Monday, April 22, 2013

“ስማርት” ወይም “ፋራ”


ፖለቲከኞችንና ጋዜጠኞችን በገፍ የሚያስርና የሚያንገላታ (እንደ ወያኔ/ኢህአዴግ መንግስት) እሱም ዕጣ ክፍሉ ከፋራዎች ጐራ ነው፡፡ በማስፈራራት የሥልጣን ዘመኑን ለማራዘም የሚሞክርም (እንደ አፍሪካ አምባገነኖች) ምድቡ ከፋራ ፓርቲዎች ነው፡፡ የሰው ነገር የማይሰማና ራሱን ብቻ የሚያዳምጥም የትም ሊመደብ አይችልም - ከፋራዎች ተርታ እንጂ፡፡ ተቃዋሚውን እያሳደደ የሚገድል መንግስትስ? እንዲህ ያለው ፋራም አራዳም አይደለም - “ንክ” ነው፡፡ እንዲህ ያለ መንግስት ሁነኛ ሆስፒታል መግባት አለበት -የአዕምሮ ሃኪም (ስፔሻሊስት) ነው ለዚህ መድሃኒቱ፡፡  በመጨረሻም ፕሮፖዛሉ ፋራና አራዳ ፓርቲዎችንና መንግስታትን በመለየት በየጐራቸው የሚመድብ ተቋም ማቋቋም እንደሚያስፈልግ ይጠቁምና ፓርቲዎች ለምርጫ ሲወዳደሩ አባላቶቻቸው “ስማርት” ወይም “ፋራ” የሚሉ ባጆችን ደረታቸው ላይ ማንጠልጠል  እንዳለባቸው ይገልፃል፡፡ ለምሳሌ - “ወያኔ/ኢህአዴግ - አራዳ ፓርቲ”ሊሆን አይችልም!ለምሳሌው ወይም “ኢህአዴግ ፋራ ፓርቲ”ትክክለኛው! አሊያም “አንድነት - አራዳ ፓርቲ” ወይም “አንድነት - ፋራ ፓርቲ”  የሚል ሊሆን ይችላል፡፡ ከዛስ? ከዛማ ቀላል ነው፡፡ ህዝብ የሚፈልገውን ይመርጣል - ከስማርትና ከፋራ ፓርቲዎች፡፡ ፕሮፖዛሌ እንደሚለው ፋራና አራዳ ፓርቲዎች የሚለዩበት ዋና ዓላማው፣ ዜጐች ድምጽ ሲሰጡ ፋራዎችን መርጠው እንዳይሸወዱ (እንዳይፀፀቱ) ለማድረግ ነው፡፡
 በተግባር ያልተፈተኑ አዳዲስ ፓርቲዎችን ለመመዘን ደግሞ የፖለቲካ ፕሮግራማቸውን መገምገም እንደሚያስፈልግ ፕሮፖዛሌ ይመክራል፡፡ የፖለቲካ ፕሮግራማቸውን በማየት ብቻ ፋራ ይሁኑ አራዳ ማወቅ እንደሚቻል አንዳንድ “ጥናቶች” ይጠቁማሉ፡፡ በነገራችን ላይ ምርጫ ቦርድ ራሱም በስማርትና ፋራ ምድብ ውስጥ እንደሚካተት ፕሮፖዛሌ ይጠቁማል፡፡ እኔ የምለው ግን ያለፉትን አራት ብሔራዊ ምርጫዎች ያስተናበረው ብሔራዊ የምርጫ ቦርዳችን “ፋራ” ነው “አራዳ”? በነገራችን ላይ አቶ በረከት የ97ና የ2002ን ምርጫ የገለፁበት ቋንቋ ማርኮኛል፡፡ (ልብ አድርጉ ቋንቋው ነው የማረከኝ! ይዘቱ አልወጣኝም!) “የ97 ምርጫ - በሰላም ተጀምሮ በረብሻ የተጠናቀቀ” ሲሉት “የ2002 ምርጫ - በሰላም ተጀምሮ በሰላም የተጠናቀቀ” ብለውታል፡፡ (ግጥም ሊመስል እኮ ትንሽ ነው የቀረው!)  ውድ አንባብያን - ፋራና ስማርት የምትሏቸውን የአገር ውስጥ የፖለቲካ ፓርቲዎች (ዳያስፖራን አይመለከትም) በመለየት ለዲሞክራሲ ባህላችን መዳበር የበኩላችሁን አስተዋጽኦ እንድታበረክቱ ተጋብዛችኋል፡፡ ስፖንሰርሺፕ ከባለሃብቶች እስኪገኝና ፕሮፖዛሉ ተግባራዊ እስኪሆን ድረስ ብቸኛው አማራጭ “አራዳ” ፓርቲዎችን ያብዛልን እያልን መፀለይ ብቻ ነው፡፡ አሳብ ስጡን እንወያይ!!
ከሰብኣዊ

No comments:

Post a Comment