Thursday, October 31, 2013

ግን ማነው ሽብርተኛ? እየሩሳሌም አርአያ

የገዢው ፓርቲ ቱባ ፈላጭ ቆራጭ ባለስልጣናት በነበሩት አቶ ገ/ ዋህድ፣ አቶ መላኩ፣ አቶ ወ/ስላሴ ወዘተ መኖሪያ ቤት ውስጥ በርካታ የጦር መሳሪዎችና የጭስ ቦንብ ጭምር በህገወጥ መንገድ እንደተያዙባቸው በክሱ ተመልክቷል። ገ/ዋህድ 10 ክላሽ
ደብቆ መገኘቱ አስደናቂ ነው። አቶ መለስ ዜናዊን ከጎኑ አስቀምጦ « ምድረ ኪራይ ሰብሳቢ አጭበርባሪ ነጋዴ አስይሻለሁ..» እያለ ሲዝት የነበረው ገ/ዋህድ ለርሱ ጉቦ ያልሰጡ 200 ነጋዴዎች በአንድ ኮንቴነር ውስጥ በማሰርና በመደብደብ ከፍተኛ በደል
ሲፈፅም ነበር። ዋናው ነጥብ ወዲህ ነው፤ ባለስልጣናቱ ያን ሁሉ የአገር ሃብት ሲዘርፉ ሕገወጥ መሳሪያ ታጥቀው እንደሆነ አውቀናል።
ይህ ድርጊት « ሙስና » ብቻ ሳይሆን ሽብርተኝነትም ነው!! 90 ሚሊዮን ሕዝብ ሕገወጥ መሳሪያ ባነገቱ አካላት
በአደባባይ እየተዘረፈ ነበር፣ አሁንም እየተዘረፈ እንደሆነ አቃቤ ህግ ነግሮናል። በዚህ አጋጣሚ ገዢው ፓርቲን እንደግፋለን ለሚሉ አንድ ጥያቄ አለኝ፤ …ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋና ሌሎቹ መኖሪያቸው ውስጥ የተገኘው ብእርና ወረቀት ወይስ ታንክና
መድፍ?…እነ አቡበክር መሓመድና ሌሎቹ የሙስሊሙ ተወካዮች ቦንብና ከባድ መሳሪያ ይዘው ነው የተገኙት ወይስ ነጭ ጨርቅ ይዘው መብታችን ይከበር ሲሉ ከማህበረሰቡ ጋር ድምፃቸው እንዲሰማ ጠየቁ?..እነ አቶ በቀለና አንዱለም ክላሽና የጭስ ቦንብ ሰብስበው ነው የተገኙት ወይስ ሰላማዊ የትግል ጥሪ ለመስበክ ሕዝብን ሰብስበው ነው የተገኙት?…ከነዚህ መካከል በየትኛው እስረኛ ላይ ነው ከመሳሪያ ጋር የተያያዘ ክስ የቀረበው?…በጭራሽ የለም። ጥያቄው ማነው ሽብርተኛው?…የሚለው ነው። አገር የሚያሸብሩት ባለስልጣናት ናቸው ሽብርተኛ መባል ያለባቸው ወይስ ሌላው?..እስቲ እንጠያየቅ?….በነገራችን ላይ በየቦታው የሚፈነዱ ፈንጂና ቦንቦች በተመለከተ በቀድሞ የደህንነት ከፍተኛ ሹም ወ/ስላሴ ወ/ሚካኤል እጅ የተገኘው የጭስ ቦንብ በቂ ማስረጃ የሰጠን ይመስለኛል። በዚህ ዙሪያ ኮድ 2 አ.አ 057557 ስለሆነች የደህንነት መኪናና ስለቦንብ ቅንብር ድራማ እመለስበታለሁ። ..ግን ማነው ሽብርተኛ?

No comments:

Post a Comment