Thursday, October 31, 2013

በዳኞች መካከል የሚታየው አለመግባባት የፍርድ ሂደቱን እያጓተተው ነው

 ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ በከፍተኘው ፍርድ ቤት ባለው የአስተዳደር ቊንጮ ማለትም በዋናው ፕሬዚዳንት በዳኛ ውብሸት ሽፈራውና በምክትሉ ማሃል ያለው አለመስማማት እየጨመረ በመሄዱ የፍርድ አሰጣጥ ሂደቱን እያበላሸው መሆኑን ውስጥ አዋቂዎች ገለጹ ።አሁን ባለው አሰራር ተሰሚነት ያለው የኢሃዴግ አባል የሆነው ምክትሉ ሲሆን ፣  ፕሬዘዳንቱ የኢሃዴግ አባል ባለመሆኑ ተሰሚነት አጥቷል ይላሉ ምንጮች:።

ሌሎች ዳኞችም ከዋናው ፕሬዘዳንት ይበልጥ የኢሃዲግ አባል ለሆነው ለምክትሉ አክብሮት ያላቸው ሲሆን፣  ለሚቀርብላቸው ትእዛዝም ቅድምያ የሚሰጡት ከዋናው ፕሬዘዳንት ይልቅ ለምክትሉ እንደሆነ ውስጥ አዋቂ ምንጮች ይናገራሉ።
አንድ የከፍተኘው ፍርድ ቤት ዳኛ ልጁን ለማሳከም ከአንድ ባለጉዳይ ጋር በመነጋገር ወደ ሳውዲ አረብያ መውሰዱን  የከፍተኛው ፍርድ ቤት ፕሬዘዳንት መረጃ ቢደርሳቸውም፣ ሁኔታውን  አጣርተው እርምጃ ከመውሰድ ይልቅ ዳኛው የኢህአዴግ አባል በመሆኑና ከምክትሉ ፕሬዚዳንት ድጋፍ በማጣታቸው በዳኛው ላይ የዲሲፕሊን እርምጃ ሳይወሰድ ቀርቷል።
በከፍተኛው ፍርድ ቤት ያለው የዳኝነት ጥራት ከእለት ወደ እለት እየቀነሰ በመሄዱ ተገልጋዮች አቤት የሚሉበት ማጣታቸውን ይናገራሉ።

No comments:

Post a Comment