Friday, December 26, 2014

ለሥልጣን ለውጥ ወይስ

ይድነቃቸው ከበደ
ይህን ለማለት የሚያስደፍረው በአገራችን የሚካሄደው ምርጫ፣ የፖለቲካ ወይም የዲሞክራሲ ቅንጦት ሣይሆን፣ የአገር እና የዜጎች የእልውና ጉዳይ መሆኑ የሚያረጋገጥ የበዛ ምክንያት በመኖሩ ነው፡፡
----------------------
የትኛውም የፖለቲካ ፓርቲ እራሱን ለምርጫ በማቅረብ ያወዳድራል፤በምርጫም ካሻነፈ የመንግሥትነትን ሥልጣን ይይዛል፡፡በምርጫ ዕድል ካልቀናው የተቃዋሚውን ቦታ ይዞ መንግስት ለሚያቀርበው ፓሊስ እና ፕሮግራም ነቀፌታ ወይም አማራጭ አሳብ በማቅረብ የተለመደው የፖለቲካ ሥራ ይሰራል፡፡ እንዲህ አይነቱ የፓርቲዎች አደረጃጀት እና አሰራር በሰፊው የተለመደ ጤናማ አካሄድ ነው፡፡የፖለቲካ ሊቃውንት ከላይ የተገለፀውን አካሄድ ጤናማ ነው ሲሉ፣ዋንኛ መመዘኛቸው ያልተንዛዛ በዛ ቢባል ፣ከሁለት ዙር ያለፈ የስልጣን ዘመን እንደማይኖር ታሳቢ በማድረግ ነው፡፡በተለይ እንዲህ አይንቱ የፓርቲዎች እንቅስቃሴ ፣በከፍተኛ ዲሲፕሊን እና በተቀናጀ የሙሉ ጊዜ የፓርቲ ስራ ላይ በሚያሳልፉ ታጋዮች የሚከናወን ጥበባዊ ስራ ነው፡፡

Wednesday, December 24, 2014

የብአዴን ካድሬዎች የአዲስ አበባ ስብሰባ ካለመስማማት ተበተነ: – ‪ምንሊክ ሳልሳዊ‬

ካድሬዎቹ በባህር ዳር የተደረገውን ግድያ በንጹሃን ዜጎች ላይ የተፈጸመ ነው ሲሉ ተናግረዋል::
- ባለፈው አርብ በባህር ዳር ሰላማዊ የሆነ ጥያቄ ይዘው አደባባይ በወጡት ንጹሃን ዜጎች ዙሪያ እና በመጭው ምርጫ ዙሪያ በአዲስ አበባ ብአዴን ካድሬዎቹን በመሰብሰብ ያደረገው ውይይት ክለመስማማት መበተኑን ለምንሊክ ሳልሳዊ የውስጥ አዋቂ ምንጮች ገልጸዋል::
እንደ ምንጮቹ ዘገባ ከሆነ ካድሬዎቹ ሕዝብን ማሳመን የማንችልበት ደረጃ ላይ ደርሰናል::ንጹሃን በአደባባይ መግደል የፖለቲካ ትርፉ ምንድነው የሚሉ እና በባህር ዳር የተደረገው ድርጊት በመጭው ምርጫ ላይ ከባድ ተጽእኖ ያጠላበታል ሲሉ አስተያየታቸን እና ጥያቄዎቻቸውን ሰንዝረዋል::

በሕዝብ ላይ የሚካሄደውን ቀጣይ ጭፍጨፋ ለማስቆም በጋራ እንነሳ! (ሸንጎ)

የሚሊዮኖች ድምፅ የመጀመሪያው ሰላማዊ ሰልፍ በባህርዳር በቅርቡ ይደረጋል!

ገዢው ፓርቲ ሕወሃት/ኢሕአዴግ የእምነት ነጻነትን በመጋፋት ፣ ታቦት ቢወጣበትና የጥቅምት በዓል በሚከበርበት በባህር ዳር የመስቀል አደባባይ “ልማት” በሚል ስም ለባለሃብቶች ቦታዎች ሊሰጥ ማሰቡን ተከትሎ ሕዝቡ ለአስተዳደሩ ብሶቱን በደብዳቤ ለማስገባት፣ በቦታው ሄዱ ለማነጋገር ቢሞክር፣ ለሕዝብ ጥያቄ ደንታ የሌላቸው የሕወሃት/ኢሕአዴግ ባለስልጣናት፣ ቦታውን ለባላሃብቶች ለመስጠት በመወሰናቸው፣ ሕዝቡ የእምነት ነጻነቱን ለማስከበር ባለስልጣናት ዉሳኔያቸዉን እንዲቀለብሱ ለማድረግ፣ በራሱ አነሳሽነት ፣ በሺሆች በመሆን ሰለፍ መዉጣቱ ይታወቃል።

የቆምጬ አምባው ጨዋታዎች (አፈንዲ ሙተቂ)

ጓድ ቆምጬ አምባው በስማቸው የሚነገሩትን ጨዋታዎች በኔ ስም የተፈጠሩ ተረቶች ይሏቸዋል፡፡ ሰውዬውን በቅርበት የሚያውቁት ግን በርሳቸው ስም የተፈጠሩት ጨዋታዎች ከፊል እውነታ እንዳለባቸው ይናገራሉ፡፡ በርካታ ሰዎች ጨዋታዎቹን እያወሱ የሰውዬውን ጅልነት ሊያሳዩ እንደሚፈልጉ ይታወቃል፡፡ ሆኖም ቆምጬ አምባው ነገር የገባቸው ብልጥ ነበሩ እንጂ በጭራሽ ጅል አይደሉም፡፡ ይህንን ለማሳየት እንዲቻለንም በርሳቸው ስም ከሚነገሩት ጨዋታዎች መካከል ጥቂቶቹን እንጽፍላችኋለን፡፡
*****
በደርግ ዘመን የመሰረት ትምህርት ፕሮግራም ተጀምሮ ነበር፡፡ ያ ፕሮግራም በግዴታ የሚከናወን በመሆኑ አብዛኛው ሰው ሰበብ እየፈጠረ ከትምህርቱ ይጠፋ ነበር፡፡ ይህንን የተመለከቱት ቆምጬ አምባው በወረዳው ላይ አንድ አዋጅ አሳወጁ፤ “መሰረተ ትምህርት የማይማር ቡዳ ነው” የሚል፡፡፡ በመሆኑም የሀገሬው ህዝብ “ቡዳ ነው” ላለመባል ትምህርቱን ቀጥ ብሎ መማር ጀመረ፡፡

ለመኢአዶች ያለኝ መልእክት – ግርማ ካሳ

መኢአድ (የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት) አንጋፋ ድርጅት ነው። ከመስራቹ ከፕሮፌሰር አስራት ጀመሮ የዚህ ድርጅት አባላትና ደጋፊዎች እጅግ ብዙ ዋጋ ከፍለዋል። ብዙዎች ሞተዋል፤ ብዙዎች ታስረዋል። ከማንም ድርጅት ባልተናነሳ ገዢው ሙሸት አማረ በሚመራዉና በአቶ አበባው በሚመራው ቡድን መካከል ያሉ ልዩነቶች በአሁኑ ወቅት መኢአድ ትንች በተጠናከረ መልኩ ወደፊት እንዳይሄድ አድርጎታል።

የነዚህ ሁለት ቡድኖች ዉዝግብ ገና አልተፈታም። ሕጋዊዉ የመኢአድ አመራር የቱ እንደሆነ ገና አልታወቀም። ምርጫ ቦርድ ያሉ መረጃዎችን መርምሮ ዉሳኔ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል። አንዳንድ ምንጮች እንደሚጠቁሙት ምርጫ ቦርድ ለአቶ አበባው መሐሪ እውቅና ሳይሰጥ እንደማይቀር ነው። ይህ ከሆነ የነ አቶ ማሙሸት ቡድን ምንድን ነው የሚሰማው የሚል ጥያቄ ብዙዎች ሊያነሱ ይችሉ ይሆናል።

ለሰብአዊነት ቅድሚያ የሰጠ ኢትዮጵያዊ! አብርሃ ደስታ – ከፍኖተ-ነፃነት

ትግራይ ክልል ላይ የሚፈፀሙትን ጭቆናዎች ሳይታክት አጋልጧል። ዘረኝነትን ፣ አምባገነንነትን ፣ ሙሰኝነትን ፣ ኢ-ፍትሐዊነትን አውግዟል። ሰብአዊነትን በማስቀደም ሰውን በሰውነቱ የሚለካ ምርጥ ኢትዮጵያዊ ነው-አብርሃ ደስታ፡፡ አብርሃ ፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ የብዙ ሰዎችን ቀልብ ለመሳብ ከመቻሉም በላይ ፤ “ፌስቡክን” ከፌዝ-ቡክነት በመታደግ የተለያዩ ጠቃሚ መረጃዎችን ሲያቀብለን ነበር፡፡
በመግቢያችን ላይ በአጭሩ እንደተገለጸው ይህ ድንቅ ኢትዮጵያዊ ፣ የአሁኑ የፖለቲካ እስረኛ አብርሃ ደስታ በአንድ ወቅት ከፍኖተ-ነፃነት ባልደረባ ጋር ያደረገው ወግ እንደሚከተለው ቀርቧል፡-
በቀዳሚነት የቀረበለት ጥያቄ “በመጪው ምርጫ ተቃዋሚዎች የሚያሸንፉ ይመስልሀል? የሚል ነበር፡፡ የሠጠው ምላሽ
“በተቃውሞ ጎራ ውስጥ ያሉ ሀቀኛ ተቃዋሚዎች ምርጫን እንደ ግብ ማየት የለባቸውም፡፡ በምርጫ መሳተፍን እንደ መንገድ (means) እንጂ እንደ ውጤት (end) ሊወስዱት አይገባም፡፡ በምርጫ መሳተፍን የሚቀበሉ የምርጫ ፓርቲዎች የተናጠል ጉዞ የትም እንደማያደርስ ተገንዝበው አንድ ላይ መስራት ይጠበቅባቸዋል፡፡

Tuesday, December 23, 2014

የሄሊኮፕተሩ ጉዳይ! *****

እኔ ወንድማችሁ ማነፍነፍ እወዳለሁኝ  በሳሙኤል ግደይ አስተባባሪነት ተጠለፈ የሚባል ዜና ከጅምሩ ለወሬውም አልተመቸኝ። እስኪ ትንሽ ልታገስ ብዬ ቆይቻለሁኝ። አሁን ግን አንድ ፍንጭ አግኝቼያለሁ።
ለወትሮ እንዲህ ኣይነት ነገር ሲከሰት ወያኔ የውሸት መግለጫ ነው የምታወጣው። የቴክኒክ ችግር፡ ነዳጅ ምናምን። ይህን በተደጋጋሚ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነ ችግር ሲገጥመው ታዝበናል። ለምሳሌ ሃይለመድህን ጠለፈ የተባለ ጊዜ የተሰጠውን መግለጫ አስታውሱ። በ2010 እኤአ በሊባኖስ ያጋጠመውንና እስከ መጨረሻ ድረስ ይሰጥ የነበረውን የውሸት ምክንያት ልብ በሉ።

ይድረስ ለግንቦት ከየካቲት – ደራሲ ዶ/ር ነገደ ጎበዜ ትችት አብርሃም በየነ

የካቲትን ደራሽ፤ ግንቦትን ደግሞ ተደራሽ አድርጎ በትርክቱ ፍሰት እንደ ወራጅ ውሃ አንባቢውን ይዞ የሚነጉደውን የዶ/ር ነገደ ጎበዜን የሃሳብ ሙላት የዋኘሁት በሁለት መልኩ ነበር። በታሪክ “መረጃነቱና” በስነ-ጽሁፍ ውበቱ። ትርክቱ እንደ ውሃ ሙላት እያሳሳቀ ይዞ ስለሚነጉድ ቆም ብሎ የድርጊቶችን ጊዜና ቦታ የትና መቼ? እንዴትና በማን? ብሎ ኩነቶችን ለማስታወስ አንባቢውን ፋታ ስለሚነሳ ዐይንና ገጽ ሳይነጣጠሉ እንዲተሙ  ትንታኔው የማስገደድ ባህሪይ አለው። ድርሰቱ ሶስት ዓይነት ትውልድ አንባቢ ያለው መሰለኝ። የመጀመሪያው ትውልድ የደራሲው ጓደ- ዘመን ትውልድ ሲሆን ሁለተኛውና ሶስተኛው ደግሞ የየካቲቱና የድህረ-የካቲቱ ትውልዶች ናቸው። አዲሱ ትውልድ በትርክቱ መሳሂብ ተውጦ ከጫፍ እስከ ጫፍ ያለማቋረጥ በንባቡ ሊነጉድ ይችላል። ለየካቲቱ የታሪክ ኩነቶች ባዕዳ ስለሆነ ዕውነቱንና ውሸቱን ለመለየት መቼ? የት? ለምን? በማንና እንዴት? የሚሉ ጥያቄዎችን እንዲያነሳ አይጠበቅበትም። ቀዳሚዎቹ ሁለቱ  ትውልዶች ግን የመጀመሪያን ክፍል አንብበው ከየካቲቱ ትርክት ላይ ሲደርሱ የኩነቶቹን ይዘትና ዕውነታ ከጊዜና ቦታ ጋር እያገናዘቡ መቼ? ለምን? እንዴትና በማን? ማለታቸው አይቀርም።

በፍቅር ልንወድቅ የሚገባ ከማሸነፍ ወይስ ከትግል አይነት። (ዳዊት ዳባ)

ዳዊት ዳባ
አምርረህ ልትታገልበት የሚገባ በቂ ምክንያት ካለ አላማው አንድና አንድ “ማሸነፍ” የሆነ ትግል እንጂ የትግል አይነት የሚባል ነገር የለም። አዎ ያለው ትግል ነው። ቢቸግር ነው እንጂ ችግሩ “አይነት” የሚለው ቃል ችግር ሆኖ አይደለም። ትግሉ ላይ ሲሆን አጠቃቀማችንና አረዳዳችን ግን በጣሙኑ  ግራ ያጋባል።  “ምግብ” ለሚለው ያጋራ መገለጫ ስር ጨጨብሳ፤ ሙዝ ፤ ወተት የመሳሰሉ ምግቦች እንዳሉ ለማሳያት  ሳይሆን   የጣሳ፤ ፅጌሬዳንና የሚዳቋን ዝምድና ለማሳያት መከራ የምናይበት እየመሰለ ነው።
ቂጣ መጋገርያ የስንዴ ድቄት ብቻ ላለው ሰው ዱቄቱ ግሉቶን የሚባል የሚያወፍር ንጥረ ነገር ስላለው አትብላ ተርበህ ሙት ተብሎ አይመከርም። እንዲሁ ወርጅብኝ እየወረደበትና  ለመረረው ህዘብ በዚህ ወይ ባዛ ብቻ ካልታገልክ ብሎ መጨቅጨቅ ግብዝነት ነው።

ኢትዮጵያ የማን አገር ናት ?፦ (አንተነህ ገብርየ)

በለው ግንባሩን በዚያው ይመለስ፤
አይቀርምና ተሰርቶ መፍረስ!! (አንተነህ ገብርየ)
ኢትዮጵያ ኢትዮጵያዊ ዘር ላለን የሁላችንም አገር ናት።የዘረኝነት ልክፍት እያጦዘው ያለው ህወሃት ወደ ሥልጣን ብቅ ካለ በኋላ ግን ኢትዮጵያ የህወሃት ባለሥልጣናት፤አባላትና የኮር አባላት እንዲሁም የሆዳሞችና አድር ባዮች ብቻ እንድትሆን ለማድረግ ከፍተኛ ሴራ ተሸረበ ዛሬም እየተሸረበ ይገኛል።ይህ የጥፋት ተላላኪ ድርጅት ወደ ሥልጣን ከመምጣቱ በፊት ደርግ ሳይወድቅ ኢትዮጵያ ከየት ወደ የት? በሚል ርእስ አንድ መጣጥፍ አቅርቦ ለህወሃት/ኢህአዲግ የወደፊት ሥጋቶች የሚሆኑት ሻእብያና ኦነግ እንደሆኑ ደስኩሮ ነበር። ደርግ በወደቀ ማግስት ግን ዱላውን ማሳረፍ የተፈለገው በአማራው ነገድ ሕዝብ ላይ ሆነ።ህወሃት ከሻእብያም ሆነ ከኦነግ ጋር የምር ጠብ አለው የሚባለው ለማስመሰል እንጅ ውስጡን ለሚያውቅ ገልጽ ወዳጃሞች መሆናቸው ይታወቃል።ምክንያቱም የሥልጣን ሽኩቻው እንጅ በሌላው የዓላማ ጉዳይ አንድ የሚያደርጋቸው መነሻ በመኖሩ ነው።

[የባህርዳሩ ግድያ ጉዳይ] አባቶች፣ ማኅበረ ቅዱሳንና በሃገር ቤቱ ሲኖዶስ ስር ገብተን እንታገላለን ያላችሁ የታላችሁ?

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን።
ዘደብረጊዮርጊስ
ቤተክርስቲያንን ትጠብቋት ዘንድ የተሾማችሁ ሆይ፤ ለቤተክርስቲያን ከእኛ ወዲያ ላሳር ያላችሁ ማኅበረ ቅዱሳን ሆይ፤ ውስጥ ገብተን እንታገላለን ያላችሁ ሰላምና አንድነት አደፍራሾች ሆይ ወዴት አላችሁ ???
bahrdar 7
ሰሞኑን በባሕር ዳር ከተማ የቤተክርስቲያን ታላላቅ በአላት ከሆኑትና ኃይማኖታዊ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያዊነት ባሕልም የሚገለጽበትን የጥምቀት በአል የሚከበረበትን ቦታ ለልማት ይፈለጋል በሚል በንጹሃን ወገኖቻችን ላይ የተፈጸመው ጭፍጨፋ እጅጉን አሳዝኖናል አስቆጭቶናል።
ቤተክርስቲያንን ለማዳከምና ለማጥፋት የተነሳው በስልጣን ላይ ያለው ኃይል በልማት ስም በተደጋጋሚ የቤተክርስቲያንን መብትና ይዞታ ሲደፍር ሁሌም የሚገርመኝ አባቶች ተብለው ቤተክርስቲያንን እንዲጠብቁ የተሾሙት ሰዎች ዝምታ ነው። እነኝህ አባቶች በዛ ደረጃና ሥልጣን የሚሾሙት ቅዳሴ እንዲቀድሱ እና ስብከት እየተዘዋወሩ እንዲሰብኩ አይደለም። ለዛ አገልግሎት የቅስና ማዕረ ብቻ ይበቃዋል።

Hiber Radio: የባህርዳሩ ጉዳይ ልዩ ዘገባና ቃለምልልስ… የአንዳርጋቸው ባለቤት አቤቱታ… በሃረር ቤተክርስቲያን ሊፈርስ መሆኑ… ሌሎችም

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ
ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

የህብር ሬዲዮ ታህሳስ 12 ቀን 2007 ፕሮግራም

< ... የባህር ዳር ሕዝብ ለረጅም ዘመን ሲገለገልበት የነበረው የመስቀል አደባባይ መደፈር ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ ተማሯል አጋጣሚውን ተጠቅሞ ሆ ብሎ ወጥቷል የጭካኔ እርምጃው አስገራሚ ነበር ...በየትኛውም ታሪክ ሕዝብ ተሸንፎ አያውቅም በመሳሪያ እየረገጡ በዚህ መንገድ መቀጠል አይቻልም...>
ወጣት ተስፋሁን ዓለምነህ የመኢአድ የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ በባህርዳር የደረሰውን ተቃውሞ በስፍራው እና የአገዛዙን በንጹሃን ላይ የተሰነዘረ ጥቃት በተመለከተ የዐይን እማኝነቱን ከህብር ሬዲዮ ጋር በደረገው ቃለ ምልልስ ገልጿል (ሙሉውን ያዳምጡ)
<...ኢህአዴግ የሕዝብ ታዛቢዎች በሚል የራሱን ሰዎች አስመርጧል። ምርጫው ከወዲሁ ምን ሊሆን እንደሚችል በግልጽ ያሳየ ነው ...> የህዝብ ታዛቢዎች ምርጫን የታዘቡ የሰማያዊ፣የአንድነት ወጣቶች ይናገራሉ

አሁን የተጀመረው ትብብር በአጭር ግዜ የሚከስም ሳይሆን ግቡን ውህደት አድርጎ መንቀሳቀስ የሚፈልግ ከሆነ አንድነትም …

አቶ በላይ ፍቃዱ የአንድነት ፓርቲ ፕሬዘዳንት
አንድነት ትብብሩ ውስጥ የሚገባ ከሆነ በየደረጃው ክፍለ ሀገር ያለው መዋቅር አዲስ አበባ ያለው መዋቅር እስከላይ አመራር ድረስ ያለው መዋቅር ከሰማያዊ መዋቅር ጋር መዋሀድ አለበት ብለን ነው የምናምነው፡፡ስለዚህ እኔ ባህርዳር ሄጄ የአንድነት መዋቅር ፤የመኢአድ መዋቅር ወይም የአንድነት መዋቅር የሚባል አይደለም የሚያስፈልገው አንድ ወጥ መዋቅር ነው የሚያስፈልገው፡፡በዚህ አግባብ ከተስማማን ትብብሩን አንድነት ጆይን አድርጎት ለተሻለ ውጤት እንሰራለን፡፡አሁን የተጀመረው ትብብር በአጭር ግዜ የሚከስም ሳይሆን ግቡን ውህደት አድርጎ መንቀሳቀስ የሚፈልግ ከሆነ አንድነትም ተቀላቅሎ የተሸለ ስራ ይሰራል ብለን ነው የምናምነው፡፡

የህዝብ ታዛቢ ሆነው ከተመረጡት ውስጥ አብዛኞቹ የኢህአዴግ አባላት መሆናቸው ተገለጸ

ታህሳስ 12 ቀን 2007 ዓ.ም በተካሄደው የህዝብ ታዛቢ ምርጫ አመራረጥ ሂደት ላይ የገዢው ፓርቲ አባላት በብዛት መመረጣቸውን የምርጫው ተሳታፊዎች ለሚሊዮኖች ድምፅ ገለፁ፡፡
2007 election
የምርጫ ታዛቢዎችን በማስመረጥ ሂደት ውስጥ በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች የሚኖሩ የሚሊዮኖች ድምፅ ያነጋገረቻቸው የምርጫው ተሳታፊዎች እንደገለፁት አስመራጮችም ሆነ ተመራጮች የቀበሌ አስተዳዳሪዎች መሆናቸውን ፣ የህዝብ ታዛቢዎች ምርጫ ምንም ትኩረት እንዳልተሰጠው እና ለመራጩ ህዝብ በመገናኛ ብዙሃናት በቂ ጥሪ ያልተደረገለት መሆኑን ፣ ህዝቡ ስለምርጫው ምንም መረጃ ያልነበረው እንደሆነ ፣ የምርጫ ቦታዎችን ለማወቅ ነዋሪው ህዝብ እንደተቸገረና የምርጫ ቦታዎች እንዳይታወቁ መደረጉን ፣ የመስተዳድሩ ሀላፊዎችና የካቢኔ አባላት መድረኩን በመምራት ያሻቸውን ሲሰሩ እንደነበሩ የገለጹ ሲሆን በሁሉም ቦታዎች በቂ የምርጫ ተወካዮች አለመኖራቸውን አስረድተዋል፡፡ አዳራሾቹም በገዢው ፓርቲ መፈክሮች መሞላታቸውን ከእነዚህም ውስጥ ከመሪ ድርጅታችን ኢህአዴግ ጋር ለዘላቂ ልማት ወደፊት! የሚል እንደሚገኝበት አስታውቀዋል፡፡

የሕወሓት አስተዳደር የአስመራው መንግስት ሄሊኮፕተሩን በሱዳን በኩል እንዲመልስለት መጠየቁ ተሰማ

(ምንሊክ ሳልሳዊ) ስርአቱን ከዱ የተባሉት አብራሪዎች ከድሬዳዋ ተነስተው በጅቡቲ ድንበር አስታከው በአሰብ ዘልቀው ኤርትራ ያሳረፉት ሄሊኮፕተር በሱዳን በኩል እንዲመለስለት ሻእቢያን መጠየቁን የሱዳን ዲፕሎማቶች ጠቆሙ::
captured-ethiopian-mi-24-by-eritrea
ወያኔ በኢትዮጵያውያን ላይ የሚያደርገውን ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት እና በአየር ሃይሉ ውስጥ የሚፈጸመውን ደባ በመቃወም ከድተዋል የተባሉት 2 ፓይለቶች(ካፒቴን ሳሙኤል እና ቢሊሊኝ )እና አንድ ቴክኒሽያን(ጸጋ ብርሃን)ለኤርትራ መንግስት እጃቸውን የሰጡ ሲሆን ይህንንም የወያኔው ቴሌቭዥን ጣቢያ እማኝነቱን ሰቷል::

Monday, December 22, 2014

የእምዬ ሚኒሊክ ታሪክና የኛ ፖለቲካ፡- ዛሬ ከትላንት ሲደድብ

(Zeryihun Kassa)
የሰሞኑን በሚኒሊክ ጉዳይ የያዝነውን የማህበራዊ ሚድያ አተካራ ላየ ከታሪክ የሚማሩ ሳይሆን በታሪክ የሚባሉ ብንባል ሳይሻል አይቀርም። በትላንት ተባላን። ትላንትናን እንደነበረ መረዳት ተሳነን። ትላንትናን ከደማችን ተነስተን ሳይሆን በመረጃ ደርጅተን መቃኘት ቋቅ እያለን ነው። ትላንትና ግን አደለም ዋናው ችግር። ዋናው ችግር ትላንትናን መረዳት እና ለነገ ፋይዳ ባለው ሚዛናዊ አቋም ላይ መገኘት ያልቻለው ዛሬያችን ነው።
ሚኒሊክ በደቡቡ የሀገራችን ክፍል ኦሮምያንና ወላይታን ጨምሮ ጦርነት ማድረጋቸውን ታሪክ መዝግቦታል። እኛም በተጣመመም ይሁን በቀና መንገድ ያን ታሪክ ተምረነዋል። በቁምነገሩ ሚኒሊክ ጦርነት አድርገዋል። ጦርነት ደግሞ ክቡር ነፍስ ይነጥቃል። ሽንፈቱ አዋራጅ ሆኖ፤ ሞቱ ደግሞ ቁጭት ትቶ ሊያልፍ ይችላል። ጦርነቱ አሰቃቂ እንደነበር ይነገራል። እውነትነቱ መጠርጠር የለበትም። ይህን መካድ ነው ነውረኛ የሚሆነው።

“የድሆች መናጢነት የሚመጣው ሰነፍ ስለሆኑ አይደለም” አዳም ረታ (መብትን መጠየቅ በረብሻ ሃራራ የማደግ ውጤት አይደለም)

adam reta

“. . . ፖለቲካ ለሀገር ማሰብ ነው፡፡ ፖለቲካ መታደል ከተጨመረበት ለአገርና ውስጥዋ ለሚኖረው ለሕዝብ መልካም ለመስራት መጣር ነው፡፡ ከራስ በላይ ነፋስ በሚባለው ነገር አላምንም፡፡ ከራስ በላይ ቤተሰብ፣ ዘመድ፣ ሰፈር፣ ወረዳ፣ አውራጃ ክፍለሀገርና አገር አሉ፡፡ የቻለበትም አህጉርና አለምን በልቦናው ይከታል፡፡
“የአገራችን አንድ የሚታይ ማንም የሚያወራበት ፀባይዋ በደሃና በተራራ የተሞላች መሆኗ ነው፡፡ አንድ ሰው በሀገሩ ደሃ መሆን የለበትም:: ቢያንስ መሰረታዊ ፍላጎቶቹና መብቶቹ መጠበቅ አለባቸው፡፡ የድሆች መናጢነት የሚመጣው ሰነፍ ስለሆኑ አይደለም፡፡ የለፉበት ውጤት በጥቂት ማንአለብኝ ባዮች ስለሚዘረፍ ነው፡፡

አገሬ! (ብሌን ከበደ)

poor
የኔነት መለያ ~ የናት ያባቴ አገር ~ የተወለድኩባት፣
ስረ መሰረቴ ~ ቅርንጫፍ ሀረጌ ~ እትብቴ ያለባት፣
ተስፋዬ : ውጥነኔ ~ ህልሜ ሚፈታባት፣
ሀገሬ የኔ ናት~ ፣
ሀገሬ እርስቴ ናት~።
አፈሩን ፈጭቼ ፣
ውሀ ተራጥቼ ፣
ዘልዬ ቦርቄ ~ ያደኩበት መንደር ፣
በሀሳብ በርሬ ~ በምናብ ከንፌ~ የማርፍባት ሰፈር ፣
የማንነቴ ምንጭ ~ መመኪያ አገሬ፣
አድባሬ አውጋሬ ፣
የዘወትር ህልሜ ~ የድካሜ እፎይታ ~ ማረፊያዬ ጎጆዬ፣
የትም የትም ዞሬ ~ ማሳረጊያ ቤቴ ~ አንገት ማስገቢያዬ፣
አገሬ እማማዬ ።

Sunday, December 21, 2014

***ድመት አይጥ እንዲይዝ ተብሎ ችቦ አይበራለትም! ስለዚህ ጽንፈኞች ኢትዮጵያን አታዋርዱ!***

ጽንፈኝነት ኢትዮጵያ ከምትታወቅባቸው ከፍተኛ የሞራልና የሥነ ምግባር እሴቶች መርህ ጋር በእጅጉ የተራራቀና የላሸቀ መንፈስ መገለጫ ነው፡፡ ኢትዮጵያዊ ጨዋነትን፣ በፍቅር አብሮ መኖርና መተሳሰብን የሚንድ የዝቅጠት ማሳያ ነው፡፡
ጽንፈኝነትን የሚያራምዱ ኃይሎች ደግሞ ከአጥናፍ እስከ አጥናፍ የሚታወቀውን የኢትዮጵያዊነት መገለጫ የሆነውን አገር ወዳድነት የሚፃረሩ ናቸው፡፡ ኩሩውና ጀግናው ሕዝባችን ለጽንፈኝነት ቦታ ባይሰጥም፣ የዚህ አስከፊ ድርጊት አራማጆች ግን በየጊዜው ብቅ ጥልቅ ሲሉ ይታያሉ በህወሃትና ጀሌዎቻቸው፡፡ የአገርን ክብር ለማዋረድ ላይ ታች ይላሉ፡፡
አገሩን ከራሱ በላይ አስበልጦ የሚወድ ማንም ኢትዮጵያዊ የገዛ አገሩን ለማዋረድ የሚቅበዘበዙ ኃይሎችን አይታገስም ለዚህም ነው ዛሬ ብዙ ታጋዮች መስዋትነት እየከፈሉ ያሉት፡፡ የፓን አፍሪካኒዝም ርዕዮተ ዓለም መሠረት የሆነችው አገራችን ኢትዮጵያ ከጠባብ መንደርተኝነት አስተሳሰብ እስከ አክራሪነት ድረስ ያሉትን ሞራል አልባ ተግባራት ህዝብ አይታገስም፡፡

ግፍና አፈና ዐመጽን ይወልዳሉ! (ያሬድ ኃይለማርያም)

የዐመጸኛ አፍ ጥልቅ ጉድጓድ ነው (መ. ምሳሌ ም. 22፣  ቁ. 14)
ከያሬድ ኃይለማርያም
ብራስልስ፣ ቤልጂየም
ታኅሣሥ 10፣ 2007
ethiopia_flagሰብአዊ መበቶችን በመጣስ፣ ግፍ በመፈጸምና አፈናን በማጠናከር እደሜ የሚሸምት የአገዛዝ ሥርዓት የእያንዳንዱን ሰው መንፈሳዊና አካላዉ ጥንካሬ የማዳከም፣ ቅስምን የመስበርና ፍርሃትን የማንገስ ከፍተኛ አቅም እንዳለው ሁሉ በብሶት የሚወለዱ፣ እምቢኝ ለግፈኞች፣ እምቢኝ ለአንባገነኖች፣ እምቢኝ ለነጻነቴ የሚሉ መንፈሰ ጠንካራ ጀግኖችንና ታጋዮችንም ይወልዳል:: የአለማችን ስመ ጥርና ዘመን የማይረሳቸው የነጻነት ታጋዮች እነ ማህተመ ጋንዲ፣ ማርቲን ሉተር ኪነግ፣ ማንዴላ፣ ኡንግ ሳን ሱ ኪ እና ሌሎችም ብዙዎች የፈለቁት በብሶት ከተሞላ፣ ጭቆና ካንገሸገሸውና በአፋኝ ሥርዓት ከታመቀ ማኅበረሰቡ ጉያ ነው:: አንድን ማኅበረሰብ በአፈሙዝ፣ በሕግና በገንዘብ ኃይል ጭፍሎቆና አፍኖ ማቆየት የሚቻለውም ለተወሰነ ጊዜ ብቻ መሆኑን የእነዚህ ታጋዮች ገድልና የአለም ታሪክም ይመሰክራል:: አንድ ሕዝብ በላዩ ላይ ገዢዎች እየተፈራረቁበት ረዘም ላለ ጊዜ በአገዛዝ ሥርዓት ሥር ሊቆይ ይችል:: ይሁንና እድሜ ልክ የገዛ አፋኛ ሥርዓት ግን የለም::

የአንድነት መንገድ! (አስራት አብርሃም)

አንድነት ለዴሞከራሲና ለፍትህ ፓርቲ በ2007 ምርጫ ከሁሉም ፓርቲዎች በተለየ ሁኔታ በጣም ግልፅና የማያሻማ የምርጫ እስትራቴጂ ነድፎ እየተንቀሳቀሰ ያለ ፓርቲ ነው። በዚህ ስሌትም የተዘጋውን የፖለቲካ ምህደር ህዝባዊ ንቅናቄ በመፍጠር ማስከፈት እንደሚችል አምኖ በምርጫው በሙሉ ልብ ለመሳተፍ ወስኗል። በዚህ ምክንያትም የያዘውን የምርጫና የሰላማዊ ትግል መስመር አስቀድሞ በይፋ በማወጅ የመርህ ፓርቲ መሆኑ አስመስክሯል።

አክራሪ … አሸባሪ … የሰለቸን መንግስታዊ መዝሙር … የፖለቲካ የበላይነት የፈጠረው አክራሪነት/አሸባሪነት የህዝቦች ስጋት ነው፡፡

ምንሊክ ሳልሳዊ
ሃገሪቱን የሚያሰጋት የሃይማኖት አክራሪነት/አሸባሪነት ሳይሆን የፖለቲካ የበላይነት የፈጠረው አሸባሪነት ጽንፈኝነት እና አክራሪነት ነው:: ጥላችሁን እንዳታምኑ እየተባለ ሃይማኖት መንግሥታዊ ቅርጽ ይዞ እንዲወጣ ለማድረግ መሞከር አክራሪነት ነው፡፡
Ethiopian soldiers ride on an army truck on the road to Afgooye, south of Mogadishu«መጾም፣ መጸለይ፣ ሥርዓተ-አምልኮን መፈጸም ሃይማኖታዊ አልባሳትን መልበስ ለሃይማኖቱ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ እንጂ አክራሪነት ሊባል አይችልም፤»…የአክራሪ ክርስትና ወይንም እስልምና ቡድን መኖር የክርስትና እና እስልምና ተከታዮችን በሙሉ «አክራሪ» አስብሎ ሊያስፈርጃቸው አይችልም::አክራሪ ተብሎ የሚፈረጀው የሚራመዱ የፖለቲካ ጡዘቶች በሰዎች ላይ ሌላ እምነትን በመጫን በግዳጅ እና በሃይል ሊያስገድዱ ሲሞክሩ ይህ ማለት አህበሽን እና ተሃድሶን በጥንታውያኑ እስልምና እና ተዋህዶ ላይ በኢትዮጵያ እንደተሞከረው ማለት ነው::

እስማኤል አሊ ስሮ ለረዥም ጊዜ በክልል ፕረዝድንትነት የቆዩ ብቸኛ የኢህአዴግ አገልጋይ የሆኑበት ምክንያት ምንድነው ?

አኩ ኢብን ከአፋር
የቀድሞው የትግራይ ክልል ፕረዝደንት የነበሩት አቶ ገብሩ አስራት በ 2006 ዓ.ም በጻፉት ሉዓላዊነትና ዲሞክራሲ በኢትዮጲያ በተሰኘው መጽሀፍ ላይ ሰለ እስማእል ዓሊ ሲሮ ሲገልፁ እንዲህ ይላሉ….
(አፋር ክልልን ፍልሥሥ ብሎ የሚመራው ኢስማኤል አሊስሮ ይህ ነው)
(አፋር ክልልን ፍልሥሥ ብሎ የሚመራው ኢስማኤል አሊስሮ ይህ ነው)

በ1993 በኢህአዴግ ውስጥ ቀውስ በተፈጠረበት ወቅት የአፋር ብሔራዊ ዴሞራሲ ፓርቲ ሊቀመንበርና የክልሉ ፕረዝድነት የነበሩ ዓሊ ሲሮ አፈንጋጮችን ደግፎ ለተወሰኑ ቀናት የመለስን ቡዱን ተቃውሞ ነበር።

መለስ ድል አድረግያለሁ የባለንጣዎች ጃኬትም አውልቀያለሁ ካለ በኃላም ዓሊ ሲሮ ደስተኛ አልነበረም።

የፍረጃ ፖለቲካ አይጠቅመንም! መልስ ለሁኔ አቢሲኒያ ( ግሬስ አባተ)

በመጀመሪያ ይህን ፅሁፍ የምፅፍልህ ሌላውን ወገን ወግኜ ሳይሆን ይህ አካሄድ በመሰረታዊነት ትግሉን የሚጎዳ ስለሚመስለኝ ነው፡፡ በምንም ጉዳይ ትግሉን አንድ ኢንች በሚጎዳ ነገር ዝምታን አልመርጥም፡፡ ሲጀመር ሰራዊት ፍቅሬንና የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉን በአንድ ሚዛን ላይ የሚቀመጡ ግለሰቦች አንዳይደሉ በደንብ የምታውቅ ይመስለኛል፡፡ የቆሙለት አላማ በራሱ ይህንን አስረግጦ ስለሚነግረን በዚህ ላይ ጊዜ ማባከኑ ትርጉም የለውም፡፡ የመረጥከው ርዕስ በራሱ ሶስቱን ለይተህ ማቅረብህ ግራ የሚያጋባ ነው፡፡ ያልመረጥናቸው ስትል ቀሪዎቹን ወይ መርጠሃቸዋል ወይ ይሁንታ ሰጥተሃቸዋል ማለት ነው፡፡
(ግርማ ሰይፉ)
(ግርማ ሰይፉ)
ያልመረጥናቸው ከምትል ይልቅ በምን መስፈርት ተመረጡ ብትል ጥሩ ይሆን ነበር፡፡ መብትህም ስለሆነ ! እንደምታውቀው የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉ የተቋውሞው ፖለቲካ ብቸኛ የፓርላማ ተወካይ ናቸው፡፡ እንደምታውቀው የተቃውሞ ጎራው የግድቡን ጉዳይ ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ መዋሉ በተለይም የአረቡ አብዮት ወደ ኢትዮጵያ እንዳይመጣ ለማስቀየሻ የተመዘዘ እና በቂ ጥናት ሳይደረግበት ወደ ስራ በመገባቱ እንጂ የሚቃወሙት ግድቡ ለምን ተገነባ በሚል አይደለም፡፡ ስለዚህ አቶ ግርማ የፓርላማ አባል በመሆናቸው ብቻ የዚህ ልዑክ አካል መሆን ቢችሉ ብዙም የሚገርም አይደለም፡፡

ምርጫ የዴሞክራሲያዊ ስርአት መገለጫ ብቻ ሳይሆን የሰላማዊ ትግል ስልት አካል ጭምር ነው!

ተሾመ ዳባ
ምርጫ በአንባገነን መንግስት ውስጥ?
2007 electionምርጫ የዴሞክራሲያዊ ስርአት መገለጫ የሚሆነው ነጻ፣ ፍትሃዊና ተወዳዳሪ (free, fair and contested) ባህሪያትን የተላበሰ እንደሆነ ብቻ ነው፡፡ በኢ-ዴሞክራሲዊ መንግስት ውስጥ የሚደረጉ ምርጫዎች በምንም መመዘኛ የዴሞክራሲ ስርዓት መገለጫዎች አይሆኑም፡፡ በሀገራችን በአጼው፣ በደርግ እና በኢህአዴግ ዘመነ-መንግስታት ተደርገው የነበሩ ምርጫዎች የአጼውን፣ የደርጉንና የኢህአዴግን የአገዛዝ ስርዓቶች የስልጣን ዘመን ለማራዛም የተደረጉ (“mechanism of regime maintenance”) ምርጫዎች እንጂ አንዳቸውም የዴሞክራሲዊ ምርጫ ባህሪያትን የተላበሱ አይደሉም፡፡ በእርግጥ በባለፉት ሁለት የመንግስት ስርአቶችም ሆነ በኢህአዴግ ዘመነ-መንግስት የተደረጉ ምርጫዎች በተለያዩ የፖለቲካ አገዛዝ ስርአቶች ውስጥ እንደመደረጋቸውና በወቅቱ ካለው የሀገራችን የፖለቲካ ዕድገት አንጻር የተለያዩ ባህሪያትን የተላበሱ ነበር፡፡ ይህ ሁኔታ ግን በኢትዮጵያ ብቻ የታየ ሳይሆን በማንኛው ኢ-ዴሞክራሲያዊ መንግስት ውስጥ የሚደረጉ ምርጫዎች አጠቃላይ ገጽታ ነው፡፡

Saturday, December 20, 2014

ድንበር ዘለሉ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ካድሬዎች አፈና እና የጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ እጣፈንታ !

nebyu sirak
ነብዩ ሲራክ ላለፉት አስርት አመታት በመካከለኛው ምስራቅ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ድምጽ በመሆን በአረቡ ዓለም ወገኖቻችን ላይ የሚደርሰውን መረን የለቀቀ ስቃይ እና በደል መቋጫ እንዲበጅለት በድህረ ገጹ በማስተጋባት ላይ የሚገኝ ጋዜጠኛ ነው ። ይህ ጋዜጠኛ በተለይ ያለምንም ቅድመዝግጀት እና ሁለትዮሽ፡ስምምነት በቤት ሰራተኝነት በደላሎች ተወናብደው ቁም ስቅላቸውን እያዩ ሰለሚገኙ እህቶቻችን አሰቃቂ ተእይንት በማለዳ ወጎቹ በማስቃኘት በአጭር ግዜ ውስጥ የአያሌ ወገኖችን ትኩረት መሳብ የቻለና የጉዳዩ ባለቤት በሆነው ህዝብ ዘንድ አንድናቆትና ክበርን ያተረፈ መሆኑም ይነገራል።

ተስፋዬ ገ/አብ ገዳ ከሰመረ አለሙ

ተስፋዬ ገ/አብ ለኤርትራ ነጻነት ታግሎ አገሬ የሚለዉን አገር ነጻ ከወጣ በሗላ በየጊዜዉ ኢትዮጵያን ሰፈር የሚያደርገዉን ቅሌት አስመለክተዉ ብዙዎች ዘግበዉታል በተለይም የተከበሩ የኢትዮጵያ ልጂ ኢንጂነር ዘዉገ አስፋዉ ተስፋዬ ስለሰዬ የማላዉቀዉ የለም ብሎ ሲቀባጥር በምሁር ብእራቸዉ ቢያበራዩትም ግለሰቡ ለእዉቀት ያልታደለ በመሆኑ አሁንም ኢትዮጵዉያን ሰፈር መተናኮሱን አላቆመም። ኤርትራ ዛሬ ምድር ላይ ያለ ችግር ተጠራቅሞ እሷ ላይ እንዳላረፈ ሁሉ ተስፋዬ ግን ለዉጊያ የመረጠዉ ሀገር ይችኑ ኢትዮጵያችንን ነዉ።
Tesfaye Gebreabተስፋዬ ገ/አብ በወጣትነት ዘመኑ በዘመኑ ሀገሪቱ ዉስጥ እንዳሉት ወጣቶች ተምሮ ወይ ተቀጥሮ ሊሰራ ባለመቻሉ በችሎታ ማነሰ ምክንያት ማለቴ ነዉ በወቅቱ በገፍ ልዩ ችሎታ ሳይጠይቅ ሁሉንም ያስተናግድ በነበረዉ በዉትድርና ዘርፍ ዉስጥ ተቀጥሮ ደርግን ሲያገልግል የቆየ ነበር። ችግሩ ዉትድርናዉንም በሀሞተ ቆራጥነት ሊወጣዉ ባለመቻሉ አንዴ በካድሬነት አንዴ በግጥም አንባቢነት የወቅቱን ጌቶቹን ሲያገለግል ቆይቶ የደርግ ዉድቀት አይቀሬ በመሆኑ ዘር አቋጥሮ ወደ ጠላት ጎራ ተቀላቅሎ ለመቀላቀሉ ግን የራሱን የሆን አንካሳ ምከንያት እየሰጠ በየጊዜዉ በመገለባበጥ የሚኖር ኤርትራዊ ነዉ።

ግርማ ሠይፉ፣ ሠራዊት ፍቅሬና ቴዎድሮስ አድሐኖም ያልመረጥናቸው የህዝብ ልዑካን (ሁኔ አበሲኒያ)

ከሠሞኑ ወደግብፅ የሚያቀና ህወሀታዊ የልዑካን ቡድን ሲቋቋም ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሊጠብቀው በማይችለው መልኩ የልኡካን ቡድኑ ውስጥ የአንድ ሠው ስም ተሠማ “ግርማ ሠይፉ” የሚል በርካቶች ተገረሙ ወይ አንቺ ሐገር ሲሉም አዘኑ፡፡ ከዚህ ቀደም ብቸኛ የተቃዋሚ ፓርቲ አባል በፓርላማ ተብለው በተቀመጡባቸው ያለፉት 4 ዓመታት ለሐገራችን ፖለቲካ ያንን ያህል ለውጥ ባያመጡም፤ የህሊና እስረኞቹ ይፈቱ ዘንድ አሁንም ያንን ያህል ጠንከር ያለ ስረ ባይሠሩም አቶ ግርማ ሠይፉን ሌሎች አካላት ሲተቿቸው ግርማ ሠይፉን ደግፈው ከሚቆሙ አካላት መካከል አንዱ እኔ ነበርኩኝ ብዬ አስባለው፤ አስባለው ያልኩት ስለግርማ ሠይፉ ከኔ በላይም የሚያስብ ሌላ ህወሀት የተሠኘ የሠዎች ስብስብ መኖሩን ስላልተረዳሁና በቅርቡ እየታዩ ያሉትን የግርማን መንሸራተቶች ባለመመልከቴ ነበር፡፡

ምርጫ ቦርድ በETV የሚለው ሌላ፤ በደብዳቤ የሚለው ሌላ!

10856636_745893688828901_7283862591598194371_o

“አሸባሪው” የ72 ዓመት አዛውንት

qeno abajobir
የ72 አመቱ አቶ ቀኖ አባጆቢር የሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት ውስጥ የጥበቃ ሰራተኛ ናቸው፡፡ የሚኖሩት ከ10 አመት ልቻቸው ጋር ነው፡፡ ይህን ልጅ እሳቸው ብቻ ነው የሚያሳድጉት፡፡ ትናንት ሰላማዊ ሰልፈኞቹ ከታፈሱ ከሰዓታት በኋላ ስራ ውለው ወደ ቤታቸው ሲሄዱ በደህንነቶች ታፈኑ፡፡ አቶ ቀኖ የጥበቃ ስራ ከመስራት ውጭ ሰልፉ አስተባባሪም ተሳታፊም አልነበሩም፡፡ ግን ታጥሮ ከሰነበተው የሰማያዊ ቢሮ የወጣ ሁሉ ሲለቀም ነበርና እሳቸውንም አፈኗቸው፡፡ ምን አልባትም ተደብድበው ይሆናል፡፡
ይህ ስርዓት እነ ይልቃልን፣ ብርሃኑን፣ አቤልን፣ በላይን፣ ጣይቱዎቹን . . . ሰማያዊን ብቻ አይደለም የሚፈራው፣ የሚያፍነው፣ የሚያፍሰው፣ የሚደበድበው፡፡ አቶ ቀኖንም የሆነ ነገር ያደርጋሉ ወይንም አድርገዋል በሚል (በራሱ ትርጉም) አፍኖ አስሯቸዋል፡፡ አሁን አቶ ቀኖ አዲስ አበባ ፖሊስ ጣቢያ ይገኛሉ፡፡ አይጠየቁም፡፡ ምን አልባትም ጨለማ ቤት ውስጥ ከታሰሩት መካከል ሳይሆኑ አይቀሩም፡፡

ልማታዊ ሙስና? ለአንድ ካሬ ሜትር መሬት 305 ሺሕ ብር

305
ባለፈው ዓርብ በተከፈተው የመሬት ሊዝ ጨረታ በአንድ ካሬ ሜትር 305 ሺሕ ብር ቀረበ፡፡ ይህ ዋጋ በከተማው ታሪክ እጅግ ከፍተኛ መሆኑ የሊዝ ጨረታን የወቅቱ አነጋጋሪ ክስተት አድርጓል፡፡
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ መርካቶ በርበሬ አካባቢ 449 ካሬ ሜትር ቦታ ለጨረታ ቀርቧል፡፡ በካሬ ሜትር የቀረበው ገንዘብ ሲሰላ ይህ አነስተኛ ቦታ 136.9 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ሆኗል፡፡ 20 በመቶ ብቻ የተከፈለበት ይህ መሬት ከነወለዱ እስከ 300 ሚሊዮን ብር በ30 ዓመት ሊደርስ እንደሚችል ባለሙያዎቹ ገልጸዋል፡፡ ይህ ክስተት ለአዲስ አበባ ሊዝ ሥሪት ባለሙያዎች እንዲሁም በጨረታው ለታደሙ ባለሀብቶች የቀረበው ዋጋ ብዥታን ፈጥሯል፡፡ በጨረታው ላይ ሁለተኛ ሆኖ የቀረበው ዋጋም ከዚህ ቀደም ቀርቦ የማያውቅ ሲሆን፣ የቀረበውም በካሬ ሜትር 288 ሺሕ ከ90 ሳንቲም ነው፡፡ “በአዲስ አበባ የሊዝ ዋጋ ላይ ቆም ተብሎ ካልታሰበ አደገኛ ውጤት ሊኖረው ይችላል፤” ሲሉ የአዲስ አበባ አስተዳደር የሊዝ ባለሙያ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

አገር ውስጥ እየኖሩ መሞት፣ በስደት ጉዞ መሞት፣ በስደት እየኖሩ መሞት! “መጪው ጊዜ ከኢህአዴግ ጋር ብሩህ ነው!”

ethiopians and their plight

* አገር ውስጥ “ባርነት”፤ ከአገር ተሰድዶ “ባርነት”

ከጥቂት ቀናት በፊት በአገራቸው መኖር ያቃታቸው 70 ኢትዮጵያዊያን ቀይ ባህርን በጀልባ አቋርጠው ወደ የመን ሲያመሩ በደረሰ አደጋ ሁሉም መሞታቸው ተገልጾዋል። ኢህአዴግ እነዚህ በእርግጥ ኢትዮጵያውያን ለመሆናቸው ማስረጃ እንደሌለውና “እያጣራ” መሆኑን በቃል አቀባዩ በኩል ተናግሯል፡፡
በዚህ ዓይነት ሁኔታ ከአገራቸው እየተሰደዱ ለባህር፣ ለአውሬ፣ … የተዳረጉት ወገኖቻችን ብዛት ተቆጥሮ አያልቅም፡፡ ይህንን ሁሉ አልፈው ወዳሰቡት የደረሱት ደግሞ በስደት የሚኖሩባቸው በተለይ የአረብ አገራት ይህ ነው የማይባል ሰቆቃ ይደርስባቸዋል፡፡ ይህንን ሁሉ የሚሰማው ወገን አሁንም በየኤምባሲው ቪዛ ለማስመታት በተገኘው ቀዳዳ ከአገሩ ለመውጣት ይጥራል፡፡ በዚህ በኩል ያልተሳካለት ድንበር በማቋረጥ አስጨናቂውንና አስፈሪውን ጉዞ ይጀምራል፡፡

ዓለም አቀፍ ሕብረት ለፍትሕ – የኢትዮጵያ ጉዳይ

GLOBAL_ALLIANCE
ጋዜጣዊ መግለጫ
ዓለም አቀፍ ሕብረት ለፍትሕ-የኢትዮጵያ ጉዳይ በፍትሕ ለሚያምኑ ድርጅቶችና ሰዎች በሙሉ መልካም ምኞቱን እየገለጸ በቫቲካን ድጋፍ በመርዝ ጋዝ ጭምር በመጠቀም ኢትዮጵያ ላይ ስለ ተፈጸመወ የፋሺሽት የጦር ወንጀል የሰው እልቂትና እጅግ ከፍ ያለ ውድመት  የካቲት 12-14 ቀኖች 2007 ዓ/ም ወይም በዚያን ሰሞን በየሐገሩና በየከተማው የመታሰቢያ ክብረ በዓል በማዘጋጀት እንዲዘክሩት ግብዣውን በትሕትና ያቀርባል።

ሱስ ትውልድና ሀገር! (ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው)

shishaበእኅታችን በሐና ላላንጎ ላይ ያ አደጋ በደረሰ ጊዜ ይሄንን ከባድ ዜና በለጠፉ ዋና ዋና ድረ ገጾች ላይ አንድ አስተያየት ሰጥቸ ነበር “ሆን ተብሎ በሱስ ትብትብ እንዲተበተብ ከተደረገ የዚህ አገዛዝ ትውልድ ከዚህ የተለየ ምን ይጠበቃል? እንደ ማኅበረሰብ ወንድም እኅቶቻችንን እናም ልጆቻችንን ከዚህ የሱስ ማጥ ውስጥ ካልታደግን በስተቀር ገና ከዚህ የከፋ ብዙ ነገርም ያሰማናል ያሳየናል” የሚል፡፡ አንዳንዶቹ የአገዛዙ ደጋፊዎች አጋጣሚውን ሆን ብየ ለፖለቲካ ፍጆታ ለመጠቀም የፈለኩ መስሏቸው አስተያየቴ ትክክል እንዳልሆነ ሲናገሩ አንዳንዶችም በመሳደብ ከአስተያየቴ ስር ምላሽ ሰጥተው ነበር፡፡ እኔ ግን ስም ለማጥፋትም አጋጣሚውን ለመጠቀምም አልነበረም፡፡ ያልኩት ነገር ለመሆኑ መረጃው ስለነበረኝ እንጅ፡፡ ወያኔ ፍጹም በደነቆረ አመክንዮና በጠላትነት ሰብእና ትውልዱን ሆን ብሎ በሱስ ማጥ ለማስጠም ሲሠራ ቆይቷል፡፡

ድንቄም ጠቅላይ ሚኒስትር! (ወንድሙ መኰንን፣ ከብሪታኒያ)

hailemariam pmብዙ ተብሏል። እኔም አንድ ነገር ልጨምርና ልገላገለው። “የጊዮርጊስን መገበሪያ የበላ ሲለፈልፍ ይኖራል” ነው የሚባለው? ተናግሮ ከሚያናግር ይሰውራችሁ! ውሀን ምን ነበር የሚያናግረው? ድንጋይ! የሰውም ድንጋይ እራስ አለ! ይቅርታ አንጀቴ አርሮ ነው!
ሦስት መንግስታትን የማየት ዕድል አጋጥሞኛል። ተወልጄ፣ አድጌ፣ ተምሬ ለዩኒበርሲቲ የበቃኹት በንጉሠ ነገሥቱ ዘመነ መንግሥት ነበር። ዕውነቱን እንናገር ከተባለ፣ ንጉሡ ሲናገሩም ሆነ ሲራመዱ፣ የርዕሰ ብሔርነት ግርማ ሞገስ ነበራቸው። “በንጉሥ መገዛቱ ጊዜ ያለፈበት፣ ያረጀ ያፈጀ፣ ገበሬውን በገባርነት ጠፍንጎ የያዘ፣ አገሪቱ በዕድገት ወደፊት እንዳትራመድ ያገዳት፣ ኋላ ቀር የፊውዳል ሥርዓት ነውና ወደሶሻሊዝም እንለውጣት” የሚሉ ድምጾች ከተማረው ክፍል አካባቢ እያየሉ መጡና እኛንም እንደጎርፍ ይዘውን ነጎዱ። ተከተልናቸው።

የኦባንግ ጉዞና ለዲያስፖራው ፖለቲካ ያለው አስተዋጽኦ (ሽመልስ ወርቅነህ)

obang in israel
የስብሰባው መሪ ሀሳብ “ስለ እያንዳንዳችን ከመናገር እያንዳንዳችን እንነጋገር” የሚል ድፍረትን፣ ግልፅነትን፣ መከባበርን፣ መነጋገር መቻልን ሃላፊነት በተሞላበት ስሜት ይቀርቡ በነበሩት አስተያየቶች የሚያረጋግጡ ከመሆናቸውም በላይ የተለየዩ የፖለቲካ አመለካከት፣ እምነት እንዲሁም የተለየዩ ብሄረሰቦች ዉሁድ ኢትዮጵያውያን በአንድ ጠረጴዛ ዙርያ ተቀምጠው ያነሱዋቸው የነበሩት ሃሳቦች በጥንታዊት ኢትዮጵያና በአዲሲቱ ኢትዮጵያ የፖለቲካ ገመድ ጉተታ ግራ ለተጋቡ ጥሩ አስተማሪ መድረክ ነበር::

ኢህአዴግ በባህር ዳር ግድያ ፈጸመ! በባህርዳር ዋይታ ሆነ!

በእምነት ቦታ ይገባኛል ነዋሪዎች ባሰሙት ጥያቄ ኢህአዴግ የጥይት መልስ ሰጠ፡፡ ድርጊቱን በምስል በማያያዝ በተለያዩ ማኅበራዊ ገጾች ያሰራጩት ክፍሎች አዛውንትና መነኮሳት ሳይቀሩ መደብደባቸውንና መቁሰላቸውን በምስል አስደግፈው አመልክተዋል፡፡
አኻዙ በትክክለኛው ባይታወቅም አምስት የሚደርሱ ሰዎች ሕይወታቸው እንዳለፈ በማኅበራዊ ገጾች የተበተኑት መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ አንዳንድ የድረገጽ ዜናዎችም በአኻዝ ከመለያየት በስተቀር የግድያውንና የድብደባውን መጠን በመግለጽ ዜናቸውን አስፍረዋል፡፡
ድርጊቱን የፈጸመው ኢህአዴግ ስለሞቱትና ስለተደበደቡት መነኮሳትና አዛውንት እንዲሁም ሌሎች ወገኖች ይህንን መረጃ እስካጠናቀርንበት ጊዜ ድረስ ይፋዊ ማስተባበያ አልሰጠም፡፡ ይልቁንም ከሁለት ሳምንት በፊት ኢህአዴግ የፌዴራል ምክት ሚ/ሩን በፖሊስ ፕሮግራም በማቅረብ የፌስቡክ ዜናዎችን አትመኑ በማለት ማሳሰቢያ ሲሰጥ ነበር፡፡

Friday, December 19, 2014

ለጋዜጠኞች ቦታ የነፈገው፤ “በአርቲስቶች” ፍቅር የተንሸዋረረው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ጽ/ቤት

በአንድ ወቅት የኢትዮ-ቻናል ጋዜጣ ዘጋቢ ጋዜጠኛ፣ ወደ ሕዳሴ ግድብ በተደረገ ጉዞ ጋዜጠኞች ላይ የደረሰውን እንግልት አስመልክቶ “የጋዜጠኛ ዋጋው ስንት ነው” በሚል ርዕስ አንድ ጹሁፍ አስነብቦ ነበር። ይህን ጽሁፍ ከመፃፉ በፊት በጉዞው ላይ የነበርነውን ጋዜጠኞች ብዙ አነጋግሯል። ችግሩ የተፈጠረው ወደ ሕዳሴ ግድብ ጉዞ እያደረግን በነበረበት ጊዜ ነበር። የጹሁፉ ይዘት ከሕዳሴው ግድብ ጋር እንዳይያያዝ ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበት ምክረ ሃሳብ እንዳስቀመጥን አስታውሳለሁ። አንዳንዶቻችን ከዚህም በላይ ርቀን ሄደን፣ ሊፃፍ የታሰበው ጽሁፉ ቀርቶ ቅሬታውን ለሚመለከተው አካል ሪፖርት ማድረግ በአማራጭነት አቅርበንም ነበር። በመጨረሻ ግን መፃፍ ወይንም አለመፃፉ የሚዲያ ተቋሙ ውሳኔ እንዲሆን ተስማማን።

Wednesday, December 17, 2014

ከሞት በስተቀር ወደ ኋላ እሚመልሰን ምንም ሃይል የለም!

by Eyerusalem Tesfaw 
ነፃነት ለፍትሃዊ ምርጫ በሚል ሰማያዊ ፓርቲን ጨምሮ ዘጠኙ ፓርቲዎች በጋራ ያዘጋጁት የአንድ ወር መርሃ ግብር መቋጫው ህዳር 27 እና 28 እሚደረገው የአዳር ሰልፍ ነው ይህ የአዳር ሰልፍ ከተጠራ ወዲህ በወያኔ/ኢህአዴግ ዘንድ ከፍተኛ መደናገጥ ተፈጥሮ እንደነበር በግልፅ ሲታይ የሰነበተ ነገር ነው እስሩ እንግልቱ እና ማዋከቡ ሰልፉ አንድ ሳምንት ሲቀረው ተባብሶ የቀጠለ ሲሆን ከእሮብ ህዳር 24 ጀምሮ የነበሩትን ቀናት ላስታውሳችሁ ወደድኩ

በዚች ቀን በቅስቀሳ ላይ የነበሩ አባላቶቻችን ታሰሩብን በተለያየ አቅጣጫ ብዙ ሺህ ወረቀቶችን የበተኑ ሲሆን ብዙዎቹ በሰላም ሲመለሱ አምስት ልጆች በቁጥጥር ስር ዋሉ ወይኒ ንጉሴ እና ሚሮን አለማየሁ ማታ በመታወቂያ ዋስ የወጡ ሲሆን ማቲ ባህረ እና ሲሳይ በአሁን ሰዓትም ጉቶ ሜዳ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ወረዳ 9 በእስር ላይ ይገኛሉ

የአርበኞችና ግንቦት ሰባት ዲሞክራሲያዊ ግንባር በአስመራ ሊመሰረት ነው::የግንቦት ሰባት አመራር አባላት አስመራ ገቡ ::

Image
የአማራ ዲሞክራሲያዊ ሃይሎች (Amara Force) እኛ በውህደቱ የለንበትም ብሏል::
Minilik Salsawi ምንሊክ ሳልሳዊ - ከአስመራ ከተማ የሚገኙ ምንጮቼ በስልክ እንዳስታወኩኝ ካለፈው ሃሙስ ጀምሮ የግንቦት ሰባት አመራር አባላት የሆኑት አቶ ነእመን ዘለቀ:የአቶ አንዳርጋቸው ወንድም አቶ ብዙአየሁ ጽጌ አቶ አበበ ቦጋለ እና ሌሎች የኢሳት ሪፖርተሮችን አስከትለው አስመራ የገቡ ሲሆን የአርበኞች ግንባር አመራሮች ወደ አስመራ የሚልኩትን ሰው መርጠው ባለመጨረሳቸው እንደዘገዩ ሲጠቆም እስከ እሁድ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል::ዶክተር ብርሃኑ ነጋ መግባታቸውን ለማረጋገጥ ቢሞከርም ሆተሎች ጥብቅ የጸጥታ ክትትል ስለሚደረግባቸው መረጃዎች ለጊዜው እንዲዘገዩ ተደርጓል::

CPJ: at least 220 journalists imprisoned around the world

PanARMENIAN.Net – There are at least 220 journalists imprisoned around the world, with 132 of them held on anti-state charges of terrorism or subversion, says a report released Wednesday, Dec 17, by the Committee to Protect Journalists (CPJ).
According to Al Jazeera, the CPJ census on jailed journalists indicates that 2014 is the second worst year for jailed journalists since the organization started conducting its annual census in 1990. The worst year was 2012, when 232 journalists were jailed.
The report does not count journalists being held by nonstate actors, such as the Islamic State of Iraq and the Levant (ISIL or IS), which the CPJ estimates is holding 20 journalists.
The number of journalists held by nonstate actors — about 80 have been taken by various groups since the Syrian conflict started in 2011 — is unprecedented, according to Robert Mahoney, deputy director at the CPJ.

Ethiopian Man could spend 12 yrs in jail in 2013 strangulation death of his wife

HIGH POINT, North Carolina
An Ethiopian refugee will spend at least 12 years in prison after pleading guilty Tuesday in the 2013 strangulation death of his wife during a fight about money.
g2582580000000000008bdf0fad2fba25c18e7428aec1ebc327623730ddArab Mohamed Ali, 35, was charged in February 2013 with the first-degree murder of 23-year-old Safaya Dadacha.
He struck a deal Tuesday with the High Point District Attorney’s Office and pleaded guilty to the lesser charge of second-degree murder, receiving a sentence between 12 and nearly 15-and-a-half years imprisonment with credit for time served.
High Point police responded the afternoon of Feb. 18, 2013, to 2113 Wingate Place in reference to a domestic violence call, prosecutor Christon Halkiotis said during the Tuesday proceedings. Ali called 911, she said.
Officers found Ali and the two children he had with Dadacha, ages 5 and 2, outside the residence. Dadacha was discovered on the floor inside, unresponsive, her head covered by a green cloth.
Halkiotis said police asked Ali if the woman was asleep.
“‘I think she died,’” Ali responded, according to the prosecutor. “Officers noted the defendant was not emotional and did not act as if anything was wrong.”

አሳዛኙ ብሔራዊ ውርደታችን

ኢትዮጵያ መንግስት አላት ወይ? የአሜሪካ አምባሳደር ለኢትዮጵያ መንግስት በቀይ ባህር ለሞቱት ኢትዮጵያውያን የሃዘን መግለጫ ላኩ።ኢህአዲግ/ወያኔ እስካሁን አንዳች አልተነፈሰም።Statement by Patricia Haslach, U.S. Ambassador to Ethiopia

Patricia Haslach, U.S. Ambassador to Ethiopia
Patricia Haslach, U.S. Ambassador to Ethiopia
በያዝነው ሳምንት መጀመርያ ላይ ዓለም አቀፍ የዜና አውታሮች በየመን የባህር ዳርቻ፣ በቀይ ባህር ውስጥ ከሰባ በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች መስመጣቸው መሰማቱ ይታወቃል።ጉዳዩ በሀገር ቤት እና በመላው ዓለም በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ከፍተኛ ሃዘን አስከትሏል።
ከእዚህ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያውያንን ልብ ያደማው ጉዳይ ደግሞ የኢትዮጵያ መንግስት ይህንን ቢቢሲን ጨምሮ በርካታ የዜና አውታሮች የተቀባበሉትን ጉዳይ ላይ አንዳች የሃዘን መግለጫ አለማሰማቱ ነው።በትናንሽ አደጋ ለሞቱ ለሌላ ሀገር ዜጎች የሃዘን መግለጫ በማውጣት እና በመላክ የሚታወቀው ኢህአዲግ/ወያኔ ለኢትዮጵያውያን ሞት አንዳች አልመተንፈሱ ሌላው የብሔራዊ ውርደታችን መገለጫ ነው።በሳውዲ ጉዳይ መንግስት እንደሌለን አውቀን ነበር።ዘንድሮም በቀይ ባህሩ አደጋ አረጋገጥን።በፌስቡክ ገፃቸው የእየእለቱን ውሎ የሚለጥፉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ሰሞኑን ከ 300 ሚልዮን ብር በላይ ወጣበት ስለተባለው በአሶሳ ስለነበረው ብሔር ብሄርሰቦች በዓል ማውሳታቸው ኢትዮጵያ መንግስት አላት ወይ? ብለው ብዙዎች እንዲጠይቁ ማስገደዱ አልቀረም።

ግንቦት ሰባት ሆይ…. ከሄኖክ የሺጥላ


Henok Yeshitila
Henok Yeshitila

ውድ ወዳጆቼ ሆይ ፣ ዛሬ ተክሌን መሆን አምሮኛል ( ተክሌ ይሻውን ሳይሆን ተክለሚካዔል ሳህለ ማርያምን )። ልጅ ተክሌ መቼም እኔ’ነቴን ለምን ወሰድክብኝ እንደማትለኝ ነው ። እንኩዋን እኔነት ፣ የእኔነት መፈጠሪያ የሆነችውን ሀገርህን ወስደዋትስ የለ ።

የዛሬ ጽሁፌ የሚያጠነጥነው ትልቁንና እና ጠንካራውን ድርጅት ግንቦት ሰባትን ላይ ነው ። እንደውም ጽሁፌን ከማውጠንጠን ማነጣጠር ሳይሻል አይቀርም ( የታጠቀን እንዲያ ነው እንጂ !) ። እና የምወደውን ግንቦት ሰባት ፣ ባልሞትለት እንክዋ የምደማለት ግንቦት ሰባትን ፣ የኔ የምለውን ግንቦት ሰባት ፣ የ አንዳርጋቸውን ግንቦት ሰባት ፣ የብርሃኑ ነጋን ግንቦት ሰባት ፣ የዔፍሬም ማዴቦን ግንቦት ሰባት ፣ የአበበ ገላውን ግንቦት ሰባት ፣ አዎ ስለሱ ነው ።
andargachew
አንተ ግንቦት ሰባት ሆይ ፣ አንተን ካወቅኩበት ቀንና ሰዓት ጀምሮ ትቢት ትቢት ይለኛል ፣ ወያኔ ምን ለማስፈራራት ቢሞክር ፣ ነገራቸው ሁሉ ድንፋታ እንጂ አንዳች ፍርሃት ልቤን ይሁን ሆዴን ቅም አይለውም ፣ ስላንተ ሳስብ አባቱን ከሩቅ እንዳየ ህጻን እፈነድቅአለሁ ፣ ስምህ በክፉ ሲነሳ ፊቴ ደም ይለብሳል ፣ የባንክ ደብተሬ እንኩዋ ዜሮ እያሳየ ስላንተ ስሰማ ምን እንደሆነ ባላውቅም መንዝር መንዝር ይለኛል ፣ ዘርዝር ዘርዝር ይለኛል ፣ ያም ሆኖ አንዳርጋቸው ከታሰረ ወዲያ ላንተ ያለኝ ፍቅር ወደ ንዴት እየሄደ ነው ። ይሄም የሆነው አንዳርጋቸው በመያዙ ሳይሆን ፣ የአንዳርጋቸውን መያዝ ተከትሎ ይህ ነው የሚባል አጸፋዊ እርምጃ ባለመውሰድህ ነው ። ሰማያዊ እንኩዋ ነጭ እርግብ ጭንቅላቱ ላይ አድርጎ ሰላም ሰላም እያለም ፣ እየተገፈተርም ቢሆን ሰልፍ ወጥቶዋል ፣ “የምንገለው ባይኖረንም የምንሞትለት ሕዝብ ግን አለን” ብሎ ይሄው እሳት ከጨበጠ ጋ በ እስክርቢቶ ትግሉን ሀ ብሎ ከጀመረ ቆየ ፣ አረ እንደውም እስክርቢቶ መግዣውን እኔም ተባብሬያለሁ ( በሱም በጣም ደስተኛ ነኝ ) ።

‹‹የኢትዮጵያና የጂቡቲ ሕዝቦች ፍላጎት ከሆነ ውህደትን ተግባራዊ ማድረግ አለብን›› የጂቡቲው ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ዑመር ጌሌ

የጂቡቲው ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ዑመር ጌሌ
የጂቡቲው ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ዑመር ጌሌ

ረፖርተር

የጂቡቲው ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ዑመር ጌሌ፣ ጥንታዊና ታሪካዊ የሆነው የኢትዮጵያና የጂቡቲ ግንኙነት በአሁኑ ጊዜ ጥልቅ እየሆነ መምጣቱንና አንዱ አገር ለአንዱ አስፈላጊ የሆነበት ደረጃ ላይ መድረሱን ገለጹ፡፡
የሁለቱ አገሮች ሕዝቦች የውህደት ፍላጎት ካላቸውም ይህንኑ ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
ከኢትዮጵያ የተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን የተወጣጡ ባለሙያዎች ባለፈው ሳምንት  ጂቡቲን በጎበኙበት ወቅት፣ ፕሬዚዳንቱ ከጋዜጠኞቹ ጋር አጭር ቆይታ አድርገው ነበር፡፡
በጂቡቲ መንግሥት ግብዣ ወደ አገሪቱ የተጓዙት ጋዜጠኞች ለአምስት ቀናት በነበራቸው ቆይታ ከተለያዩ የመንግሥት ኃላፊዎች የተገነዘቡትን የጂቡቲና የኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ቁርኝት ፕሬዚዳንቱ በድጋሚ አረጋግጠዋል፡፡

የኢትዮጵያን ዲሞክራሲ ለመዉለድ ስንት ዘመን ይፈጃል? (ከ ቶፋ ቆርቾ)

ከ ቶፋ ቆርቾ
የምርጫ ወግ
electionምርጫ ደርሷል አይደል? ለዛ መሆን አለበት በአንድ በኩል EBC ‘ምርጫ ቦርድ ለምርጫ አስፈፃሚዎች ስልጠና ሰጠ … ኮሮጆ አሰራጨ’… ሌሎች መገናኛ ብዙሃን ደግሞ ‘ምናምን የሚባል ፓርቲ ሰልፍ ጠራ’ … ‘የነእከሌ ፓርቲ ትየንተ ህዝብ በፖሊስ ሃይል በሃል ተበተነ’ ….. ዱዱዱዳ…እንዲያም እንዲህም የሚሉ ወሬዎች መስማት ከመሰንበቻዉ የተለመደ ሆኗል፡፡
እኛ ሃገር ስለምርጫ አምስት ዓመት እየጠበቁ ማዉራት የተለመደ ተከታታይ ድራማ (series TV show) ይመስላል… የመጪዉ ግንቦት አምተኛዉ ምእራፍ (Season 5) መሆኑ ነዉ ማለት ነዉ? ቂቂቂቂ….! እኔ የምለዉ ግን ለይመሰል ብቻ ምርጫ ማድረግ ምን ይጠቅማል? መጨረሻዉን ቀድመዉ ያወቁትን ፊልም ማየት ወይ ‘ልብ አንጠልጣይ’ የተባለ ልብ ወለድ መፃፍ ማንበብ ጊዜ ማሳለፊያ አልያም የደራሲዉን ችሎታ ለመገምገም ካለሆነ በቀር ምኑ ይነሽጣል? እሺ አንድ ሁለቴ እያወቁ መሸወድ ያለ ነዉና ምን አይደል እንበል…. አመስቴ ስሆንስ? አራዶቹ  ቢሰሙ ‘አይከይፈፍም’ ይሉናል ከምር ኩሸት ይሆናል! ልጆች ሆነን ‘ክስክስ’ የምንለዉ አይነት አክሽን ፊልም ስናይ ‘አክተሩ’ አይሞትም ምናመን ብለንና አምነን አሳምነን ፊል ማየት እንጀምራለን እዉነትም ፊልሙ ሲገባደድ አክተሩ ጠላቶቹን ያሸንፋል በቃ አይሞትም…. የኛም ሃገር ምርጫም ልክ እንደዛዉ ነዉ….. መሪ ተዋናዩ የማይሸነፍበት አክሽን ፊልም! ልየነቱ በሚሊዮነች የሚቆጠሩ መሪ እና አጃቢ ተዋንያን የሚሳተፉበት መሆኑና ለወራት የሚወራለት መሆኑ ብቻ ነዉ! የሆነዉ ሆኖ አሸናፊዉና አጃቢዎቹ ቀድሞ ዉጤቱ የታወቀበትን ምርጫ የሚባል ድራማ መሰል ነገር ማካሄድ ለምን አስፈለጋቸዉ? ቃለ ተዉኔቱን… ዝግጅቱን… ቀረፃዉን…. ዳኝነቱን አንድ አካል ብቻዉን በተቆጣጠረበት ቲያትር ዉስጥ መግባት የሚያስገኘዉ ትርፍ ይኖረዉ ይሆን?

አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የኢትዮጵያን ህዝብ የስልጣን ባለቤት አደርጋለሁ አለ (VOA)

አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የሚልዮኖች ድምጽ ለነጻና ፍትሀዊ ምርጫ ባለው ዘመቻ የኢትዮጵያን ህዝብ የስልጣን ባለቤት አደርጋለሁ አለ። ፓርቲው በአሁኑ ጊዜ በመላ የሀገሪቱ ክፍሎች መዋቅሩን መዘርጋቱናን በየትኛውም ደረጃ የምክር ቤት እጩዎችን ለማቅረብ እንደሚችል ገልጿል።
አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በሚቀጥሉት የምርጫ ወራት በሚልዮኖች ድምጽ ለነጻና ፍትሀዊ ምርጫ የኢትዮጵያ ህዝብ የስልጣን ባለቤት እንዲሆን እናደርጋለን ሲል ዛሬ ረፋዱ ላይ በጽህፈት ቤቱ በሰጠው መግለጫ ላይ ባሰራጨው ጽሁፍ ግልጽ አድርጓል።

ደማቅ ህዝብዊ ስብሰባ በኖርዌ በርገን ከተማ ቅዳሜ Dec 13.2014 ዓ.ም ተካሄደ

ለዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌ በርገን ቅርንጫፍ አዘጋጂነት የተካሄደው ይህ ህዝባዊ ስብሰባ ከመላው የኖርዌ ከተሞች እና በአቅራቢያዊ ከሚገኙ አጎራባች ሀገሮች የመጡ ኢትዮጵያዊያኖች ተሳታፊ ሆነውበታል:
23
ስብሰባው የተጀመረው ኢትዮጵያ ውሰጥ ባለው አስከፊ ስርዓት በቀጥታ የመንግስት ትእዛዝ በስውርም ይሁን በግለጽ ህይወታቸውን ላጡ ፣ቤተሰባቸው ለተበተነባቸው፣ትዳራቸው ለፈረሰ፣ ጧሪ ቀባሪ አጥተው የስቃይ ህይወት ለሚገፉ፣ በጎረቤት ሀገሮች እስር ቤቶች ውስጥ ለሚሰቃዩ፣ በስደት በበረሃውና በባህር ውሰጥ ህይወታቸው አልፎ ያለቀባሪ ለቀሩት ወገኖቻችን የአንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎት በማድረግ ነበር።

‹‹ከዓለም የቦንድ ገበያ እንድንበደር የተፈቀደልን እስከ ሁለት ቢሊዮን ዶላር ነው›› ሚኒስትር ሱፍያን አህመድ

ረፖርተር
የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትሩ አቶ ሱፍያን አህመድ፣ ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፍ የቦንድ ገበያው አንድ ቢሊዮን ዶላር ብድር ማግኘቷን፣ ፓርላማው ደግሞ እስከ ሁለት ቢሊዮን ዶላር የቦንድ ገበያ ብድር እንደፈቀደ አስታወቁ፡፡
ሚኒስትሩ ማክሰኞ ዕለት በጽሕፈት ቤታቸው በሰጡት መግለጫ በቦንድ ሽያጩ በ6.625 በመቶ ወለድ ክፍያ አንድ ቢሊዮን ዶላር መገኘት መቻሉን አብራርተዋል፡፡
TPLF Police Found Millions of Birr, Dollars and Euros in Ato Gebrewahid Wolde Giorgis Houseሶቨሪን ቦንዱን ለመሸጥ በሚኒስትሩ የተመራው ቡድን እ.ኤ.አ. ዲሴምበር 5 ቀን 2014 ሽያጩን በአሜሪካ ያጠናቀቀ ሲሆን፣ ከአንድ ቢሊዮን ዶላር ውስጥ 70 በመቶውን የገዙት በአሜሪካ የሚገኙ ኢንቨስተሮች ናቸው፡፡ የተቀረውን 30 በመቶ ደግሞ በአውሮፓ የሚገኙ መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡ በመጀመርያ ለመሸጥ ታስቦ የነበረው ሁለት ቢሊዮን ዶላር መሆኑንና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትም እስከ ሁለት ቢሊዮን ዶላር የሶቨሪን ቦንድ ሽያጭ ማፅደቁን ገልጸዋል፡፡

Tuesday, December 16, 2014

ሕዝባዊ ዕንቢተኝነት ለኢትዮጵያ ትንሳኤ!

ነብዩ ኃይሉ
ባሳለፍነው ሳምንት ቅዳሜ ህዳር 27 ቀን 2007 ዓ.ም ዘጠኝ ፓርቲዎች ያቋቋሙት ትብብር የጠራው የአዳር የተቃውሞ ሰልፍ፣ በገዢው ቡድን ውንብድና ከተስተጓጎለ በኋላ ስለሰላማዊ ትግል አይረቤነት የተለያዩ አስተያየቶች በመሰጠት ላይ ናቸው፡፡ የተወኑት አስተያየቶች “ትግሉ አልጋ በአልጋ መሆን አለበት” ከሚል የዋህ ልቡና የመነጩ የተስፋ መቁረጥ ስሜቶች ቢሆኑም፤ ጥቂት የማይባሉት ግን የህብረተሰቡን ቀልብ ከሰላማዊ ትግል አውድ ለማፋለስ ታቅደው የሚሰነዘሩ ይመስላሉ፡፡
Tensaye
በመሰረተ-ሀሳብ ደረጃ የትኛውንም የአገዛዝ ስርዓት ለመጣል የሚደረግ ትግል በአንድ ወጥ ቀኖናዊ የትግል ስልት ላይ ብቻ መመስረት ይገባዋል የሚል ድምዳሜ መስጠት አይቻልም፡፡ ሆኖም ከኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ አንፃር የትኛው የትግል ስልት ያዋጣል የሚለውን በኃላፊነት ስሜት የመምረጡ ተግባር ለታጋዩ የሚሰጥ ነው፡፡ በየትኛውም መለኪያ በትግል ላይ የሚፈጠር እንቅፋት ሁሉ ስልቱን ጥያቄ ምልክት ውስጥ ሊከት ግን አይችልም፡፡