Monday, April 8, 2013

በዋሽንግቶን ዲሲ ኢትዮጵያውያን ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ



በአማራ ብሄር ተወላጆች ላይ እየተፈጸመ ያለውን የዘር ማጥፋት ዘመቻ በመቃወም ከወትሮው እጅግ ቁጥሩ የበዛ ሰላማዊ ሰልፈኛ የተገኘበት ደማቅ የተቃውሞ ሰልፍ በዋይታውስ ፊት ለፊት ዛሬ ከጠዋቱ 9 ጀምሮ ሲደረግ አርፍዷል።
ሰልፉን ያስተባበሩ ታዋቂ የመብት ተሟጋቾች እንዳሉት ለወገን ደራሽ ወገን ነው በሚል ደማቅ የተቃውሞ ሰልፍ ተደርጓል  ይህ አይነቱ ተቃውሞ በሌሎች ሀገሮችም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው።
ሰሞኑን በቤንሻንጉል ጉምዝ በህጋዊ መንገድ እየሰሩና ለመንግስት ግብር እየገበሩ ይኖሩ የነበሩ የአማራ ብሄር ተወላጆች ዘራቸው አማራ በመሆኑ ብቻ ንብረታቸው እየተነጠቀና እየተደበደቡ አካባቢውን እንዲለቁ እየተደረገ ነው።

No comments:

Post a Comment