Tuesday, April 16, 2013

የርዕዮት ሽልማትና የእኛ ዝምታ


ጋዜጠኛና መምህርት ርዕዮትአለሙ የቤተሰቦቿ የመጀመሪያ ልጅ እንደመሆኗ መጠን ሃላፊነት ነበረባት፡፡ይህንን ሃላፊነት ለመወጣትም ርዕዮት ከማስተማር ሞያዋ ጎንለጎን በትርፍ ጊዜዋ ህጻናትን ታስተምር ነበር፡፡ከዚህ የሚገኘው ገቢ ደግሞ የቤተሰቡን ኑሮ ይደጉማል፡፡በሩጫ የተሞላው የጋዜጠኛዋህይወት በአንድ ማለዳ ቀለም ወደ ምትመግባቸው የምስካዬ ህዙናን ትምህርት ቤት ተማሪዎች ክፍል ለመግባት ስትዘጋጅ የእስር ማዘዣባወጡባት የፌደራል ፖሊሶች እጅ ወደቀች፡፡ርዕዮት ታስራለችና ቤተሰቡ ከእርሷ ያገኘው የነበረውን ድጉማ ማጣቱ ግድ ሆነ፡፡
አምላክ ሳይደግስ አይጣላምእንደሚሰኘው እስከዳር የርዕዮትን ፍኖት በመከተል የቤተሰብ ግዴታዋን ለመወጣት በሞያዋ ስራ ማፈላለጉን ተያያዘችው፡፡እናም ተሳካ፡፡በጥሩደሞዝ በአንድ የግል ድርጅት ውስጥ ተቀጠረች፡፡ይህ ከርዕዮት መታሰር በኋላ ለቤተሰቡ የተደመጠ የመጀመሪያው መልካም ዜና መሆኑ ነው፡፡ቹቹ(የእስከዳር የቤት ስም ነው)ባገኘችው አዲስ ስራ ብዙም መቀጠል አልቻለችም፡፡ቀጣሪዋ ወደ ቢሮው ጠርቷት‹‹የሆኑ ሰዎች ትናንት አንቺከቢሮ ከወጣሽ በኋላ መጥተው ነበር፡፡
ይህቺን ልጅ ካላስወጣችኋት ድርጅታችሁ ከመንግስት አንዳች ነገር ቢፈልግ ትብብር አይደረግለትምብለውኝ ወጡ፡፡ስለዚህ እባክሽ ምን እናድርግ?››እስከዳር አላመነታችም‹‹ምንም ችግር የለም በእኔ ምክንያት እናንተ መጉላላት የለባችሁምስለዚህ ስራውን መልቀቅ እችላለሁ››ቢሮውን ለቅቃለት ወጣች፡፡ከትንሽ መውጣትና መውረድ በኋላ ቹቹ ሌላ ስራ አገኘች፡፡የዚህን ስራየአንድ ወር ደሞዝ እንኳን መብላት ሳትችል አሰሪዋ ‹‹ውጪልኝ ሰዎች መጥተው ከእሷና ከድርጅትህ አንዱን ምረጥ ብለውኛል ››አላት፡፡እየሳቀችስራውን ለቀቀችለት፡፡
በቅርቡ ግን ያጋጠማትለየት ያለ ነው፡፡ጥሩ ስራ በመገኘቱ ያለሽን የትምህርትና የስራ ልምድ አስገቢ ተብላ በጓደኞቿ በመወትወቷ ነገ ሊያሥወጡኝ በሚልስሜት ወደ ተባለው ቦታ አመራች፡፡ለስራው ብቁ የሚያደርጋትን ማስረጃ አስገብታ ከገባችበት ቢሮ ስትወጣ አንድ ጉስቁስቁል ያለ ወጣትከአፉ የሚያወጣቸውን ቃላት ጠንከርና ረገጥ እያደረገ‹‹አትልፊ እኔ እያለሁ አንቺ ስራ አትቀጠሪም››ብሏት ሊቀጥራት ወዳናገራት ድርጅትመሰስ ብሎ ገባ ይሄው ድርጅቱም እስካሁን ድረስ አልደወለላትም፡፡ቹቹ አሁን በዚህች አገር ሰርታ መኖር እንዳትችል የሆነ የፈረደባትአካል እንዳለ ማመን በመጀመሯ ከአሁን በኋላ ስራ ፍለጋ እግሬን ንቅንቅ አላደርገውም የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሳለች፡፡
ብዙዎቻችን እንደምናውቅየርዕዮት አባት አቶ አለሙ የህግ ባለሞያ ናቸው፡፡ልጃቸው ቃሊቲ ከመውረዷ በፊት የተለያዩ የፍርድ ቤት ጉዳዩችን በመያዝ ገቢ አግኝተዋል፡፡አሁንግን ጥብቅና እንዲቆሙላቸው የሚጠይቁ ደምበኞች ወደ እርሳቸው ቢሮ እንዳይመጡ አንድ ስውር እጅ ሆነ ብሎ እየቀሰቀሰባቸው ይገኛል፡፡‹‹እርሳቸውየሚይዙት ጉዳይ ፍርድ አያገኝም››ወደ አቶ አለሙ ቢሮ ለማምራት ለሚፈልጉ ሰዎች የሚነገር ማሸማቀቂያ ነው፡፡እናም የስራ ነገር ለአቶአለሙ አሁን እጅግ ከባድ ሆኗል፡፡
የርዕዮት የሞያና የፍቅርአጋር የሆነው ጋዜጠኛ ስለሺ ሀጎስ ከእጮኛው መታሰር በፊት ህይወትን ለማሸነፍ በሁሉም አቅጣጫ የሚታትር ብርቱ ነበር፡፡ ቃሊቲ ፍቅሩንከነጠቀችው በኋላ ግን የህይወት ትግሉ ላይ በረዶ እንደተደፋበት ስሜቱ ቀዝቅዟል፡፡የጸሀይ ብርሃንን የፈራ ያህል ለቃሊቲ ጉዞ ካልሆነበቀር ከቤቱ መውጣትን አይፈቅድም፡፡የርዕዮት መታሰር ስንቱን እንዳሰረ አያችሁን?
እርግጥ ነው እኛ ኢትዮጵያዊያንጀግኖች እንዲወለዱ እንጸልያለን እንጂ የተወለዱት ጀግኖች መከራ በደረሰባቸው ጊዜ አብረናቸው አንቆምም፡፡ርዕዮት፣እስክንድር፣ ውብሸት፣አንዷለም፣ናትናኤልናሌሎቹም ከራሳቸው ርቀው ስለ ህዝብ በመጮሃቸው የቃሊቲ ደጃፍ ተቆልፉባቸዋል፡፡የእነዚህ ሰላማዊ ታጋዮች መታሰር በቤተሰቦቻቸው፣በሚረዷቸውሰዎችና በልጆቻቸው ላይ ከሚያደርሰው የህሊና እና የስነ ልቦና ቀውስ በተጨማሪ የኢኮኖሚ ምስቅልቅሉ በቃላት ሊገለጽ የማይችል ነው፡፡የታጋዮቹአሳሪዎችም ከምንም በላይ የህዝቡን አለመደጋገፍ የሚገነዘቡ በመሆናቸው የሚያቀርቡት የመጀመሪያ ጥያቄ‹‹ለምን ለልጆችህ ለመኖር አትፈልግም››የሚል ነው፡፡
የውብሸት ልጅ ውብሸትበመታሰሩ ምክንያት ለትምህርት ቤት የሚከፍልለት አጥቶ ወደ ዝቅተኛ ትምህርት ቤት እንዲሸጋገር መደረጉ ስድቡ ውብሸትን አደንቀዋለሁለምንለው እኛ እንጂ ለእርሱ አይደለም፡፡ይህንን እያዮና እየሰሙ እንዴት ሌሎች ውብሸቶች ይፈጠሩ?ውብሸት የታሰረ ሰሞን እኔና ጋዜጠኛነብዮ ሀይሉ ከውብሸት ጋር አብሮ ይሰራ የነበረን አንድ የአውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ባልደረባ ቀጥረን አገኘነውና‹‹ውብሸት በመታሰሩቤተሰቡ ችግር ላይ ሊወድቅ ይችላል፡፡ስለዚህ ለምን የሆነች መዋጮ በማድረግ የምንችለውን አናደርግም ››አልነው፡፡ምላሹ ያልጠበቅነውነበር‹‹መንገስት እርሱን መንግስት ያሰረው በሽብርተኝነት ጠርጥሮት በመሆኑ አሁን እገዛ ብናደርግ እኛንም ተባባሪ ሊያደርገን ይችላል››አለን፡፡ውብሸትይቅርታ ጠይቆ ሊወጣ ነው በተባለ ሰሞን ይህ ጋዜጠኛ የፌስ ቡክ ገጹን በውብሸት ፎቶግራፍ ሞልቶ ማየቴም እፍረት አሳድሮብኝ ነበር፡፡
ለማንኛውም ዛሬ ማለዳያደመጥኩት ዜና ድብልቅልቅ ያለ ስሜት ፈጥሮብኛል፡፡ፈረንጆች ለእኛ የመብት ተሟጋቾች እውቅና በመስጠት ሽልማት እያበረከቱ ነው፡፡በዚህመነሻነትም ርዕዩት ሃሳብን በነጻነት ለመግለጽ በከፈለችው መስዋዕትነት የተነሳ 25.000 ዶላር  አሸናፊ ሆናለች፡፡ ከገንዘቡ ባሻገር በርዕዮት ዙሪያ ላሉ ሰዎች በሙሉ ይህትልቅ ማበረታቻ ነው፡፡እናም የርዕዮት እህት፣ አባትና እጮኛ በመሆናቸው ብቻ ዋጋ እየከፈሉ ያሉትን በሙሉ በዚህ አጋጣሚ እንኳንደስ አላችሁ ማለት ወደድኩ፡፡ከወሬ የዘለለ ማድረግ ላልቻልን ከቃሊቲ በመለስ ላለን ለእኛ ግን አፈርኩ፡፡
ከዳዊት ሰለሞን


No comments:

Post a Comment