Monday, September 30, 2013

የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል ውሎ በኖርዌይ

የግንቦት 7 ሕዝባዊ  ኃይል ድጋፍ ማሰባሰቢያ በደማቅ ሁናቴ ተጠናቀቀ
ቅዳሜ ሴፕቴበር 28  በኦስሎ ኖርዌይ ለግንቦት 7 ሕዝባዊ  ኃይል የገቢ ማሰባሰቢያ በደመቀና በተሳካ እንዲሁም የሕዝቡ ቁርጠኝነት በታየበት ሁናቴ ተከናወነ ።
በዲሞክራቲክ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ሰጪ ድርጅት ኖርዌይ አስተባባሪነት ለግንቦት 7 ሕዝባዊ  ኃይል ድጋፍ ለመስጠት የተዘጋጀው የገቢ ማሰባሰቢያ በተሳካና በአማረ ሁናቴ እንዲካሄድ በማድረግ በኖርዌይ የሚገኙ በዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ሰጪ ድርጅት አባላትና ደጋፊዎች ፣የግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ አባሎችና ደጋፊዎች፣በኖርዌይ የሚገኙ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን እንዲሁም ከተለያዩ አገራት  ከስዊዲን፣ከኢንግላንድ፣ከሲዊዘርንድ የመጡ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን በፕሮግራሙ ላይ በመገኘት ለአገራቸው ለውጥ ለማምጣት  የገቢ ማሰባሰቢያውን ገንዘብ በማዋጣት ለግንቦት 7ሕዝባዊ  ኃይል አለኝታ መሆናቸውን አሳይተዋል።

ቃለመጠይቅ – ከተስፋዬ ገብረአብ ጋር (“ላይፍ” መፅሄት)

…የምንሰማው እውነት ከሆነ ከመቀሌው አባይ በስተጀርባ ቴዎድሮስ ሃጎስ አለ። ከአዲሳባው አባይ ስር እነ ጌታቸው አሰፋ፣ እነ ደብረፅዮን መሰለፋቸው ይሰማል። ሳሞራ የአዲሳባውን አባይ ተቀላቅሎአል። አዜብ ‘አርፈሽ ቁጭ በይ! የመለስን ፋውንዴሽን ተከታተይ’ ተብላለች። እብድ ስለሆነች ያልተጠበቀ ነገር እንዳትፈፅም በመስጋት ሰንሰለቷን ሁሉ በጣጥሰውባታል። የዘረፋ ቀዳዳዎቿን እየዘጉባት ነው። ያም ሆኖ አዜብ አርፋ ትቀመጣለች ተብሎ አይታመንም። መሞከሯ አይቀርም።

የእስራት ዜና

1. አቶ የሺዋስ አሰፋ የሰማያዊ ፓርቲ ምክር ቤት / ሰብሳቢ
2. አቶ ስሜነ ፀሃይ የሰማያዊ ፓርቲ ምክር ቤት አባል የሆኑት ለእስራት ተዳረጉ፡፡
አንድነት ፓርቲ በትላንትናው ዕለት በመንግስት አፈና የተደረገበት የተቃውሞ ሠልፍ ማካሄዱ የሚታወቅ ነው፤በተቃውሞ ሠልፍ ላይ ለመሣተፍ ብቸኛው የተቃዋሚ ፓርቲ የፓርላማ አባል እና የአንድነት ፓርቲ / ፕሬዝዳንት የሆኑቱ የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉ ወደ ተቃውሞ ሠልፍ በማምራት ላይ እያሉ ፒያሳ በሚገኘው አፍሪካ ወርቅ ቤት አካባቢ በደንነቶች እና በፖሊሶች ወከባ የተፈፀመባቸው ሲሆን ይህን ወከባ በመከላከል እና በመቃወም አጋርነታቸው እና ወገናዊነታቸውን ያሳዩ ለእስራት ተዳረጉ፡፡

የህወሓት ሁለቱ ቡድኖች (የመቐለና አዲስ አበባ) ዉዝግብ እንደቀጠለ ነው።

የህወሓት ሁለቱ ቡድኖች (የመቐለና አዲስ አበባ) ዉዝግብ እንደቀጠለ ነው። በፖለቲካ ዘርፍ የአዲስ አበባው ቡድን ጥሩ እየተጫወተ ነው። አብዛኞቹ የመቐለ ቡድን አቀንቃኞች (ግን አዲስ አበባ አከባቢ የሚኖሩ) በሙስና ሰበብ እየታሰሩ (ሌሎችም እየደነገጡ) ከጨዋታ ውጭ እየሆኑ ሲሆን ለአዲስ አበባው ቡድን ደግሞ ዓቅም እያስገኙ ነው።

ግን የአዲስ አበባ ቡድን ሙሉ በሙሉ ማሸነፍ ይችላል የሚል ግምት የለኝም። ምክንያቱም የመቐለው ቡድን የትግራይ ክልል መንግስታዊ መዋቅር ለግል ፍላጎቱ በማዋል አብዛኞቹ የህወሓት አባላት በቁጥጥር ስር ለማድረግ እየመከረ ነው።

የህወሓት የሃይል ሚዛን ከኣብርሃ ደስታ

የህወሓት ሁለቱ ቡድኖች (የመቐለና አዲስ አበባ) ዉዝግብ እንደቀጠለ ነው። በፖለቲካ ዘርፍ የአዲስ አበባው ቡድን ጥሩ እየተጫወተ ነው። አብዛኞቹ የመቐለ ቡድን አቀንቃኞች (ግን አዲስ አበባ አከባቢ የሚኖሩ) በሙስና ሰበብ እየታሰሩ (ሌሎችም እየደነገጡ) ከጨዋታ ውጭ እየሆኑ ሲሆን ለአዲስ አበባው ቡድን ደግሞ ዓቅም እያስገኙ ነው።

ግን የአዲስ አበባ ቡድን ሙሉ በሙሉ ማሸነፍ ይችላል የሚል ግምት የለኝም። ምክንያቱም የመቐለው ቡድን የትግራይ ክልል መንግስታዊ መዋቅር ለግል ፍላጎቱ በማዋል አብዛኞቹ የህወሓት አባላት በቁጥጥር ስር ለማድረግ እየመከረ ነው። በትግራይ ክልል ቢሮ የሚሰራ የህወሓት አባል ለአዲስ አበባው ቡድን ለመደገፍ ይቸገራል። ምክንያቱም ለአዲስ አበባው ቡድን የደገፈ የትግራይ ባለስልጣን ከሓላፊነቱ ይባረራል። ስለዚህ አይሸናነፉም።

ብቃት ያለው የሲኖዶስ አደረጃጀት፣ ነውር ነቀፋ የሌለበት የጳጳሳት ሹመት ያስፈልገናል

  • ‹‹[ቅዱስ] ሲኖዶሱ አሁን ያለችውን ቤተ ክርስቲያን በብቃት የሚመራበት ደረጃ ላይ ነው ወይ? ለውጡ መጀመር ያለበት ከራሱ ከ[ቅዱስ] ሲኖዶሱ ነው፡፡››
  • ‹‹ወደፊት የሚመጡ ጳጳሳት ይኖራሉ፡፡ የጳጳሳቱ አመራረጥ የሕዝብን ይኹንታ የሚያገኝ ነው[ን] የሚለው ገና የሚታይ ነው፡፡››
  • ‹‹ዕርቀ ሰላሙን እኛ ቀድመን ብናመጣው ጥሩ ነው፡፡››

Dn. Daniel Kibret
ዲ/ን ዳንኤል ክብረት
ሰባኬ ወንጌል እና ጸሐፊ ዲ/ን ዳንኤል ክብረት ከዕንቊ መጽሔት ጋራ ያደረገው የቃለ ምልልስ ቆይታ ሁለተኛ ክፍል ቅዳሜ፣ መስከረም ፲፰ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም ታትሞ በወጣው ቅጽ 6 ቁጥር 102 የመጽሔቱ እትም ለንባብ በቅቷል፡፡ ቃለ ምልልሱ፥ በታሪክ እና ቅርስ ምንነት፣ አጠባበቅና ጠቀሜታ ላይ የሚታዩ የአመለካከትና ተግባር ችግሮች፤ የቤተ ክርስቲያን፣ መንግሥትና ምእመናን ድርሻዎች፤ በቅዱስ ሲኖዶስ አሠራርና በዕርቀ ሰላሙ ቀጣይ ኹኔታዎች ዙሪያ ትኩረት አድርጓል፡፡

የ‘ፍም እሳቶች’ እምቢ ባይነትና ጽናት የሚያኮራን ነው

ማን ነው የሚለየው? የሚደፍረው?
ይህም ትውልድ ፍም እሳት ነው።
የታለ አንድነቱ…. የፍቅር ተምሳሌቱ?
አረ ጎበዝ…..
እምቢ በል!
እምቢ…. እምቢ…እምቢ…..

የማደንቃቸው ሮቤል አባቢያ ዲሞክራሲ ከደጅ እያንኳኳ ነው በሚለው ጽሁፋቸው ዘመነኛ ቀስቃሽና ነገን አመላካች የሆኑ የዜማ ርዕሶችን እያደናነቁ የሀገራችንን ትንሳዔ ህልውና አብሳሪ የሆነውን ቀስተደመና መሰል ሰንደቅዓላማ ወጣቶች ከፍ አድርገው ስለማውለብለባቸው በውብ ብዕራቸው ከኛም አልፎ ሌሎች እንዲረዱት በእንግሊዝኛ አቅርበውት ነበር። ፕሮፌሰር አለማየሁም ይህንን ከሰጡት በላይ መልሶ ለመስጠት የተዘጋጀን አቦሸማኔ ወጣት ትውልድ አድንቀው ጽፈዋል። ልሂቃኑ ባሉት ላይ በማከል የሀገራችንን ትንሳዔ በወጣቶቻችን ለነፃነት ቀናዒነትና አልበገር ባይነት እናይ ዘንድ እውነት መሆኑን የሚያመለክት ከዘረኝነት በላይ፣ ከሀይማኖት ልዩነትም ያለፈ፣ ከፖለቲካ ድርጅቶች አጥርም የዘለለ ሀገራዊ አንድነቱን ከፍ ያደረገ ማንነትን ሲገልጹ ማየት እጅግ አኩሪ መሆኑን ደግሞ ደጋግሞ መናገር ያስደስታል።

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ይህንን የማፊያ ቡድን በማፍረስ ታሪክ ይስሩ! በግርማ ሠይፉ ማሩ

Girma-Seifu2
በግርማ ሠይፉ ማሩ
ግርማ ሠይፉ ማሩ
በ2005 ዓ.ም የምክር ቤት ዘመን መጨረሻ ላይ የደህንነት መስሪያ ቤቱን በሚኒስትር ደረጃ ለማዋቀር የሚረዳ አንድ አዋጅ ለምክር ቤት ቀርቦ ፀድቆዋል፡፡ ይህ አዋጅ ሲፀድቅ ከነቅሬታዬ ያለኝ ድጋፍ መስጠቴ ይታወቃል፣ ለዚህ አዋጅ ድጋፍ መስጠት የፈለኩት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ከበረሃ ይዘውት የመጡት ልዩ ልዩ አፋኝ ቡድን ስለማይኖራቸው እንዲሁም ቀደም ሲል የነበሩትን አፋኝ ቡድንች ወደ አንድ መዋቅር በማጠቃለል ተጠሪነቱ ከተለያዩ መዋቅሮችና ግለሰቦች ወደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ (ወደ ተገቢው ማለት ነው) ቁጥጥር በማስገባት ለዜጎች ስጋት ሳይሆን ለዜጎች እና ለሀገር ደህንነት የሚስራ ተቋም ይሆናል በሚል ተስፋ ነው፡፡ ይህ ተስፋዬም ዝም ብሎ ሳይሆን በአዋጁ አንቀፅ 3 “ይህ አዋጅ በመላው ሀገሪቱ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡ በፌዴራልም ሆነ በክልል መንግስታት ደረጃ ሌላ የመረጃና ደህንነት ተቋም ማቋቋም አይቻልም” የሚል ድንጋጌ በመያዙ ነው፡፡ በመስከረም 19 እሁድ ዕለት አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በጠራው ሰላማዊ ሰልፍ “በሰላም” ከተጠናቀቀ በኋላ እጅግ አሰገራሚ የሆነ ተግባር አጋጥሞናል፡፡ ተስፋዬንም ስለአጨለመብኝ ይህን ጉዳይ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲያውቁትና የብሔራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎቱ ኃላፊውን ጠርተው ማብራሪያ እንዲጠይቁ መነሻ ለመስጠት ነው፡፡

ከአንድነት ፓርቲና ከ 33ቱ ፓርቲዎች የተሰጠ መግለጫ

udj 4 19አንድነት ፓርቲ ከ33ቱ ፓርቲዎች ስብስብ ጋር በመሆን ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ ለማድረግ ያቀዱት ሰላማዊ ሰልፍ በገዢው ፓርቲ (መንግስት) ክልከላ ሠልፉ ሊደረግበት ወደነበረው መስቀል አደባባይም ሆነ በአማራጭ ነት ያቀረቡት 9 አደባባዮች እንዳይንቀሳቀስ ተደርጎ ከአንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት እስከ ቀበና አደባባይ ባለው አስፋልት ላይ ቁጥሩ ከ80 ሺህ በላይ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በተገኙበት ደማቅ ሕዝባዊ ንቅናቄ ተደርጓል፡፡
ለዚህ ደማቅ ሕዝባዊ ንቅናቄ የአንድነት ፓርቲና የ33ቱ ፓርቲዎች አመራሮች አባላትና ደጋፊዎች ያደረጉት ያላሰለሰ ጥረትና ሕዝቡ የመንግሥትን ፀጥታና የፖሊስ ኃይሎች ማስፈራራት አልፎ የላቀ አዎንታዊ ምላሽ ከፍተኛ ድርሻ አበርክተዋል፡፡

የተቃውሞ ፓርቲዎች ሠላማዊ ሰልፍ በአዲስ አበባ

udj 5 19
አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትኅ ፓርቲ ከ 33ቱ ፓርቲዎች ጋራ በመሆን ለዛሬ በመስቀል አደባባይ የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ በፖሊስ ክልከላ የአንድነት ጽ/ቤት በሚገኝበት ቀበና መካሄዱ ተገለፀ።
የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር ሰልፉን ተከታትሎ ባደረሰን መረጃ መሰረት እጅግ በርካታ ሠላማዊ ሰልፈኞች ሠልፉን ለማከናወን ወዳቀዱበት መስቀል አደባባይ እንዳይሄዱ ፖሊስ መንገዱን በመዝጋት ተከላክሎዋል። ከ ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር ጋ ያደረግነውን ቃለ መጠይቅ ከድምፅ ዘገባው ያገኙታል።

ሀገር ማለት (ሠዓሊ አምሣሉ ገ/ኪዳን አርጋው)

faces-of-ethiopia

“መስቀል የሚያቃጥል (አይደለም)” ከሠማይ ወረደ ስለተባለው መስቀል ሲኖዶሡ ውሣኔ ይሰጣል - አቡነ እስጢፋኖስ

abune estifanos
በአቃቂ ቃሊቲ ገላን ጉራ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ባለፈው ነሐሴ ወር መጨረሻ ላይ ከሠማይ ወረደ ስለተባለው መስቀል ቅዱስ ሲኖዶስ ውሣኔ እስኪያስተላልፍ ህዝቡ በትዕግስት እንዲጠባበቅ የአዲስ አበባና የጅማ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ አሣሠቡ፡፡ “መስቀል ከሠማይ ወርዷል አልወረደም? ትክክለኛ ነው አይደለም?” የሚለውን ለመመለስ የግድ ቅዱስ ሲኖዶሡ ጉዳዩን መርምሮ ውሣኔ ሊያስተላልፍበት ይገባል ያሉት ብፁዕነታቸው፤ ይህን ለማድረግም ጉዳዩን ለቅዱስ ሲኖዶሱ ቋሚ አባላት እንዳሣወቁ ተናግረዋል፡፡ መስቀሉ እንደተባለው ከሠማይ የወረደ አለመሆኑ ከተረጋገጠም የቤተክርስቲያኒቱ ሃላፊዎች ይጠየቁበታል ብለዋል-ብፁዕነታቸው፡፡

አዲሱ የኢህአዴግ አሰላለፍ (ተመስገን ደሳለኝ)

Temesgen Desalegn
ኢህአዴግ ከቀድሞ ሊቀ-መንበሩ አቶ መለስ ዜናዊ ህልፈት በኋላ በተከሰተበት ውስጣዊ ልዩነት በተለዋዋጭ የኃይል ሚዛን ሥር ለማደር በመገደዱ የስልጣኑን መዘውር የሚያሽከረክረውን አካል ለመለየት አዳጋች ነበር፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ይህ ሽኩቻ መፍትሄ ማግኘቱን የሚያመላክቱ ሁናቴዎች መፈጠራቸውን የውስጥ አወቅ መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡
እንደ መግቢያ
ድንገቴው የመለስ ህልፈት ህወሓትን ቢከፍለውም፣ ብአዴን ራሱን እንዲያጠናክር መደላድል ፈጥሮለታል፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያት መለስ ዘመኑን ሙሉ በብአዴን ታማኝነት ላይ ጥርጣሬ ስላልነበረው ቀድሞውንም እንዲዳከም ባለማድረጉ ይመስለኛል፡፡ እርሱ በአይነ ቁራኛ ይጠብቀው የነበረው ህወሓትን ነበር፤ በተለይም በሠራዊቱ እና በደህንነቱ ውስጥ ‹‹ተፅእኖ መፍጠር ይችላሉ›› የሚባሉት አቦይ ስብሃት ነጋ እና የትግራይን መዋቅር በእጁ ያደረገው የቀድሞ የክልሉ አስተዳዳሪ ፀጋዬ በርሄ በጥርጣሬ ዓይን የሚታዩ ሆነው ቆይተዋል፡፡

አዲሱ የኢህአዴግ አሰላለፍ (ተመስገን ደሳለኝ)

Temesgen Desalegn
ኢህአዴግ ከቀድሞ ሊቀ-መንበሩ አቶ መለስ ዜናዊ ህልፈት በኋላ በተከሰተበት ውስጣዊ ልዩነት በተለዋዋጭ የኃይል ሚዛን ሥር ለማደር በመገደዱ የስልጣኑን መዘውር የሚያሽከረክረውን አካል ለመለየት አዳጋች ነበር፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ይህ ሽኩቻ መፍትሄ ማግኘቱን የሚያመላክቱ ሁናቴዎች መፈጠራቸውን የውስጥ አወቅ መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡
እንደ መግቢያ
ድንገቴው የመለስ ህልፈት ህወሓትን ቢከፍለውም፣ ብአዴን ራሱን እንዲያጠናክር መደላድል ፈጥሮለታል፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያት መለስ ዘመኑን ሙሉ በብአዴን ታማኝነት ላይ ጥርጣሬ ስላልነበረው ቀድሞውንም እንዲዳከም ባለማድረጉ ይመስለኛል፡፡ እርሱ በአይነ ቁራኛ ይጠብቀው የነበረው ህወሓትን ነበር፤ በተለይም በሠራዊቱ እና በደህንነቱ ውስጥ ‹‹ተፅእኖ መፍጠር ይችላሉ›› የሚባሉት አቦይ ስብሃት ነጋ እና የትግራይን መዋቅር በእጁ ያደረገው የቀድሞ የክልሉ አስተዳዳሪ ፀጋዬ በርሄ በጥርጣሬ ዓይን የሚታዩ ሆነው ቆይተዋል፡፡

Sunday, September 29, 2013

ኢሕአዴግ የሕዝቡን ልብ ያውቃል፤ ይፈራዋልም!

በፍቃዱ ዘ ሀይሉ
የዛሬውን ሰልፍ ለመታደም ስወስን ብዙ ሰው እንደሚገኝ ገምቼ ነበር። አልተሳሳትኩም፣ የዞን ዘጠኝ ጓደኞቼን ጨምሮ ሌሎችም በፌስቡክና ከፌስቡክ ውጪ የማውቃቸው አራማጅ/ተራማጆች ሁሉ በጠዋቱ ተሰባስበዋልተያይዘን ስንሄድ፤ ቀበና ያለወትሮዋ በእሁድ ምድር ደምቃለች።
ሰልፉ ገና ከመነሻው መድመቁ መንገዱን ካልዘጉት በመቶ ሺሕዎች የሚቆጠር ሰው እንደሚታደም እርግጠኛ ሆንኩ።ሰልፈኛው ቁጥሩ እየገፋ ቢመጣም የትራፊክ ፖሊሶቹ መኪና ማገድ የፈለጉ አይመስልም። ፖሊስ በቀበና ዞረን ወደ ጃንሜዳ እንድንሄድ ግፊት ማድረጉን ቀጠለ። የፖሊስ አባላት አጥር ሰርተው በመቆም ሰው እንዳያልፍ ጣሩ። ኃላፊዎች ጃንሜዳ ሰልፍ ማድረግ ሕገወጥ ነው ተብለው ዘጠኝ አማራጭ ቢሰጣቸውም አሻፈረኝ አሉ። ሕዝቡ ገፍቶ መንገዱን ሲጀምር ትራፊክ ቢቋረጥም ፖሊሶችም መንገዱን አጥረው ያዙት። በየመንገዱ ዳር ተኮልኩለው የሚጠብቁትን ሰዎችም የመንግሥት ኃይሎች ይበትኗቸው ነበር። ሰልፉን ለመቀላቀል ከኋላ ካልሆነ በቀር ከፊት ትንሽ ድፍረትም፣ ትግልም ይጠይቅ ነበር።