Thursday, October 31, 2013

እረፍት የሚነሳው ህምም የኮንትራት ሰራተኞች ስቃይ፣ የእኛ ፍርሃትና የፖለቲከኞች ጭካኔ

saudi 1
አዎ ተንቀሳቃሽ ምስል ጭምር በመረጃነት የታጨቀባቸውን የመልዕክት መረጃ ጭብጦች እውነታ ለማረጋገጥ ወደ ጅዳ ቆንስል አመራሁ … መኪናየን አቁሜ ትንሽ እንደ ተራመድኩ እያለ ከፊት ለፊቴ  አንዲት ልጅ እግር ኢትዮጵያዊ ብቻዋን እያወራች ስታልፍ ስመለከት በመደናገጥ ሰላምታ አቅረብኩላት፣ መልስ ሳትሰጠኝ አለፈች!  ደነገጥኩና ባለሁበት ቆሜ በአይኔ ተከተልኳት …

በዳኞች መካከል የሚታየው አለመግባባት የፍርድ ሂደቱን እያጓተተው ነው

 ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ በከፍተኘው ፍርድ ቤት ባለው የአስተዳደር ቊንጮ ማለትም በዋናው ፕሬዚዳንት በዳኛ ውብሸት ሽፈራውና በምክትሉ ማሃል ያለው አለመስማማት እየጨመረ በመሄዱ የፍርድ አሰጣጥ ሂደቱን እያበላሸው መሆኑን ውስጥ አዋቂዎች ገለጹ ።አሁን ባለው አሰራር ተሰሚነት ያለው የኢሃዴግ አባል የሆነው ምክትሉ ሲሆን ፣  ፕሬዘዳንቱ የኢሃዴግ አባል ባለመሆኑ ተሰሚነት አጥቷል ይላሉ ምንጮች:።

ሰርካለም ፋሲል እጅግ ልብ የሚነካ ደብዳቤ እስር ቤት ለሚገኘው እስክንድር ነጋ በድምጽ ላከች።

የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ባለቤት ጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል ከ3ወራት ዝምታ በኋል ተነፈሰች። እጅግ ልብ የሚነካው የሰርካለም መልዕክት ዛሬ በኢሳት ሬዲዮ ላይ ታገኙታላችሁ። በ3 የደህንነት ሃይሎች መሃል አዲስ አበባ ላይ የታፈኑት የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ብሄራዊ ምክር ቤት አባል አቶ አበበ አካሉ መናገር የማልፈልገውን ፈጸሙብኝ ይላሉ። ለባሌቤቴም ለልጆቼም አልተናገርኩም። ሆድ ይፍጀው! አሉ። ምን ይሆን?

የወያኔ ዘረኝነት ፖሊሲ ትግርኛ የማይናገሩ ኢትዮጵያዉያንን የበይ ተመልካች እያደረገ መሆኑን የግንቦት 7 ጥናታዊ ሪፖረት አጋለጠ

የወያኔ ዘረኝነት ፖሊሲ ትግርኛ የማይናገሩ ኢትዮጵያዉያንን የበይ ተመልካች እያደረገ መሆኑን የግንቦት 7 ጥናታዊ ሪፖረት አጋለጠ

ethio-metal-coorporation_jan_2013-small

ባለፈዉ ሳምንት ኢትዮ ተሌኮም ዉስጥ ስር እየሰደደ የመጣዉን የወያኔ ዘረኝነት በመረጃ በተደገፈ ጥናታዊ ዘገባ ለህዝብ ይፋ ያደረገዉ የግንቦት 7 የአገር ዉስጥ ኢንተሊጀንስ ዘርፍ በዛሬዉ ዕለት ደግሞ በተመሳሳይ ደረጃ አደረጃጀቱን፤ አወቃቀሩንና የሰዉ ኃይል አመዳደቡን ለአንድ አመት ሙሉ በቅርበት የተከታተለዉን የኢትዮጵያ ብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮርፖሬሺንን ጥናታዊ ዘገባ ለኢትዮጵያ ህዝብ ይፋ አድርጓል። ለኢትዮጵያ ከባድ እንዱስትሪ ግንባታ መሠረት ለመጣልና በአገሪቱ ኮንስትራክሺን እንቅስቃሴ ከፍተኛ ሚና እንዲጫወት ታስቦ የተዋቀረዉ የብረታብረት እንጂኔሪንግ ኮርፖሬሺን የኢትዮጵያ መሆኑ ቀርቶ ሙሉ በሙሉ በትግርኛ ተናጋሪ የህወሀት መኮንኖች እጅ መግባቱን ያጋለጠዉ የኸዉ የግንቦት 7 ጥናት ኮርፖሬሺኑ ከዋና ዳይረክተር እስከ ተራ ቴክኒሺያኖች ስረስ የህወሀት አባል በሆኑ የትግራይ ተወላጆች ቁጥጥር ስር ወድቋል ብሏል። የጥናቱ ሙሉ ዘገባ እንደሚገተለው ቀርቧል።

International Commission of Jurists (ICJ): Ethiopian Leaders to Face a Trial for Genocide

by Betre Yacob
The International Commission of Jurists (ICJ) reported to have begun to work to bring Ethiopian authorities to justice for having committed a genocide in the Ogaden region. The International Commission of Jurists is a known international human rights organization composed of jurists (including senior judges, attorneys, and lawyers). The commission is known for its dedication to ensuring respect for international human rights standards through the law.

Ethnic politics versus individual rights


Ethiopia_Regional_map_of-FDRE
By Messay Kebede (PhD)
The prevailing assumption, which originates from the ideologues of ethnic politics, is that identity politics is a direct consequence of social inequalities resulting from the political or/and economic marginalization of groups of people defined by linguistic, racial, cultural, or religious particularisms. In response to the discrimination perpetuated by dominant groups, excluded groups politicize their particularisms to fight back and win equal treatments.

(Wikileaks) the Late Prime Minister Meles zenawi terrified by the ONLF a serious threat.

220px-Meles_Zenawi_-_World_Economic_Forum_Annual_Meeting_2012
oct31.2013
US cable: Ethiopia govt terrified by ONLF rebels
[ONLF fighters from Ethiopia's Ogaden region]
ONLF fighters from Ethiopia’s Ogaden region
© ONLF/afrol News
afrol News – The low-level conflict in Ethiopia’s Ogaden region is far more dangerous to the government’s survival than earlier assumed, a secret US report reveals. Government fears for its future.

የተበተኑ የኢትዮጵያ ፍርስራሾች

ዳኛቸው ቢያድግልኝ
አገር ማለት ሕዝብ ነው ሕዝብም የሰዎች ስብስብ፡፡ መልክዐምድሩና የተፈጥሮ ሀብት ደግሞ የሰዎችን አኗኗርና አስተሳሰብ የሚቀርጽና ማንነትንም የሚያላብስ ነው። በየመንደሩና አካባቢው ያለው የተለያየ የአኗኗር ሁኔታ የቋንቋና የባህል መስተጋብር ደግሞ ትብብርንና አንድነትን የሚያወርስ እኔነትንና የእኔነትን የሚሰጥ ይሆናል። ኢትዮጵያዊነትም እንደዚያ ነው።
ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ግን በሁሉም አቅጣጫ ጥቃት ተሰንዝሮባቸው ያቺ የሰውን ዘር ትልቅ የመሆን ተስፋን የሰነቀች ምንጭ ትደርቅ ዘንድ የራስዋ ልጆች እኔ እበልጥ እኔ እበልጥ እያሉ በፉክክር ሊያጠፏት ይሽቀዳደማሉ።

የኢዴፓ_ገበና_ሲገለጥ (ሊነበብ የሚገባው ደባ)

የልደቱ_አያሌው_ኢዴፓ_በየትኛው_ሞራሉ_ነው_ተቃዋሚውንም_ይሁን_ገዢውን_ፓርቲ_የሚተቸው??
የአቶ ልደቱ አያለውን መጽሃፍ የጻፈው በወያኔ ልዩ ትእዛዝ አቶ
ገነነ አሰፋ ነው።
ዶክተር በየነ ጴጥሮስ እና ሻለቃ አድማሴ መላኩ በአቶ መለስ ትእዛዝ የወር ደምወዝ ነበራቸው።
ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በኢዴፓ ህልውና አያምንም። ዘላለም ህዝቡ ኢዴፓን በበጎ መንፈስ አያየውም። በአሁን ሰአት ለተፈጠረው ኢህአዴጋዊ አክራሪነት እና የፖለቲካ ጽንፈኝነት ተጠያቂው ኢዴፓ እና አመራሩ ናቸው። ኢዴፓ ብሎ ራሱን የሚጠራው በኢሕኣዴግ የጎለበተው ድርጅት ባካሄደው ስብሰባ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን እና ገዢውን ፓርቲ እንደተቸ እየሰማን ነው።

ግን ማነው ሽብርተኛ? እየሩሳሌም አርአያ

የገዢው ፓርቲ ቱባ ፈላጭ ቆራጭ ባለስልጣናት በነበሩት አቶ ገ/ ዋህድ፣ አቶ መላኩ፣ አቶ ወ/ስላሴ ወዘተ መኖሪያ ቤት ውስጥ በርካታ የጦር መሳሪዎችና የጭስ ቦንብ ጭምር በህገወጥ መንገድ እንደተያዙባቸው በክሱ ተመልክቷል። ገ/ዋህድ 10 ክላሽ
ደብቆ መገኘቱ አስደናቂ ነው። አቶ መለስ ዜናዊን ከጎኑ አስቀምጦ « ምድረ ኪራይ ሰብሳቢ አጭበርባሪ ነጋዴ አስይሻለሁ..» እያለ ሲዝት የነበረው ገ/ዋህድ ለርሱ ጉቦ ያልሰጡ 200 ነጋዴዎች በአንድ ኮንቴነር ውስጥ በማሰርና በመደብደብ ከፍተኛ በደል
ሲፈፅም ነበር። ዋናው ነጥብ ወዲህ ነው፤ ባለስልጣናቱ ያን ሁሉ የአገር ሃብት ሲዘርፉ ሕገወጥ መሳሪያ ታጥቀው እንደሆነ አውቀናል።

Wednesday, October 30, 2013

ኢትዮጵያ- የፖሊስ መንግስት ያንሰራፋባት ሀገር (ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረ ማርያም)

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረ ማርያም
ትርጉም ከነጻነት ለሀገሬ
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ ህገመንግስት በህግ ከለላ ጥላ በቁጥጥር ስር የሚውሉ ዜጎችን አስመልክቶ የሚከተሉትን መብቶች ያጎናጽፋል፡፡“በህግ ከለላ ጥላ በቁጥጥር ስር የዋለ ማንኛውም ሰው በህግ አግባብ መብቱ ተጠብቆ ይያዛል፡፡ ማንኛውም ሰው በሀሰት ለመረጃ ጠቀሜታ ተብሎ በማስገደድ እንዲያምን  ወይም የተባለውን እንዲቀበል አይገደድም፡፡ ማንኛውም በማስገደድ የተገኘ መረጃ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡“ ይላል አንቀጽ 19(2)(5)፡፡ እውነታው ሲታይ ግን ይህ የይስሙላ ሙበት የተጻፈበትን ወረቀት ዋጋ ያህል የለዉም፡፡

“የእስስት ምስል . . .አፈር ሲሏት ቅጠል“

by ጥላሁን ዛጋ /Tilahun Zaga/
ይህን የድሮ ዘመን ተረት ሳመጣ እስስት የምትባለዋን እንስሳ ስነ ተፈጥሮ፣ ተፈጥሮአዊ ምድቧን /ከየትኛው የእንስሳት ክፍል እንደምትመደብ/ ከአጥቢ ወይም ከሌላኛው እንደሆነ ለማጥናት እንዳልሆነ በቅድሚያ ልብ ይበሉልኝ. . .
ድሮ ድሮ በልጅነታችን ኳስሜዳ ወጥተን ከኳስ በኋላ ለኛ ብርቅዬ የሆነችውን እስስት ለማየት ብዙ ቀናትን ማድፈጥ ይጠበቅብናል፣ እንስሳይቱ እንዲሁ እንደዋዛ የምትገኝ ባለመሆኗ፣ ብትገኝም አብዛኛውን ጊዜ ካለችበት አካባቢ ጋር ስለምትመሳሰል ስትንቀሳቀስ ካልሆነ በስተቀር እሷነቷን ለማወቅ እጅግ በጣም አዳጋች ነው

ሕዝባዊ እምቢተኝነት በውጭ አገር፤ እንዴት?

ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በሁለገብ ትግል ወያኔ ማስወገድ ይገባል ብሎ የሚያምና ለዚህም የሚታገል ድርጅት ነው። “ሁለገብ ትግል” ሲባል ሰላማዊም ሰላማዊ ያልሆኑም የትግል ስልቶችን መጠቀም ማለት ነው። “ሁለገብ ትግል” ሲባል በአገር ውስጥም ከአገር ውጭም የሚደረጉ ትግሎች ማለት ነው።
ከዚህ አንፃር በውጭ አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ሚና ምን ሊሆን ይገባል?
በግንቦት 7 እምነት በውጭ አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን በድጋፍ ሰጭነት ሳይወሰኑ የትግሉ ቀጥተኛ ተሳታፊዎች መሆን ይኖርባቸዋል። በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን በወያኔ ጥቅሞችና ተቋማት ላይ በማመጽ ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚገኙ ኢትዮጵያዊያን አርዓያ መሆን ይኖርባቸዋል።

የፖለቲካ ርዕዮተ አለም ህሳቤዎች ከሰበአዊ መብት አስተምሮት አንጻር ሲቃኙ __ (ክፍል አንድ)

በሸንቁጥ አየለ (shenkutayele@yahoo.com)
እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ የፍቅር አስተምሮት ባለ አዕምሮ የሆኑ የሰበአዊ ፍጥረታትን ነብስ ከአጽናፍ አስከ አጽናፍ መሳጭ በሆነ መግነጢሳዊ ሀይል የመሳብ ብሎም በተስፋ ዓለም የማማለል ጉልበትን የተላበሰዉ የሰበአዊ መብት ህግ አስተምሮት የፖለቲካ የርዕዮተ አለም ቀማሪዎችን እና ተግባሪዎችን ወገብ ግን አማራጭ በማሳጣት ሲያንቀጠቅጣቸዉ ይስተዋላል:: የሰበአዊ መብት አስተምህሮት ብሎም ተግባራዊ አፈጻጸም ዋና የጉሮሮ አጥንት ሆኖ የሚገኘዉ ጉዳይ ግን በአንዲት አገር ዉስጥ የዲሞክራሲያዊ መንግስት መኖር ጉዳይ ስለሆነ የአስተምህሮቱ አቀንቃኞች ራስ ምታት ሆኖ ይገኛል::

የፖለቲካ ርዕዮተ አለም ህሳቤዎች ከሰበአዊ መብት አስተምሮት አንጻር ሲቃኙ

በሸንቁጥ አየለ (shenkutayele@yahoo.com)
  ክፍል ሁለት
በቀደመዉ ጽሁፍ ሰበአዊ መብት ምን እንደ ሆነ እና እንዴት በአለም የፖለቲካ አስተምህሮቶችን ፈተና ዉስጥ እንደጣላቸዉ ከሞላ ጎደል ለመዳሰስ ሞክረናል:: በተለይም የሰበአዊ መብት አስተምህሮት አንዳንድ አንባገነን እና ብልጣብልጥ መንግስታት ልማታዊ መንግስት ነን በማለት ልማት የማህበረሰቡ ሰበአዊ መብት መሆኑን በመዘንጋት ልማት የእነሱ ብቻ አጀንዳ እንደሆነ በማስመሰል ጥቂት ልማት ስለሰራን ለዘላለም በወንበሩ ላይ እንኑር የሚለዉን ክርክራቸዉን የሰበአዊ መብት አስተምሮት እንዴት ዉሃ የማይቁዋጥር ክርክር እንዳደረገባቸዉ ለማዬት ሞክረን ነበር::

የቦሌ ሩፋኤል ቤተክርስቲያን የድረሱልኝ ጥሪ አሰማች

ኢሳት ዜና :- የቦሌ ለሚ ቅ/ሩፋኤል የጻዲቁ አቡነ ኤዎስጣቲዎስ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ የሆኑት መልአከ ብርሀን ተከስተ ካሳሁን “የድረሱልን ጥሪን ይመለከታል” በሚል ርእስ ለለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የብጹዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ ረዳትና የጅማ ሀገረ ሰብከት ሊቀ ጳጳስ ለሆኑት ለ ብጹዕ አቡነ እስጢፋኖስ በጻፉት ደብዳቤ ላይ፣ የመንግስት ባለስልጣናት ቤተክርስቲያኑዋን በ7 ቀናት እንዲያፈርሱ እንዳዘዙዋቸው ተናግረዋል።

የኢትዩ ምህዳር አዘጋጆች አደጋ ደረሰባቸው

ዛሬ ሐዋሳ ፍርድ ቤት ለመቅረብ ትናንት ምሽት ወደ ስፍራው ያመሩት የኢትዩ ምህዳር ሶስት ጋዜጠኞች ማለዳ ላይ በሲዳማ ፍርድ ቤት ቀርበው ጉዳያቸውን ይመለከቱ የነበሩት ዳኛ ለከሰዓት 9፡00 ሰዓት እንዲቀርቡ ይነግሯቸዋል፡፡ጋዜጠኞቹ ጊዜውን በከንቱ ላለማባከን በማሰብ በሐዋሳ ዜና ፍለጋ ይሰማራሉ፡፡
በባጃጅ ተጭነው ወደ ሚያውቁት አንድ የሞያ አጋራቸው ማቅናት እንደጀመሩ ከፊት ለፊታቸው አንድ ሞተር ሳይክል እየከነፈ ይመጣል፡፡

“ትግራይ ከአንድ ፋብሪካ እንደወጣ ሳሙና”

 ዛሬ አንድ ታሪክ ያስታወሰኝ አስተያየት አነበብኩ። በ97 ምርጫ ቅስቀሳ ወቅት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪ ነበርኩ። በኢህአዴጎችና ቅንጅቶች መካከል የነበረ ክርክር እከታተል ነበር። የማናቸው ደጋፊ ወይ ተቃዋሚ አልነበርኩም። አንድ ሲኔራችን ነበር። ሁሌ ወደ ዶርማችን እየመጣ ስለነዚህ የቅንጅት መሪዎች መጥፎ ታሪክ ይነግረናል፤ ለትግራይ ህዝብ መጥፎ አመለካከት እንዳላቸው (እንዲህ አደረጉ፣ እንዲህ አሉ እያለ)፣ የደርግ ከፍተኛ ባለስልጣናት የነበሩና ወንጀለኞች መሆናቸው ወዘተ።
በተደጋጋሚ ሲተርክልን የልጁ ዓላማ ግራ ገባኝና “እስቲ ይሄ ተናገሩት ወይ አደረጉት የምትለውን አምጣውና አሳየኝ” አልኩት። “እሺ አሳየሀለሁ” ብሎ በዛው ጠፋ (ቢያንስ ወደ ዶርማችን እየመጣ አይዋሽም)። ከተወሰኑ ቀናት በኋላ “ይሄ አብርሃ የሚሉት ተከታተሉት፣ ቅንጅት ይመስለኛል” ብሎ ለሌሎች ተማሪዎች (የህወሓት አባላት) እንደተናገረ ሰማሁ። ተጠራጠርኩት። ለካ ልጁ የህወሓት ሰላይ ነበር።

የሳዲቅ አህመድ ንግግር (ዋሽንግተን ዲሲ) የታሰሩት የሙሰሊም መሪዎች የሰላም አምባሳደሮች

የሳዲቅ አህመድ ንግግር (ዋሽንግተን ዲሲ)
የምንወዳት የምንሳሳላት እናት ሀገራችን ኢትዮጲያ ልጆቼን አያለች በምትጣራበት ወቅት ላይ እንገኛለን። የናት አገር ጥሪንም ሰምተን እዚህ  መገኘታችን ታላቅ ዋጋ አለው! በዚህም ሳቢያ የታደልን የኢትዮጲያ ለጆች ነን ለማለት እወዳለሁ።እርስ በርስ እንድንፈራራ አንዱ-አንዱን  እዲጠራጠር የተከፈተብን የስነ-ልቦና ጦርነት ቀላል አይደለም፤ ይህንን የስነ-ልቦና ጦርነት ለመርታትም እዚህ ተገኝተናል። የዜጎች ሁለንተናዊ አንድነትን ለመናድ የሚደረግ ሴራ እዉን  አይሆንም፤ ለምን ካላችሁ እኛ  ለዘመናት ያካበትነው ውዴታ፣ እኛ ለዘመናት በራሳችን ላይ አስርፀን ያቆየነው ፍቅር፣ አንድ ኣምባገነናዊ ስርአት ሊፈጥረው ከሚችለዉ ስነ-ለቦናዊ ጫና በጣሙን የላቀ ነውና በኢትዮጲያዊነታችን ሁሌም ልንኮራ ይገባል! በኢትዮጲያዊነት ፍቅር ሁለም ልንፀና ይገባል። አላሁ-አክብር!

ተስፋየ ገብረአብ እና የመከነ ብእሩ፡ ከቡርቃ ዝምታ እስከ የስደተኛው ማስታወሻ

መስፍን አማን
(ከሃርለም፣ኔዘርላንድ)
ከጥቂት ሳምንታት በፊት አንድ ቅዳሜ ሻይ ቡና ለማለት አምስተርዳም ከወዳጆቼ ጋር በነበረኘ ቀጠሮ ላይ እንደአጋጣሚ ተስፋየም በመሃላችን ተገኝቶ ነበር።የባጥ የቆጡን ስናወራ፣ስለአዲሱ የተፋየ መጽሃፍ አንስቶ የውይይታችንን አቅጣጫ ቀየረው።በመሃሉ ተስፋየ፣ከመጽሃፉ ውስጥ አንዳንድ የማልወዳቸው ምእራፎች ቢኖሩ ትችቶቹን የምቀበል ስለመሆኔ አስረግጦ ጠየቀኝ?።እኔም መጽሃፋን ካነበብኩት በሁዋላ ለጥያቄው መልስ ብሰጥ እንደሚሻል ገልጨለት በዛው ተለያየን። አይደርስ የለም መጽሃፉን ለህዝብ ከመበተኑ በፊት ረቂቁን አነበብኩት። ረቂቁን አንብቤ እንደጨረስኩ ለተስፋየ ጥያቄ መልስ መመለስ እንዳለብ ወሰንኩኝ።

ምርመራ ያልተካሄደባቸው ሰባት ሰዎች ወደማረሚያ ቤት በድንገት እንዲሄዱ ተደረገ

“ማረሚያ ቤቱ የጠያቂ ገደብ ጥሎብናል” ተከሳሾች
“ለደህንነታቸው ሲባል ነው” የማረሚያ ቤት ተወካይ

በአሸናፊ ደምሴ

የፌዴራሉ የሥነ-ምግባርና ፀረ- ሙስና ኮሚሽን ዓቃቤ ሕግ ክስ በመሰረተባቸው የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣናት፣ ባለሀብቶችና ግብረ-አበሮቻቸው ላይ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ የክስ መሰማቱ ሂደት የቀጠለ ሲሆን፤ በትናንት የችሎት ውሎውም በቀደሙት ጊዜያት በአካል ያልተገኙ አዳዲስ ተከሳሾችን ጨምሮ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15ኛ ወንጀል ችሎት ጉዳዩን በመመርመር ትዕዛዝ ሰጥቷል።

አቶ ሬድዋን ሁሴን የኢቲቪ ቦርድ ሰብሳቢነቱን ከአቶ በረከት ስምኦን ተረከቡ - የሹመቱ አግባብነት ጥያቄ አስነስቷል - አፈጉባዔ አባዱላ ጠ/ሚኒስትሩ በሹመቱ ላይ ማብራሪያ ለመስጠት አይገደዱም አሉ


በፍሬው አበበ

የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት ለኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የሥራ አመራር ቦርድ ኃላፊነት ጠ/ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝ ያቀረቡትን ሹመት ተቀብሎ አጸደቀ። በዚሁ መሠረት ድርጅቱን ለረዥም ጊዜ በቦርድ ኃላፊነት ባገለገሉት አቶ በረከት ስምኦን ምትክ አቶ ሬድዋን ሁሴን የድርጅቱ ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ተሹመዋል።
ጠ/ሚኒስትር ኃ/ማርያም ትናንት ለም/ቤቱ በላኩትና የአማካሪ ም/ቤት አስቀድሞ ሳይመክርበት በድንገት በቀረበው ደብዳቤ መሰረት ለኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ስምንት አባላት ያሉት የስራ አመራር ቦርድ አባላትን መሾማቸውን አሳውቀዋል።

Tuesday, October 29, 2013

ስብሃት ህወሃት ጠቦ ታሪኩን እንደሚቋጭ አረጋገጡ

ህወሃትን ገልብጦ “ከየትኛው ክልል ድጋፍ ሊገኝ?”
sebhat nega
ስብሃት ነጋ የኢህአዴግ አባትና ፈጣሪ የሆነው ህወሃት የመጨረሻው ታሪኩ ጠቦ እንደሚቋጭ ይፋ አደረጉ። ችግር የህወሃት ልዩ በረከትና ስጦታ እንደሆነ በማመልከት ህወሃት ውስጥ ልዩነትና መፈርከስ አደጋ ተከስቶ እንደማያውቅ ሸመጠጡ።
አቶ ስብሃት ጠቦ የሚጠናቀቀውን የህወሃት ስውር አጀንዳ የገለጹት ከጋዜጠኛ ደረጃ ደስታ ለቀረበላቸው ጥያቄ መልስ በሰጡበት ወቅት ነበር። በኢህአዴግ የመከላከያ መዋቅር ውስጥ ከፍተኛ መከፋፈልና የኩዴታ አደጋ ሊያስከትል የሚችል አደጋ እንደተረጋገጠ ተጠቅሶ ለቀረበላቸው ጥያቄ አቶ ስብሃት “አዲስ አበባ መንግስት ገልብጠው የክልሎችን ድጋፍ ቢጠይቁ ማን እሺ ይላል” በማለት ነበር የመለሱት።

የጤና ጥበቃን ሙስና ማን አቤት ይበለው?


Author, Demesew Desta
ደምሰው ደስታ
የፀረ ሙስና ኮሚሽን መረጃ በአንድ መስሪያ ቤት ውስጥ የተካሄደን የሙስና ምዝበራ በሪፖርቱ መጠቀስ ያለበትን ሳይጠቀስ ማለፉ አግራሞትን አጭሮብኛል። ነገሩ እንዲህ ነው ለረጅም አመት በመድሀኒት ዘርፍ የኢትዮጵያ መድሀኒትና የህክምና መገልገያ እቃዎች በማስመጣት ለመላው ሀገሪቱ በማከፋፈል (ፋ.ር.ሚ.ድ) በመባል የሚታወቀው ድርጅት ጉለሌ ጳውሎስ ሆስፒታል ፊት ለፊት የሚገኝ መስሪያ ቤት ሲሆን በሀገሪቱ በሁሉም ሊባል በሚችል ደረጃ ቅርንጫፎች ያሉትና በጣም ጥሩ አገልግሎት ለህብረተሰቡ የሚሰጥ ተወዳዳሪ የሌለው መስሪያ ቤት ነበር።

የሳዲቅ አህመድ ንግግር (ዋሽንግተን ዲሲ) የታሰሩት የሙሰሊም መሪዎች የሰላም አምባሳደሮች

የሳዲቅ አህመድ ንግግር (ዋሽንግተን ዲሲ)
የምንወዳት የምንሳሳላት እናት ሀገራችን ኢትዮጲያ ልጆቼን አያለች በምትጣራበት ወቅት ላይ እንገኛለን። የናት አገር ጥሪንም ሰምተን እዚህ  መገኘታችን ታላቅ ዋጋ አለው! በዚህም ሳቢያ የታደልን የኢትዮጲያ ለጆች ነን ለማለት እወዳለሁ።እርስ በርስ እንድንፈራራ አንዱ-አንዱን  እዲጠራጠር የተከፈተብን የስነ-ልቦና ጦርነት ቀላል አይደለም፤ ይህንን የስነ-ልቦና ጦርነት ለመርታትም እዚህ ተገኝተናል። የዜጎች ሁለንተናዊ አንድነትን ለመናድ የሚደረግ ሴራ እዉን  አይሆንም፤ ለምን ካላችሁ እኛ  ለዘመናት ያካበትነው ውዴታ፣ እኛ ለዘመናት በራሳችን ላይ አስርፀን ያቆየነው ፍቅር፣ አንድ ኣምባገነናዊ ስርአት ሊፈጥረው ከሚችለዉ ስነ-ለቦናዊ ጫና በጣሙን የላቀ ነውና በኢትዮጲያዊነታችን ሁሌም ልንኮራ ይገባል! በኢትዮጲያዊነት ፍቅር ሁለም ልንፀና ይገባል። አላሁ-አክብር!

"ድምጻችን ይሰማ ዘኦርቶዶክስ የተዛባ አመለካከት አገልግሎታችንን አያደናቅፈውም ማኅበረ ቅዱሳን

ማኅበረ ቅዱሳን እንዴት ወዳጆች አፈራ? ጠላቶችስ ለምን ተነሡበት? በእግዚአብሔር ፈቃድ በቅዱስ ሲኖዶስ ይሁንታ የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት ለመደገፍና ለማጠናከር የተመሠረተው ማኅበረ ቅዱሳን ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ አያሌ ፈተናዎችን እያሳለፈ ዓመታት ተጉዟል፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን በዓመታት ጉዞው ባከናወናቸው መልካም ተግባራት ታላላቅ የቤተክርስቲያን አባቶችን ጨምሮ እጅግ በርካታ ወዳጆችን እንዳፈራ ሁሉ ጥቂት በተቃራኒው የቆሙ ስሙን በየጊዜው በክፉ የሚያነሱ ቡድኖችም ተነሥተውበታል፡፡ ወዳጆቹ የቤተ ክርስቲያን ወዳጆች ናቸውና በአገልግሎቱ ተማርከው በሚሠራቸው መልካም ሥራዎች ተስበው ቤተ ክርስቲያን ያለባትን የአገልግሎት ክፍተት ለመሙላት በጋራ ከማኅበሩ ጋር በመሥራት ሲተባበሩ፤ በአንጻሩ ጠላቶቹ ደግሞ የተለያዩ አጋጣሚዎችን እያስታከኩ ማኅበሩን ለመወንጀል እየተጣጣሩ ይገኛሉ፡፡

የሁለት ኢትዮጵያውያን ሁለት አንቀጽ ወግ እና እኔ…(አቤ ቶኪቻው)

የሁለት ኢትዮጵያውያን ሁለት አንቀጽ ወግ እና እኔ…
ዳዊት ከበደ እና ተስፋሁን ጫመዳ
ተስፋሁን ጫመዳ የተባለ አንድ ወጣት ኢትዮጳያዊ ነበር፡፡ የገዢው ግንባር ኢህአዴግ ነገረ ስራ አልመችህ ቢለው በተለያየ አጋጣሚ ተው ማለት ጀመረ፡፡ ኢህአዴግዬ ግን ተው ባይ አይወድምና በክፉ አይኑ ተመለከተው ይሄኔ ተስፋሁን የሚመጣበትን ጦስ ሸሽቶ መጪው ጊዜ መልካም እንደሚሆን ተስፋ አድርጎ እስኪያልፍ ያለፋል ብሎ ሀገሩን ትቶ ተሰደደ፡፡ ኢህአዴግ ግን ዝም አላለውም ከተሰደደበት ሀገር አፍኖ ወደ ሀገርቤት መለሰው፡፡ መመለስ ብቻም አይደለም እስር ቤት ዶለው፡፡ መዶል ብቻም አይደለም በቅርቡ ተስፋሁን በእስር ቤት በቂ ህክምና አጥቶ ህወቱን ተነጠቀ፡፡

የአቶ መለስ ዜናዊ “ያልተገለጡ ገፆች”

ከበትረ ያዕቆብ
ዉድ የሀገሬ ልጆች ከሁሉም በማስቀደም እንደምን ናችሁ ? ደህና ናችሁ ? 2006 እንዴት ይዟችኋል ? ስል የጠበቀ የወዳጅነት ሰላምታየን ማቅረብ እወዳለሁ፡፡ እዚህ ላይ ይህ ሰዉ ምን ነካዉ!? ባልተለመደ መክኩ ሰላምታ አበዛሳ !? ልትሉ ትችላላችሁ፡፡ ሆኖም አትፍረዱብኝ፡፡ “አሸባሪ ፣ አክራሪ ፣ ጅሀዳዊ ፣ ተለጣፊ ፣ ነጭ ለባሽ”… ወዘተ የሚል ቅፅል ስም ለሀገር ወዳድና ለመብታቸዉ መከበር ድምፃቸዉን ለሚያሰሙ ሁሉ በጅምላ እየተሰጠ ዜጎች በሀሰት በሚወነጀሉበት ሀገር ፤ በእያንዳንዷ ቀን እንደ መልካም ተግባር መሰል ዜጎችን ጠልፎ ለመጣል የተንኮል ወጥመድ ሲጠመድ በሚዋልበት ጊዜ ፣ ንፁህ ዜጎች በግዳጅ ያልፈፀሙትን ኃጢያት እንዲናዘዙ በሚገደዱበት ዘመን ፤ በልቶ ማደር ፍፁም በከበደበት በዚህ የጭንቅ ወቅት አጥብቆ ደህንነትን መጠየቁ ተገቢ ሆኖ ስለታየኝ ነዉ፡፡

ንጉሠ ነገሥት አብርሃም ያዬህ ሆይ! መፍትሔው ይሄው ነው በቃ?

ይሄይስ አእምሮ
“የአፄ አብርሃም ያዬህን ጽሑፍ አንብበን ስንጨረስ ነገር ማብላላታችንን ትተን ዝም ብለን መጋደም አልቻልንም፡፡ ዘመናችን ብዙ የሚሠራበት ሣይሆን ብዙ የሚወራበትና የሚጻፍበት መሆኑን እናውቃለንና አግራሞታችን ወሰን አልነበረውም፡፡ ጥሎብን “ሌላ ሥራ የላቸውም ወይ?” እስክንባል ድረስ በዬቀኑ ብዙ እናነ(ብ)ባለን፤ ስለዚህም ሲሆን በምታዘበው ሁሉ እናነባለን፡፡ ሕዝባችንን የሚጠቅም ነገር ለማከናውን የዛሬ አሥራ ሁለት ዓመት ገደማ ብዙ ብንጥርም የአማራ ኤሊቶች እያወኩን ጥረታችን ስንዝር ሳይራመድ ተኮላሽቶ እንዲቀር አደረጉብን፡፡ ያዘጋጀነው በመቶ ሺዎች የሚገመት ዘመናዊ ጦርም ሳይዋጋ ወደየመጣበት ተበተነብን፡፡ አሁን ደግሞ እነሙሉጌታ ሉሌ ትናንት እንዳልሰደቡን አሁን ደግሞ እኛን ተመሳሰሉና ለነአንትና እየሰገዱ አስደሰቱን፤ በሣቅም ፈጁን፡፡

የኢትዮሚዲያ ወቅታዊ መፈክር

ክፍሉ ሁሴን
“ከ40 ግድብ አንድ የቀይ ባሕር ወደብ!”የኢትዮሚዲያ ድረገጽ የወቅቱ መፈክር ነው።ከመፈክሩ ጋር ወይም በመፈክሩ ላይ ምንም ችግር የለብኝም።ይልቁንም ወያኔ ከሌሎች ክፉ ነገሮች በተጨማሪ ወደባችንን አስበልቶ በምድር ብቻ ተቀርቅበን የቀረን አገር ስላደረገን እስከ ዛሬ ድረስ ከሚንገበገቡት ኢትዮጲያውያኖች አንዱ ነኝ።የባሕር በር ባለቤትነታችን በእኔ እድሜ እንኳ ባይመለስ ቢያንስ የባሕር በር እንድናጣ ባደረጉን ዋና ዋና ከሃዲዎች ላይ በአገር ክህደት ወንጀል ክስ ሲመሰረት በሕይወት ዘመኔ ለማየት ከፍተኛ ጉጉት አለኝ።በነገራችን ላይ በዚህ ክስ በቀንደኛነት እንዲካተቱ ከምፈልጋቸው ሰዎች ውስጥ አንዱ መንግስቱ ኃይለማሪያም ወልዴ ነው።ስለምን?በዋናነት የተበላነው እሱ የ”አብዮታዊ ጦር ጠቅላይ አዛዥ”በነበረ ጊዜ ነውና።

Monday, October 28, 2013

“ከ40 ግድብ አንድ የቀይ ባሕር ወደብ!

ክፍሉ ሁሴን
“ከ40 ግድብ አንድ የቀይ ባሕር ወደብ!”የኢትዮሚዲያ ድረገጽ የወቅቱ መፈክር ነው።ከመፈክሩ ጋር ወይም በመፈክሩ ላይ ምንም ችግር የለብኝም።ይልቁንም ወያኔ ከሌሎች ክፉ ነገሮች በተጨማሪ ወደባችንን አስበልቶ በምድር ብቻ ተቀርቅበን የቀረን አገር ስላደረገን እስከ ዛሬ ድረስ ከሚንገበገቡት ኢትዮጲያውያኖች አንዱ ነኝ።የባሕር በር ባለቤትነታችን በእኔ እድሜ እንኳ ባይመለስ ቢያንስ የባሕር በር እንድናጣ ባደረጉን ዋና ዋና ከሃዲዎች ላይ በአገር ክህደት ወንጀል ክስ ሲመሰረት በሕይወት ዘመኔ ለማየት ከፍተኛ ጉጉት አለኝ።በነገራችን ላይ በዚህ ክስ በቀንደኛነት እንዲካተቱ ከምፈልጋቸው ሰዎች ውስጥ አንዱ መንግስቱ ኃይለማሪያም ወልዴ ነው።ስለምን?በዋናነት የተበላነው እሱ የ”አብዮታዊ ጦር ጠቅላይ አዛዥ”በነበረ ጊዜ ነውና።

ሃብታሙ ስዩምና ሸገር ሬዲዩ ተለያዩ // ሃብታሙ ‹‹ነጻ ሚዲያ ስትሆኑ እመጣለሁ››ብሏቸዋል

በቅርቡ‹‹አስራ ሰባት መድፌ››የተሰኘ ፖለቲካን እያዋዛ በቀልድ መልክ የተረከበትን መጽሀፍ ለንባብ አብቅቷል ሃብታሙ ስዩም፡፡በራዲዩ ፋና ግጥምና መጣጥፎች በማቅረብ ከራዲዩ አድማጮች ጋር የተዋወቀው ሃብታሙ የገጣሚና ጸሀፊ በእውቀቱ ስዩም ታናሽ ወንድም ነው፡፡
ከፋና ወደ ሸገር ራዲዩ በመምጣትም መጠነኛ ነጻነት እንዳለው በሚነገርለት ሸገር 102 ራዲዩ አዝናኝ አስተማሪ ወጎችን ሲያቀርብ ቆይቷል፡፡ከራዲዩ መርሃ ግብር በተጨማሪ ሃብታሙ በሳምንታዊው አዲስ ጉዳይ መጽሔት በአምደኝነት ፖለቲካዊ ሽሙጦችን፣ለህይወት የቀረቡ ወጎችንና ቁም ነገሮችን ለአንባቢያን እያካፈለ ይገኛል፡፡

ተስፋ የቆረጠው ጸሐፊ

በዮሴፍ አባይ
የተስፋዬ ገብረአብን ‹‹የስዯተኛ ማስታወሻ›› ኢንተርኔት ሊይ ተሰድ አግኝቼ አብዛኛውን ምእራፍን በወፍ በረር ቅኝት (አሰሌቺ ስሇሆነ) ፤ ቀሪውን ዯግሞ በጥሞና አነበብኩት፡፡ እርግጥም ብዙ ጸሀፊያን ከዚህ ቀዯም በጻፋቸው ስራዎቹ ጭምር (የቡርቃ ዝምታ ፤ የጋዜጠኛው እና የዯራሲው ማስታወሻ) ሊይ ግሳጼ ቢጽፉሇትም ማዯመጥ የሚሻው የአዴናቂዎቹን ጭብጨባ ብቻ ስሇሆነ መታረም አሌቻሇም፡፡ በተሇይ ‹‹ተስፋዬ ጥሩ የስነ-ጽሁፍ ችልታ አሇው ፤ ሇአማርኛው ስነ-ጽሁፍ ባሇውሇታ ነው›› የሚለ ሙገሳዎች ሒሶችን እንዲይሰማቸው ህሉናው ውስጥ የተሰነቀረ ጋሻ ሆኖሇታሌ-በቅንነት ስናየው፡፡

ይድረስ ለአቶ መስፍን አብርሃ

/ማኅሌት ሰለሞን ከጀርመን/
«መርዓዊና መንታ መንገዳቸው» በሚል ርዕስ የጻፉትን ተመለከትኩት። ገና ከጅምሩ ሊቀ ካህናት ዶ/ር መርዓዊ ተበጀ የኮሎኝ ቅ.ሚካኤል ቤ.ክ ብቻ አስተዳዳሪ መሆናቸውን፥ በጀርመን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ.ክ ኃላፊነታችው ግን እንደተሻረ ነግረውን ማን እንደ ተሾመ ግን አልነገሩንም። ሊነግሩንም አይችሉም። የተሻረም ሆነ የተሾመ የለምና ።
ነሐሴ ፳፬ እና ፳፭ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም በግብጾች ገዳም በተካሄደው ስብሰባ ላይ አቡነ ሙሴ በጀርመን መንበረ ጵጵስና አቋቁሜያአለሁ ያሉትን ይዘው ከሆነ በጀርመን ሕግ መሠረት የተቋቋመ ሀገረ ስብከት እያለ፧ መፍረስም ካለበት በሕጉ መሠረት ይፈርሳል እንጂ በቃል ሊፈርስ እንደማይችል፧ አባታችን ለሀገሩ/ለሕጉ/ እንግዳ፧ ለሰው ባዳ በመሆናቸው ባይረዱት/ምንም እንኳን የሀገር ቤቱን ሲኖዶስ አውግዘው በእንግሊዝ ሀገር የፖለቲካ ጥገኝነት ጥያቄ ያቀረቡ፧ ቆየት ብለው ደግሞ ያንኑ ሲኖዶስ ይቅርታ የጠየቁ አዲስ ሹመኛ መሆናቸው ቢታወቅም / እርሰዎ ግን ካፍ ነጥቀው ከሚያራግቡ ቀረብ ብለው ሊያስረዷቸው ይገባ ነበር ።

ተስፋዬ ገብረአብ--ኢሰብዓዊ እና የሞራል ድሃ!

ገላነው ክራር
ከኢትዮሚድያ ዝግጅት ክፍል - ይህ ጽሁፍ ከአንድ አመት በፊት ለንባብ የበቃ ነው። ተስፋዬ ገ/አብ አገራችንን ለማበጣበጥ እንቅልፍ ካጡት ጠላቶች ጎራ እንደተሰለፈ በቅርቡ በዳኛ ወ/ሚካኤል መሸሻ እና በወጣት አለማዮሁ መሰለ በኩል የተለቀቁት ማስረጃዎች ያስረዳሉ። የገላነው ክራር አጭር መል እክትም ቀደም ብላ እኛኑን አስጠንቅቃን ነበር “ከጭቃ ውስጥ እሾህ” እንጠንቀቅ ብላ።
* * * * *
ጥቂት ቀደም ሲል “አጼ ሚኒሊክ እና እቴጌ ጣይቱ በደራሲ ተስፋዬ ገ/አብ አይን” በሚል ርእስ በለቀቅሁት ጽሁፍ ሳቢያ በርካታ አንባቢያን የተለያዬ አስተያየት ልከውልኛል። አንዳንዱ “ይህን እየወጣ ያለ ደራሲ ወደታች ባትጎትተው ምናለ?” ሲል ሌሎችም “አበጀህ” ብለውኛል።

የሂውማን ራይትስ ዋች የሰሞኑ ዘገባ

ለወያኔ ፋሽስታዊ ግፍና የውገን ሰቆቃ ምላሽ መስጠት ይገባል

በኤፍሬም የማነብርሃን
በዓለም ታዋቂው የሰብዓ መብቶች ትሟጋች ድርጅት ሂውማን ራይትስ ዋች (Human Rights Watch) ሰሞኑን ባወጣው ዘገባ፡ የአፍሪቃ አንድነት ዋና ከተማ በምትባለው በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የወያኔ መንግስት በኢትዮጵያውያን ላይ እያካሄደ ያለውን የግፍ ግፍ ለዓለም አጋልጧል፡፡ በዚች ደቂቃ ማዕከላዊ ፖሊስ ጣቢያ እየተባለ በሚጠራው የሰቆቃ ቦታ በንጹሃን ኢትዮጵያውያን ላይ ለኢትዮጵያዊነት ፍቅርና ክብር በሌለው የወያኔ ወንጀለኛ መንግስት ይህ ነው የማይባል ወንጀል እየተፈጸመበት ይገኛል። በ”ሕጋዊ” መንገድ እንዲሰሩ “ተፈቅዶላችው” የሕዝቡን ሰቆቃ በመስማትና የሚፈጸመው ግፍና በደል እንዲቀርና በሰላማዊ መንገድ በውድ አገራችን ላይ ደሞክራሲ እንዲለመልም እየታገሉ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ላይ፤ የወያኔ ፋሽስታዊ መንግስት በአንድ ወገን ዓለምን ለማታለልና ዲሞክራሲ እንዳለ ለማስመሰል ፓርቲ ማቋቋም ይቻላል ብሎ ካስወራ በኋላ፤ ከዓለም እይታ በስተጀርባ ግን ይህ ነው የማይባል ፋሽስታዊ ጭካኔ በንጹኅን ኢትዮጵያውያን ላይ እያካሄደ አንደሚገኝ የመብት ትሟጋች ድርጅቱ አጋልጧል። እንዲህ ያለ ወንጀል በውዲቷ ዋና ከተማችንና በታላላቆች የሃይማኖት መጻሕፍት በቅድስናዋ ደጋግማ በምትጠቀሰው አገራችን ሲፈጸም እንዴት ዝም ብለን እናያለን? እያንዳንዱ እትዮጵያዊ ባለው ዐቅሙ ሊያደርግ የሚገባውን ለማድረግ ለምን አይረባረብም?

አድዋዉ ልጅ አድዋ ገባ” የአርማጭሆ ልጅ የት ይግባ?!! (ናደዉ ከዋሽንግተን ዲሲ)

የአድዋዉ ልጅ አድዋ ገባ”
የአርማጭሆ ልጅ የት ይግባ?!!
እንደምን ከረማችሁ ዉድ የኢካዴፍ እድምተኞች “እስቲ ቂማችንን ጥቂት እናቆየዉ” በሚል ርእስ የጀመርኩትን መጣጥፍ “በአሳ ጎርጓሪ ዘንዶ ያወጣል” ቀጥዪ ከክፍል 1-7 ድረስ ይህ ድህረ ገፅ ለንባብ አብቅቶልኛል ክፍል 8-9 ግን ከአንድም ሁለቴ በአደራ ደብዳቤ ሳይቀር ልኬ ሚዛን ባለመድፋቱ ለንባብ አልበቃም(የቅርጫት ራት ሆኗል) ሚዛን የሚደፋ ፅሁፍ ለማቅረብ አስቤ ፅሁፎቼን ቆየት ማድረግ በወሰንኩ ማግስት ዛሬ October 24, ምሽት አንድ ወዳጄ ስልክ ደዉሎ ሰበር ዜና ጀባ አለኝ የአዉራምባዉ አምደኛ ተጋዳላይ ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ ወደ ዘረኛ ግብረአበሮቹ ጉያ መሸጎጡን አጫወተኝ ከላይ በጠቀስኩት ርእስ እንደጠቀስኩት ይህ ሰላይ የትግራይ ጉጅሌ መልእክተኛ አዚህ ሰሜን አሜሪካ ኢሳትንና ሌሎች ጠንካራ ናቸዉ የሚባሉትን ተቃዋሚ ድርጅቶች የመሰለል ተልእኮዉን አጠናቅቆና የዳያስፖራዉን ተቃዋሚ ጓዳ ጎድጓዳ ሰልሎ የቃረማቸዉን የኦዲዮ ቪዲዮና ዳጎስ ያለ ጥራዝ ተሸክሞ አሜሪካ በገባበት አኳኋን ተመልሶ በኢትዮጵያ አየር መንገድ በአራት ኪሎ ቤተመንግስት ገባላችሁ ቡራኬዉንም ተቀብሎ በአዲስ አበባዉ ሸራተን ሆቴል የወሬ ቅራቅምቦዉን ለህወሀት የዜና አዉታሮችና የስለላዉ መረብ ክፍል አለቆቹ እያጋታቸዉ መሆኑን ዉስጥ አዋቂ ምንጮች ሹክ አሉን።

አደባባዩ ምን ያህል ይርቃል?

ከተመስገን ደሳለኝ
እነሆ ይቺ ሀገር ኢትዮጵያ ናትና የመብት (የለውጥ) ጥያቄዎች፣ እንደ አህጉር ተጋሪዎቿ ሁሉ መልስ የሚያገኙት ከአደባባይ ጩኸት ብቻ ይሆን ዘንድ ባህል ሆኖአል፡፡ ትውልድ ተሻጋሪ ታሪኳም የሚነግርህ በየወቅቱ ከተፈራረቁ ገዥዎቿ አንዳቸውም እንኳ ለህዝብ ፍላጎትና ውሳኔ ተገዝተው አለማወቃቸውን ነው፤ ጠመንጃ አሊያም ተፈጥሮ ወደ ግብአተ መሬት ካልሸኛቸው በቀር፡፡ የሩቁን (የጨለማውን ዘመን) ትተን፣ የቅርቡን እንኳን ብንመለከት በወጡበት መንገድ፣ ቁልቁል ተምዘግዝገው መውደቃቸውን መረዳቱ አይቸግርም፡፡

የኢዴፓ ገበና ሲገለጥ (ሊነበብ የሚገባው ደባ) ዶክተር በየነ እና ሻለቃ አድማሴ በአቶ መለስ ትእዛዝ የወር ደምወዝ ነበራቸው::

Image
የዴፓ ገበና ሲገለጥ (ሊነበብ የሚገባው ደባ)


የልደቱ አያሌው ኢዴፓ በየትኛው ሞራሉ ነው ተቃዋሚውንም ይሁን ገዢውን ፓርቲ የሚተቸው??
#Ethiopia #EPRDF #UDJ #EDP #BLUEPARTY 
ምንሊክ ሳልሳዊ
የአቶ ልደቱ አያለውን መጽሃፍ የጻፈው በወያኔ ልዩ ትእዛዝ አቶ ገነነ አሰፋ ነው::
ዶክተር በየነ ጴጥሮስ እና ሻለቃ አድማሴ መላኩ በአቶ መለስ ትእዛዝ የወር ደምወዝ ነበራቸው::
ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በኢዴፓ ህልውና አያምንም::ዘላለም ህዝቡ ኢዴፓን በበጎ መንፈስ አያየውም::
በአሁን ሰአት ለተፈጠረው ኢሕኣዴጋዊ አክራሪነት እና የፖለቲካ ጽንፈኝነት ተጠያቂው ኢዴፓ እና አመራሩ ናቸው::

በደረሰባት ከፍተኛ የአሲድ ጥቃት ጉዳት ደርሶባት የቆየችው ከሚላት መሀዲ እሁድ እለት የጋብቻ ስነ ስርዓቷን ፈፅማለች።

አስደሳች ዜና:
ከጥቂት አመታት በፊት በደረሰባት ከፍተኛ የአሲድ ጥቃት ጉዳት ደርሶባት የነበረው እና የህዝብ መነጋገሪያ ሆና የቆየችው ከሚላት መሀዲ በክቡር ዶ/ር መሀመድ ሁሴን አላሙዲን ድጋፍ በከፍተኛ ወጪ በፈረንሳይ ሀገር የፕላስቲክ ሰርጀሪ ሲደረግላት ቆይታ በዛሬው እለት የጋብቻ ስነ ስርዓቷን ፈፅማለች።

በሰላማዊና በህጋዊ መንገድ ተቃውሞ ቢያቀርቡም የኢህአዴግን ጆሮ ማግኘት ያልቻሉ ተበዳዮች ርምጃ ወሰዱ።

በሰላማዊና በህጋዊ መንገድ ተቃውሞ ቢያቀርቡም የኢህአዴግን ጆሮ ማግኘት ያልቻሉ ተበዳዮች ርምጃ ወሰዱ። ሕዝብ ወዶና ፈቅዶ ያልተቀበለው ኢንቨስትመንት ከዘረፋ ተለይቶ እንደማይታይ የአካባቢው ነዋሪዎች አስታውቀዋል። ውድመት የደረሰበት የህንድ ኩባንያ በልማት ባንክ ላይ ኪሳራ ሊያስከትል እንደሚችል ስጋት አለ። ለደረሰው ጉዳት “ተጠያቂው ማን ነው?” የሚል ጥያቄ ተነስቷል። በጥርጣሬ የሚታሰሩ መበራከታቸው በክልሉ ባሉ ተመሳሳይ የእርሻ ኢንቨስትመንት ባለቤቶችን ስጋት ላይ ጥሏል።

Sunday, October 27, 2013

የጀነራል መኮንኖች የምደባ ለውጥ ተካሄደ

ሜጀር ጀነራል አደም መሀመድ የአየር ሀይል አዛዥ ሆነው መሾማቸውንና የአዛዥ ጄነራሎች ላይም የምደባ ለውጥ መደረጉን ምንጮቻችን አመለከቱ፡፡ በአየር ሀይል አዛዥ በነበሩት ሜጀር ጀነራል ሞላ ሀይለማርያም ምትክ የተሾሙት ሜጀር ጀነራል አደም የአየር ሀይል ፓይለት የነበሩና በሱዳን አቢዬ ግዛት የሠላም አስከባሪ ሀይል ምክትል አዛዥነት ያገለገሉ እንዲሁም የመከላከያ ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ ነበሩ፡፡ 

ትክክለኛው የኢትዮጵያ ካርታ ኤርትራ በተገነጠለችበት ወቅት መሆን ያለበት ይህ ነበር።

ትክክለኛው የኢትዮጵያ ካርታ፡ በሊግ ኦፍ ኔሽን የሚታወቀውና፡ እንደአውሮፓ አቆጣጠር በ1961 የተባበሩት መንግሥታት ካጸደቃቸው ሦሥቱ የኤርትራ ሁኔታ ውሳኔ፡ ” ኤርትራ የፊዴሬሽኑን ሁኔታ ሕዝቡ ካልፈለገና ካርታዋ ከተገነጠለች፡ ኢትዮጵያ በሊግ ኦፍ ኔሽን ወደሚታወቀው እዚህ ላይ ወደሚታየው ካርታዋ ይመለሳል ነበር። 
የኢትዮጵያውያን ጠላት የነበረው የፋሽስት ወያኔ ሞተር መለስ ዘባንዳዊ፡ ወደብ ሸቀጥ ነው በሚል የብልግናና የውንብድና ንግግሩ፡ ኢትዮጵያውያን የሚከፍሉትን የግብር ገንዘብ ለጂቡቲ በቀን ከ6 ሚሊዮን ብር በላይ እንደሚገብር ታውቃላችሁን? 

“ኢቴቪ” የዜና መረጃዎችንና የሰዎችን መልክ ይደፈጥጣል

በኢቴቪ የምናያቸው ቪዲዮዎችና ምስሎች፣ የተደፈጠጡና የተጣመሙ ሆነዋል – ስንት ወሩ? አልተስተካከለም።
በኢቴቪ የሚሰራጩ የተዛቡና የተሳሳቱ ዜናዎች ወይም ዘገባዎች ያሳፍራሉ፤ ደግሞም መላ ያለው አይመስልም።
አንዳንዴ፣ በኢትዮጵያ ሬድዮና ቴሌቪዥን የሚሰራጩ ዜናዎችን መስማት ያሳቅቃል፤ ወይም ያዝናናል። በሌላ በኩል ደግሞ ቀሽም ስህተት ስለሆነ ያዝናናል። ከግማሽ ምዕተ አመት በላይ እድሜ ያስቆጠሩ የአገሪቱ ብቸኛ የቴሌቪዥንና የሬድዮ አንጋፋ ድርጅቶች መረጃ ሲሳሳቱና ሲያዛቡ ማየት ያሳቅቃል። 

የ“ፖለቲካ ኳሳችን” የት እንደገባች አልታወቀም!

ከኤልያስ
ኢሕአዴግም ተቃዋሚም “ኳሷ እኛ ጋ የለችም” ብለዋል
ባለፈው ሰሞን ጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ፤ በፓርላማ የተቃዋሚ ተወካይ ለሆኑት የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉ ጥያቄና አስተያየት የሰጡትን ምላሽ ሰምታችሁልኛል? (ካልሰማችሁ አመለጣችሁ!) የተከበሩ አቶ ግርማ እንዲህ አሉ፡- (ሃሳባቸውንበጥቅሉ አቀርባለሁ) “መንግስት ከተቃዋሚ ኃይሎች ጋር ምክክር ካላደረገ የውጭ ኢንቨስተሮችን መሳብ አይሞከርም” የሚል ነው - ሃሳቡ፡፡ ጠ/ሚኒስትሩ ሲመልሱም (ሌላውን ትተን አንኳሩን ብቻ) “እስካሁን የውጭ ኢንቨስተሮች ለመስራት ሲመጡ ሌላ ሌላውን እንጂ ከተቃዋሚዎች ጋር ትመካከራላችሁ ወይ? አላሉንም” ብለዋል (ጨዋታ ጨምረዋል ልበል!) 

“ስለ ኢትዮጵያ ዝም አንልም ግብረ ሶዶማዊነት በኢትዮጵያ የ666 አሰራር” በደረጀ ነጋሸ ዘወይንዬ

ስለ ኢትዮጵያ ዝም አንልም ግብረ ሶዶማዊነት በኢትዮጵያ የ666 አሰራር” በደረጀ ነጋሸ ዘወይንዬ


በኢትዮጵያ ከግማሽ ክ/ዘመን በላይ የቆየማንዴላን የተመለከተ የደህንነት ሚስጥር ዛሬ ይፋ ሆነ።ሚስጥሩን ማንዴላም እስካሁን ድረስ አይውቁትም።

ኔልሰን ማንዴላ እና ጄኔራል ታደሰ(የማንዴላ አሰልጣኝ በወቅቱ ኮ/ል የነበሩ)ኮልፌ ፖሊስ ማሰልጠኛ
ኔልሰን ማንዴላ የደቡብ አፍሪካ የፀረ-አፓርታይድ (የዘር-መድሎ) ተዋጊ አርበኛ መሆናቸው ይታወቃል።ለእስር የተዳረጉት ኢትዮጵያ ውስጥ ወታደራዊ ስልጠና ወስደው እንደተመለሱ ነበር። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ 1962 ዓም ማንዴላ በኢትዮጵያ ቆይታቸው በወቅቱ ለማንዴላ ኢትዮጵያ ፓስፖርት በመስጠት አጋርነቷን የገለፀች ብቸኛ ሀገር ነበረች።
ከዘመናት በኃላ ማንዴላ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ወቅት  የግድያ ሙከራ ተደርጎ እንደነበር ሚስጥሩን ከግማሽ ክፍለዘመን በላይ ይዘው የቆዩ በቀዳማዊ አፄ ኃይለስላሴ ዘመን የኢትዮጵያ ፖሊስ መኮንን ዛሬ ጥቅምት 15/2006 ዓም ለመጀመርያ ጊዜ በሸገር ራድዮ የዜና እወጃ ላይ ገልፀዋል።

Saturday, October 26, 2013

ሲኖዶሱ የፓትርያርኩን ውሳኔ አስቀየረ

ቅዱስ ሲኖዶሱ በትናንትናው የስብሰባ ውሎው ከሃላፊነታቸው እንዲነሱ በአብላጫ ድምጽ ወስኖባቸው የነበሩት የአዲስ አበባው ሊቀ ጳጳስ አቡነ እስጢፋኖስ በዛሬው ዕለት ፓትርያርኩ አቡነ ማቲያስ ‹‹አዲስ አበባ የእኔ ልዩ ሐገረ ስብከት በመሆኑና ማንም ሊያዝበት ስለማይችል ሊቀ ጳጳሱ በቦታቸው እንዲቀጥሉ በመወሰን የትናንቱን ውሳኔ ሽሪያለሁ››ማለታቸውን ምንጮቻችን ተናግረዋል፡፡

የተስፋዬ ተካልኝ መከራና የማይሞተው የነፃነት ሕልሙ

ዳኛቸው ቢያድግልኝ
ሀዘኑ በተስፋ እንዲተካለት ከልብ የምመኝለት የወያኔ ቅጥረኞች ቁምስቅሉን ያሳዩትን ወጣት ቃለ ምልልስ ኢሳት ላይ እንድመለከት ስጋበዝ ስሜቴን ሰቅዞ የሚይዝ በእጅጉ የሚያስቆጣኝ ጉዳይ እንደነበር አልገመትኩም። ምክንያቱም መከራ ለምደናል፣ ሀዘን ከቤታችን ወጥቶ አያውቅም። ነውጠኞች፣ ባለጌዎች፣ ጎጠኞችና ክብረጠሎች ከእንስሳ ያነሰ ሆዳም ደመነብስ ይዘው ሀገር ማፍረሱን ከያዙ ስለቆዩ ምንም አዲስ ነገር የለም በማለቴ ነበር። ተሳስቻለሁ ተሥፋዬ ከሀዘን ይልቅ ብርታትን፣ ከውድቀትም በላይ መነሳትን ሲናገር ሞትን ፊት ለፊት እየተመለከተ መሆኑ በወጣቱ ትውልድ እጅግ እንድኮራ አድርጎኛል።

የአማራ ወጣቶች የጋራ ንቅናቄ ሶስት የአማራ ክልል አመራሮችን ማገቱን አስታወቀ

ESAT

 የአማራ ወጣቶች የጋራ ንቅናቄ በአማራ ክልል ላኩማ ወረዳ ሁለት የሚሊሽያ ሀላፊዎችንና አንድ የወረዳ አስተዳዳሪን በቁጥጥር ስራ ማድረጉን ገለፀ፡፡
ንቅናቄው ሰሞኑን 22 የፖለቲካ አመራሮች በላኩማ ወረዳ በሚገኘው በሰላ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ በስብሰባ ላይ እንዳሉ በቁጥጥር ስር ካዋለ በኋላ መልቀቁን ገልጾ ሶስቱን አመራሮች ግን አሁንም ድረስ በቁጥጥር ስር አድርጎ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡
የተያዙት አመራሮች በቁጥጥር ስር ውለው ከነበሩት ፓለቲከኞች ዋነኛ እና የአካባቢውን ህብረተሰብ በመበደል የሚታወቁ እንደሆነ ንቅናቄው አመልክቷል፡፡

ሁለት ታላላቅ አቅርበዉና አጉልተዉ የሚያሳዩ መነጽሮች ወይም ቴሌስኮፕ እንጦጦ ተራራ ላይ መተከላቸዉ

ሁለት ታላላቅ አቅርበዉና አጉልተዉ የሚያሳዩ መነጽሮች ወይም ቴሌስኮፕ እንጦጦ ተራራ ላይ ትናንት መተከላቸዉ ተሰምቷል።
ወደ15 ሺ ኪሎ እንደሚመዝኑ የተነገረዉ አቅርቢና አጉሊዉ መነጽሮቹ በሕዋ ብቻ ሳይሆን የመሬትን ምርምርም ሆነ የአየር ንብረት ጉዳይ ላይ የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ እንዳለም ተገልጿል።

የሳውዲ የምህረት አዋጅ መገባደድና የኢትዮጵያውያን ስጋት

ብዙዎች በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ መስሪያ ቤት አስፈላጊውን አገልግሎት በአፋጣኝ አልሰጠንም በማለት እንደሚያማርሩ እና ስጋት እንደገባቸው የጅዳዉ ወኪላችን ገልጿል። የሳውዲ መንግስት ሕገ ወጥ ስደተኞችን አስመልክቶ ያወጣውን መስፈርት ለሚያሟሉ ዜጎች የመኖሪያ ፈቃድ ለመስጠት የሰጠው የተራዘመ የምህረት አዋጅ፤በቀጣዩ ሳምንት ጥቅምት 24 ቀን 2006 ዓም ተግባራዊ ይደረጋል።

የአሲምባ ፍቅር (ክፍል ሁለት)

የአሲምባ ፍቅር
ደራሲ- ካህሳይ አብርሀ (አማኑኤል)
ትችት-(ሐተታ)- ሽፈራው
Assimba.org web site ethiopian information
አንባቢ ሆይ : በክፍል አንድ ባጭሩ አንደገለፀሁት ጓድ “አማኑኤል” ጋር በሕብረ ብሔራዊዉ የኢትዮጵያ ህዝባዊዉ አቢዮታዊዉ ሠራዊት (ኢሕአሠ) በወሎ፣ በቤጌምድር እና በትግራይ በብዙ ፈተናና ችግር አብረን ተካፍለናል። ከ30 አመት በኋላም ተገናኝተን ስለ ኢሕአሠ መጽሃፍ ለመጻፍ እንዳሰበ ሲነግረኝ እንደምረዳዉ ቃሌን ሰጥቸ በሰፊው አስተዋጽዖ አድርጌአለሁ ።መጽሐፉ እስኪወጣ ብዙ ጓጉቻለሁ ጠብቄአለሁ። እንደወጣም በተቻለኝ አቅም በብዙ መንገድ ለአንባቢያን እንዲደርስ አድርጌአለሁ። በፌስ ቡኩ(Face book) እና በጉግል(Google) እውነተኛ ታሪክ ሁሉም ሊያነበው የሚገባ በማለት አስተዋውቄአለሁ።

Friday, October 25, 2013

ዚምባቡዌ በሕገወጥ መንገድ ድንበሯን በማቋረጥ ወደ ደቡብ አፍሪካ ሲያቀኑ ነበሩ ያለቻቸውን 38 ኢትዮጵያውያንን በቁጥጥር ሥር ማዋሏን አስታወቀች፡፡

Government bans citizens from travelling abroad for work

 ኢሳት ዜና :-የኬንያው ዴይሊ ኔሽን እንደዘገበው ኢትዮጵያውያኑ የተያዙት ሙታሬ በምትባለውና ከሞዛምቢክ ጋር ድንበርተኛ በሆነችው ከተማ በኩል አድርገው ወደ ደቡብ አፍሪካ ሲያቀኑ በፖሊስ እንደተያዙ ማክሰኞ ማምሻውን ተዘግቧል፡፡
ተጠርጣሪ ስደተኞቹ በግምት ከ20 እስከ 30 ባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ እንደሚገኙ የተገለጸ ሲሆን፣ ከዚምባቡዌ በሕገወጥ መተላለፊያ በኩል መግባታቸውን ያስታወቁት፣ በዚምባቡዌ ቤት ብሪጅ ዲስትሪክት የፖሊስ ኮማንደር ዋና ሱፐር ኢንቴንዳንት ላውረንስ ቺኔንጎ ናቸው፡፡