገው ሰዓትና ወቅት ራሱ ተግባራዊ በማድረግ፣ አንዳንዶቹንም ለማስመሰል ያህል በእንቅልፋምና ደናቁርት የ“ፓርላማ” አባላቱ አማካይነት በዐይን ጥቅሻ በሚታዘዝ የሆዳም ማይማን ጭብጨባ “አጸድቆ” ሥራ ላይ በማዋል ሀገርንና ሕዝብን ማተራመስ ከያዘ ሁለት ዐሠርት ዓመታትን ጨርሶ የሦስተኛውን ዐሠርት አንድ ሦስተኛ ያህል ጊዜ ለማገባደድ ጥቂት ወራት ብቻ ይቀሩታል፡፡

ህወሓት እስከመቼ ደም ማፍሰሱን ይቀጥላል ? (አቶ ሀብታሙ አያሌው UDJ)

ሀገር የመገንጠል ዓላማ ይዞ የተነሳው የህወሓት ጁንታ በስውር እና በአደባባይ የጫካ ልማዱን መሰረት አድርጎ ሲገድል መኖሩ አዲስ ባይሆንም ከሰሞኑ መረር ያለ እርምጃ ‹‹ግድያ›› ማሰቡን ከጓዳው የወጣ የወሬ ምንጭ ደረሰን፡፡ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት በአዲስ አበባ አስተዳደር ጽ/ቤት ተገኝቼ ነበር፡፡ የመገኘቴ ዓላማም የፊታችን እሁድ ሚያዚያ 26 የሚደረገውን ሰላማዊ ሰልፍ አስመልክቶ የዕውቅና ደብዳቤውን ለመስጠት የተያዘውን ቀጠሮ በማክበር ነበር፡፡ የሰላማዊ ሰልፍ እውቅናን በተመለከተ ኃላፊ የሆኑት አቶ ማርቆስ ፎርም እንዲሞላ አዘዙ፤ የተባለውን ፎርም ሞላን፤ ያን ጊዜ የአቶ ማርቆስ የቢሮ ስልክ አንቃጨለ፤ አነሱት ……ቀጭን ትዕዛዝ ከወዲያ ማዶ…………… ‹‹የአንድነትን ሰላማዊ ሰልፍ በተመለከተ ዕውቅናው እንዳይሰጥ ይቆይ›› አቶ ማርቆስ ፊቱ ተለዋወጠ ‹‹ ይቅርታ አድርግልኝ የኔ ችግር አይደለም›› ሌላ ቃል ካፉ አልወጣም፡፡

ስለፍትህ ሲባል ስርዓቱ ይፍረስ! ክፍል ሶስት (ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ)

ልዕለ ኃያሏ ሀገረ-አሜሪካን ዛሬ ለተጎናፀፈችው የሕግ የበላይነት የተከበረበት ሥርዓት መሰረት የጣሉት እነ ቶማስ ጃፈርሰን በነፃነት አዋጃቸው ላይ ‹‹ሁሉም ሰዎች በእኩልነት የተፈጠሩ ናቸው›› በማለት ሲደነግጉ፤ እንግሊዛዊው ደራሲ ጆርጅ ኦርዌል ደግሞ “Animal Farm” በሚለው መፅሐፉ፣ ጉልበታም ‹‹ገዥ›› አድርጎ በሳላቸው ገፀ-ባሕሪያት አማካኝነት ‹‹…አንዳንድ እንስሳት (ሰዎች) ግን የበለጠ እኩል ናቸው›› ይለናል፡፡ በርግጥ ሁለቱም አይነት አስተዳደሮች መሬት ወርደው ዓለማችንን ዲሞክራት እና አምባ-ገነን በማለት በሁለት ጎራ የከፈሉ የመሆናቸው ጉዳይ አከራካሪ አይደለም፡፡ ራሷ አሜሪካንን ጨምሮ አብዛኛው የአውሮፓ አገራት ከሞላ ጎደል በዜጎች እኩልነት ላይ የተመሰረተ ማሕበረሰብ መገንባት ከቻሉት ውስጥ ሲመደቡ፤ ብዙሃኑ የአፍሪካ እና የእስያ መንግስታት ደግሞ ‹‹አንዳንድ ሰዎች ይበልጥ እኩል ናቸው›› በሚል መንፈስ የተቃኘ አገዛዝ አንብረው፣ የትኛውንም ተግዳሮት በጠብ-መንጃ ዓይን መመልከትን ፈቅደዋል፡፡ ከእነዚህኞቹ መካከል የእኛይቷ ኢትዮጵያ ዋነኛዋ ናት፡፡

Wednesday, April 16, 2014

አባይን ለመንከባከብ የጎሰኛነት አገዛዝ በዲሞክራሳዊ አገዛዝ መተካት አለበት (ዶ/ር አክሎግ ቢራራ)

አክሎግ ቢራራ (ዶ/ር)

Click here for PDF

Ethiopia's dam on Abbay/Nile river
ክፍል አንድ
“ለምንወደው ለዛሬው ሕዝባችንም ሆነ፤ ከዘመን ወደ ዘመን ለሚከተለው ትውልድም ጭምር፤ የዓባይን የውሃ ሃብት ለሕይወቱ ደህንነትና ለፍላጎቱ ማርኪያ እንዲውል ማድረግ፤ ኢትዮጵያ ከፍ ያለ ግምት የምትሰጠውና በቅድሚያ የሚያሳስባት ጉዳይ ነው።
አምላካችን ያበረከተላትን ይህን ሃብቷን ለሕዝባቸው ህይወትና ደህንነት በማዋል እንዲጠቀሙበት ከጎረቤት ወዳጅ አገሮች ጋር በለጋስነት በጋራ ለመካፈል ዝግጁ ብንሆንም፤ ይህን የውሃ ንብረቷን በቁጥር እየጨመረ ለሚሄደው ሕዝቧና በማደግ ላይ ላለው ኢኮኖሚ ጥቅም እንዲውል ማድረግ የኢትዮጵያ ተቀዳሚና የተቀደሰ ግዴታዋ ነው።”
ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ፤ ጥቅምት 1957 ዓም

በሞት አፋፍ ላይ ተቀምጠው እውነትን የፈሩ

ብሩክ ሲሳይ (አዲስ አበባ)
ያለወትሮዬ ሴንትራል ሆቴል ቁጭ ብያለሁ ከጎኔ ሁለት ሽማግሌዎች ተቀምጠዋል ብቻዬን በመሆኔ እና የሽማግሌዎች ወግ ስለምወድ እነዚህ ሁለት አዛውንቶች የሚያወሩት ወሬ ላይ ጆሮዬን ጥያለሁ፤ ከአገራችን ፖለቲካ ጀምሮ እስከ ልጅነት ህይወታቸው እና ሌሎችም ብዙ ነገሮችን እያነሱ ያወራሉ። ከወሬያቸው እንደተረዳሁት አንደኛው አዛውንት ከአሜሪካ ቨርጂኒያ ለእረፍት የመጡ ዲያስፖራ ናቸው ሌላኛው ደግሞ በኢህአዴግ የፖለቲካ ስልጣን በተለያዩ የኃላፊነት ደረጃወች ያገለገሉ እና ኢህአዴግ መጥጦ መጥጦ የወረወራቸው አዛውንት ናቸው። ወሬያቸው ግሏል ግንቦት 7 እና የግብፅ እና የሻብያ ተላላኪዎች፣ የጨረቃ ቤቶች፣ የመተማ እና የሱዳን ጠረፍ መሬቶች፣ መለስ ዜናዊ፣ ብርሀኑ ነጋ፣ ሟች ጳጳስ ጳውሎስ፣ አልማ፣ የዲያስፖራው አክራሪነት ወዘተ አይነት ነገሮች እየተወሩ ነው። ጋባዥ ስለሆኑ ነው መሰለኝ ብዙ የሚያወሩት ዲያስፖራው አዛውንት ናቸው ተጋባዥ አዛውንት ደግሞ ራሳቸውን በመነቅነቅ ድጋፍ ይሰጣሉ።

ስለፍትህ ሲባል ስርዓቱ ይፍረስ! ክፍል 2 (ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ)

በዚህ ርዕስ ሥር ባለፈው ሳምንት በይደር ካቆየሁት ተከታይ ጽሑፍ በፊት አንድ እርምት የሚያሻው ጉዳይን በአዲስ መስመር ላስቀድም፡፡
ሬዲዮ ፋና እና “አምደኞቹ”
በ1988 ዓ.ም በኤፈርት ባለቤትነት ስርጭቱን አሀዱ ያለው “ሬዲዮ ፋና”፣ ከምስረታው አንስቶ ዛሬም ድረስ ልክ እንደ በረሃው ዘመን ሁሉ የሥርዓቱ ቀኝ እጅና የርካሽ ፕሮፓጋንዳው ማስተላለፊያ ቱቦ ሆኖ መዝለቁ ለወዳጅም ለጠላትም የማያከራክር ገሀድ የወጣ ሐቅ ነው፡፡ በተለይ ደግሞ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተወሰኑ የግል ሚዲያዎች ላይ የርግማን ዘመቻ የታወጀ ይመስል ለተከታታይ ሳምንታት “ስመ-ጥር” ረጋሚዎችን ጣቢያው ድረስ ጋብዞ ማብጠልጠልና ማውገዙን ቀንደኛ ሥራው አድርጎ ይዞታል፡፡ በርግጥ ይህ ዘመቻ ከወራት በፊት በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እና የፕሬስ ድርጅት በኩል በ“ጥናት” ስም የወጣው ውንጀላ ቅጥያ ሲሆን፣ በቅርቡ ኢቲቪ ሰርቶ እንዳጠናቀቀው የሚነገርለት ዶክመንተሪ ፊልም ደግሞ “ሳልሳዊ” ዘመቻ ሆኖ ለጥቆ የሚቀርብ መሆኑን የመረጃ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡

አንድ ባርያ ነጻ የሚወጣው መቼ ነው? ሲፈቅድ ነው? ወይስ ሲፈቀድለት? (ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም)

በአለፈው ሳምንት (ፋክት ቁጥር 36) ወይዘሮ መስከረም የተለያዩ መጻሕፍትን በመጥቀስ በሴቶች ላይ ያለውን መጥፎ ጫና በደንብ ያስመሰከረች ይመስለኛል፤ ግን እኮ በሴቶች ላይ ያለው ጫና የቆየ፣ ክፉና ጎጂ መሆኑን ማንም ያውቀዋል፤ ቁም-ነገሩ ያለው ከዚያ የባህል ጭነት በራስ ጥረት ወጥቶ፣ ነቀፌታንም ሆነ እርማትን ለመቀበል ሳይፈሩና ሳያፍሩ እንደመስከረም በአደባባይ ሀሳብን በመግለጽ በአገርና በወገን ጉዳይ መሳተፍና ሌሎችም እንዲሳተፉ የተቻለን ሁሉ ማድረጉ ላይ ነው፤ ለዚህ ነው ይህንን መልስ የምጽፈው፤ ወይዘሮ መስከረም በአጋጠሟትና በምታያቸው እንቅፋቶች ላይ ማተኮርዋ እንደርስዋ መንፈሳዊ ወኔው የሌላቸውን ያስፈራራቸዋል እንጂ አያበረታታቸውም፤ የማንንም አፍአዊ ጫና ተቋቁመው በራሳቸው የውስጥ ኃይል እንዲመሩ እናድርግ።

የሩዋንዳ የዘር ማጥፋት ረዥም ጥቁር ጥላዉን በ(መካከለኛው) አፍሪካ ጥሎአል

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
የ1994 የሩዋንዳ የጭፍጨፋ እና የእልቂት ጸጸት በ2014 የመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ሰማይ ላይ እያንዣበበ ነው!
ባለፈው ሳምንት የሩዋንዳ ህዝብ እርስ በእርስ የተራረደበትን 20ኛውን ዓመት የሩዋንዳ የዘር ፍጅት መጥፎ ገጽታ ለማስታወስ የሀዘን ሳምንት አውጆ ድርጊቱን በመራር ሀዘን ዘክሮታል፡፡ እ.ኤ.አ በኤፕሪል 6/1994 በመንግስት የስልጣን እርከን ላይ የነበሩ አክራሪ የሁቱ ጎሳ አመራሮች፣ የእነርሱ የፖለቲካ አመለካከት ደጋፊዎች እና የተደራጁ ታጣቂ ሚሊሻዎች  ስልታዊ የግድያ ወንጀሎችን በማቀናጀት እና በግንባር ቀደምትነት በመምራት 100 ተከታታይ ቀናት የወሰደ እልቂትን በማደራጀት ከ800 ሺ በላይ ሰላማዊ ህዝቦች በተለይም የቱትሲ እና አክራሪ ያልሆኑ የሁቱ ጎሳ አባላትን ፈጅተዋል፡፡ እ.ኤ.አ በ1994 ሩዋንዳ 5.5 ሚሊዮን ህዝብ የነበራት ሲሆን ከዚህ ውስጥ 14 በመቶ የሚሆኑት የቱትሲ ጎሳ አባላት ነበሩ፡፡ በአሁኑ ጊዜ ሩዋንዳ 11.5 ሚሊዮን ህዝብ ያላት ሲሆን ከዚህ ውስጥ የቱትሲ ጎሳ አባላት ህዝብ ብዛት ከ10 በመቶ ያነሰ ነው፡፡

በተወሰኑ ስኬቶች የተሸፈኑ በርካታ ፈተናዎች

ኢትዮጵያ አገራችን አንገቷን በኩራት ቀና የምታደርግባቸው ስኬቶች እየታዩ መሆናቸውን፣ የአገሩን ዕድገት በጉጉት የሚከታተል ማንኛውም ዜጋ የሚመሰክረው ነው፡፡
በተለይ በኢኮኖሚው መስክ የሚስተዋለው በተከታታይ ዓመታት የተገኘው ውጤት ኢትዮጵያ አገራችን በታሪኳ አይታው የማታውቀው ነው፡፡ ለበርካታ ዓመታት ድህነትና ኋላ ቀርነት በተንሰራፋባት አገር ውስጥ ተስፋ ሰጪ ጅምሮች እየታዩ ናቸው፡፡ እነዚህ ስኬቶች እየተገኙ ያሉት ደግሞ ይህ ትውልድ እየከፈለ ባለው ዋጋ ነው፡፡ 
ስኬቶችን አንስተን ስንወያይ ደግሞ ችግሮችን መሸፋፈን የለብንም፡፡ በአገሪቱ ውስጥ ታላላቅ የመንገድ አውታሮች፣ ታላላቅ የኃይል ማመንጫዎች፣ የቴሌኮምና የኢንዱስትሪ መሠረተ ልማቶች በከፍተኛ ወጪ እየተገነቡ ናቸው፡፡ እነዚህን ስኬች ከለላ በማድረግ የሚፈጸሙ ሕገወጥ ድርጊቶችም አሉ፡፡ ስኬቶችን የሚያደናቅፉ ፈተናዎች ስላሉ የተወሰኑትን ማየት ይገባናል፡፡

Saturday, April 12, 2014

በኢትዮጵያ የመብቶች ትግሎች ሁሉ ህወሓትን ከሥልጣን ወደ ማስወገድ አቅጣጫ ያመራሉ! (ግንቦት 7)


Ginbot 7 weekly editorialየሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ መሪዎች የክስ ሂደት በበርካታ አሳዛኝ ጉዳዮች የታጀቡ ቢሆኑም የሚሰጡት ትምህርት ግን ከፍተኛ ነው። እነዚህ ወገኖቻችን “ችሎት” በተሰኘው የአገዛዙ የድራማ መድረግ በመገኘት ፍትህን ለመግደል ካባ ለብሰው “ዳኞች” ተብለው ለተኮፈሱ የአገዛዙ ተላላኪ ካድሬዎች እና ለመላው ኢትዮጵያ ሕዝብ ያደረጓቸው ጠንከር ያሉ ንግግሮች ካድሬ “ዳኞችን” አሳፍረዋል፤ ኢትዮጵያዊያንን ግን አኩርተዋል። እኚህ ወገኖቻችን ከወያኔ ችሎት ፍትህ ይገኛል የሚል ብዥታ ባይኖራቸውም መድረኩን መልዕክት ለማስተላለፊያነት ተጠቅመውበታል። በዚሁ መድረክ በአገዛዙ እጅ ከወደቁበት ጊዜ ጀምሮ እየደረባቸው ስላለው ሰቆቃ ሲናገሩ አድማጮች ሊቆጣጥሩት የማይችሉት ሐዘንና እልህ ውስጥ እንዲገቡ አድርጓቸዋል።

Thursday, April 10, 2014

የቶሮንቶና የነቀምት ግንባር፣ የአንድነት የሶስት ወር ዘመቻ

ተክለሚካኤል አበበ፤ ቶሮንቶ
የማርቆስ ብዙነህ ደብዳቤ፤
1-     “በርካታ ትምህርት ቤቶች፤ ዩኒቨርስቲና የመንግስት ተቋማት በሚገኙበት አካባቢ ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ የማይቻል በመሆኑ፤ የተጠየቀው የሰላማዊ ሰልፍ እውቅና ጥያቄ ተቀባይነት ያላገኘ መሆኑን እንገልጻለን” ይላል፤ በአዲስ አበባ መስተዳድር የሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቅ ክፍል ሀላፊ፤ በአቶ ማርቆስ ብዙነህ ማንደፍሮ፤ መጋቢት 23 ቀን 2006/2014 የተፈረመው ደብዳቤ፡፡ አንድነት፤ ሰልፉን ለማድረግ ያቀረባቸው መስመሮች 3 ሲሆኑ፤ ሶስቱም መስመሮች ከቀበናው የአንድነት ጽ/ቤት ይነሳሉ፡፡ አንደኛው መስመር በአራት ኪሎና በፒያሳ አድርጎ፤ ወደ አዲስ አበባ መስተዳድር ጽ/ቤት ያመራል፡፡ ሁለተኛው አማራጭ በአራት ኪሎ ተጉዞ፤ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን አልፎ መስቀል አደባባይ ያበቃል፡፡

በስምምነት ላይ የተመሰረት ባህላዊ ውህደት Vs ህገ-መንግስታዊ ቀናዒነት

ገለታው ዘለቀ
መግቢያ
በዚህ ጽሁፍ ሥር ለውይይት ይሆን ዘንድ የምናነሳው ኣሳብ   constitutional patriotism   ወይም ህገ መንግስታዊ ቀናዒነት ወይም ኣርበኝነት የሚባለው ጽንሰ ሃሳብ ባለፈው በተከታታይ ካቀረብኳት የ  Conventional Cultural Unity  ወይም በስምምነት ላይ የተመሰረት ባህላዊ ውህደት ካልኩት ኣሳብ ጋር እንዴት እንደሚለያይና  በኢትዮጵያ ሁኔታ ከሁለቱ ኣሳቦች የትኛው ተገቢና ችግር ፈቺ ሊሆን እንደሚችል  ኣሳብ ለማፍራት ነው።
በቅድሚያ ኣንድን ፖለቲካዊ የሆነ ፍልስፍና ወይም ቲየሪ በኣንድ ሃገር ፖለቲካ ውስጥ መሰረታዊ የመጫወቻ ወለል ኣድርገን ከማንጠፋችን በፊት ቲየሪው ወይም ኣሳቡ በጣም መጠናትና ግልጽ መሆን ኣለበት። ግልጽነት ሳይኖረውና ሳንረዳው በስሜት ከተከተልነው ሁዋላ ላይ ጉምን እንደ መጨበጥ ይሆንና እናርፋለን።

ብርሃኑ ዳምጤ – ደቡር፣ አባ መላ፣ ዘ-አገምጃ

መስፍን ቀጮ/ወፍ
የሚቀጥለውን ትረካ ለመጻፍ ብዙ ሀሳብ ውስጥ ገብቼ ነበር፡፡ ብጽፈውስ ምን ዋጋ አለው የሚል ስሜትም ተጭኖኝ ነበር፡፡ ሆኖም ‹ጅብ በማያውቁት ሀገር ቁርበት አንጥፋልኝ› እንዲሉ ከላይ የተጠቀሰው ብርሃኑ ደቡር አባ መላ በአዲሶቹ አለቆቹ የተረቀቁለትን ቃለ መጠይቆች ሲያነበንብ መስማቱ ስለሰለቸኝ ‹ማን ያውጋ የነበረ ማን ያርዳ የቀበረ› በማለት የልጅነት ጓደኛዬን ሳልወድ ለማጋለጥ ወሰንኩ፡፡Berhanu Damte Ethiopian regime supporter
እኔና ብርሃኑ ዳምጤ በአንድ ማዕድ እየበላን በሰፈር ወንዝ እየተራጨን እየተንቦራጨቅን ብይና አርቦሽ እየተጫወትን ሌላም ሌላም ነገር እየሰራን ያደግን ልጆች ነበርን፡፡ ብርሃኑና እኔ ት/ቤት ስንገናኝ እንዲሁ ጓደኛሞች ሆነን እኔ ከእሱ በዕድሜ አራት ዓመት አንስ ስለነበር ትምህርት የጀመርኩት ከሱ በኋላ ነበር፡፡ አንደኛ ክፍል ስገባ እሱ ወደሶስተኛ ተዛውሯል፡፡ ከሱ በእድሜ ከማነሴ በላይ ደቃቃ በመሆኔ ‹ቀጮ› የሚል ቅፅል ስም ወጥቶልኝ ነበር፡፡ ብርሃኑ በዚያን ጊዜ ከክፍል ልጆች በዕድሜ ይበልጥ ነበር፡፡ በትምህርቱ ደካማ ስለነበር ክፍል ስለሚደግም ታናናሾቹ ይደርሱበትም ይቀድሙትም ነበር፡፡ ለዚህም ነው እኔና እሱ ስድስተኛ ክፍል ላይ የተገናኘነው ብርሃኑ በጣም ወፍራምና ለፍላፊ ነበር፡፡

Friday, April 4, 2014

የጥላቻው እሳት ቆስቋሹን ያቃጥለው

ዳኛቸው ቢያድግልኝ
የትግል መሰረቱን ጎጥ ላይ ያደረገ፣ የእድገት ልኩን ዘረፋ ላይ ያዋለና የእውቀት ጥጉን ውሸት ላይ የመሰረተ እንዴትም ሆኖ የነጻነት ታጋይ አይሆንም። ይልቁንም በሕዝብ ጫንቃ ላይ ተንፈራጥጦ እንዲኖር የክፋት መርዙን ይረጫል እንጂ። ምንም በሁኔታዎች አስገዳጅነት ቢተጣጠፍ እንኳ ኢትዮጵያዊነትን ከፍ የማድረግ አቅም ስለሌለው ሕብረት ያስፈራዋል፣ ነጻነት ያጥወለውለዋል፣ አንድነትም ያስበረግገዋል። ኢትዮጵያ ለወያኔ ትርፍ እስካስገኘች ድረስ እንደምትታለብ ላም ነች። ከዚያ በላይ ወያኔዎች ሀገራዊ ራዕይ የሚባል ነገር የላቸውም።

ነጻ መብራት፣ ስልክ እና ውሃ በካሳ መልክ ሊሰጥ ነው

ዳዊት ከበደ ወየሳ
በመብራት መቆራረጥ የሚሰቃየው የኢትዮጵያ ህዝብ “እፎይ” የሚልበትን ቀን ሁሉም ይናፍቃል። የአባይ ወንዝ ከተገደበ በኋላ የሚመነጨው የኤሌክትሪክ ሃይል ከኢትዮጵያ አልፎ ለሱዳን እና ለግብጽ እንደሚበቃም ይነገራል። ከዚህ ግድብ በተጨማሪ የግልገል ጊቤ 2 እና 3 ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ ኢትዮጵያ የሚኖራት የመብራት ሃይል በአስር እጥፍ እንደሚጨምር የዘርፉ ሙያተኞች ይመሰክራሉ።
በዚህ አጋጣሚም በመብራት መቆራረጥ እና እጦት የሚሰቃየውም ህዝብ የሚካስበት አጋጣሚ ይፈጠራል። መብራት ሃይል ዛሬ ያወጣው መግለጫ እንዳረጋገጠው ከሆነ፤ “እስካሁን መብራት ያጣውን የኢትዮጵያ ህዝብ ነጻ የኤሌክትሪክ ሃይል ወይም ግምቱ ታውቆ በጥሬ ገንዘብ ካሳ ይከፈለዋል።” ተብሏል። የቴሌኮምዩኒኬሽንም በበኩሉ የመብራት ሃይልን ተነሳሽነት አድንቆ በቴሌም በኩል እስካሁን በኔት ዎርክ መቆራረጥ ሲሰቃይ የነበረውን ህዝብ ለመካስ፤ በኢትዮጵያ የሚሰራውን “አባ ዱላ” የሚል ስያሜ የተሰጠውን የስልክ ቀፎ ለደንበኞቹ በነጻ እንደሚሰጥ ወይም ከመቶ እስከ 1ሺህ ብር ዋጋ የሚያወጡ ሲም ካርዶችን የሚያድል መሆኑን አሳውቋል።

የማሕበረ ቅዱሳን የመጨረሻዎቹ ቀናት (ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ )

“ማሕበረ-ወያኔ”
በኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም የሚመራው መንግስት ከናቅፋ እስከ ጉና ተራራ ያሉ ምሽጎቻቸውን ከሰማይ በጦር አይሮፕላን፣ ከምድር እሳት በሚያዘንቡ ቢ.ኤሞችና መድፎች ሳያቋርጥ ቢደበድብም፤ በሀገሪቱ ሰሜናዊ አካባቢ ከቀን ወደ ቀን ግዛታቸውን እያሰፉ የተጠናከሩት ‹‹ወንበዴዎች›› ራስ ምታት ሆነውበታል፡፡ የኤርትራ ‹‹ነጻ አውጪ›› ቤዝ-አምባው በተወሰነ መልኩም ቢሆን ለጥቃት የመጋለጥ እድሉ አናሳ በሆነው የሳህል በረሃ በመሆኑ አብዛኛው የአመራር አባል መሸሸጊያው አድርጎታል፡፡Temesgen Desalegn "Fact" Ethiopian Amharic newspaper editor
በተመሳሳይ መልኩ በትግራይ አካባቢ የሚንቀሳቀሱት የወያኔ መሪዎች ምሽጋቸው እንደ ሳህል ምቹ ባለመሆኑ፤ በርካታ ክፉ ቀናትን ያሳለፉት በተራራማ አካባቢዎች በሚገኙ የኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ገዳማት ውስጥ ተደብቀው እንደሆነና ከቦታ ቦታ መዘዋወር ሲፈልጉም የመነኮሳቱን አልባሳት ይጠቀሙ እንደነበረ በትግሉ ዙሪያ የተዘጋጁ ድርሳናት ያወሳሉ፡፡ በተለይም ታጋይ መለስ ዜናዊ፣ አባይ ፀሀዬ፣ ግደይ ዘርአፅዮን፣ ስዩም መስፍን፣ ስብሐት ነጋን…. የመሳሰሉ የአመራር አባላት የገዳማቱ ቤተኛ ነበሩ፡፡

[በአባይ ግድብ ዙሪያ የተጻፈ አጭር ሀተታ] ትንሹዋ ወያኔና ትልቁ ወያኔ አላኖሩኝም

ነፃነት ዘለቀ (አዲስ አበባ) 
ለለውጥ ያህል ከራሴ ችግር ብጀምር ምን አለበት? ግለሰብ ካልኖረ ማኅበረስብ አይኖርም፡፡ ደሞም የኔ ችግር የሁሉም ፣ የሁሉም ችግር የኔ መሆኑን የማያምን አንባቢ ቢኖር ችግር አለበት ማለት ነውና በጊዜ ራሱን ፈትሾ መድሓኒት ቢጤ ቢያፈላልግ ሳይሻለው አይቀርም፡፡TPLF is just like a Rat
ትንሹዋ ወያኔ ጠምሳኛለች፡፡ እኔን ብቻም አይደለም የጠመሰችው፡፡ ብዙዎች ኢትዮጵያውያንንም እንጂ ነው፡፡ ከወያኔ ባልተናነሰ ሁኔታ ኑሯችንን እያቃወሰችው ትገኛለች – ትልቁ ወያኔ በደጅና በቤት ውስጥ እርሷ ደግሞ በቤት ውስጥ ብቻ በተናጠልና በቡድን እየተጋገዙ ወዲያ ወዲህ ውልፊት ልንል በማይቻለን ሁኔታ ወጥረውናል፡፡ ምን እንደምናደርግም ጨንቆናአለ፡፡ ይቺ የቤት ውስጥ ወያኔ ዐይጥ ናት፡፡

ህግን ተላልፈን ከህገወጦች ጋር አንተባበርም! (ከአንድነት የአዲስ አበባ ም/ቤት የተሰጠ መግለጫ)

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)
ከአንድነት የአዲስ አበባ ም/ቤት የተሰጠ መግለጫ
Andenat Party UDJ
የእሪታ ቀን በሚል መሪቃል በመዲናችን አዲስ አበባ ያሉ ማህበራዊና ኢኮ ኖሚያዉ ቀውሶችን አስመልክቶ በተለይም ከተማዋን ወደ ማህበራዊ ቀውስ እየመሯት የሆኑትን የውሃ፣ መብራት፣ ስልክ፣ የትራንስፖርት ችግር እንዲቀረፍ ህዝቡ የተቃውሞ ድምፁን እንዲያሰማ መጋቢት 28 ቀን 2ዐዐ6 ዓም ለማካሄድ ያቀደውን ሕዝባዊ ሠላማዊ ሠልፍ አስመልክቶ በህዝብ መገናኛ ብዙሃን ይፋ ካደረግንበት ቀን ጀምሮ የሚጠበቅብንን ህጋዊ የማሣወቅ ሥራዎችን ስንሠራ የቆየን መሆኑና መድረስ ለሚገባው አካል ሁሉ አካል ሁሉ በተገቢው ሁኔታ ማሳወቃችን ይታወቃል፡፡ ነገር ግን ጥሪው ለሕዝብ ይፋ ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ የሚመለከተው የሠላማዊ ሠልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ክፍል በህግ የተቋቋመበትን ኃላፊነት በመዘንጋት ለጠየቅነው ጥያቄ ቀጥተኛ መልስ ከመስጠት ይልቅ ህግ በመተላለፍ ክልከላ አዘል ደብዳበ ልኳል፡፡ ሆኖም የአንድነት የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት በትላንትናው እለት ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ ለሠላማዊ ሠልፍ ማሳወቂያ ክፍል የላከው ደብዳቤ በአዋጅ ከተደነገገ ህግ ጋር የሚጣረስና የዜጎችን መብት የሚያፍን መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ የአንድነት ምክር ቤት ግንዛቤ በመያዝ ከዚህ የሚከተለውን የአቋም መግለጫ በማውጣት ለመገናኛ ብዙሃን እንዲተላለፍ ወስኗል፡፡

ትንሽ ምላጭ አገር ትላጭ! መጠላለፍ ወደየትኛው ገደል እየመራን ነው? (ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም)

የአዲስ አበባን መኪናዎች በተለይም በጫት የሚሽከረከሩት ታክሲዎችን በማንኛውም መስቀልኛ መንገድ ላይ ለአምስት ደቂቃ ቆሞ የተመለከተ ሰው በቀላሉ እንደሚረዳው ‹እኔ ካላለፍሁ ማንም አያልፍም!› በሚል መመሪያ መኪናዎቹ ተቆላልፈው እንዲቆሙ ማድረግ ነው፤ እንደሚመስለኝ የአባቶቻችንን ዕዳ እየከፈልን ነው፤ ዱሮ በደጉ ዘመን ሁለት ኢትዮጵያውያን መስቀልኛ መንገድ ላይ ሲገናኙ አንተ-እለፍ አንተ-እለፍ እየተባባሉ የሰማዕታቱንና የቅዱሳኑን ስም እየጠሩ ይገባበዙ ነበር! ይህ ባህል በጠንካራ የሥልጣኔ ላጲስ ተደምስሶ ጠፍቶ በምትኩ እኔ ካላለፍሁ ማንም አያልፍም መንገዱን ሁሉ መቆላለፍ አዲስ የመጠላለፍ ባህል እየተተከለ ነው፤ የመጠላለፍ ባህል የሚታየው በባቡር መንገዶች ላይ ብቻ አይደለም፤ በብዙ ነገር መጠላለፍ ባህል እየሆነ ነው! የዚህ ዝንባሌ መጨረሻው አሸናፊ የሌለበት ሙሉ ጥፋት ነው።

Tuesday, April 1, 2014

የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋብቻና ፍቺ አልተጣጣመም!

  • ከኤልያስ
  • ኢትዮ-ቴሌኮም በኖኪያ ቁጥጥር ስር የነበሩ የኔትዎርክ ወረዳዎችን ነፃ አወጣ!
  • አንድነት እና መኢአድ ሳይጋቡ በመፋታት ሪከርድ ሰብረዋል
  • “ድር ቢያብር አንበሳ ያስር” ትዝ የሚላቸው ምርጫ ሲቃረብ ነው

        የአፍሪካ አንድነት የሰላም አስከባሪ ኃይልን የተቀላቀለው የአገራችን መከላከያ ኃይል ሶማሊያ ውስጥ አልሻባብ ተቆጣጥሯቸው የነበሩትን ቦታዎች ማስለቀቁን በኢቴቪ ዜና እወጃ ላይ ሰምቼ ደስ ብሎኝ ነበር (ኢትዮጵያዊ ሆኖ ድል የማይወድ አለ እንዴ?) በነጋታው ነው መሰለኝ … ሌላ የምስራች ደግሞ ሰማሁ፡፡ ኢትዮ-ቴሌኮም በኖኪያ ቁጥጥር ስር የነበሩትን አየር ጤና፣ ቄራና ዓለም ባንክ አካባቢዎች ነፃ ማውጣቱ ተነገረ-በዜና ሳይሆን በተባባሪ ወሬ፡፡ እናላችሁ …. ሁለቱ አካባቢዎች አሁን ኔትዎርካቸው ያለመቆራረጥ እየሰራ ነው፤ ተብሏል (ኢንተርኔትና ፌስቡክም ያለችግር ማግኘት ችለዋል) ኢትዮ-ቴሌኮምን የማሳስበው ግን በዚህ የድል ብስራት ተኩራርቶ ሌሎቹን በቁጥጥር ስር ያልዋሉ የኔትዎርክ ወረዳዎች ነፃ ከማውጣት እንዳይዘናጋ ነው። ያለዚያ እኮ የሦስቱ አካባቢዎች ነፃ መውጣት ትርጉም የለውም (ተመልሰው በ“ጠላት እጅ” ሊወድቁም ይችላሉ!) እናላችሁ … ሌሎች የመዲናዋ አካባቢዎችም ከ “ባዕድ እጅ” ነፃ ሲወጡ ነው እነ ዓለም ባንክ ነፃነታቸውን በቅጡ የሚያጣጥሙት፡፡ እስከዛ እኮ እርስ በርስ ብቻ ነው ኮሙኒኬሽኑ!