Wednesday, April 10, 2013

ውጭ ጉዳይ ሚ/ሩ ለግራዚያኒ የሚሰራውን ሀውልት አለም እንዲያወግዘው ጠየቁ


አወዛጋቢ ንግግር በመናገር የሚታወቁት የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ሚያዚያ 1 ቀን ሚኒስተሩ በሰጡት አስተያየት የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሀኖም የአለማቀፉ ማህበረሰብና የአፍሪካ ህብረት በኢትዮጵያ እና በሊቢያ ዜጎች ላይ ጭፍጨፋ ላደረሰው ግራዚያኒ ሀውልት ለማቆም የሚደረገውን ጥረት እንዲያወግዝ ጠይቀዋል።ሚ/ሩ ይህን የተናገሩት በሩዋንዳ የደረሰውን ዘር ማጥፋት 19ኛ አመት ለማስታወስ በተጠራ ዝግጅት ላይ ነው።
የኢትዮጵያን እና የሊቢያን ዜጎች በግፍ የጨፈጨፈው ግራዚያኒ ሀውልት አይገባውም ብለዋል ሚኒስትሩ።የሚኒሰትሩ ንግግር መጋቢት 8 ቀን 2005 ዓ.ም አ/አ ስድስት ኪሎ የካቲት 12 መታሰቢያ ሐውልት እስከ ጣሊያንኤምባሲ ሰልፍ በማድረግ በጣሊያን ለፋሽስቱ ግራዚያኒ መናፈሻና ሙዚየም መሰራቱን በመቃወማቸው አለማቀፍ የህግ ባለሙያውን ዶ/ር ያእቆብ ሀይለማርያምን ጨምሮ 38 ያህል ሰዎች በፖሊስ ታስረው ከተፈቱበት ድርጊት ጋር የሚቃረን ሆኖ ተገኝቷል።የኢትዮጵያ መንግስት በወቅቱ በወሰደው እርምጃ ከፍተኛ ትችት ሲደርስበት እንደነበር ይታወሳል።

No comments:

Post a Comment