Monday, April 8, 2013

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እንዲለቀቅ መጠየቁ


ለጋዜጠኞች መብት የሚሟገተው ድርጅት ሲፒጄይ እንዲሁም መንግስታዊ ያልሆነውና በተለያዩ ምክንያቶች ለታሰሩ ግለሰቦኖች የሚሟገተው ድርጅት «ፍሪደም ናው» ዛሬ ባወጡት መግለጫ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በአስቸኳይ ከእስር እንዲለቀቅ ጥሪ አሰምተዋል።
ዋና ፅህፈት ቤቱን ዋሽንግተን ዲሲ ያደረገው «ፊሪደም ናው» የተሰኘው አምስት ጠበብትን ያቀፈው የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት አጥኚ ቡድን እስክንድርን ለዕስር የዳረገው በሰላማዊ መንገድ ሀሳብን በነፃ የመግለፅ መብትን በመጠቀሙ እንደሆነ በዘገባው ገልፅዋል። ቡድኑ እስክንድር ነጋ እንዲፈታ የጠየቀበትን ምክንያት «በፍሪደም ናው» ድርጅት አቃቢ ህግ የሆኑት-ፓትሪክ ግሪፊዝ ያስረዳሉ፤ « በቡድኑ አስተያየት መሰረት የኢትዮጵያ መንግስት አቶ እስክንድር ነጋን ያሰረው በመሰረታዊ መብቱ በመጠቀሙ ነው። በዓለም አቀፉ ህግ የሚፈቀድለትን በርካታ የፍርድ ሂደትንም ነፍጎታል። እስራቱ ኢትዮጵያ የፖለቲካ መብቶችን ለማክበር የገባችውን ግዴታ የሚጥስ ካለፍርድ ሂደት በዘፈቀደ የተፈፀመ ነው። በዚህም የተነሳ ነው ጉዳዩን የተከታተለው ቡድን አቶ እስክንድርን አሁኑኑ እንዲፈታ የጠየቀው።

ለጋዜጠኞች መብት የሚሟገተው ሲፒጄይ እና ሌሎች ድርጅቶች በተደጋጋሚ ለታሰሩ ጋዜጠኞች ይቆማሉ። ሆኖም እስክንድር አሁንም በእስር ላይ ነው የሚገኘው፤ ታድያ ቡድኑ ከኢትዮጵያ መንግስት ምንድን ነው የሚጠብቀው?
« ተስፋ የምናደርገው ወይንም ተስፋ ያደረግነው የኢትዮጵያ መንግስት አሰባስበን ጉዳዩን ለሚመለከተው ቡድን ለላክነው ፊርማ መልስ ይሰጣል ብለን ነበር። ነገር ግን ያሳዝናል መልስ አልሰጡም። የተባበሩት መንግስታት አስተያየትን የያዘ ነበር አዲስ የስክንድርን ጉዳይ በተመለከተ። በርካታ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች አሉ እንዲፈታ የጠየቁ ። እንዲሁ በርካታ ቁጥር ያላቸው አለም አቀፍ ተቋማትም ጉዳዩ እንደሚያሳስባቸው አሳውቀዋል። ይህ ግን የመጀመሪያው ነበር አንድ አለም አቀፍ አቋም መጥቶ መፈታት አለበት ሲል። ይህንን በዚህ ሳምንት ሊያደርግ ይችላል። በዚህ ሳምንት ውስጥ ብይን እንደሚሰጥ ቀጠሮ ነበር። እና ትኩረት ሰጥተው የፊርማውን ጉዳይ ይመለከታሉ እና ይፈቱታል ብለን ተስፋ እናደርጋለን። »
ከእስክንድር ነጋ ሌላ ሌሎች ጋዜጠኞችም በእስር ላይ እንደሚገኙ በዘገባው ተካቷል። የሌሎቹስ ጉዳይ ምን ይመስላል? በምን ሁኔታ ላይ ነው ያሉት?
« በሌሎቹ ጉዳዮች ላይ ራሴን ባለሙያ አድርጌ መቁጠር አልሻም ምክንያቱም እኛ ህግን ተከትለን የምንሰራ እና ለግለሰብ ደንበኞቻችን የቆምን ነን። እርግጥ ሌሎች እንደ ርዕዮት ያሉ እንዳሉ አውቃለሁ። እስክንድር ፤ በጥልቀት የሚያተኩር ኢትዮጵያ ውስጥ በሰፊው የታወቀ ጋዜጠኛ ነው። እናም በአሸባሪነት ተከሰው ጋዜጠኞች በእስር ላይ ጊዜያቸውን እንዲገፉ ማድረግ በእርግጥ የሚያሳስብ ጉዳይ ነው። የእስክንድር መታሰር በተናጥልም ቢሆን ቢያዩት እንደሚመስለኝ የኢትዮጵያ መንግስት በሰፊው በሚነቀፈው አሻሚነት ባለበት የፀረ ሽብር ደንብ የሚያከናውነውን ተግባር በሰፊው የሚያመላክት ነው።»
ሀሳብን በነፃ በመግለፅ ሂደቱ የአለም አቀፍ ጫና መፍትሄ ስለመሆኑ ፓትሪክ ግሬፌዝ አክለው ሲገልፁም፤ እንደ ዮናይትድ እስቴትስ ያሉ መንግስታት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋ የምግብ ዋስትናን በተመለከተ ቅርብ ትስስር ስላላቸው መንገዱ ይኖራቸዋል ብለዋል።

No comments:

Post a Comment