Sunday, July 26, 2015

የተደበቀው የህወሓት ማንነት ከደደቢት እስከ ቤተ መንግስት – ክፍል አንድ

tigrai
ታላቋንና ገናናዋን ምድር ኢትዮጰያ ሲያስተዳድር እና ሲመራ ለሺህዎች ዓመታት የዘለቀው የዘውድ ስረዓት ህልፈቱን ዓይቶ ግብዓተ መሬቱ ተፈፅሞ 225ኛው ንጉሰ ነስት ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ ከዙፋናቸው ወርደው ደርግ በትረ ስልጣኑን ጨብጦ የአገሪቱ ፖለቲካዊ መፃኢ ሁኔታ በአምባገነናዊና ዴሞክራሲያዊ መንታ መንገድ ላይ ቆሞ ወደ የትኛው አቅጣጫ እንደ ሚሄድ ሳይታወቅ ከአያቶቻቸው ክህደትን እየተማሩ ያደጉት አባቶቻቸው አገርና ወግናቸውን ለነጭ ሸጠው የሚያገኙትን እና አያቶቻቸው ገላቸውን ለጣሊያን ቸርችረው የሚለቅሙትን ሶልዲ እየበሉ ያደጉ የባንዳ ልጆች በህዝብ ላይ ጭምር በቀል አርገዘው ደደቢት በርሃ በመውረድ ሸፈቱ፡፡

በሕወሓት ወታደሮች ውስጥ አለመተማመኑ ነግሷል – በጀነራል ሳሞራ የኑስ ቡድን እና በሌ/ጀነራል አብረሀ ወ/ማርያም ቡድን መካከል ያለው ልዩነት ተካሯል

* ህዝባዊ‬ ወያኔ ሓርነት ትግራይ በሚቆጣጠረው መከላከያ ሰራዊት ውስጥ እርስበርስ አለመተማመንና ጥርጣሬ አይሏል፡፡
‪* የህወሓት‬ አገዛዝ ከሱዳን ጋር የተፈጠረውን ወታደራዊ ግጭት የህዝቡን ትኩረት ሊያስቀይርበት በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡
* የህወሓት አገልጋይ የሆኑ “የአማራ ክልል” ባለስልጣናት ወደ ወልቃይት ሄደው በአካል ህዝቡን እንዲያነጋግሩ ከህወሓት ከፍተኛ ባለስልጣናት ቀጭን ትዕዛዝ መተላለፉ ታወቀ፡፡

ቁልቁለት መንገድ !

ስለዚህ ልጅ ላለማውራት ብዙ ጥሪያለሁ፣ ግን ስለኔ ካላወራቹ ብሎ ጨቀጨቀን፣ ያው በስራው ነው የጨቀጨቀን፣ የሚሰራቸው ስራዎች ትዕግስት ያስጨርሳል ሰዎች በወዳጅነት ቤታቸው አስገብተው ያሳዩትን ዛሬ እነሱን ማጥቂያ አድርጎ ሲጠቀመው ማየት ያሳዝናል፣ ያሳፍራል፣ በእልህ እያደረጋቸው ያሉ ነገሮች አድርባይ፣ ዘረኛ፣ ሌሎችም የሚገልፁት አይመስለኝም በጣም እየወረደ ነው ያለው ቁልቁል መውረድ የጀመረ እየተንከባለለ በመሃል ሊሞት ይችላል ግን ሞቶም ቁልቁል መውረዱ አያቆምም ይሆናል፣ ያ ማለት አልሞተም ማለት አይደለም፣ ያው የቁልቁል ጉዞ ቀላል ሰለሆነ ሬሳም ይጓዘዋል ማለት ነው !!!

ፍርድ ቤቱ ከጅብ ላያስጥል

ሐምሌ 2 /2004 ለሊት ሰባት ሰዓት ማዕከላዊ የደረሰው ጋዜጠኛ የሱፍ ጌታቸው ፍርድ ቤት በቀረበበት ወቅት የደረሰበትን አሰቃቂ ድርጊት አስረድቷል፡፡
በዚህ የተበሳጩት የማዕከላዊ ቢሮ ቁጥር 49 መርማሪዎች ኢንስፔክተር አለማየሁ፣ዘመድኩንና ጸጋዬ የተባሉ የሱፍን ከፍርድ ቤት መልስ ቢሯቸው ድረስ በማስመጣት
‹‹ፍርድ ቤት ሄደህ መጥሪያ ይዘህልን መጣህ አሉ ባክህ?››
‹‹የደረሰብኝን ከመናገር ውጪ ምን አጠፋሁ?››
ባገኙት ነገር ሁሉ ወረዱበት ጾሙን ለመፍታት እየተዘጋጀ የነበረው የሱፍ ዱላውን መቋቋም ተስኖት ተዝለፍልፎ ወደቀ፡፡

ፖለቲካን በቅርበት የሚከታተለው የሃገሬ ሰው ደስ የሚለኝ

ፖለቲካን በቅርበት የሚከታተለው የሃገሬ ሰው ደስ የሚለኝ አንድ ባህሪው በብሶቱ የሚያላግጡ ተቃዋሚ ፖለቲከኛ ነን ባዮችንና ያልሆኑትን ለፕሬስ ነፃነት የማሆነው የለም ባይ ጋዜጠኞችን እንደሞተ ሰው የሚረሳው ነገር ነው፡፡ ለምሳሌ አቶ ልደቱን ቀብሮ እንደገባ እርስት አድርጎ ያን “አቴንሽን” ፈላጊ ፍጥረት ቀዝቀዝ ያለ የጨዋ በቀል ተበቅሎታል፡፡ ልታይ ልታይ ባዩ ልደቱ ከምንሰድበው ይልቅ ስንረሳው ያቃጠለንን ያህል የተቃጠለ ይመስለኛል፡፡ “ሶስተኛ አማራጭ ነኝ ፤የማርያም መንገድነኝ" ቢልም ጆሮ የሚያውሰው አላገኘምናየፖለቲካ ሞቱን ተቀብሎ እየሞታት ነው! የምንሰድበው ጊዜማ ‘የኢትዮጵያ ህዛብ ሁሉ አሉባተኛ ነው፣ የኔ ምጡቅ አስተሳሰብ ከአስር አመት በፊት የሚገባውም አይመስለኝ እናም ይህ ትውልድ ካተቀየረ የኔ ምቱቅነት ሊታወቅ አይችልም’ እያለ ሲመፃደቅ ነበር፡፡ አሁን ግን የማይወደውን መረሳት ተቀብሎ ከፖለቲካ ድንዛዜው ጋር ቀርቷል፡፡ 

Saturday, July 11, 2015

ወያኔ አርበኞች ግንቦት 7 ጥቃት እንደሰነዘረበት አመነ

ሰሞኑን የአርበኞች ግንቦት 7 የነጻነት ታጋዮች በትግራይ እና በወልቃይት-ጠገዴ በተለያዩ ቦታዎች በወያኔ ሰራዊት ላይ ድንገተኛ የሽምቅ ውጊያ ጥቃት መሰንዘራቸውን በቃል-አቀባያቸው አማካኝነት ለኢሳት ቴሌቪዥን እና ራድዮ ሲገልጹ ሰንብተዋል።
ዜናው በኢሳትና በተለያዩ የማህበራዊ ድረገጾች በስፋት ሲሰራጭ በነበረበት ወቅት ዝምታን መርጦ የነበረው ወያኔ ኋላ ላይ የተዛቡ መረጃዎችን ሲያሰራጭ ከርሞ ዛሬ በራድዮ ፋና አማካኝነት አርበኞች ግንቦት 7 ጥቃት እንደሰነዘረበት ለማመን ተገዷል።
ራድዮ ፋና ባሰራጨው ዜና “ከሰላሳ የማይበልጡ የሻብያ ተላላኪዎች ከኤርትራ በሚያዋስነን ድንበር አካባቢ ሰርገው ለመግባት ሲሞክሩ ተደምስሰዋል” ብሏል።
ይሁንና ራድዮ ፋና በዜና ዘገባው ግጭቱ የተፈጠረባቸውን ቦታዎች እና ጊዜ ሳይጠቅስ ማለፍን መርጧል።

ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር የተናገሩት

‘’ንቅናቄያችን በአንድ ሰው ላይ፤ በሁለት ሰው ላይ፤ በአስር ሰዎች ላይ ብቻ የቆመ የፖለቲካ ድርጅት ሳይሆን የኢትዮጵያና የኢትዮጵያውያን የነፃነትና የዲሞክራሲ ስሜት መገለጫ የሆነ፤ ለዛ እስከመጨረሻው ድረስ ለመሄድ ዝግጁ የሆነ፤ በጣም ብዙ የተማሩ፤ ያውቁና የበቁ ብዙ የተሻለ ኑሮ መኖር ሲችሉ ለኢትዮጵያ ነፃነት እስከመጨረሻው ድረስ እንታገላለን ብለው የቆረጡ ሃይሎች ያሉበትና የተሰባሰቡበት ድርጅት ነው።

በአገርቷ ሁሉ ያሉ የቶርቸር እሥር ቤቶች የወያኔን ጭካኔ ነው የሚያሳዩት – የሚሊዮኖች ድምጽ

የወያኔው ሬድዋን ሁሴን ፣ እነ ርዮት አለሙ የተፈቱት መንግስት ማግናኒመስ (ትልቅ) ስለሆነ ነው እያለን ነው፣ ድርጅታችውን መልአካዊ አድርጎ ለማቅረብ ሲሞከር።ሆኖም፣ የገዢውች ማንነትን፣አ አዉሬነትን አሁን በአገሪቷ ዙሪያ ሁሉ ካሉ የቶርቸር ቻምበሮች (ክፍሎች) የሚሰሙ የሰቆቃ ጩኸቶች በትልቁ እያጋለጡ ነው።
ባልሰሩትና ባልፈጸሙት ወንጀል፣ ቢያንስ ሃያ ዘጠኝ የሚሆኑ በእሥር የሚማቁ የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችን አባላት አሉ። ፍርድ ተነፍገው በፍርድ ቤት የሚጉላሉ። ፍርድ ተዛቦቶ፣ በዉሸት ምስክርና በፖለቲካ መመሪያ ጥፋተኛ ብለው፣ በቃሊቲ፣ በዝዋይ፣ በሸዋሮቢት በቂሊንጦና፣ በማእከላዊና በተለያዩ ዘግናኝ ጉላግ እሥር ቤቶች፣ ሰብዓዊ መብታቸው ተረግጦ፣ በአሁኑ ሰዓት እየተሰቃዩ ነው።

በሰማያዊ ፓርቲ አባላት ላይ ተከፈተው የእስር ዘመቻ ዛሬም ቀጥሏል

ዛሬ ሐምሌ 4 2007ዓ.ም ረፋዱ ላይ አቶ መርከቡ ሃይሌ ሰሞኑን ሲከታተሉት በነበሩ ደህንነቶች እና ፖሊስ ታፍኖ ለጊዜው ወደአልታወቀ ቦታ ተወስዷል፡፡
በተመሳሳይ ሁኔታ ትናንት በኢህአዴግ የታሰረው አቶ ደብሬ አሸናፊ ዛሬ ረፋዱ ላይ ቤቱ በከፍተኛ የታጠቁ ሃይሎች ተከቦ ፍተሻ የተካሄደበት ሲሆን አሁን በጉለሌ አካባባቢ ላዛሪስት ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ እንደሚገኝ ተረጋጧል፡፡

ሰበር ዜና ከወደ ሸዋሮቢት!!!


የሸዋሮቢት ከተማ የሰማያዊ ፓርቲ አመራርና የቀድሞው አንድነት አባላት ዛሬ ከ3:00— 4:00 ሰአት በታጠቁ የመንግስት ሀይሎች ከያሉበት ታድነው በመታሰር ላይ መሆናቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል። በዚህም መሰረት እስካሁን ድረስ
1 አቶ ዘነበ ደሳለኝ
(የተወካይ ም/ቤት እጩ የነበረ።

ጀግናው የዓርበኞች ግንቦት 7 ሠራዊት ያቀጣጠለው የነፃነት እሳት አሁንም በሰሜን ተራሮች እየጨሰ ነው፥

ጀግናው የዓርበኞች ግንቦት 7 ሠራዊት ያቀጣጠለው የነፃነት እሳት አሁንም በሰሜን ተራሮች እየጨሰ ነው፥
ጦርነቱ እንደቀጠለ ነው፣ አያያዙም እጅግ ኃያል ነው፤
የተጀመረው ትንቅንቅ እስከነፃነት አደባባይ ነውና፤ የተነሳውን ማዕበል የሚመልስ አንዳች ምድራዊ ኃይል የለም።

Thursday, July 9, 2015

የህዝበ ሙስሊሙ ኮሚቴ ጠበቃ ተማም አባቡልጉ የጥብቅና ሙያቸው ኮሚቴዎቹ የጥፋተኝነት ብይን በተላለፈበት ቀን መሰረዙ ታወቀ

ጠበቃ ተማም አባቡልጉ
ጠበቃ ተማም አባቡልጉ

ሰበር ዜና ቢቢኤን
ቢቢኤን ሃምሌ 2/2007

የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ጠበቃ የሆነው ጠበቃ ተማም አባቡልጉ በፍርድ ቤት ላይ በሚያደርጋቸው ክርክሮች በተለይም መንግስት ከጅሃዳዊ ሀረካት ጀምሮ የሰራቸውን ሸፍጦችና ኢትዪጲያዊ ውስጥ የፍትህ ስርአቱን ዝቅጠት በመረጃና በህግ በማጣቀስ በተለያዩ ሚዲያዎች ላይ በማጋለጣቸው ምክኒያት ከዚህ ክስ ተመስርቶባቸው እንደነበር ይታወቃል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ማስፈራሪያና ዛቻዎች ከመፈጸማቸውን ሌላ እብድ በሚመስል ሰው በመላክ ድብደባ እንደተፈጸመባቸው ይታወቃል፡፡

2 ዓለም አቀፍ ሽልማቶችን እስር ቤት ሆና ያሸነፈችው ርዕዮት ዓለሙ

reyot
ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ ተፈታች
(ዘ-ሐበሻ) ጋዜጠኛና መምህርት ርዕዮት ዓለሙ ትናንት ጁላይ 9 ቀን 2015 ዓ.ም የ እስር ጊዜዋን አጠናቃ ተፈታች። የመንግስት ሚድያዎች ጋዜጠኛዋ የአመክሮ ጊዜ ተሰጥቷት እንደተለቀቀች አድርገው ቢዘግቡም እውነታው ግን ርዕዮት የአመክሮ ጊዜዋን ጨርሳ የነበረው ባለፈው ጥቅምት ወር ነበር።
በሽብር ወንጀል ተከሳ 14 ዓመት ተፈርዶባት የነበረችው ይህችው ጋዜጠኛ በይግባኝ ቅጣቱ ወደ 5 ዓመት ዝቅ ብሎላት የነበረ ሲሆን እነዚህን ዓመታት በእስር አሳልፋ ከቤተሰቦቿ ጋር ተቀላቅላለች።

የርዕዮትን: የማህሌትንና የኤዶምን ከህወሀት ማጎሪያ እስር ቤት ነጻ መሆን ውስጤ የፈጠረውን

የርዕዮትን: የማህሌትንና የኤዶምን ከህወሀት ማጎሪያ እስር ቤት ነጻ መሆን ውስጤ የፈጠረውን �ደስታ እያጣጣምኩ እያለ ድንገት በትዝታ አምስት ወራት ወደ ሁዋላ ሄድኩኝ- -ከኤርትራ በረሃ:: ይህቺን ኢትዮጵያን ከህወሀት እስር ቤት ነጻ ለማውጣት ብረት ያነሳችውን እህታችንን ላስተዋውቃችሁ::
አርበኛ ሀና ትባላለች:: የ23 ዓመት ወጣት ናት:: የአርበኞች ግንቦት 7 ተዋጊ ወታደር ስትሆን በተለያዩ አውደ ውጊያዎች ተሳትፋለች:: በኤርትራ በረሃ ስማቸው ከጀግንነት ጋር ከሚነሳላቸው አርበኞች መሃል ሀና ግንባር ቀደም ናት:: ስሟ በአርበኞች መንደር ገኖ ይነሳል::

Sunday, July 5, 2015

በምስራቅ ጎጃም ዞን አርሶ አደሮች በጅምላ እየታሰሩ ነው ተባለ

ዜጎች በፖለቲካ አመለካከታቸው ከቀያቸው እየተፈናቀሉ ነው
በምስራቅ ጎጃም ዞን አርሶ አደሮች ‹‹የማዳበሪያ ዕዳ አልከፈላችሁም›› በሚል በገፍ እየታሰሩ መሆኑን ምንጮች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ አርሶ አደሮቹ ከ1989 ዓ.ም ጀምሮ ወስዳችኋል የተባሉትን የማዳበሪያ እዳ እንዲከፍሉ እየተጠየቁ እንደሆነ የገለጹት ምንጮች በአንድ ቀበሌ ብቻ በመቶዎች የሚቆጠሩ አርሶ አደሮች በጅምላ መታሰራቸውን ገልጸዋል፡፡ አርሶ አደሮች እነሱ ወስደውታል የተባለውን ብቻ ሳይሆን በሞት የተለዩትን ዘመዶችን ዕዳ ጭምር ካልከፈላችሁ ተብለው ለእስር እየተዳረጉ መሆኑም ተሰምቷል፡፡ የጅምላ እስሩ ከሰኔ 15/2007 ዓ.ም እንደተጀመረ የገለፁት የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ለሳምንት ያህል የታሰሩት አርሶ አደሮች ሰኔ 21/2007 ዓ.ም ቢለቀቁም ሌላ ዙር እስር በመጀመሩ በርካታ አርሶ አደሮች ለእስር ሰለባ ሆነዋል ብለዋል፡፡

ሮን አለማየሁ 6 ወር ተፈረደባት

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
መንግስት አይ ኤስ አይ ኤስን ለመቃወም በጠራው ሰልፍ ሰበብ ታስራ ‹‹ሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ በማወክ›› የተከሰሰችው ሜሮን አለማየሁ የ6 ወር እስር ተፈረደባት፡፡ ሜሮን አለማየሁ ሚያዝያ 14 በተጠራው ሰልፍ ላይ ‹‹ወያኔ ሌባ፣ መንግስት የለም፣ አትነሳም ወይ፣ የታረደው ወገን ያነተ አይደለም ወይ›› በሚል ሁከትና ብጥብጥ ፈጥራለች ተብላ በተከሰሰችበት በዋስ ወጥታ ጉዳዩን ስትከታተል የቆየች ሲሆን ዛሬ ሰኔ 26/2007 ዓ.ም በጎፋ ፍርድ ቤት ቀርባ 6 ወር ተፈርዶባታል፡፡

በህወሓት መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ አዛዦች መካከል ተፈጥሮ የቆየው መከፋፈል ተካሯል

በህወሓት መከላከያ ሰራዊት ውስጥ ተፈጥሮ የቆየው መከፋፈል በሁለት ፅንፍ የቆመ ሲሆን አንደኛው ቡድን በኤታማጆር ሹሙ ጀነራል ሳሞራ የኑስ ስር ሁለተኛው ቡድን ደግሞ የምስራቅ ዕዝ አዛዥ ከነበረው ሌ/ጀነራል አብርሃ ወ/ማርያም ጎን የተሰለፉ ናቸው፡፡ ሌ/ጀነራል አብርሃ ወ/ማርምን ከዕዝ አዛዥነቱ አንስቶ ወደ መከላከያ መምሪያ የማዛወሩ የእነ ጀነራል ሳሞራ የኑስ ቡድን ዕቅድ በሌ/ጀነራል አብርሃ ቡድን የበላይነት ሊከሽፍ ችሏል፡፡ ሆኖም ግን ሌ/ጀነራል አብርሃ ወ/ማርያም ከምስራቅ ዕዝ ተነስቶ የደቡብ መስራቅ ዕዝ አዛዥ መሆኑ ታውቋል፡፡

ተቃዋሚዎች የኦባማን ጉብኝት ተቃወሙት

በኢትዮጵያ ስላለው የመብት ረገጣ 90 ሚሊዮን ህዝብ ምስክር ነው”
– ለእድገታችን አሜriካ ምስክር ሆነችልን ማለት ውጤት አያመጣም – ዶ/ር መረራ
በአለማቀፍ ታላላቅ የሚዲያ አውታሮች መነጋገሪያ ሆኖ የዘለቀው የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ኢትዮጵያን የመጐብኘት ውጥን አሜሪካ አምባገነን መንግስታትን ከመደገፍ የመነጨ በመሆኑ እምብዛም ትኩረት የሚሠጠው ጉዳይ አይደለም ብለዋል – የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች፡፡
ዶ/ር መራራ ጉዲና
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሣይንስ መምህር እና የመድረክ የፖለቲካ ማህበር አመራር ዶ/ር መረራ ጉዲና የፕሬዚዳንቱ ጉብኝት ዋነኛ ትኩረቱ የሽብር ጉዳይ ነው ይላሉ፡፡

ወያኔ አርበኞች ግንቦት 7 የከፈተበትን ጦርነት ከህዝብ ለመደበቅ እየሞከረ ነው

ባለፉት ሦስት ቀናት የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዮች ትግራይ ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች የወያኔን ሃይል ገጥመው የወያኔ መኮንኖችን ጨምሮ በርካታ የወያኔ ሰራዊት አባላትን እንደገደሉ በቃል-አቀባያቸው አማካኝነት ለኢሳት ቴሌቪዥን ገልጸዋል። ለጥቀውም እስከ ትላንት ድረስ ውጊያው ቀጥሎ እንደሚገኝ በድጋሜ ዜናውን አብስረዋል።

በወያኔ ዘረኛና ግፈኛ አገዛዝ የተንገፈገፈው የኢትዮጵያ ህዝብም ጆሮውን አቅንቶ ሁኔታውን በመከታተል ላይ ነው። ቀድሞውንም የወያኔ ሥርዓት ያለ ሃይል ትግል አይንበረከክም፣ ኢትዮጵያ ውስጥ የፖለቲካም ሆነ የሥርዓት ለውጥ ሊመጣ የሚችለው በተቃውሞው ጎራ የተሰለፉት ተባብረው በወያኔ ላይ ክንዳቸውን ሲያሳርፉ ብቻ ነው ብለው የሚያምኑት ኢትዮጵያውያን አርበኞች ግንቦት 7 በወያኔ ላይ የከፈተውን ማጥቃት በከፍተኛ ደስታ ነው የተቀበሉት።
አንዳንዶች አርበኛውን በገንዘብ ለመደገፍ እና ለማጠናከር ከወዲሁ እንቅስቃሴ ጀምረዋል።

በህወሓት አገዛዝ እየተሰቃዩ ላሉ ወገኖቻችን ደህንነት የሚደረገው ዓለም አቀፍ ጫና ይቀጥል!

def-thumbከሣምንት በፊት የብሪታኒያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን የሚመለከት አንድ መግለጫ አውጥቷል። በዚህ መግለጫው፣ አንዳርጋቸው ጽጌ ለአንድ ዓመት ሙሉ መሠረታዊ የሆኑ የታሳሪዎች መብት እንኳን ተነፍጎት ባልታወቀ እስር ቤት የሚገኝ መሆኑ እና በእንግሊዝ ባለሥልጣናትና በቤተሰቦቻቸው እንዲጠየቅ፣ ቋሚ የቆንስላና የህግ ምክር እንዲያገኝ በተደጋጋሚ የቀረበው ጥያቄ በወያኔ አገዛዝ ውድቅ መደረጉ በሁለቱ አገራት መካከል ያለው መልካም ግንኙነት የሚያሻክር መሆኑ ከወትሮው ጠንከር ባሉ ቃላት ገልጿል። አዲስ አበባ የሚገኘው የብሪታኒያ አምባሳደርም እንደዚሁ ከተለመደው ዲፕሎማሲያዊ ለስላሳነት ወጣ ያለ ያለ መግለጫ አዲስ አበባ ውስጥ ለሚታተመው ሪፓርተር ጋዜጣ ሰጥቷል።

አይቀሬዉ የድል ፊሽካ ተነፋ!! አርበኞች ግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል በወያኔ ሰራዊት የኃይል ጥቃት ሰነዘረ



 ሀሙስ ዕለት ሰኔ 25 2007 ዓ.ም የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ሰራዊት በትግራይ ክልል ቀፍታ መሲል፣ ሆርጃሞ እና ማይሰገል ላይ ህወሓት ከሚቆጣጠረው የ24ኛ ክፍለ ጦር፣ ፌደራል ፖሊስና ልዩ ኃይል ጋር ባደረገው ለአራት ሰዓታት የዘለቀ ከባድ ጦርት ከፍተኛ ጉዳት አደረሰ፡፡

የአርበኞች ግንቦት 7 አርበኛ ተጋዮች በትግራይ ቀፍታ መሲልና ሆርጃሞ ላይ መሽጎ ያገኙትን ከሶስት ክፍሎች ማለትም ከ24ኛ ክፍለ ጦር፣ ከፌደራል ፖሊስና ከልዩ ኃይል የተውጣጣና እስከ አፍንጫው የታጣቀ ቁጥር ስፍር የሌለው ጦር ከቀኑ ሰባት ሰዓት እስከ አስር ሰዓት ለተከታታይ ሦስት ሰዓታት በጥይት ቆልተውታል፡፡