Wednesday, April 24, 2013

ቅቡር ጠ.ሚኒስተር ሀይለመለስ ደሳለኝ ህዝቡ ለመብቱ የሚያደርገው ትግል ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳሰቡ!


የልማታዊው መንግስታችንና አባታችን (ነፍስ ይማር?!!(ግን እየመሩን አይደል እንዴ!!)) የራዕይ ልዑክ ቅቡር .ሚኒስተር ሀይለመለስ አሉ: “ባደጉት ሀገሮች ህዝቡ ለመብቱ በጣም ነው የሚታገለው…….ሁሉም ሰው ለመብቱ ባንድነት ቢጮህ ኖሮ……..!!” ኧረ ቅቡርነትዎ የህዝብ ጩኸት ዋጋ እንዳለው ያውቃሉ ማለት ነው!!? ታዲያ ህዝብዎ ሲጮህነና ሲያነባ ጆሮዎን ተጫምተውት ነበር እንዴ??? ባያዩ እንኳን አይደንቅም!! እንዴት ነው ነገሩ? ለነገሩ አንሶላ የሚያህል ጆሮ ባንጠለጠለ ቢሆን ኖሮ እርሶና ዝሆኖች የኢትዮጵያውያንን ጩኸትና ዋይታ በሰማችሁ ነበር! በእምነትና በዘር እያሳበባችሁ ከፋፍላችሁን ስታበቁ በየማሰቃያ ቤቶቻችሁ እንደ እባብ እየቀጠቀጣችሁት ብሎም እየገደላችሁ ዱካውን እያጠፋችሁት ያለውን፤ በብሄር ደም ልታፋስሱት ከቀዬው በረጅሙ እጃችሁ ስታፈናቅሉት ያለው ህዝብ ህዝብ አይመስላችሁማ? አይዞኣችሁ ኢትዮጵያዊ ህዝብ ሆኖ የሚታያችሁ ቀን ይመጣል!!!

አይ የርሶ ነገር!! ዛሬ በፓርላማ ሲቀላቅሉ በሳቅ አነፈሩኝኮ!!! ወይ ……..!! እኚህ ሰው ጉድ አሰሙኝ፡ ከላይ ባወሩበት አፋቸው ቀጠል አደረጉና…. “ ግመሉም(የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ድርጅት/Human Rights Watch) ይሄዳል፣ ውሻውም(ኢህአዴግ/ወያኔ) ይከተላልብለው እርፍ!……ከከከከከከከከከከከከካካካካካከካከካካከኩኩኩኩኩኩኩኩ……ካካ!
……….! ውሸት እንኳን በርሶ በዋናው መለሰም አያምርም ነበር፣ ደሞ እነዚህን ሚስኪን ለፍቶ አርሶ አደር ወገኖችን ሲያፈናቅል የኖረው ኢህአዴግ/ወያኔን ሊያጠሉልን ”……አፈናቃዮቹ በሌብነት የተጨማለቁ ናቸው፡፡ይሉናል፤ አዎ ለነገሩ ገብቶናል ቅኔ ትንሽ ከርሶ…..! እናም እርሶዎና ከላይዎም ከታችዎም እንደ ድፎ ዳቦ የሚያነዱዎ የኢህአዴግ/ወያኔ ቦተሰቦችዎ ማለትዎ እንደሆነኮ ተረድተነዋል፡፡ ግንኮ ይሄ ጥሩ አይደለም፤ አሁን እስቲ ምን ጎደላችሁ!!? ሁሉም ነገር በጃችሁ ሁሉም በደጃችሁ(የምትፈልጉትን በበቃኝ ዘርፋችኋል እስቲ አሁን ወደ ፍቅር ብትመልሱንስ?)!!! ታዲያ ግፉና ሰቆቃው እስራቱና ግርፋቱ ስደቱና ፍንቀላው ቢቆምልንስ? የምር ቢቀር ይሻላል! አማራ መሆን በናንተ ዘመን እንደምን ወንጀል ሆነ???ሙስሊሞቹ ላይ የምታደርሱት ግፍና በደል(እነሱ ላይ ስለበዛ ነው ያሰቀደምኳቸው) በአማራውና በጉሙዙ፤ በአፋሩና በኦሮሞው የምታደርሱትን ስደትና እልቂት በቅቶ ኢትዮጵያውያን የሰላም አየር እንዲተነፍሱ ብትጥሩ ምልካም እኮ ነው፤ በዚህ የመከራ እሳት የምትለበልቡት ትውልድ በኋላ ያስተነፍሳችኋልና!! መሳሪያና የወታደር አቅማችሁን ብቻ በመተማመን እስከመቼ የምትዘልቁ ይመስላችኋል? ህዝባችሁን ብትተማመኑና ህዝባችሁም ቢተማመንባችሁ ለሁላችንም አይሻልም ትላላችሁ?
ደሞም እዚህ ለፋስቡክ ብቻ አሰልጥናችሁ ያሰማራችኋቸው ካድሬዎቻችሁ ደግሞ ………! ምንም እርጥቦች አይገልፃቸውምኮ! እስቲ ቦርቀቅ አድርገው እንዲያስቡም አሰልጥኗቸው፤ አፋቸውም ምላሳቸውም……. ኧረ ምናቸውም ያልተገረዙ ናቸው!! ማገናዘብ እንዲችሉ አድርጋችሁ ብታጠምቋቸው ለሀገርም ይጠቅማሉ፤ እናንተም ሀገር ለመጥቀም ተቀልበሱ!! እናልዎ ቅቡር ተጠቅላይ ሚኒስትራችን ህዝቡ እንኳን እርሶ ባያሳስቡትም ትግሉን አጠናክሮ ይቀጠላል፤ ቢሸሻችሁም ሞትና እንግልት አልቀረለትም፣ ታዲያ እንደአይጥ በየስርቻው ከሚሞትና ከሚሳቀቅ ለነፀነቱና ለመብቱ መሞትና መንገላታት ክብሩ አይደልንዴ!
from Abenezer Shasho 


No comments:

Post a Comment