Monday, April 15, 2013

ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል ያለው ማነው?


በዚህ ቀረርቶ ማነው የሸለለው? ... እስኪ እጁን ያውጣ …. ከምር እጁን ያወጣ ካለ ይገረፍ !

በማንበብ ሰው ሲጎድል እንጂ ሙሉ ሲሆን አጋጥሞኝ አያቅም ወዳጄ፤ ከምር ማንበብ አልወድም፤ ምን ያደርጋል ለመጀመሪያ ጊዜ ያነበብኩት ግን ይሄን መፈክር ነው፤ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል!” ይሄንን ያነበብኩበትን ቀን እረግማለሁ፤ ለማንበብ ፈልጌ ሳይሆን አንብበኝ ብሎ ነው እኔ ጋር የመጣው፤ እኔ እንደምታቀኝ የዋህ ነኝ እኔን ብሎ መጥቶ አላሳፍረውም ብዬ አነበብኩት፤የምን ቱልቱላ ነውአንተን ብሎ እንዴት መጣ? ለሚል አልፈርድበትም፤ እኔን ያቀኛል ማለት ነው! በልጅነቴ አንቱ የተባልኩ መጽሐፍ ሸቃይ ነበርኩ፤ ገዝቼ ሳይሆን ከቤት ሰርቄ! …. በል አዳሜኪስህን ተጠንቀቅ! … ..በዝ እንዲህ ነው እንጂ! ….. ኪስ የምታክል ነገር መጠበቅ ካቃተህ ታዲያ ሃገር የሚባለውን ነገር እንዴት ልጠብቅ? እኔስ ለኪሴ አይደል መጽሐፍ ምሸጠው፤ ያስ ለኪሱ አይደል ሃገር የሚሸጠው …… ያን ሁሉ መጽሐፍ ይዤ ሸቀላ ስወጣ ግን እርእሱን አነበዋለሁ ብለህ ነው? እኔን አንዴ ግን ይሄን መፈክር አነበብኩማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል!”

ያነበብኩት የስኳር መጠቅለያ ላይ ነው፡፡ ስኳር ስገዛየዘንድሮ ልጅ ስኳርን በኪሎ እንጂ በጥቅልል አያቃትምጨዋታው በኪሎ እና በግራም ነው!

ስኳሩም በግራም
ወርቁንም በግራም
ጫቱንም በግራም
ተሰቃየን እኮ ፓራራም፤ ፓራራም ….. የሚል ግጥም ጻፍ ያሰኘኛል፤ እኔ ግን አልጽፍም፤ መጻፍ ስለማልችል ሳይሆን ሰውን እንዳላጎድል፤ እንዴት ነው ይሄን ግጥም ብጽፍለት ሙሉ ሚሆነው፤

መፈክር ማንን አልገደለ( አላስገደለ) ብለህ፤ ቀን ጥሎን እኛም ተሸወድን ማንበብ ጀመርን
አንድ
ሁለት
ሦስት መጽሐፍ እንዳነበብኩ ጎዶሎነት ተሰማኝ፤ መሳቀቅ ጀምርኩ፤ ይሄን ስለው (ትውልዱን አይደለም) ስለው ይሄአልገባ አለኝ! … ጭራሽ ከጎዶሎነት ወደ ባዶነት ወረድኩ ….. በቃ! እውነቴን ነው ምልህ አታንብብ ካነበብክ ጎዶሎነት እንጂ ሙሉ ነት አይሰማህም …. 5ኛው መጽሐፍ ላይ ማንበቤን ትቼ መጽሐፍ ይዤ ከአንባቢዎች ጋር መዋል ጀመርኩ አንባቢ ለመባል፤ ከማንበብ ይልቅ አምባቢ መባል እንደሚያስደስት ገባኝ! ደስ አለኝ!

አታንብ ብያለሁ አታንብ፤ ካለዚያ ባዶነት ይሰማሃል፤ ባዶ ስትሆን ደግሞ ትገነፍላለህ …. መገንፈል ከሙላት ብቻ ነው ያለው ማነው? የጎዶሎ ግንፍልም አለልህ …. የጎዶሎ ግንፍል እስካሁን አልጠቀመንም (ትገነፍላለህ ስልህ ስለ አብዮት እያወራሁ እንዳይመስልህ)…. ስለዚህ አታንብ ፤ካነበብክ ጎዶሎ ትሆናለህ፤ ከጎደልክ ትገነፍላለህ፤ ኢትዮጵያ ታንብብ የሚሉትን አትስማቸው ኢትዮጵያን ሊጠቅሙ ሳይሆን ሊያገነፍሉ ያለሙ ናቸው!

** አንድ ነገር ደግሞ በጆሮህ ሹክ ልበልህ?** ** ጅል አንባቢ ከሆንክ የኔን ምክር ሰምተህ ማንበብ ታቆማለህ!**

ከአገኘው አሰግድ

No comments:

Post a Comment