Thursday, April 11, 2013

በአዲስ አበባ የወያኔ/ኢህአዴግ ደጋፊ ሴቶች ቃለ ማህላ ፈጸሙ


በአዲስ አበባ የሚኖሩ ሴቶች ሚያዚያ 2 ቀን 2005 ዓ.በአዲስ አበባ ስታዲየም በመገኘት ኢህአዴግን እንደሚመርጡ አስታውቀዋል
ኢህአዴግ ያለጠንካራ ተቃዋሚ በሚሮጥበት የአዲስ አበባ እና የክልል ምርጫ በአዲስ አበባ ሴቶች ሊግ አማካኝነት የቤት ለቤት ቅስቀሳ እና ማስፈራሪያ ሲደረግ ቆይቷል።
ሴቶቹ በነፍስ ወከፍ ኮፍያ እና ቲሸርት የታደላቸው ሲሆን አንዳንዶ አበል እንደተከፈላቸውም ሲናገሩም ደምጠዋል። በተለያዩ መኪኖች ላይ ቅስቀሳ ያደርጉ የነበሩ ሴቶች የአቶ መለስ ዜናዊን ፎቶ የያዙ ቲሽርቶችን በመልበስ እንዲሁም ፎቶግራፋቸውን በመያዝ ድጋፋቸውን ገልጸዋል።

ሴቶቹ እጅ ለእጅ በመያያዝ አቶ መለስን ራእይ እናሳካለን በማለት ቃል መግባታቸው ታውቋል።
አንድ አስተያየት ሰጪ የምርጫ ቅስቀሳው አቶ መለስ ዜናዊ ከሞት ተነስተው ለምርጫ እየተወዳደሩ ነው እንዴ ያስብላል ብሎአል። የምርጫ ቅስቀሳው ኢህአዴግን ምረጡ ሳይሆን መለስን ምረጡ ሆኗል ብሎአል።
ኢህአዴግ 2002 የተደረገውን አገራዊ ምርጫ 99 ነጥብ 6 በመቶ ድምጽ ማሸነፉ ይታወሳል። የሚቀጥለውን ሳምንት ምርጫም አሀዙን በነጥብ ሶስት በማሳደግ፣ 99 ነጥብ 9 ያሸንፋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ይነገራል

No comments:

Post a Comment