Monday, October 28, 2013

ተስፋ የቆረጠው ጸሐፊ

በዮሴፍ አባይ
የተስፋዬ ገብረአብን ‹‹የስዯተኛ ማስታወሻ›› ኢንተርኔት ሊይ ተሰድ አግኝቼ አብዛኛውን ምእራፍን በወፍ በረር ቅኝት (አሰሌቺ ስሇሆነ) ፤ ቀሪውን ዯግሞ በጥሞና አነበብኩት፡፡ እርግጥም ብዙ ጸሀፊያን ከዚህ ቀዯም በጻፋቸው ስራዎቹ ጭምር (የቡርቃ ዝምታ ፤ የጋዜጠኛው እና የዯራሲው ማስታወሻ) ሊይ ግሳጼ ቢጽፉሇትም ማዯመጥ የሚሻው የአዴናቂዎቹን ጭብጨባ ብቻ ስሇሆነ መታረም አሌቻሇም፡፡ በተሇይ ‹‹ተስፋዬ ጥሩ የስነ-ጽሁፍ ችልታ አሇው ፤ ሇአማርኛው ስነ-ጽሁፍ ባሇውሇታ ነው›› የሚለ ሙገሳዎች ሒሶችን እንዲይሰማቸው ህሉናው ውስጥ የተሰነቀረ ጋሻ ሆኖሇታሌ-በቅንነት ስናየው፡፡
በጥሩ ስነ-ጽሁፍ ችልታ ሊይ የተዯበቀ ክፉ አሊማ እና ምኞት በኛው በጉዲዩ ባሇቤቶች ሀይ ካሌተባለ ግን ነገ መዘዙን መዘን ሌንጨርሰው አንችሌም፡፡ ተስፋዬ አባት አገሩ ሊሌሆነችው ኢትዮጵያ ሀሊፊነት ይሰማዋሌ ማሇት የዋህነት ይመስሇኛሌ፡፡ የተስፋዬ ክፉ አባዜ ከአሊማው አንጻር ወድ የተጣባው ስሇሆነ በቀሊለ ይተወዋሌ ሇማሇት ይከብዲሌ፡፡ ፈጽሞ መታረምን አይሻም፡፡ ‹‹በስዯተኛው ማስታወሻ›› አራት መቶ ገጽ አባክኖ ያሳየንም እንዲገረሸበት ነው፡፡
ወዯ ስዯተኛው ማስታወሻ ስመሇስ በምእራፍ ሰባት ሊይ ‹‹ጫሌቱ እንዯ ሔሇን›› በሚሌ አርእስት ያሰፈረው ‹‹የቡርቃ ዝምታ›› እና ‹‹የቢሾፍቱ ቆሪጦች››ን ያህሌ ውሀ ያነሳሇት አይመስሌም፡፡ ምክንያቱም ሇከተማ እንግዲ ከሆነ ስም እና የፊት ንቅሳት የመጣችው ጫሌቱ ፤ ከጎንዯርዋ ዲሳሽ ፤ ከወሇዬዋ በሊይነሽ ፤ ከጎጃምዋ የጎጃምወርቅ እንዱሁም ከትግራይዋ ፍታው የከፋ እና የተሇየ በዯሌ ስሊሌተፈጸመባት፡፡ የከተማ አሊዋቂነት በተሇያዩ የክፍሇሀገር ሰዎች ሊይ የስነ-ሌቦና ተጽእኖ ፈጥሯሌ፡፡ ምጽሊሌ ፤ ዲሳሽ ፤ የጎጃም ወርቅ እና የመሳሰለት ስሞች ሌክ አንዯ ጫሌቱ የአንዲንዴ ከተሜዎች ማሊገጫ ሆነዋሌ፡፡ በስሙ ባሇቤቶች ሊይ የስነ-ሌቦና አዴርሰዋሌ፡፡ ይህ በዯሌ እና ሰውን ዝቅ አዴርጎ ማየት በአንዴ ብሔር አባሊት ብቻ ሊይ የተፈጸመ በዯሌ ሳይሆን ‹‹ከተሜ ቀመስ›› ስም በላሊቸው አብዛኛዎቹ ኢትዮጵያውያን ሊይ የዯረሰ ችግር ነው፡፡ የዚህ ጽሁፍ አቅራቢም የቅመ-አያቴን ስም ‹‹እንቋይ›› አብሮ አዯግ ጓዯኞቼ ሲያንጓጥጡበት እንዯነበር እናም በነሱ ስዴብ መሳይ ሹፈት እናዯዴ እንዯነበር አስታውሳሇው፡፡ ሆኖም ግን በእዴሜ እና በአስተሳሰብ ስበስሌ ይህ ስም እንዯማንኛውም ሇመጥራት ጣፋጭ ከሚመስለ የእብራይስጥ ስሞች ባሊነሰ ጥሩ ትርጉም ያሇው መሆኑን ስሇተረዲው የሌጅነት ስሜቴ እስከአዋቂነት ዘሌቆ ወዯ ህመምነት አሌተቀየረም፡፡
ከዚህ አንጻር የጫሌቱ ታሪክ ሇምን እንዯገባ አይገባም (እንዯበዙዎቹ ምእራፎች)፡፡ የጫሌቱን በዯሌ በጣም በማጮህ ኦሮሞውን ኢትዮጵያዊያን ያንቋሽሹሀሌ ብል ከፋፍል የማባሊት ዴርሰት ነው ያስነበበን፡፡ ምናሌባትም ተስፋዬ ይህን ጽሁፍ እና መጽሀፍ ሲጽፍ የኢሳይያስ አፈወርቂን ‹‹የመቶ አመት የቤት ስራ እሰጣችኋሇው፡፡›› ዛቻ ተግባራዊ ሇማዴረግ ሇአባት አገሩ የበኩለን አስተዋጽኦ ሇማዴረግ ይሆናሌ፡፡
ምእራፍ ስምንት ሊይ ያሇው ‹‹አጸዯ አዴዋ›› ተስፋዬ እጁ ተመቶ ማበጡን ግን ተመቶ መዴማቱን አይነግረንም፡፡ ጥይት ሳያዯማ እንዯሚያሳብጥም አሊውቅም፡፡ ግን ቁስሇኛ ሆኖ ስቃዩን እያስታመመ ሳሇ የዘፈን ትርኢት ግብዣ ከአጸዯ ሲቀርብሇት በዘፈኑ ሇመዝናናት ሳይሆን ዯስ እንዱሊት ሇመሔዴ እንዯፈሇገ ይተርካሌ፡፡ እኔ ከተስፋዬ የከዚህ በፊት ጽሁፎቹ እና ከዚሁ መጽሀፉ አገሊሇጽ እንዯተረዲሁት ግን አብሯት የሔዯው በውበትዋ ከተማረከው አጸዯ አጠገብ ሊሇመራቅ ይመስሊሌ፡፡ ቆስል ህመሙን ከማስታመም የፍትወት ሲቃውን ማዲመጥ የመረጠ ይመስሊሌ፡፡ ሇዚህም እማኝ የሚሆነው በገጽ 108 ሊይ ያሇው የራሱ ጽሁፍ ነው፡፡
‹‹ያነገተችው ጠመንጃ የእጅ ቦምብ የመሰለ ጡቶቿን አቋርጦ በማሇፉ ፤ የግራ ጡቷ ጡጫ መስል ከዘሇበቱ አፈንግጦ እንዯነበር አይረሳኝም፡፡ በክሽፏ ያበጠ እጄን ስትጠመጥምሌኝ እንዯተፈሇቀቀ ትኩስ እሸት ፤ ሙቅ ትንፋሷ በአፍና በአፍንጫዬ በመግባቱ ካሇሁበት ቦታና ሁኔታ ጋር ፍጹም ተቃራኒ የሆነ አስገራሜ ስሜት እየተሰማኝ ነበር፡፡…..›› ይሇናሌ፡፡
እንዱህ ሲሇን ተስፋዬ ተታኩሶ በጥይት የቆሰሇ ሳይሆን የሴት እርቃነ ስጋ ሲመሇከት በስሜት ናውዞ ተንሸራትቶ መሬት በመውዯቅ እጁ ያበጠ ነው የሚመስሌ፡፡ እናም ሲያያት የነበረችው አጸዯ፡፡
ምእራፍ ዘጠኝ ‹‹ባሌና ሚስት›› ሮተርዲም ኢትዮጵያዊ ባሇትዲሮች ጋር ተጋብዞ የታዘበውን ነው የጻፈው፡፡ ጽሁፉ ባድ ቢሆንም ‹‹እኔ ፓሇቲካ አሌወዴው፡፡›› የምትሇው አባባለ አስገርማኛሇች፡፡ ተስፋዬ የስፖርት ጋዜጠኛ የነበረ ፤ ወይም የፍቅር ሌብወሇዴ ዯራሲ ይመስሌ ‹‹ፖሇቲካ አሌወዴም›› የምትሇውን አባባለን እንዯወረዯ የምንቀበሌ ሞኝ አዴርጎ አስቦናሌ ማሇት ነው፡፡ ይሔም ንቀት ነው፡፡
ምእራፍ አስራ አንዴ ‹‹የህይወት ጥሪ›› ሊይ ‹‹የኢትዮጵያ ህዝብ ሰነፍ ነው፡፡ ተጎሌቶ ስሇዴህነት ያወራሌ፡፡›› ይሌና በጅምሊ እንዲሌሰዯበን ሇማረቅ የጉራጌ ብሔርን ብቻ ጎበዝ አዴርጎ ያቀርብሌናሌ፡፡ ‹‹የህይወት ጥሪው›› ነጋዳነት እንዲሌሆነና ጥሪው የስነጽሁፍ ስራ እንዯሆነ ሇመግሇጽ የፈሇገ ቢመስሌም ሇኔ እንዯገባኝ የተስፋዬ የህይወት ጥሪ በኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት መዘባበት እና መቀሇዴ እንዱሁም እኛ ኢትዮጵያውያንን የሚሰዴብበትን ስራ ሇራሳችን ጽፎ መክበር እና መግነን ነው፡፡ የተስፋዬ የህይወት ጥሪ በፖሇቲካ ንግዴ መክበር
ነው፡፡ በዚሁ ምእራፉ እንዯ ጀብደ የሚቆጥረውን ሴት አውሌነቱን አሊማ እና ፍትወት ተጣርሰውበት ሇንግዴ የተሰጠውን እና ያጠራቀመውን ገንዘብ ሴት ጭን ውስጥ እንዯበተነው ይናዘዛሌ፡፡
ቀሪዎቹ ምእራፎች ብኩኖች ናቸው፡፡ ‹‹የጨሇሇቃ ዝይ-ምእራፍ 12›› ራሱን ያሞገሰበት ፤ ‹‹ዯስተኛ ዝይ-ምእራፍ 13›› የቃሊት ብክነት ፤ ‹‹የክሊራ ፈጣሪ-ምእራፍ 14›› ባድ ፤ ‹‹አጽምና ስጋ-ምእራፍ 18›› ሩህና ጅስም የላሇው…. ሆነው ነው ያገኘኋቸው፡፡
ምእራፍ ሀያ ሁሇት ‹‹አባት አገር›› ተስፋዬ ስሇ ኤርትራ ብዙ ይሌበታሌ ብዬ ነበር፡፡ ግን ቀብቃባ ሆኖበታሌ፡፡ ሔኖክ በርሔ ብቻ የገዘፈበት ምእራፍ ነው፡፡ ኤርትራ ሴቶቿን የሚያገቡሊት አንዴ ሔኖክ የመጣ ይመስሌ በአጭር ጊዜ እንዳት ዝናው እንዯናኘ በመተረክ ነው ምእራፉን የጨረሰው፡፡
ይሌቁንም በምእራፉ የተሰነቀረው የሌጅነት ትዝታው ተስፋዬ ቤተሰቦች ቤት በዯርግ ጊዜ ምን ሲዯረግ እንዯነበረ ወዯኋሊ ሔዯን እንዴንጠይቅ የሚጋብዝ ነው፡፡ ተስፋዬ ቤታቸው ውስጥ ናቅፋ በሹክሹክታ ትወራ እንዯነበር ተርኳሌ፡፡ እናቱም የአዋቂዎች ወሬ ሲያዲምጥ እንዯሚያባሩት እንዯነበረ ሲተርክ የሚባረረው የሰማውን ወሬ ሇሰፈር ሌጆቹ እንዲያወራ እንዱርቅ ተፈሌጎ ነው የሚሆነው፡፡ በእርግጥም ተስፋዬ የሰማውን ውጭ ተናግሮ ወሬው ቢናፈስ ሇቤተሰቦቹ አዯጋ ነው፡፡ ቤተሰቦቹ በሻእቢያ ወሬ አቀባይነት ዘብጥያ ሉወርደ ይችለ ነበር፡፡ አብረዋቸው ሲያንሾካሽኩ የነበሩቱም ተሇቅመው ምናሌባት የዯርግ ዯህንነት የዯብረዘይቱን የሻእቢያ ትሌቅ አሳ ሇማጥመዴ ያግዘው ነበር፡፡
ናቅፋ የዯርግን እና የሻእቢያን የጦርነት ውጤት የወሰነች ሆና ሳሇ ሁሇት ገጽ ብቻ ተስፋዬ ሲሰጣት ሇምን ጓጉቶ እንዯሔዯ እና ካየው ያሌጻፈው እንዲሇ መረዲት ይቻሊሌ፡፡ ከ30 አመት በፊት በአለ ግርማ በ‹‹ኦሮማይ›› መጽሀፍ ካስነበበን ውጪ ተስፋዬ ምንም የተረከው ነገር የሇም፡፡ ቢያንስ ናቅፋ ሆዴ ውስጥ አለ ተብሇው የሚወሩት የሻአቢያ የአፍሪካ ምርጡ ጋራዥ እና ቢሮዎች ቢጽፋቸው ሇአሇቆቹም ይጠቅም ነበር፡፡ በአጠቃሊይ ተስፋዬ ኤርትራ ተጉዞ ክፉም ዯግም ያሌጻፈው ሻእቢያ በተሇያየ አቅጣጫ ተርጉሞት ወዯ አባት አገር መመሇሻ ከገባም መውጫ አጣሇው ብል ፈርቶ ይሆናሌ፡፡
ምእራፍ ሀያ አምስት ‹‹የልሚ ተረት›› የተስፋዬ ተረት ነች፡፡ እቴሜቴ የልሚሽታ የሚሇውን የሌጆች ጨዋታ ወዯ ተረት ሇውጦ ኢትዮጵያውያንን መዘባበቻ ማዴረጊያው ጽሁፍ ነች፡፡ ሌጅዋን 3000 ድሊር ከፍሊ በሉቢያ አዴርጎ አውሮፓ አዴርጎ እንዱገባ የፈሇገችው ምስኪን ኤርትራዊት በሌጅዋ መሞት ማበዴዋን እንዯሰማ በጥቂት ቃሊት ገሌጾ ፤ ኢትዮጵያዊ እናት ሊይ ሲሆን ሌጅዋን ማሳዯግ አትችሌም ተብሊ ስሇተነጠቀች አእምሮዋ ስሇተዛባ ሴት በሰፊው ሉነግረን ይፈሌጋሌ፡፡ ግን በሴትየዋ ታሪክ ውስጥ አዴርጎ ሉነግረን የፈሇገው እንዯማንረባ እና በእጃችን ያሇውን መንከባከብ እንዯማንችሌ በመተረክ ሇመሳሇቅ ነው፡፡ ጽሁፉ ቅኔ ይሆን ቀሌዴ?
ምእራፍ 27 ‹‹የሳባ ንግስት›› አንዴ ነገር አስታወሰኝ፡፡ ኢትዮጵያዊነቱ የተመሰከረሇት ፑሽኪን አሁን ዯግሞም ላሊ አገርህ የኛ ነው የሚሌ ቡዴን መጥቶበታሌ-ኤርትራ፡፡ ኤርትራ ሇፑሽኪን ሀውሌት አሰርታ በሩስያ ባሇስሌጣናት እንዲስመረቀች በቅርብ የምናውቀው ነው፡፡ አሁን ዯግሞም የመን የኔናት የምትሊትን ሳባ ፤ ሶስተኛ አገር ኤርትራ በተስፋዬ ታሪክ አማካኝነት የራሴ ነች እንዴትሌ ተስፋዬ የሚገፋፋ ይመስሊሌ፡፡ በዚህ ምእራፉ አንዳ ሳባ የምትባሌ ንግስት የሇችም ሲሇን ፤ ላሊ ጊዜ ዯግሞም ጎርኪይ ‹‹የወሲብ ሴሰኛ ናት›› አሇ ሲሇን ዯግሞም ኤርትራዊ እያዯረግ ንግስት ሳባን ክፉኛ አንገሊቷታሌ፡፡ እንዯሇመዯው እያንዲንደን የኢትዮጵያ ነገስታትን (አሇማየሁ ገሊጋይ በዯንብ ገሌጾታሌ) ማዋረዴ ፤ ማኮሰስ ፤ ከተቻሇም ታሪካቸውን ጥሊሸት መቀባት ተስፋዬ አሊማው አዴርጎ ከተነሳ ቆይቷሌ፡፡ አጼ ቴውዴሮስን 28 ውሽማ እንዯነበራችውና አገር ከማቅናት ሴት ሲያሳዴደ ህይወታቸው እንዲሇፈ ሉያሳምነን ይነግረናሌ፡፡ ቀስ ብል አጼ ቴውዴሮስ እንግሉዞቹን እነ ካሜሮንን ያገተው ሴቶቻቸውን ማማገጥ ፈሌገው ነው ሳይሇን ይቀራሌ ብሊችሁ ነው፡፡ አጼ ፋሲሇዯስን ዯግሞ የተገናኛቸውን ሴቶች ገል የሚቀብር አረመኔ አዴርጎ በዚህ ‹‹በስዯተኛው ማስታወሻ›› ጽፏሌ፡፡ የተስፋዬ ዴፍረት መረን የላሇው ነው፡፡ ተው ማሇት ዯግሞም የኛ የኢትዮጵያውያን ፋንታ ነው፡፡
ተስፋዬ ሇምን አማርኛ አስተምራ ፤ በስነ-ጽሁፍ ኮትኩታ ፤ አሳዴጋ እና ተንከባክባ ሇዚህ ያበቃችውን አገር በብእር ሇመውጋት እንዯሚፈሌግ ራሱ ነው የሚያውቀው፡፡ የኤርትራዊነት ዯም አስክሮት ነው እንዲሌሌ እጅግ በጣም ብዙ የኤርትራ ሰዎች የኢትዮጵያን ጉዲት እንዯራሳቸው እንዯሚያዩ አውቃሇሁ፡፡ ማሇት የምችሇው በተሇያየ ምክንያት ተስፋዬ ተስፋ ቆርጧሌ፡፡ ተስፋ ቢስ ሰው ዯግሞ ሲፈራገጥ እዚህም እዚያም መጠነኛ ጉዲት ማዴረሱ አይቀርም፡፡ ግን በዯንብ ከተያዘ አዯብ ባይገዛም ጉዲቱን ማጥፋት ይቻሊሌ፡፡ ከዚህም አንጻር የተስፋዬ ጽሁፍ በአማርኛው ውበቱ እንዯወረዯ ሳይወሰደ ታኝከው እና ተብሊሌተው የሚተፋውን መትፋት አሇብን፡፡ ካጣጣምነው ግን የመጨረሻ ጉዲቱ ሇኛ ነው፡፡

No comments:

Post a Comment