Friday, January 31, 2014

ወያኔን ያሸበረው የግንቦት 7 መንገድ ምንድነው?

የትግራይን ሕዝብ ከብሄር ጭቆና ነጻ አወጣለሁ በሚል ጠባብ ዓላማ ተደራጅቶና ታጥቆ ለበትረ ሥልጣን የበቃው ህወሃት ወይም ሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ሥልጣን ከተቆጣጠረ 23 አመት ሊሞላው እነሆ ጥቂት ወራቶች ብቻ ቀርተውታል።
ለጋራ ቤታችን ለሆነቺው አገራችን ኢትዮጵያና በአስተዳደር በደል ለከፋ ድህነት ለተዳረገው መላው ሕዝቦቿ የሚሆን አንዳችም ራዕይ ሳይኖረው ለመንግሥትነት ሥልጣን የበቃው ይህ ቡድን ላለፉት 23 ዓመታት ከግል ኑሮአቸው አሻግረው የአገርንና የወገንን ጥቅም ማየት የማይችሉ ወይም የማይፈልጉትን በዙሪያው አሰባስቦ እያካሄደ ካለው ዘርፈ ብዙ የሃብት ምዝበራ ወንጀል በተጨማሪ እየፈጸመ ያለው የመብት ጥሰትና አፈና ተዘርዝሮ የሚያልቅ አይደለም።

Thursday, January 30, 2014

የታመቀው የኢትዮጵያውያን ምሬት፡ የሕይወት ማሽቆልቆልና በፍርሃት መሽማቀቅ አፋጣኝ መፍትሄ ይሻል

ኢትዮጵያ በሕወሃት ዘመነ አመራር የታወቀችባቸው ብዙ ነገሮች ሊኖሩ ይችላሉ። ብዙ “እንዴ!”የሚይሰኙ ጥሩ አሳቦችም ፈልቀዋል – አፈጻጸማቸው እትይለሌ ቢሆንም። ከነዚህም መካከል መሠረተ ልማት፡ በጤናና በትምህርት መስኮች መሻሻሎች መታየታቸው ወዘተ መልካም ይነገርላቸዋል – የቢል ጌትስን የራስ ተጠቃሚነትና ኢምፓየር ግንባታ ወደጎን ትተን! በዕጦት ደረጃም በሀገራችን የስብዓዊ መብቶች አለመክበር፣ የፍትህ አለመኖርና ለአብዛኛው ሕዝባችን የምግብ ዕጦት ዋና ዋና ተጠቃሽ ችግሮች ናቸው።

“ታሪክ ለባለ ታሪኩ”

ገብረመድህን አርአያ፣ አውስትራሊያ
Ato Gebremedhin Araya is one of former Tigray People Liberation Front (TPLF) leaders
አቶ ገብረመድህን አርአያ የቀድሞ የሀወሀት ገንዘብ ያዥ
ኢትዮጵያ ሃገራችን ትልቁ እድሏ ከጥንት ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ብዙ የታሪክ ሊቃውንትና ጸሓፍት ያፈራች ሃገር መሆኗ ነው።
በጥንቱ ዘመን በኢትዮጵያ መቀመጫቸውን አክሱም ያደረጉት ነገሥታት ታሪካቸውን እና ጥበባቸውን በሳብኛና በግእዝ እያጻፉ አዘጋጀተዋል። በመቀጠልም መቀመጫቸውን ወደ ዛጔ፣ ላስታ ላሊበላ፣ ወሎ ሲተላለፍ በዚያ የነገሡ ነገሥታትም ታሪካቸውን እና ጥበባቸውን በግእዝና በአማርኛ እያዘጋጁ አልፈዋል። የነገሥታቱ መቀመጫ ከወሎ ወደ ሸዋ፤ ከዛም ወደ ጎንደር ሲሸጋገር፣ የነበረው ታሪክ፣ ጥበብና የነገሥታቱ ዝርዝር ሁኔታ ተዘጋጅተው ተመዝግበዋል።

Tuesday, January 28, 2014

ስኬታማ ውድቀት (Successful Failure!)

ይሄይስ አእምሮ (አዲስ አበባ)
ለውድቀት ስኬት “የምሥራች!” ወይም “እንኳን ደስ ያለን!” የማይባል ነገር ሆኖብኝ እንጂ ከነዚህ የደስታ ማብሠሪያ አባባሎች በአንደኛው ጽሑፌን መጀመር ቃጥቶኝ ነበር፡፡ ለማንኛውም ሀገራችን በማንኛውም ዘርፍ በገባችበት ውድቀትና ኪሣራ ምክንያት ልባችሁ ያዘነና ቅስማችሁ የተሰበረ ወገኖቼን “እግዚአብሔር ያጽናችሁ፤ የሀገራችሁን ትንሣኤም ፈጣሪ በአፋጣኝ እውን እንዲያደርግላችሁ የእግዚአብሔርን ልብ ያራራላችሁ” በሚለው የልመና ቃል ፈጣሪን እየተማጸንኩ ወሬየን ልቀጥል፡፡ ትንሽ በንዴት እንድትንጨረጨሩ ፈቃዳችሁ ይሁንልኝ፤ መልካም መንጨርጨር!Ethiopian books review
ሰሞኑን ለራሴ የጥሞና ጊዜ እንዲኖረኝ ፈለግሁና በንባባዊ አርምሞ ሰነበትኩ፡፡ በግሌ እንደብዙዎች ሰዎች ብዙ ጉድለት አለብኝ፡፡

ህወሓቶች አደብ ግዙ! (አብርሃ ደስታ)

በሌሎች ላይ የምትፈፅሙት ተግባር ሁሉ በራሳቹ ላይ እንደምትፈፅሙ (እንደሚፈፀም) አስቡ። በስልጣን ላይ ያለ ሁሉ በስልጣን አይኖርም። የስልጣን ዕድምያቹ በጣም አጪር መሆኑ እናንተም ታውቁታላቹ። በሰዎች ላይ ግፍ ስትፈፅሙ ሰዎች ይጠሏችኋል። በሰዎች ስትጠሉ የስልጣን ዕድምያቹ ያጥራል። እናንተ ያላቹ የህዝብ ድጋፍ ሳይሆን ጠመንጃ ነው። ጠመንጃ ስልጣን ለመያዝ ይረዳ እንደሆነ እንጂ በስልጣን ለመቆየት አያስችልም። ስለዚህ በጠመንጃ አፈሙዝ የስልጣን ዕድምያቹ ለማራዘም የምታደርጉት ጥረት ከንቱ ልፋት ነው።

የወያኔ የውሸት ዘገባዎች ሲጋለጡ

Ginbot 7 weekly editorial“ኦክስፋም” በመልካም ሥራቸው ከታወቁ ትላልቅ ዓለም ዓቀፍ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች አንዱ ነው። በቅርቡ አንድ መቶ ሀያ አምስት አገሮችን ያካተተ ከምግብ አቅርቦትና አጠቃቀም ጋር የተያያዘ ጥናት ውጤት ይፋ አድርጓል። ጥናቱ አራት ዝርዝርና አንድ አጠቃላይ አመላካቾች አሉት።
1. አመላካች አንድ: የምግብ እጥረት
ይህ አመላካች “በየአገሮቹ ምን ያህል ለበላተኛው የሚበቃ ምግብ አለ?” የሚለውን ይለካል። በጥናቱ ውጤት መሠረት በምግብ እጥረት እጅግ የተጎዱ የመጨረሻዎቹ አስር አገሮች የሚከተሉት ናቸው: – ቡሩንዲ፣ የመን፣ ቻድ፣ ኢትዮጵያ፣ ማዳጋስካር፣ ናይጄሪያ፣ ላኦስ፣ ባንግላዴሽ፣ መካከለኛዉ አፍሪካ ሪፑብሊክ እና ህንድ። ኢትዮጵያ አገራችን ከመጨረሻ አራተኛ ናት።

በልቡ የሸፈተ ህዝብ የካድሬዎች ጋጋታና ሽብር አይገታውም

በዲያስፖራ የአረና ትግራይ ድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ

ሰሞኑሰሞኑን በትግራይ የህወሓት መሪዎችና ካድሬዎቻቸው ከየመንደሩ የተውጣጡ ነብሰ ገዳይ፣ ስብሰባ በታኝና አፋኝ የዱሪየ ቡድኖችን በተለያየ መልኩ በማደራጀት በአረና ትግራይ አባላትና አመራር ላይ የከፈቱትን አዲስ የመንጥርና የድብደባ ዘመቻን አስመልክቶ

ህወሓት/ኢሕአዴግ በትረ ስልጣኑን ከተጎናፀፈና ካደላደለ ወዲህ ከሱ የተለየ አመለካከትና ሃሳብ ያላቸው ወገኖች ሁሉ የተለያዩ ቀለማ ቀለሞችን በመቅባት፣ የፈጠራ ስም በመለጠፍና ሰበብ አስባብ በመፈለግ በቀጥታም ሆነ በረቀቀ መንገድ የመመንጠር፣ የማፅዳት፣ የመሰወር፣ የማሰር፣ የመግደልና እርስ በርስ የማናቆር ስራ ዋነኛ የስርዓቱን ባህርይ መገለጫ ሆኖ መቆየቱ እሙን ነው። የእርምጃው ዋናው ምክንያትም እውነት ተቃዋሚዎቹ የሀገርና የህዝብ ጠላቶች ስለሆኑ አይደለም። ነገር ግን ጥያቄያቸው “ስለ ሀገራችንና ህዝባችን ጉዳይ እኛም ያገባናል!! አባቶቻችን ደም ከፍለው ያቆዩልንን ሀገር የመጠበቅ የኛም ግዴታ ነው!!

Sunday, January 26, 2014

ጃዋር መሀመድን ለፍርድ ለማቅረብ እንቅስቃሴ መጀመሩን ተገለጸ

የጃራ ሽባብ ተበሎ በሚጠራው የኦሮሞ የእስልምና አክራሪዎች ቡድን መሪ የሆነው ጃዋር መሀመድ በክርስቲያኖችና በኢትዮጵያውያኖች ላይ የአለምን አቀፍ ህግን በመጣስ ዘርን ከዘር ፣ሀይማኖትን ከ ሀይማኖት ለማጫረስ አንዳንድ ተራ ነገሮችን ሰበብ በማድረግ በከፍተኛ ደረጃ በሳይበር በአገር ውስጥ በተለይም በዲያስፖራ ለተጀመረው የጥላቻ ቅስቀሳ ለማስቆምና ግለሰቡን ወደ ፍርድ ለማቅረብ የህግ ባለሙያዎች እየተሰባሰቡና ምረጃዎችንም በመሰብሰብ ላይ ናቸው።የአለም አቀፍ ህግ ዘር ማጥፋትን ሳይሆን ቅስቀሳን ማድረግ በራሱ ትልቅ ወንጀል ነው።

Tuesday, January 21, 2014

የኢትዮጵያን ታሪክ ጥላሸት የመቀባት አባዜ (ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም)

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
ጥር 7 ቀን 2006 ዓ.ም
በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ያለው ገዥው አካል በ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያ ንጉስ የነበሩት የዳግማዊ አጼ ምኒልክ መቶኛ የሙት ዓመት በዚህ በያዝነው ዓመት (በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር) እየተከበረ ባለበት ወቅት ሙሉ ጊዜውን በመስጠት ንጉሱ የሰሩትን ታላቅ ስራ ሁሉ በማጣጣል እና ጥላሸት በመቀባት ዘመቻ ላይ በመጠመድ ታሪክ የማጠልሸት ድራማውን በመተወን ላይ ይገኛል፡፡ የታሪክ ማጠልሸት ዘመቻው በዋናነት እየተከናወነ ያለው ለገዥው አካል ቅርበት ባላቸው ታማኝ ሎሌዎች፣ የጥቅም ተጋሪዎች እና የእራሳቸው ስብዕና በሌላቸው አሻንጉሊቶች አማካይነት ነው፡፡ ገዥው አካል ሲያስነጥሰው መሃረብ ይዘው በሚቀርቡ አጎብዳጆቹ አማካይነት የጥላቻ መርዛማ ቃላትን፣ የሚቆጠቁጡ ባዶ ዲስኮሮችን እና እርባናየለሽ ምዕናባዊ ስዕል በአዕምሮው ላይ እየፈጠረ አጼ ምኒልክ የግዛት ማስፋፋት ጥማታቸውን ለማርካት ሲሉ በዜጎች ላይ የጭካኔ ተግባራትን እንደፈጸሙ በማስመሰል ለምንም የማይጠቅሙ እርባናየለሽ እና ተራ አሉባልታዎችን በማሰራጨት ላይ ይገኛል፡፡

የወያኔ ነፍስ በበረከት ስምዖን በኩል ስትቃዥ

ነፃነት ዘለቀ (አዲስ አበባ)
አንደኛው መስከረም ጠብቶ ሌላኛው መስከረም እስኪጠባ ድረስ ባሉት የ365.25 ቀናት ውስጥ ስንት ጉድ መስማት እንዳለብን የሚጠቁም አሃዛዊ መረጃ ሊኖር እንደማይችል መቼም ግልጥ ነው፤ ነገር ግን የዘመናችን ኢትዮጵያ የታሪክ ጎርፍ ያመጣብን ከወያኔና መሰሎቹ በስተቀር ሌሎቻችን ያልጠበቅነው ዱብዕዳ ክስተት ምሥጋና ይንሳውና በዬቀኑ የማንሰማውና የማናየው ዕንቆቅልሽ እንዳይኖረን ሆነናል፡፡ በዚህ መልክ በተለይ ባለፉት 22.8 ዓመታት ውስጥ የታዘብነው የታሪክ ምፀትና ወኔያዊ የውሸት ስንክሳር በረጂሙ ታሪካችን ታይቶም ሆነ ተሰምቶ እንደማያውቅ ማንም ጤናማ ኅሊና ያለው ዜጋ የሚመሰክረው ይመስለኛል፡፡ ለዛሬ አንዱን የወያኔ ነጭ ውሸት እንመለከታለን፡፡

ግራና ቀኝ ጠፋን! (ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም)

ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም
በአለፉት ሃያ ዓመታት ውስጥ ወያኔ-ኢሕአዴግ የሚወቀስበት ሥራ በጣም ቢያመዝንም የሚመሰገንበት ሥራ የጽሑፍ ቁጥጥርን ማስቀረቱ ብቻ ነው፤ ሁልጊዜም አንድ ጥሩ ነገር የሚያስከትለው አብዛኛውን ጊዜ የማይጠበቅ ነገር ሊኖር ይችላል፤ ለምሳሌ አጠቃላይ ነጻነት ሲመጣ ወንጀለኛነት ይጨምራል፤ እንዲሁም የጽሑፍ ቁጥጥር ሲነሣ ጸሐፊዎች ይበዛሉ፤ ትምህርት በተስፋፈበትና ማንም እንደፈለገ ለመጻፍና ለማሳተም ችሎታውም ዕድሉም በማይገኝበት፣ ሳያበጥርና ሳይሰልቅ አሰር-ገሰሩን ጽፎ በአደባባይ የሚወጣውን ጥምብ-እርኩሱን አውጥተው ሁለተኛ እንዳይለምደው የሚያደርጉ የታወቁና የሰላ አእምሮና ብዕር ያላቸው አርታእያንና ሐያስያን (ገምጋሚዎች) ባሉበት ብዕሩን የሚያባልግ ጸሐፊ አይወጣም፤ ይህ ሁሉ ባልተሟላበት እንደኛ ባለ አገር ውስጥ ብዕርን ማባለግ እንደመብት ወይም እንደነጻነት እየታየ ነው፡፡

“ወደው አይስቁ” (ክንፉ አሰፋ)

ክንፉ አሰፋ
የጥምቀት በዓልን ተሰባስበን በምናከብርበት አንድ ቤት ውስጥ ካለወትሮው ፓልቶክ ተከፍቷል። በዚያ የበዓል ድባብ፤ የፓልቶክ ንትርክ መከፈቱ ሳይገርመን፣ ርእሱ የሁላችንንም ቀልብ መሳቡ። በእርግጥ አንድም ቁም ነገር በንግግሩ አልሰማንም። አዲሱን ቋንቋ ልዋስና የፓልቶኩ ተናጋሪዎች ሙድ  የሚያስይዙ ነበሩ። ሰዎቹ በዚህ ከቀጠሉ የእነ ክበበው ገዳን ገበያ መዝጋት እንደሚችሉ አያጠራጥርም።
የድምጽ መነጋገርያውን የያዘው ሰው ጉሮሮውን ጠራርጎ ንግግሩን እንዲህ ሲል ጀመረ።  “የምኒሊክ ወንጀል በጡት መቁረጥ ብቻ አያበቃም። …  የወንዶች ብልትም ተቆርጧል።…”

በደምና በአጥንት መስዋዕትነት ተከብሮ የቆየ የሃገራችንን ዳር ድንበር ለባዕድ አሳልፈን አንሰጥም!

ብርሃኔ አሰበ አለሁድረስ
ሀገራችን ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ሃብቷ የታደለች ፣መልካም የአየር ፀባይ ያላት፣ህዝቦቿ የራሳችን አኩሪባህልና ወግያለን፣የራሳችን መልካም መልክዓ ምድራዊና አሰፋፈር ያለን በጋራ ተሳስረን አብረን የኖርንባትና የምንኖርባት በየትኛውም ዘመን ሉአላዊነቷ ያልተደፈረ ለአፍሪካ ተምሳሌት የሆነች ሀገር ናት። በተለያየ ወቅት የተፈጥሮ ሃብቷን ለመቀራመትና ሉአላዊነቷን ለመዳፈር የሞከሩ ሃገራት ሁሉ፣በውድ ልጆቿ የተባበረ ክንድ አይቀጡ ቅጣት ተቀጥተው ኢትዮጵያን ዳግም እንዳይመኟት የተባረሩበትና የኢትዮጵያን አይበገሬነት በአፍሪካም ሆነ በአለም መድረክ ያስመሰከረች፣ አንድነቷንና ሉዓላዊነቷን ጠብቃ በማቆየት በአለም ታሪካዊ ስፍራ ያላት፣ በቀደምት ውድ ልጆቿ የደም መስዋዕትነት ሀገራችን ሉአላዊነቷ ሳይደፈር ለብዙ ሺ አመታት ቆይታለች።

“ነፃነታችንን መልሱልን!?”

ከተመስገን ደሳለኝ

የኢህአዴግ መራሹ መንግስት ‹መዝገበ ቃላት› ለነፃነት የሚሰጠው ትርጓሜ ‹አራምደዋለሁ› ከሚለው ግራ-ዘመሙ አብዮታዊ ዲሞክራሲ ብያኔ አንፃር የሚተነተን በመሆኑ፣ የየትኛውም ተቋም ነፃ ሆኖ የመንቀሳቀስ መብት ላይ ረዣዥም እጆቹን ደጋግሞ እየጫነ ሲጨፈልቅና ሲያስጨፈልቅ ለመኖሩ በርካታ ማሳዎችን ማቅረብ ይቻላል፡፡ ይሁንና ከብዙዎቹ መሀል ለጊዜው የእምነት ተቋማት የነፃነት ወሰን እስከ ምን ድረስ ነው? የሚለውን ተጠየቅ በተለይም ከሁለቱ ታላላቅ ሃይማኖቶች (ክርስትና እና እስልምና) አንፃር ተራ በተራ ከፈተሽን በኋላ ተቋማቱን ከእንዲህ አይነቱ ወደ ቅርቃር ከሚገፋ ፈተና የሚታደጋቸውን ብቸኛ የመውጫ መንገድ ለማስታወስ እሞክራለሁ፡፡
‹‹እስልምናን መቆጣጠር››

“ወደው አይስቁ” (ክንፉ አሰፋ)

ክንፉ አሰፋ
የጥምቀት በዓልን ተሰባስበን በምናከብርበት አንድ ቤት ውስጥ ካለወትሮው ፓልቶክ ተከፍቷል። በዚያ የበዓል ድባብ፤ የፓልቶክ ንትርክ መከፈቱ ሳይገርመን፣ ርእሱ የሁላችንንም ቀልብ መሳቡ። በእርግጥ አንድም ቁም ነገር በንግግሩ አልሰማንም። አዲሱን ቋንቋ ልዋስና የፓልቶኩ ተናጋሪዎች ሙድ  የሚያስይዙ ነበሩ። ሰዎቹ በዚህ ከቀጠሉ የእነ ክበበው ገዳን ገበያ መዝጋት እንደሚችሉ አያጠራጥርም።
የድምጽ መነጋገርያውን የያዘው ሰው ጉሮሮውን ጠራርጎ ንግግሩን እንዲህ ሲል ጀመረ።  “የምኒሊክ ወንጀል በጡት መቁረጥ ብቻ አያበቃም። …  የወንዶች ብልትም ተቆርጧል።…”

Thursday, January 16, 2014

ፕ/ር በየነ “የአካኪ ዘራፍ ትግል አክሳሪ ነው፤ የስሜት ፖለቲካ ያብቃ” አሉ


“ከኤርትራ ጋር መስማማት አግባብ ነው፤ ግን ፍርሃቻ አለኝ”
beyene petros



“የአካኪ ዘራፍ ፖለቲካና ከስሜት ያልጸዳ የፖለቲካ ትግል መሪውንም ሆነ አምኖ የሚመራውን ህዝብ ለድል” እንደማያበቃ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ገለጹ። ከኤርትራ ጋር ስምምነት ቢደረግ መልካም መሆኑን፣ ነገር ግን ስምምነቱ የመሪዎችና የፖለቲከኞች ሳይሆን የህዝብን ስሜት የጠበቀ ሊሆን እንደሚገባውም ጠቁመዋል።
ከጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ጋር በተለይ ቃለ ምልልስ ያደረጉት ፕ/ር በየነ “አሁን ያለው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሁኔታ ከመቼውም ጊዜ በላይ አስተዋይነት የሚፈልግ፣ ዘመናዊ የትግል ስልት የሚጠይቅ ነው” በማለት ተናግረዋል። በቃለ ምልልሳቸው ደጋግመው  “አሁን በተያዘው የአካኪ ዘራፍ መንገድ የትም አይደረስም” በማለት ምክንያታቸውን ዘርዝረዋል።

Wednesday, January 15, 2014

የአፍሪካው ልዑል የተሰኘውን መጽኃፍ በሬዲዩ ፋና መተረኩ ተቃውሞ ገጠመው

ኢሳት ዜና :- በፋና ብሮድካስት ኮርፖሬት በመተረክ ላይ ባለው በታጋይ መዝሙር ፈንቴ ተርጓሚኒት  በአቶ ዳንኤል ግዛው ጸኃፊነት የቀረበው መጽሀፍ  በአማራ ህዝብ  ላይ  ጥላቻ እንዲፈጠር እያደረገ ነው በማለት የብአዴን አባላት ተቃውመውታል።
አባላቱ በብር ሸለቆ በመካሄድ ላይ ባለው ስልጠና ላይ  እንደተናገሩት ሬዲዩ ፋና ታሪካዊ ስህተት እየፈጸመ ነው ፡፡ “የህውሃት ድብቅ አላማ እውን እየሆነ ነው” ያሉት ፤ መካከለኛ እና ታዳጊ የብአዴን አመራሮች ፤ ከደቡብ ወንድሞቻችን ጋር ታሪክን በማሳሳት እና በማጥላላት የትውልድ ጠላትነትን አስፍቶ አሁንም የህውሃት የበላይነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል የሚያደርግ ነው በማለት በጽኑ ተቃውመውታል።

Tuesday, January 14, 2014

የህዝባዊ አንድነትና ሀይል የወያኔ ህወኃት ማጥፊያ መዳኒት (ሮባ ጳዉሎስ)

ካለመታደል  ሀገራችን ዛሬም ሰላም ፍትህና ዲሞክራሲ የሰፈነባት በልማትና በእድገት ጎዳና የምትራመድ ሀገር አልሆነችም። ለዚህም በርካታ ምክንያቶች ቢኖሩም እንደ ዓቢይ ምክንያት ተደርጎ የሚቀርበው የህዝብን ይሁንታን ያገኘ፡ ህዝብን በእኩልነት የሚዳኝ፡ ህዝባዊና ዲሞክራሲያዊ የሆነ መንግሥት አለመመስረቱ፡ አገርና ህዝብ የሚተዳደሩበት ዲሞክራሲያዊ ህገ መንግሥት አለመኖሩ ነው። እስከዛሬ በተጨባጭ እንደታየው በ ኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ላይ የተፈራረቁበት ገዥዎቹ በየበኩላቸው አንዱ ከሌላው የሚለዩባቸው ባህርያት ቢኖራቸውም ሁሉንም ግን አንድ የሚያስመስሏቸው ባህርያትም አሏቸው። እነሱም ሁሉም በኃይል ሥልጣን መያዛቸው፡ አምባገነንነታቸው፡ የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ ማራመዳቸው፡ በህዝብ መካከል የጋራ መተማመንና ከበሬታን ለመፍጠር፡ ሁሉም ዘላቂ ሰላምና መረጋጋትን በሀገሪቱ ለማስፈን አለመቻላቸው ደግሞ ዛሬ ለሁሉም በግልጥ እየታየ ያለ ነው።

የአቶ ገብሩ አስራት መኪና በእሳት ነደደች (በአስራት አብርሃም)

የቀድሞው የትግራይ ክልል ፕሬዚደንት እና የዓረና ሊቀመንበር አቶ ገብሩ አስራት ከባለቤታቸው ከወ/ሮ የውብማር አስፋው ጋር በመሆን በመኪና እየሄዱ እያለ ድንገት መኪናቸው በእሳት መያያዟን የተመለከቱ ሰዎች ባደረጉላቸው ጥቆማና ርብርብ ከእሳቱ ቃጠሎ ለጥቂት መትረፋቸውን ማወቅ ተችሏል። በመኪናዋን ግን እዚያ የነበረው ሰው ሁሉ ብዙ ርብርብ ቢያደርግም ከቃጠለው ማተረፍ አልተቻለም። በእውነቱ ይህን መረጃ እንደደረሰኝ አላመንኩም ነበር፤ በመሆኑም ወዲያው ወደ አቶ ገብሩ አስራት ስልክ ደውዬ እውነት መሆኑን ማረጋገጥ ችያለሁ። ነገር ግን ይሄ አደጋ ሆን ተብሎ የተቀነባበረ የግዲያ ሙከራ ይሁን አሊያም በአጋጣሚ የተፈጠረ የእሳት ቃጠሎ ይሁን ማወቅ አልተቻለም። የአቶ ገብሩ ባለቤት ወ/ሮ የውብማር አስፋው ህወሃት ባካሄደው የትጥቅ ትግል ግንባር ቀደም ሚና ከነበራቸው ጥቂት ሴት ታጋዮች ውስጥ የሚመደቡ እና “ፊኒክስዋ ሞታም ተነሳለች፥ ያልተቋጨው የትግራይ ሴቶች ትግል” የሚለውን መፅሐፍ የፃፉ ናቸው።
ለማነኛውም ለአቶ ገብሩ አስራት እና ለባለቤታቸው ወ/ሮ የውብማር አስፋው እንኳን በህይወት አተረፋችሁ ለማለት እፈልጋለሁ።

አንዱዋለም ግንቦት ሰባት ከተባለ እኔም ግንቦት ሰባት ነኝ – ግርማ ካሳ

«በሕገ መንግስቱ የመደራጀት መብታቸው የተጠበቀላቸው ፓርቲዎችን አልከሰስንም።ፓርቲዎችን ግን ሽፋን አድርገዉ ስርዓቱን ወይንም ሕገ መንግስታዊ ስርዓቱን ለመናድ እንቀሳቀሳለን የሚሉ ኃይሎችን ግን ዛሬም ፣ ነገም ፣ ሕጉን የማስከበር ግዴታና ሃላፊነት ስላለብን ከመከሰስ አያመልጡም ማለት ነዉ።»

ኢቲቪ በቅርቡ በ«ሽብርተኝነት» ላይ፣ በቅርቡ ባቀረበዉ አሳዛኝ ዶኩሜንተሪ ላይ ፣ የፌደራል መንግስት አቃቤ ሕግ፣ አቶ ብርሃኑ ወንድማገኝ የተናገሩት ነበር።
እኝህ የሕግ ባለሞያ እየደጋገሙ ሕግን ስለማክበርና ስለ ሕገ መንግስቱ ነግረዉናል። ስለሕገ መንግስት ካነሳን አይቀር አንድ ነገር ጣል ላድርግ። የሕገ መንግስቱ አንቀጽ 29 ንኡስ አንቀጽ 4 «በመንግስት ገንዘብ የሚካሄድ ወይንም በመንግስት ቁጥጥር ሥር ያለ መገናኛ ብዙሃን የተለያዩ አስተያየቶችን ለማስተናገድ በሚያስችለው ሁኔታ እንዲመራ ይደረጋል» የሚል ድንጋጌ ያካትታል።

Friday, January 10, 2014

የኢትዮጵያ ትምህርት አደረጃጀት ጋጋታ ለዉድቀት ወይስ ለጥራት!

Baile Derseh
ምህርት ሚኒስተር በ1ኛና በ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ላይ የመማር ማስተማሩን ሂደት በጥራት ለማከናወን ይረዳል በሚል ስበብ በየግዜዉ የሚፈበረኩ የአደረጃጀት ኩልኩሌ /ጋጋታ/ በማምጣት መምህራንን፤ተማሪንና ወላጅን ከማስጨነቅ አልፎ የትምህርቱን ጥራት ከመቸዉም በላይ እየዘቀጠ እንዲሄድ አድርጓል። ለዚህ መረጃ ይሆን ዘንድ ዓለም ባንክ በዲሴበር 7/2012 በ221 ገጽ በዘጠኝ ምዕራፍ በሰጡት መግለጫ አንኳር ነገሮችን አንስተዋል። እነዚህም አንኳር ጉዳዮችን በሰፊዉ በማተት የችግሩን አሳሳቢነት በማጉላት መንግስት በአስቸኳይ ርምት መዉሰድ እንዳለበት በአንክሮ ያስጠነቀቀ ሲሆን ችግሩንም በአፈጣኝ መግታት ካልተቻለ በአገርና በህዝብ ላይ ለያመጣ የሚችለዉን ችግር በግምገማዉ አስቀምጧል።

የምንናገርበትን የመገናኛ ብዙሃን ማንም እንዲመርጥልን ወይም እንዲወስንልን አንፈቅድም!

ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ
ጥር 1 ቀን 2006 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የብሔራዊ ደህንነት መረጃ እና የፀረ ሽብር ግብረ ኃይል የጋራ ኃይል አድርጎ ራሱን የሚጠራ አካል የዜጎችንና የተቋማትን ሕገ-መንግስታዊና ዲሞክራሲያዊ መብት በመጣስ ጥፋተኝነታቸው በፍርድ ቤት ሳይወሰን ወንጀለኛ ሲያደርጋቸውና ስማቸውን ሲያጎድፍ ማየት እየተለመደ የመጣ ተደጋጋሚ ጉዳይ ሆኗል፡፡ ይህ ከላይ ከተጠቀሱት ሁለት ተቋማት ተውጣጥቶም ይሁን ተቀናጅቶ የሚሰራ አካል በተደጋጋሚ ጊዜ በሽብር ወንጀል ጠርጥሬአቸዋለሁ የሚላቸውን ሁሉ በመክሰስ ወደ እስር ቤት እንዲወርዱ እያደረገ ጉዳያቸው የፍርድ ቤት ውሳኔ ሳያገኝ እንደፈለገ በሚቆጣጠረው ወይም በሚያዘው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና ሬዲዮ ድርጅት አማካኝነት የፈለገውን ዓይነት ፍረጃና ሥም ማጥፋት ሲያካሒድባቸው ቆይቷል፡፡

Tuesday, January 7, 2014

ኦሕዴድ እና ኦነግ በጋራ የፈጸሙትን ወንጀል የሚያጋልጥ ታሪካዊ ማስረጃ...

በበደኖ አርባጉጉ አሰቦት አበምሳ እና በቀሪው የኦሮሚያ ክልል የተጨፈጨፉ ዜጎች የማን ትእዛዝ ነበር?
"ለረጅም ግዜ ኣብረን የኖርን እና የተዋለድን ስለሆን አንፈርምም :የአማራ ህዝብ አይመታም መመታት ያለበት ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጭ ነው::" ሀጅ ቃሲም (ኣርባጉጉ)

የፕ/ር ዓስራት ወልደየስ የመአሕድ ፕሬዝደንት ሰኔ 1ቀን 1984ዓ.ም ቁጥር መአሕድ /48/84 ለኢትዮጵያ የሽግግር መንግስት ተወካዮች ም/ቤት በአማራ ህዝብ ላይ የደረሰዉን ጭፍጨፋ እንዲያቆሙ የጻፉት ደብዳቤ ኦሕዴድ እን ኦነግ በጋራ የፈጸሙትን ወንጀል የሚያጋልጥ ታሪካዊ ማስረጃ ነው::

ቀጣዩ የምርጫ ቅስቀሳ ቤት ለቤት ሳይሆን በፌስቡክ!

የጋዜጠኞች ማህበራት ደቡብ ሱዳንና ሶማሊያ ቢሞክሩ ያዋጣቸዋል!
ኤልፓ ለአርጀንቲና የኤሌክትሪክ ኃይል ለምን አይሸጥም?
ባለፈው ሳምንት ሁለት እምብዛም የማላውቃቸው የአገሬ የጋዜጠኞች ማህበራት ፕሬዚዳንቶች ለአዲስ አድማስ ጋዜጣ የሰጡትን ቃለምልልስ አንብቤ እንዴት እንደኮራሁ ልገልፅላችሁ አልችልም፡፡ የኩራቴ ምንጭ ግን በጋዜጠኞች ማህበር መሪነታቸው አይደለም። እኔ የኮራሁት በሌላ ነው፡፡ ለምሳሌ የአንደኛው ማህበር ፕሬዚዳንት ማህበሩ ከተቋቋመ ጀምሮ ምን እንደሰራ ሲጠየቅ “ታሪካችን መፅሃፍ ነው፤ተነብቦ አያልቅም” ሲል የመለሰው በእጅጉ ነው ያስደመመኝ፡፡ ይኸው ሳምንት ሙሉ እኮ ንግግሩ ከልቤ አልወጣም፡፡ (አንደበተ ርቱዕ አይጥፋ አቦ!)
የሌላኛው ማህበር መሪ ደግሞ በሽብርተኝነት ተከስሶ የታሰረውን ጋዜጠኛ ውብሸትን ለማስፈታት ማህበራቸው ከመንግስት ጋር ተደራድሮ ሁሉም ነገር ሊያልቅ ሲል፣ሲፒጄ ውብሸትን የተመለከተ ሪፖርት በማውጣቱ ጥረታቸውን እንዳስተጓጎለባቸው ለአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ ገልጿል፡፡

ሕዝባዊ ብሶት – የከተማ አብዮት ? ከተመስገን ደሳለኝ !

ባለፈው ሳምንት ኢህአዴግ በከተሞች ላይ የቋጠረውን ስር የሰደደ ጥላቻ ከነመግፍኤው ጨርፈን ከተመለክተን በኋላ፤ ለዛሬ፣ ታላላቅ ግድፈቶቹ ሕዝባዊ ተቃውሞ ለመቀስቀስ ሊኖራቸው የሚችለውን አስተዋፅኦና በአደባባዩ የሚነሱትን ዋና ዋና ጥያቄዎች ለመዘርዘር፤ እንዲሁም ‹‹ማኦኢዝም›› የሚበይነውን ከገጠር የሚነሳ ብረታዊ ትግል፣ ከሰላማዊው የከተማ አብዮት አንፃር ለመፈተሽ ቀጠሮ መያዛችን ይታወሳል፡፡ እናም እንዲህ እንቀጥላለን…

የኢህአዴግ ግድፈቶች
ፈረንጅኛው ‘Achilles Heels’ በሚል ስያሜ የሚገልፃቸው እና አማርኛው ደካማ ጎኖች ብሎ የሚሰይማቸው የስርዓቱ ታላላቅ ግድፈቶች ከዕለት ዕለት ራሳቸውን ማብዛታቸው ፍፃሜው የሚተነበይ አድርገውታል፤ ይኸውም ብሔር ተኮር ጥያቄዎች አለመመለሳቸው፣ ውጤት አልባው የገጠር ፖሊሲ፣ የድህረ-ደርግ የዴሞክራሲ ሽግግሩ መክሸፍ (ከፖለቲካ፣ ከሰብዓዊ እና ሀሳብን በነፃነት ከመግለፅ አንፃር)፣ የኢኮኖሚ እድገት አለመኖር፣ ድህነት ከቀድሞውም በበረታ መልኩ መስፋፋቱ፣ የትምህርት ፖሊሲው ክስረት፣ የስራ-አጥ ቁጥር አለቅጥ ማሻቀብ፣ የራስ አስተዳደር (Self-adminstration) ሙሉ ለሙሉ አለመተግበር (ከስልጤ እስከ ቁጫ ያሉ የማንነት ጥያቄዎች መቆሚያ ማጣታቸው)፣ የመሬት ፖሊሲው የአርሶ አደሩን የነፍስ ወከፍ የይዘት መጠን ከአንድ ሄክታር ማሳነሱ፣ የከተሞች ስራ-አጥነት በወጣት ከተሜ የተማሩ ልጆች ላይ መብዛቱ፣ በልማታዊ መንግስት ትግበራ እና በብሄር ፌደራሊዝም መሀከል የማይታረቁ ቅራኔዎች መኖራቸው፣ ከተሜነት እየተስፋፋ ሲመጣ በብሔር ፖለቲካ ሞት ላይ ግለሰባዊነት እንደሚነግስና ኢህአዴግም ይህንን ተቃርኖ ተከትሎ የርዕዮተ-ዓለም መሸጋሸግ ማድረግ የማይችል መሆኑ እና መሰል ተቋማዊ ክስረቶች በቀጣይ ሊያርማቸው የማይቻለው ታላላቅ ግድፈቶች በመሆናቸው እንደተለመደው ውጤቱ ቀድሞ የሚታወቀውን የይስሙላ ምርጫ ከመጠበቅ ይልቅ የአደባባይ ተቃውሞን ለማማተር ሥረ-ምክንያት ሊሆን መቻሉ አጠራጣሪ (አከራካሪ) አይደለም፡፡

ኮካኮላ የቴዲ አፍሮ ውል እንዲሰርዝ ዘመቻ ተጀመረ

በ 2014 ብራዚል ለሚካሄደው የአለም ዋንጫ ላይ ቴዲ አፍሮ የክብር እንግዳ እንዳይሆን አዲስ ዘመቻ በእነ ጃዋር መሃመድ መጀመሩ ተሰማ።
በዓለም ዙርያ ያሉ ኢትዮጵያውያን በሳውዲ ለተፈናቀሉ ወገኖች እየተረባረቡ ባሉበት በዚህ ፈታኝ ወቅት፤ ጃዋር እና ሜንጫዎቹ ጸረ-ኢትዮጵያዊነት ዘመቻቸውን በስፋት ተያይዘውታል። በዛሬው እለት ከአዲስ አበባ በደረሰን ዜና መሰረት ኮካኮላ የቴዲ አፍሮን የአለም ስፖርት ፌዴሬሽን (ፊፋ) ስፖንሰርነት እንዲያነሳ ጠይቀዋል። አዲስ አድማ ለመጀመርም ዝግጅታቸውን አጠናቀዋል።
በ 2014 ብራዚል ለሚካሄደው የአለም እግር ኳስ ዋንጫ አፍሪካን ወክሎ እንዲገኝ ኮካኮላ ቴዲን የመረጠው መሆኑ ይታወሳል። የአለም ስፖርት ፌዴሬሽን (ፊፋ) ወጣቱ ቴዲ አፍሮ አፍሪካን እንዲወክል መምረጡ ዘረኞቹን አስቆጥቶ እንደነበር የሚታወስ ነው።

Saturday, January 4, 2014

ኢትዮጵያ የብሄራዊ እርቅ ኮሚሽን ማቋቋም የሚያስፈልጋት ጊዜ ላይ ናት

ገለታው ዘለቀ  
ባለፉት ጥቂት ተከታታይ ጽሁፎች ላይ እንደተወያየነው በስምምነት ላይ የተመሰረተ ባህላዊ ውህደት ውስጥ መግባት ኢትዮጵያን እንደገና ለማነጽ ኣማራጭ መፍትሄ ይሆናል። ታዲያ በስምምነት ላይ የተመሰረተ ባህላዊ ውህደት ላሉብን ውስብስብ ሁለንተናዊ ችግሮች ሁሉ መፍትሄ ይሆናል ማለት ሳይሆን ቅድሚያ ተሰጥቷቸው ሊፈቱ የሚገባቸውን ባህላዊ ማህበራዊ ችግሮች መስመር በማስያዝ በሂደት እየተፈቱ እንዲሄዱ ከማድረጉም በላይ ሌሎች ችግሮችን ለመፍታት ደግሞ ቀጥተኛ ያልሆነ ኣስተዋጾ ስላለው ነው።   በችግር ኣፈታት ጊዜ ከሚመጡት መፍትሄዎች መካከል የትኛውን ብናስቀድም ነው ሌላውን ችግርም ኣብሮ ሊፈታልን የሚችለው ብለንም እንጠይቃለንና በዚህ ረገድ በስምምነት ላይ የተመሰረተ ባህላዊ ውህደት ውስጥ መግባት ሌሎች መጋቢና ተለጣጣቂ ችግሮችን ለመፍታት ይጠቅማል ከሚል ነው።

በቅሎና ፈረስ እኩል ፈሰስ

አቶ ዳኛቸው ቢያድግልኝ፤ ‘ልጓም የበጠሰው የፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም የስድብ ፈረስ’ በሚል አርዕስት ፕሮፌሰሩ ባቀረቧችው ሁለት ጹሑፎች ላይ ትችታቸውን አቅርበዋል። እነርሱም አበሻና ልመና፤ አበሻና ሆድ ናቸው።
አቶ ዳኛቸው የፕሮፌሰሩን ጽሑፎች መገመገማቻው ወደ ኋላ ተመልሼ አንደንድ የፕሮፌሰሩን ሥራቸው ለመከለስ አስችሎኛል፤ በዚህ አመሰግናቸዋለሁ፤ ከትችት ትምህርት ማግኘትን ግንኙነትንም ለመፍጠር መቻሉን ፕሮፌሰሩ የሚያምኑ መሆናቸውን ከአንዳንድ ጹሑፋቸው ለመረዳት ችያለሁ፤ ስለሥራቸው እንጂ ስለግድላቸው አላትትም፤ የአቶ ዳኛቸው ሐሣብ የራሳቸው መሆኑን እቀበላለሁ፤ ግን የሣቱትን በማስረጃ ለማሳየተ እሞክራለሁ፤ ጉዳዩ ስለ አቶ ዳኛቸው ወይም ስለፕሮፌሰሩ አይደለም ሁላችንንም ስለሚመለከተን የጋራ ችግር ነው።

የአንድን ህብረተሰብ ችግር የመረዳትና መፍትሄ የመፈለግ ጉዳይ - ምክንያታዊ፣ ስሜታዊ ወይም ሳይንሳዊ መንገድ!

ከፈቃዱ በቀለ
መግቢያ፣
በመጀመሪያ ደረጃ ውድ አቶ ካሳሁን ነገዎ ታዋቂ ሰዎችን ወይም ምሁሮችን ለቃለ-መጠይቅ እያቀረበ አስተያየታቸውንና አመለካከታቸውን እንድናዳምጥና ትምህርት እንድንቀምስ የሚያደርገው ጥረት የሚያስመሰግነው ነው። በዚህም መሰረት በአ.አ በ23.12.2013 ዓ.ም ዶክተር ብርሃኑ ነጋን በቅርቡ ለዕትመትና ለንባብ ባበቃው፣ „ዲሞክራሲና ሁለንታዊ ልማት“ በተባለው መጽሀፉ ዙሪያ ምን ማለቱ እንደሆነ ለቃለ-መጠይቅ ጋብዞት አንዳንዶቻችን ለማዳመጥ ችለናል። የቃለ-መጠይቁን ምልልስ በጥሞና ላዳመጠ የዶክተር ብርሃኑ ነጋ መልስ ግልጽና ብዙም የሚያከራክር ጉዳይ አይደለም።

ወያኔ ኢትዮጵያዊ አለመሆኑን ያስመሰከረው ገና ከማለዳው ነው፡፡

Click to visit the original post
ብዙውን ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው መንግስት በዜጎቹ ላይ በሚሰራው ግፍና በደል አብዛኛው ኢትዮጵያዊ እነዚህ ሰዎች ኢትጵያዊ ናቸውን? የሚል ጥያቄ ሲያነሳ ይሰማል፡፡ እኔ ግን ለዝህ ጥያቄ ጥርት ያለ መልስ አለኝ፡፡ ኢሕአዴግ ወያኔ ኢትዮጵያዊ አይደለም፡፡ ለዚህ በርካታ ምክንየቶችን ማንሳት ይቻላል፡፡ ኢሕአዴግ ማንነት የሌለው በማንነቱ የማያምን ድርጅት ነው፡፡ ከፍተኛ አመራሩ ሟች ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ ስለኢትዮጵያዊነት ስለአንድነት ስለማንነትና ስለዜግነት በሚነሱ ጥያቄዎች ላይ መልስ ከመስጠት ይልቅ ይህን ጥያቄ የሚያነሱ ፊውዳላዊ አመለካከት ያላቸው ወይም የደርግ ኢሠፓ ርዝራዦች በማለት የከሳሉ፡፡

የአቦይ ስብሐት ከኢትዮጵያዊነት መውደቅ

(ፋክት መጽሄት)
‹‹ከኢትዮጵያዊነት መውደቅ ማለት ምን ማለት ነው? አፄ ሀይለስላሴ ከኢትዮጵያዊነት ወድቀዋል የሚል የለም፡፡ ኮሎኔል መንግስቱንም የሚል የለም፡፡ . . . ከኢትዮጵያዊነት መውደቅ ማለት፤ በቃ በአጭሩ ኢትዮጵያዊ አለመሆን ነው፡፡ ሌላ ማንነት መገንባት (IDENTITY DEVELOP) ማድረግ ነው፡፡›› ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ፣ ኢትዮ-ምህዳር፣ ቅጽ 02፣ ቁጥር 47፡፡

ሀሳብን በመግለፅ ነፃነት እጅግ አድርጌ አምናለሁ፡፡ እንዲያውም ብዙዎች ‹የዲሞክራሲ መገለጫው ነፃ-ምርጫ ነው›፣ የሚሉትን ወረድ አድርጌ፣ ‹ዋናው የዲሞክራሲ መገለጫ ሀሳብን የመግለጽ ነፃነት ነው›፣ ብዬ አምናለሁ፡፡ ነፃና ዲሞክራሲያዊ የሚባለው ምርጫ በምስጢር የሚከናወን መሆኑ ነፃ ያለመሆኑ ማስረጃ ሆኖ ይሰማኛል፡፡

አይ ስብሐት ነጋ! (ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም)

በኢትዮጵያ ውስጥ ሥልጣን ሳይኖረው ባለሙሉ ሥልጣን፣ እውቀት ሳይኖረው ባለሙሉ እውቀት የሆነ ሰው ስብሐት ነጋ ብቻ ነው፤ እንዲያውም ከዚያም አልፎ ራሱን የቻለ ሉዓላዊ ነጻነት ያለው ግለሰብ ነው ለማለት የሚቻል ይመስለኛል፤ በዚህ ግለሰብ ላይ የማደንቃቸው ሁለት ነገሮች ናቸው፤ በሉዓላዊነቱ የተጎናጸፈውን ሥልጣን ሙሉ በሙሉ ይጠቀምበታል፤ ይቆጣኛል ወይም ይቀጣኛል ብሎ የሚፈራው የለም፤ ስብሐት ነጋ የሚፈራው ምንም ነገር የለም፤ ሁለተኛ በሉዓላዊነቱ ያለውን ሙሉ ነጻነት በሙሉ ልብ ይጠቀምበታል፤ ናስ በላይ ከበደ እንዳለው ‹‹የቅብጠት መዘላበድ›› ሊሆን ይችላል፤ ስብሐት ነጋ የተናገረው ነገር ትክክል ይሁን አይሁን ጉዳዩ አይደለም፤ ዋናው ነገር መናገሩ ነው።

ኦቦ ተማም ባቲ በጀነራል ከማል ገልቹ የሚመራው ኦነግ ቃል አቀባይ ውይይቱ በተለይ ከአፄ ሚኒሊክ ታሪክ ጋር የተያያዘ

Abe Tokichaw

ኦቦ ተማም ገለቶማ!!!
ኦቦ ተማም ባቲ በጀነራል ከማል ገልቹ የሚመራው ኦነግ ቃል አቀባይ ናቸው፡፡ በአንድ ፓልቶክ ሩም ላይ ቀርበው ቃለ ምልልስ ሲያደርጉ ተከታትያቸው ነበር፡፡ በጣም አስገራሚ ሰው ሆነው አገኘኋቸው፤ እናም አክብሮቴ ካሉበት ይድረስልኝ… ገለቶማ ብያቸዋለሁ!
ውይይቱ በተለይ ከአፄ ሚኒሊክ ታሪክ ጋር የተያያዘ ነበር፡፡
አቶ ተማም ያሉት ነገር በአጭር ይጠቃለል ቢባል የሚከተለውን ይመስላል፡፡

Wednesday, January 1, 2014

***ፀረ-ኢትዮጵያ ***

ወያኔና ጀሌዎቹ በታላቋ ሀገራችን ኢትዮጽያ ላለፉት 22 ዓመታት የተንሰራፋው የዘር ጥላቻ በማስፈን ፣አገርን በመሸጥ ነፃ አውጭ ነኝ ባዩ ቡድን ጠባብ ዓላማውን ለማሳካት ፍቅርን በሰበኩ፤ አንድነትን በመከሩ፤ ስለ እኩሌነት በተናገሩ የዲሞክራሲ ታጋዮችና ሠላማዊ ዜጎች ላይ ማለቂያ የሌለው ስም በመለጠፍ በእንበለ ፍርድ በየእስር ቤቱ ያጎራቸው ዜጎች ቁጥር ለመጥቀስ እስኪያዳግት ድረስ በግፍ ላይ ግፍ በበደል ላይ በደል ከመፈጸም ሊታቀብ ይቅርና ጭራሽ እየባሰበት ከመሄድ ሊገታው የሚችል ሁኔታ ባለመፈጠሩ የጭቆና የብረት ቀንበሩን በሕዝብ ላይ በመጫን ሀገሪቱን በፍጥነት ወደ ታላቅ እስር ቤትነት ለውጧታል።

ኧረ ወገን ምንድን ነው የሚጠበቀው?

ጥፋታቸውን በመቀጠል ከኢትዮጵያ ሕዝብ በስተጀርባ በምስጢር ከሱዳን መንግሥት ጋር ውል በመፈራረም፤ ርዝመቱ 1,600 ኪ.ሜ ስፋቱ ከ30 እስከ 50 ኪ.ሜ የሚደርሰውን በምዕራብ ኢትዮጵያ ድንበር የሚገኝ ለም መሬት ሱዳን በትግል ወቅት ለሰጣቸው ድጋፍ እንደ ገፀ-በረከት ለማቅረብ ተስማሙ።

ከቴዲ አፍሮ የተሰጠ መግለጫ “ለሙዚቃ አፍቃሪዎቼ በሙሉ”

ከጥቂት ሳምንት በፊት የዳግማዊ ሚኒሊክን መቶኛ አመት የሞት መታሰቢያ ምክንያት በማድረግ በእንቁ መጽሔት ተጋብዤ ቃለ ምልልስ አድርጌአለሁኝ። ይኸዉ Ethiopian Artist Teddy Afroዉይይታችን በ “አመጣጡን ያየ አካሄዱን ያዉቃል” እርዕስ ስር ለህዝብ እንደቀረበ አዉቃለሁ።

“ነፃ እስክትወጡ በደሌ አትጠጡ” ጃዋር መሀመድ

ሁኔ አቢሲኒያዊ
መቼስ ለአገር የሠራና የደከመ ቢያጠፋም እንኳን የቻለውን ያህል በመሞከሩ በክብር ማኖርና መንከባከብ የውዴታ ግዴታ ነው። የሚያሳዘነኝ ነገር ይሄ ሳይሆን እስካሁን እንዲህ ያለውን ነገር ሰምተንና አይተን ያለማወቃችን ነው ስንት የለፉላትን አገር በእነ መለስ እንዲህ መሆኗን ሳያዩ ማለፋቸው ሳይቀር ዛሬም ድረስ ቢያንስ ስራዎቻቸው በክብር እንደቅርስ አለመያዛቸው ሳያንስ በየጊዜው የሚነሱ የታሪክ ነቃፊዎች የትችታቸው ማሟሻ አድርገዋቸው ማየት ያስዝናል ለዚህም ይመስለኛል አገሪቷ የሠራላትን፣ የደከመላትንና የተቆረቆረላትን ማዋረድ እንጂ ማክበር እንደማታውቅ የሚለፈፈው። በዚያም ተዞረ በዚህ የውዷ ኢትዮጵያ ታሪክ ‘የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ’ በመሆኑ ምንም ማለት ልናዝን አይገባም።

የወገን ጩኸቱን አናፍነው! ጩኸቱን አንቀማው!

የማለዳ ወግ
ነቢዩ ሲራክ
ሰሞኑን ጠቃሚ መረጃ የምንለዋወጥባቸው ማህበራዊ ገጾቻችን በሙግት ንትርክ ማዕበል ተውጠው ተመለከትኩ … ከእምየ ምኒሊክ እሰከ በደሌ ቢራ ፣ ከድንቁ ትንታግ ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ መግለጫ ፣ እርማት እስከተሰጠበት እንቁ መጽሔት ፣ ከታሪክ አዋቂው የሃገር ሽማግሌ ፕሮፊሰር ይስሐቅ የታሪክ ቀደምት ትንታኔ ታሪክ እስከ ማይጠቅመን የጁሃር መሃመድ ዘመቻ ሁሉም ሰሞነኛ ዝብሪት በየአይነቱ ሰማን ። ይህ ሁሉ ታዲያ በፈረንጆች አመት በዋዜማው ባይሆን ደስ ባለኝ! ይህም የእኛ ነገር ፣ የእኛ ኑሮ ነውና ምን ያደርጉታል?

በ”ዲሞክራሲና ሁለንተናዊ ልማት በኢትዮጵያ”ና በሁለት ተጨማሪ መጽሀፎች ላይ የቀረበ አጭር አስተያየት

ፋሲል የኔዓለም
በፖለቲካው ዓለም ጉልህ ስፍራ ያላቸው ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ “ዲሞክራሲና ሁለንተናዊ ልማት በኢትዮጵያ” በሚል ርዕስ የጻፉትን አዲስ መጽሃፍ ያነበብኩት ዘግይቼ ነው ፤ ለመዘግየቴ ሶስት መሰራታዊ ምክንያቶች ነበሩኝ፣ አንዱና ዋናው ዶ/ሩ በተለያዩ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን አመለካከት በመገናኛ ብዙሃን በስፋት ስላቀረቡ በመጽሀፉ ውስጥ እምብዛም አዲስ ነገር ያቀርባሉ የሚል እምነት ስላልነበረኝ ነው። ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ ዶ/ሩ ራሳቸው በከፊል የጠቀሱት ነው፣ “ በአገሪቱ ለዲሞክራሲያዊ ስርዓት የሚደረገው ትግል ውስጥ ጉልህ ሚና እየተጫወተ ያለ የተቃዋሚ ድርጅት አመራር አባል መሆኑን ሲመለከት፣ ከቅንጦትም ባሻገር በተወሰነ ደረጃ “ የስራ ፈትነት” ወይንም የበለጠ ጠርጣራ ( cynic) ለሆነ ሰው “ በተግባር ስራ ለመስራት ካለመቻል “ የመጣ፤ ተግባራዊ ድክመትን ለመሸፈን የሚደረግ ሙከራ ሊመስል ይችላል” የሚለው ነው። ሶስተኛው ምክንያቴ ደግሞ ፣ ፋሽን በሚመስል መልኩ በአገር ቤት የሚኖሩ ፖለቲከኞች በተከታታይ መጽሃፎችን በማሳተማቸው ለእነሱ ቅድሚያ ለመስጠት በመፈለግ ነው።

የጃዋር መሀመድና የአንዳንድ አጨብጫቢዎች አደገኛ መንገድ በአጭሩ

ዋቅጅራ ሶሪ
“በእናቴ መንዜና ኦርቶዶክስ ክርስቲያን ነኝ፤ በአባቴ የአርሲ ኦሮሞ እና ሙስሊም ነኝ፤ ከኔ ወዲያ ለኢትዮጵያዊነት ምልክት ሊሆን የሚችል የለም” ጃዋር ይህን ያለው ከዓመት በፊት ወጣቱ ተንታኝ እየተባለ በኢሳት  በተደጋጋሚ ይቀርብ የነበረ ሰሞን ነው።Jawar Mohamed Muslim fundamentalist
የተመቼው እና ፖለቲካዊ ንግዱ የደራለት  ሲመስለው ከኢትዮጵያውያን ጋር ተመሣስሎና አድፍጦ የቆየው ጃዋር  መሀመድ ፤በግብጽ የመንግስት ለውጥ መደረጉን ተከትሎ የሙርሲ ባለስልጣናት በአባይ ግድብ ያደረባቸውን ንዴት በግልጽ በቴሌቪዥን  ተሰባስበው እየፎከሩ በኢትዮጵያ ላይ እርምጃ ለመውሰድ ሲዝ ቱ  ሰማ። የሙርሲ ባለስልጣናት  ከሰነዘሯቸው አማራጮች አንዱ፦” የኦሮሞ ነፃነት ግንባርን የሙስሊም ክንፍ ወይም ኦብነግን ማስታጠቅና መርዳት” የሚል መሆኑን የሰማው ጃዋር ሳይውል ሳያድር በአልጀዚራ ላይ ቀርቦ በግልጽ “ኦሮሞ ፈርስት” በማለት የኢትዮጵያዊነት ቆቡን አሽቀንጥሮ ጣለ። ሜንጫው ተከተለ፤የሙስሊሞችን የመብት ትግል ከኦነግ ጋር እያገናኘ ተናገረ፣ ኢትዮጵያውያን ከኦሮሚያ ይውጡ! እያለ መፈክር ሲያሰማ ተደመጠ…

ቴዲ አፍሮና የቢራው ፖለቲካ

ክንፉ አሰፋ
Teddy Afro in collaboration with Heineken Beer/Bedele will kick off his national concert tour.
በጋዜጠኛ ስህተት የወጣች አንዲት ጽሁፍ ምክንያት 18 ሺህ ፊርማ በኢንተርኔት መሰበሰቡን ሰማን። ጽሁፉን ያሳተመው መጽሄት ስህተቱን አረመ። ይቅርታም ጠየቀ። ዘመቻው ግን እንደቀጠለ ነው። ቴዲ አፍሮ ይንን እንዳልተናገረ መግለጫ ቢሰጥም ጉዳዩ እልባት ሊያገኝ አልቻለም። ከቶውንም አንድነታችንን የማይፈልጉ ምእራባውያን ጭምር ይህችን ምክንያት በመያዝ ጉዳዩን ማረገብ ጀመሩ። አንድ የዳች ጋዜጣ አጼ ምኒሊክን ከሂትለር ጋር አመሳስሎ በመጻፍ ጋዜጣውን በዚህ ሳምንት አሰራጭቷል! ያለ አንዳች መረጃ። “ለነጮች እጄን አልሰጥም!” ብሎ አድዋ ላይ ስላዋረዳቸው ምኒሊክን ለማንቋሸሽ ምንም መረጃ አያስፈልጋቸውም።

ስለ ዳግማዊ ምንሊክ የ” ኒዎርክ ታይምስ ” ጋዜጣ (ኅዳር 7/1909 ዓም እ ኤ አቆጣጠር) የዛሬ 96 አመት የፃፈው ፅሁፍ ለአሁኑ ትውልድ ታሪካዊ ማስረጃ ነው

09
ዳግማዊ አፄ ምንሊክ ፎቶ
ኢትዮጵያ በየዘመኗ በሕልውናዋ ላይ የተቃጣባት የመበታተን አደጋን ያለፈችበት መንገድ የጦርነት መንገድ ብቻ አይደለም።ሆኖም ግን ከነበሩን የግጭት ታሪኮች በዘለለ በሕዝብ ዘንድ ተወዳጅ የነበሩ እና በሕዝብ ዘንድም የተወደዱ መሪዎች ነበሩን።ከእነኝህ ውስጥ ዳግማዊ ምንሊክ አንዱ ነበሩ። አፄ ምንሊክ ሀገር የማስተዳደር ጥበብን የተማሩት በአፄ ቴዎድሮስ እጅ ሆነው እድገታቸውን በንጉሡ ቤተመንግስት ማድረግ ከጀመሩበት ጊዜ ጀምሮ መሆኑን ብዙዎች ይስማማሉ።ንጉሡ የቀደሙ አባቶቻቸው አፄ ቴዎድሮስ እና አፄ ዮሐንስ ኢትዮጵያን አንድ የማድረግ አላማቸው እውን እንዲሆን ያደረጉ እድለኛ ንጉስም ናቸው።