በእርግጥ ወያኔ/ ኢህአዴግ ላዩን ስትታይ ገናና ፓርቲ ይመስላል ግን ውስጡ ቅል ነው፣ በየጊዜው የሚከሰቱ ግጭቶችን እየገደለ፣ ደም እያፈሰሰ እድሜውን ለማራዘም ችሏል እስከመቼ? ነገር ግን፣ በሃይማኖት ተቋማት ውስጥም ሆነ፣ ሃይማኖትን ሰበብ አድርገው በተሰባሰቡ ቡድኖች መካከል የሚፈጠሩ ግጭቶች በጣም አስቸጋሪ እንደሆኑ አይካድም። በጂማ በርካታ ሰዎች ሕይወታቸውን ያጡበት ግጭት አንድ ምሳሌ ነው። የግጭቶቹ መነሻና መድረሻ አስቀድሞ ለመገመት ያስቸግራል። ግን ለመቀጣጠል ዝግጁ የሆነ ቤንዚን በአንዳች ምክንያት መቀጣጠሉ አይቀርም። ከወልቃይት ስኳር ፋብሪካና ከዋልድባ ገዳም ጋር በተያያዘ ምን ያህል ግርግር እንደተፈጠረ አይታችኋል። የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ምርጫና ከአወልያ ትምህርት ቤት ጋር በተያያዘ በአዲስ አበባና በተለያዩ የክልል ከተሞች የተከሰተውን ግጭት ታዝባችኋል። አንዳንዱ ከሃይማኖት ነፃነት ጋር የተያያዘ ነው።
በሃይማኖት ሰበብ የሚፈጠር ውዝግብና እና የአክራሪነት ግጭት በቀላሉ ከቁጥጥር ውጭ ሊሆን የሚችል ከፍተኛ የፖለቲካ አደጋ ነው። በጣም አሳሳቢው ነገር፣ የሃይማኖት ነፃነትንና የሃይማኖት አክራሪነት ለይቶ ለግለሰብ ነፃነት በፅናት የሚቆም ብዙ ሰው የለም። የሃይማኖት ነፃነትን መደገፍና የሃይማኖት አክራሪነትን መከላከል የሚቻለው፣ ለሃሳብ ነፃነት (ለግለሰብ ነፃነት) ከፍተኛ ክብር ሲኖረን ነው። ነገር ግን የሃሳብ ነፃነትን በሚጥስ የመንግስት ፕሮፓጋንዳ ተጥለቅልቀን እየኖርን፤ ለሃሳብ ነፃነት በፅናት የመቆም ብርታት እንዴት ሊኖረን ይችላል?

ከላይ እንደጠቀስኩት፤ መሰረታዊው የፖለቲካ ጥያቄ፤ እያንዳንዱ ሰው፣ የማሰብ፣ የመደራጀትና የመምረጥ ነፃነት ሊኖረው ይገባል ወይ?” የሚል ነው። “የግለሰብን ነፃነት የመጣስ ስልጣን የያዘ አካል መኖር አለበት ወይ?” ነው ጥያቄው። የመንግስት ስልጣን የያዙ ሰዎች የግለሰብን ነፃነት (የሃሳብ ነፃነት) የመጣስ መብት አላቸው የምንል ከሆነ፤ አክራሪዎችም መብት አለን ይላሉ።
ስልጣን የያዙ ሰዎች፣ ለነሱ የማጥማቸውን ሃሳብ በማፈን አገሬውን በፕሮፓጋንዳ የሚያጥለቀልቁት ለምንድነው? “ለአገር እድገትና ለህዝብ ጥቅም የሚበጅ ልማታዊ አስተሳሰብ እንዲሰፍን እንፈልጋለን” ይላሉ። ... ይህንንም አገራዊ መግባባት (national consensus) ይሉታል። እያንዳንዱ ሰው የማሰብና ሃሳቡን የመግለፅ ነፃነት ተከብሮለት፤ ተወያይቶና ተከራክሮ... አብዛኛው ሰው ተቀራራቢ አስተሳሰብ ቢይዝ ችግር የለውም። የተለያዩ ሃሳቦች እንዳይገለፁ በማፈን፣ ሁሉም ሰው በባለስልጣን የተነገረውን ሃሳብ እንዲይዝ በፕሮፓጋንዳ መጠዝጠዝ ግን ሌላ ጉዳይ ነው። የሃይማኖት አክራሪዎችምኮ ከዚህ የተለየ ብዙም ክፋት የለባቸውም። “ለሰው ልጅ ፅድቅ የሚበጅ፣ ገነት ለመውረስ የሚያስችል የፈጣሪ መንገድ እንዲሰፍን እንፈልጋለን” ይላሉ። ... ይህንንም “የሃይማኖት እምነት” ይሉታል። የመንግስት ፕሮፖጋንዳን በዝምታ የሚቀበል ስርዓት፤ አክራሪዎችን የመከላከል አቅምና መከራከሪያ መርህ አይኖረውም። ብቸኛው መከላከያ የግለሰብ የሃሳብ ነፃነት እንዲከበር ማድረግ ነውና።
ከሰብኣዊ
No comments:
Post a Comment