Friday, April 12, 2013

በኢምሬትስ በአሰሪዋ ትኩስ ዘይት የተደፋባት ኢትዮጵያዊት በዶክተሮች እርዳታ ላይ መሆኗ ተገለጸ::


በኢምሬትስ በአሰሪዋ ትኩስ ዘይት የተደፋባት ኢትዮጵያዊት በዶክተሮች እርዳታ ላይ መሆኗ ተገለጸ::
በሞሮኳዊትዋ አሰሪዋ የትኩስ ዘይት መደፋት ተጠቂ የሆነችው ኢትዮጵያዊት በተረጋጋ መልኩ በተደረገላት የቆዳ ቀዶህክምና ህይወቷን ለማትረፍ እየሰሩ መሆኑን ዶክተሮች አመለከቱ::የቃሲሚ ሆስፒታል ሃላፊዎች እንዳሉ የተቃጠለውን የሰውነት ክፍሏን አንድ በአንድ በቆዳ ስፔሻሊስቶች እያስተካከልን ሲሆን በጀርባዋ አከባቢ ያለውን የተቃጠለውን ክፍል በተሻለሁኔታ አክመን መሻሻሎች ታይተውባታል ብለዋል::
ቀዶ ህክምናው በተረጋጋ መልኩ የተካሄደ እና ከአንድ ሰአት በላይ የወሰደ ሲሆን የተቃጠለውን የሰውነት ክፍል በማስወገድ ለላ አዲስ ቆዳ እስኪሰራ ድረስ በተረጋጋ ሁኔታ ህክምናው መካሄዱን ገልጸዋል::
ይህ ከሁለት እስከ ሶስት ሳምንት የሚወስደው ህክምና አዲአ ቆዳ እንዲያድግ የተለያዩ ክሬሞች እና የህክምና እርዳታዎችን እንጠቀማለን ብለዋል::
የሻርጃ ፖሊስ አሰሪዋን በጭካኔ ተግባሯ የከሰሳት ሲሆን ሁኔታውን በመኖሪያዋ አከባቢ ከሚገኘው የዱባይ ፖሊስ በመተባበር ምርመራውን እያደረገ መሆኑን ገልጿል::የቤት ሰራተኛዋ ወደ ሆስፒታል ስትመጣ በፊቷ በጀርባዋ እና በፊቷ ላይ የአንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ የመቃጠል ጉዳት ደርሶባት ነበር::..ሁልግዜ በአሰሪዋ እንደምትሰቃይ እና ዘይት ከደፋችባት በኋላም ....ወደ ህክምና የመጣችው ከአሰሪዋ እውቅና ውጪ ነበር::ለዶክተሮች እንደተናገረችው::

No comments:

Post a Comment