Monday, April 15, 2013

አገር ወዳዱ ፕ/ር አስራት ወልደየስ በአንድ ወቅት የተናገሩት።


/ አስራት ወልደየስ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ሲሆኑ ለህዝባቸው ሲታገሉ የነበሩ ከህዝብ አእምሮ ውሌም የሚታወሱት ሰው ናቸው። በአንባገነኑ ወያኔ እስርቤት የተገደሉ ሲሆን ነብሳቸውን ይማረውና ከማይረሱ ንግግራቸው ውስጥ በአንድ ወቅት ከተናገሩት  ኢቲቪ ሰዓት ብቻ ነው እውነት የሚናገረው ያሉት አባባል በህዝብ ዘንድ አይረሳም!!
ዛሬ ውድ ሀገራችን ደብዘዋ ጠፍቶ፣ ሕዝቧ ምስቅልቅሉ ወጥቶ ፣ሥነልቡናው እየተሰለበ፣ዓይኑ እያየና ጆሮው እየሰማ፣ ባህሉ እየተንቋሸሸና እየተጓደፈ፣ ታሪኩ እየተደለዘና ቅርሱ እየተመዘበረበት የውሻ ሞት እየሞተ ነው። በእንደዚህ ያለ የመከራ ጊዜና ወቅት አንገቱን ደፍቶ፣ያልከፋው መስሎ ሆደሰፊ በመሆንና ሳይቸኩል ፈጣሪውን ለምህረት እየተማፀነ ራሱን ሳያጋልጥ ለትግል የሚሰናዳ ታላቅ ሕዝብ የኢትዮጵያ ሕዝብ ብቻ ነው።  / አስራት ወልደየስ በመአህድ የወጣቶች ስብሰባ ላይ ከተናገሩት የተወሰደ።

No comments:

Post a Comment