Tuesday, October 22, 2013

በቅድሚያ ከራስ ነው ትግል ሲባል፡ ወኔን፤ ብልህነትንና የውጭ የወያኔ ካድሬዎችን መጋፈጥን እውን ማድረግ ኢትዮጵያን ማዳን ነው።

ሌላውን ቀስቅሶ የትግል አጋር ለማድረግ፡ የቀደምት የለውጥ ሓዋርያት ወጣቶች፡ በቅድሚያ ከራስ ነው ትግል የሚለውን መርህ ከእልህና ወኔ ጋር አስተባብረው፡ በመጀመሪያ እራሳቸውን ለመስዋዕት ያቀርባሉ።

በዲያስፖራው ያለው ኢትዮጵያዊ፡ ዛሬ ዛሬ ግን የራሳቸውን ምስል ደብቀው፤ በፌስቡክና በትጥቅ ትግሉም ድርጅት በቅጽል ስም ብቻ ወያኔ በቃው፤ በቃ በማለትና ለሃገር አንድነት ጸረ ወያኔ ትግል የሚሳተፉ ኢትዮጵያውያን ብዙሃን ናቸው። አንዳንዱ ለትጥቅ ትግሉ የሚያግዝ አቋም ሲኖረው፡ ሌላው ደግሞ፡ በእውነተኛ ስሙ ከፋሽስት ወያኔ ጥቅማ ጥቅም ተቀብሎ በተለይም መሬት የማደልና የመቆጣጠር ፋሽስት ወያኔ ስልጣን ያለው ይመስል፡ የቤት መሥሪያ ቦታ ተቀብለው፡ በምስላቸውና በእውነተኛ ስማቸው መጋፈጥ የፈሩ ጸረ ወያኔ የትግል ግለሰቦች አሉ። 

አጠገባቸው የፋሽስት ወያኔ ካድሬ መጥቶ ሲሰብካቸው እንኳን፡ በአንድ ቃል ላለማሳፈር የሚንቀጠቀጡትን በግልጽ እያየን ነው። የሕሊና ባሪያዎች እንደሆኑ ግልጽ ነው። ምክንያቱም፡ በትጥቅ ትግሉም ይሁን በሰላማዊ ትግል ድርጅት ተሳታፊ ከሆኑ፡ ከወያኔ ተቀብለው የሠሩት ቤት እንደሚወረስ ማስጠንቀቂያ በወያኔ ካድሬዎች እንደደረሳቸው ግልጽ ነው።
የዚህ ተቃራኒው ደግሞ በጣም ትላልቅ ንብረትና ሃብት ተወርሶባቸው፡ በስማቸው፤ በራሳቸው ገጽ ፊት ለፊት እየተጋፈጡ ያሉ፡ የትጥቅ ትግል መሪዎቻችን ደግሞ የወደፊቷ ኢትዮጵያ መመኪያዎች ናቸው። ምክንያቱም ከራሴና ከንብረቴ በፊት ለውድ እናት ዓለም ኢትዮጵያ እናቴ ብለው፡ ለወደፊት ትውልዳቸው ነጻነት እንጂ ስለራሳቸው የማይጨነቁ ውድ እውነተኛ ዜጎችም አሉ። የነርሱን ፈለግ የተከተለ፡ የኢትዮጵያውያንን የነጻነት ቀን ያቃርባል።
በቅድሚያ ከራስ ነው ትግል ሲባል፡ ወኔን፤ ብልህነትንና የውጭ የወያኔ ካድሬዎችን መጋፈጥን እውን ማድረግ ኢትዮጵያን ማዳን ነው።
በውጭ ሃገራት ያሉ ትናንሾቹ የወያኔ ካድሬዎች መፈክር ቦንድ ግዙ ነው። ለነዚህ ሆዳሞችና መሠሪዎች ቀላሉ መልስ፡ የኢትዮጵያ የልማት መርሃ ግብርም ሆነ ማንኛውም የኢኮኖሚም ሆነ የሉአላዊነት ወሳኙ መንግሥት፡ የፋሽስት ወያኔ አረመኔው ቡድን ጨርሶ ከተገረሰሰ በኋላ ነው፤ ያለነጻነትና ሕዝባዊ መንግሥት ወይም በኢትዮጵያ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ተሳትፎ በተመረጠ መንግሥት ወደፊት ይካሄዳልና፡ ወያኔ እንድትቀሰቅስ ወይም እንድትቀስቅሺ የሰጠህ ወይም የሰጠሽ ጥቅማ ጥቅም ንዋይ፡ ከሰፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ የግብር ክፍያና፡ በኢትዮጵያ ሕዝብ ስም ወያኔ ከአለም ባንክ ተበድሮ፡ የኢትዮጵያ የወደፊት ትውልድ ዕዳ ገንዘብ ላይ ነውና በሃይማኖትም ይሁን በዓለማዊው መንፈስ ከሌባ ወንበዴ ወያኔ ሰራቂ ቡድን ነውና በንስሓም ይሁን በይቅርታ ሕሊና እርሳን ማዳን ክብር ዜግነት ያለው ኢትዮጵያዊነት ነው ብሎ መናገር የዜግነት መብታችንና ግዴታችንም ጭምር ነው።

ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!!!!!!!!!!!!!

ሞት ለወያኔ!!!!!!!!

 sebiawi

No comments:

Post a Comment