Tuesday, April 30, 2013

በውሸት ህዝባችን ደማ በኢቲቪ ! የዉሸት ፋብሪካ የሆነው ኢቲቪ ነጠላ ዜማውን ለቀቀ! ህዝቡ ግን አይሰማም !የሌባ አይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያደርቅ !


የዉሸት ፋብሪካ የሆነው ኢቲቪ ነጠላ ዜማውን ለቀቀ! ህዝቡ ግን አይሰማ እንደተለመደውጸረ ሰላም እና ጸረ ልማት ሃይሎችእያለ በቱልቱላ ጋዜጠኞቹ የህዝብን ጆሮ ሲያደማ ቆይቷለ   ምን ይህ ብቻ ያልተሰበሰበውንም ገንዘብ እንደ አስራ አንድ ፐርሰንቱ የልማት ፕሮፖጋንዳ ሊያናፍሱ እንደሚችሉ የሚገመት ነው።

/የህማማት ማሰታወሻ/ ‹‹ህዝቤን ልቀቅ!››


እስክንድር ነጋን ልቀቅ!...
ይህ ሳምንት በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ‹‹ሰሞነ ህማማት›› ተብሎ በፀሎትና በስግደት ይከበራል፡፡ ይህ የሆነው ከሁለት ሺህ ዓመት በፊት ኢየሱስ ክርስቶስ በሀሰት ተወንጅሎ ለስቅላት ተላልፎ የተሰጠበት፣ በሰው ልጅ ከሚደርስ ስቃይ፣ መከራና ግርፋት ሁሉ የከፋውን የተቀበለበት ሳምንት በመሆኑ ነው፡፡
የፖለቲካ ተንታኝና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የኦርቶዶክስ ክርስትና ሀይማኖት ጥብቅ አማኝ ነው፤ የሀይማኖቱን ትእዛዛቶች በጥብቅ ያከብራል፤ ሁሉንም አፅዋማትም ይፆማል፡፡ ዛሬ በግፍ ታስሮ በሚገኝበት የቃሊቲ ወህኒም ሆኖ እንኳ የኩዳዴን ፆም ከመፆም አልሰነፈም
 (በነገራችን ላይ እስክንድር የሚገኝበት ‹‹ዞን ሶስት›› ፈርሶ እንደገና ሊሰራ ስለሆነ እስረኞቹ ወደሌላ ቦታ ሊዘዋወሩ እንደሆነ ተነግሯቸዋል) 
እስክንድር የተወለደው ጥቅምት 27 ነው፡፡ ይህ ዕለት ደግሞ ለእምነቱ ተከታዮች ‹‹መድሐኒያለም ዕለት›› እየተባለ የሚከበረበት ቀን ነው፡፡ እርሱም ቢሆን ምንጊዜም ጠዋት ወይም ማታ ከስድስት ኪሎ ዩንቨርስቲ ከፍ ብሎ በሚገኘው ‹‹ምስኪያዙና መድሐኒያለም ቤተ-ክርስቲያ›› የፈለገ አያጣውም፡፡

Monday, April 29, 2013

የዘረፋ ውሎ በእንዳማሪያም (ገብረመድህን አርዓያ)


ስብሃት ነጋ ባለፈው ሳምንት አዲስ አበባ በሚታተመው የአዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ የሰጠውን ቃለ መጠይቅ አነበብኩት:: ስብሃት ነጋ “ኢህዴግን የመሰለ ፓርቲ በአፍሪካ የለም” እና ሌላም ብዙ ፣ ብዙ ይላል:: ይዘብታል ፣ ይፎክራል ፣ ይሸመጥጣል ፣ ያቀረሻል ፣በህዝብ ሞራል ላይም ያላግጣል:: ብዙም አልደነቀኝም:: ስብሃትም ሆኑ የዚህ ፋሺስታዊ ስርዓት አንቀሳቃሾች በብዙሃን ደም ላለፉት አርባ አመታት ታጥበዋል ፣ ታሪክ አውድመዋል፣ እጅግ ከፍተኛ ዘረፋ ፈጽመዋል ፣ አገር ቆርሰው ሸጠዋል:: በጣም ከፍተኛ ወንጀል የሰሩ ሰዎች እንደመሆናቸው በአገሪቷ የፖለቲካ ለውጥ ከመቼውም ጊዜ በላይ መቀጣጠሉ እንቅልፍ እንደነሳቸው እያየን ነው:: አዎን ስብሃት ገና ፣ ገና ከዚህም በላይ ብዙ ይናገራል ፤ ቁጣው እያየለ በሄደ ቁጥር ብዙ ወንጀሎችም ይሰራል::
Sebhat Nega
Sebhat Nega
ዛሬ ወያኔ ኢህአዴግ ከመቼውም ጊዜ በበዛ ፍጥነት እና ማን አለብኝነት ኢትዮጵያዊ የሆኑ መሰረቶችን የመናዱን ስራ አጠናክሮ እየሰራ ለመሆኑ በየእለቱ የምንሰማቸው ዜናዎች እና ዘገባዎች ያሳያሉ:: እንደ እኔ ፣ እንደ እኔ የወያኔ የጥፋት ስራ ሳይሆን የጨመረው ይልቁንስ ረጅም እድሜ ለኢሳት ይስጠውና የዜና ዘገባ ብዛት እና አይነቱ መጨመሩ ይመስለኛል:: ወያኔ ሲፈጠር ጀምሮ ኢትዮጵያዊ መሰረት ያላቸውን እሴቶችን የማጥቃት ስራን እንደ መጨረሻ ግብ(strategic goal) አስቀምጦ የሚንቀሳቀስ ድርጅት መሆኑን ቀድመን ላወቅን እና ለተረዳን ሰዎች ግን እምብዛም አዲስ ነገር አይደለም:: ዛሬ ላይ ከኢትዮጵያ ከሚወጡ ዜናዎች በብዛት የምንሰማው ብዙዎች ሲያለቅሱ እና ጥቂት ዘረኞች ደግሞ ያለ ይሉኝታ ሲዘርፉ ፣ ሰዎችን አስረው ሲያሰቃዩ፣ እና ኢትዮጵያውያንን ዘር ቆጥረው ከቀያቸው ሲያፈናቅሉ ሆኗል::

ኢትዮጵያ የአለም ንግድ ድርጅት አባል ስለምትሆንበት ሁኔታ በተለይም የህግ አገልግሎት ዘርፉ ጋር በተያያዘ ወይይት ተካሂዶ ነበር።


በውውይይቱ ላይ ከሀይለ ስላሴ ዘመነ መንግስት ጀምሮ ከህግ ትምህርት የተመረቁና በህግ ሙያው ላይ ብዙ አመት የሰሩ ጠበቆች ተገኝተው ነበር። ከእነሱ መካከል አንድ አንጋፋና ታዋቂ ጠበቃ በጉዳዩ ላይ አስተያየት ሲሰጡ:-
እናነተ አያቀረባችሁት ያለው ነገር መሬት ያልወረደ ነገር ነዉ። የዉጭ ሀገር ተቛም ወይም ግለሰብ ኢትዮጵያ ውስጥ መቶ ስለሚሰራበት ሁኔታ እና ምን አይነተ ገደብ(restrictions) መጣል እንዳለበት ነው ሁሉም ጠበቃ ተበታትኖ የየራሱን እሚሰራበት ሀገር ውስጥ ነው ያለነው ።ሁሉም ጠበቃ በአንድ ተቛም ስር (legal firm) እሚሰራበት ሁኔታ አልተመቻቸም፣ፍርድ ቤት ስንሄድ በእውቀት ያልዳበሩ እና ያልበሰሉ ዳኞችን ነዉ እምናገኘው ዳኛ ከተሆነ በኋላ ጠበቃ እሚኮንባት ሀገር ኢትዮጵያ ብቻ ትመስለኛለች። አንድ የህግ ባለሞያ ጠበቃ ሆኖ በቂ አውቀት ከያዘ በህዋላ ፣ከሰከነና ከበሰለ በኋላ ፣ከመንግስት ተፅእኖ ቀርቶ ከራሱ ተፅእኖ ተላቆ መሆን አለበት።

በኖርዌይ የሚኖር ኢትዮጵያዊያን ተቃዋሚዎች ፖሊስ ወያኔ/ጀሌዎቻቸው ሌባ በመሆን የተባረሩበት የገቢ ማሰባሰቢያ ቦንድ ሳይሳካ ተቋረጠ !


ለአባይ ግድብ ገንዘብ ለመሰብሰብ ሊደርግ የነበረው የቦንድ ሽያጭ በተቃዋሚዎች ብርቱ ጥረት እንዳይሳካ ተደረገ። ኖርዌይ ኦስሎ በተቃውሞ ተቀውጣ ውላ ነበር። ለቁጥጥር በሚያስቸግር ሁናቴ ተቃውሞ ሲደረግ ውሏል።የወያኔ ጀሌዎች በመጀመሪያ ስብሰባውን የጠሩበት አዳራሽ  በኖርዌይ አጠራር Schweigaards galleri በተባለ ቦታ በኖርወይ ሰዓት አቆጣጠር ከሰዓት በኋላ በ15 ሰዓት ወይንም በ3 ሰዓት ላይ ለደጋፊዎቻቸው በስልክ በSMS አድርገው እንደነበርና በዛም ደጋፊዎቻቸው በተጠሩበት ቦታ አካባቢ ብዙ ተቃዋሚዎች አካባቢው ላይ እንደነበሩ በሰላዮቻቸው ስለተነገራቸው ቦታውን ለመቀየር የተገደዱ ሲሆን ወያኔዎቹና ጀሌዎቹ በስውር ለመቀየር ያሰቡት ቦታ በተቃዋሚዎቹ በኩል የተጠናከረ ስራ ሲሰሩ ስለነበር ያንንም ደርሰውበት ወደ ሁለተኛው የተከራዩበት Scandinavia hotel ባለ አምስት ኮከብ ሆቴል በመያዝና ሊያዘጋጁት የነበረው ስብሰባ ተቃዋሚዎቹ እዛው ድረስ በመሄድ  የቦንድ ሽያጭ በተቃውሞና በመፈክር ያስቆሙት ሲሆን አንዳንድ ተቃዋሚዎች ወደ ሆቴሉ በመግባት ያለውን ሁናቴ ተናግረው ነበር በሆቴሉ ውስጥ ክ10 የማይበልጡ የወያኔ ደጋፊዎች እንደነበሩ ውስጥ የገቡትም እንዳይነጋገሩ ስብሰባው እንዳይደረግ በማድረግ ከፍተኛ ሚና እንደተጫወቱም የአይን ምስክር ሰተዋል።በተለይ ከሆቴሉ ፖሊስ አትገቡም የተባሉት ተቃዋሚዎች በቁጥር ከፍተኛ ሲሆኑ በልህና በስሜት ሆነው ሲያሰሙት የነበረው የተቃውሞ ድምፅ ለፖሊስ ሁላ አስቸጋሪ እንደነበርና ፖሊስም ሁኔታውን ለመቆጣጠር የፖሊስ ሀይል በከፍተኛ ሁናቴ እንዲጨመር በማድረግ በሁናቴው የነበረው ክስተት ሲናገሩ የነበሩት ተቃዋሚዎች ያስረዳሉ።በዚህም ሁናቴ የተለያዩ የኖርዌይ ቲቪ እንዲሁም ጋዜጣ ስለ ተቃውሞ የዘገቡ ሲሆን ሁናታው ከባድ የሆነ ተቃውሞ እንደነበርም ገልፀዋል።

አንድነት ፓርቲ መድረክ በአስቸኳይ ውህድ ፓርቲ እዲሆን ጠየቀ


ላለፉት 5 ወራቶች የመድረክን የስራ አፈፃፀም ሁኔታ በቅርብ ሲገመግም የነበረው የአንድነት ብሔራዊ /ቤት የመድረክ አባል ድርጅቶች በአስቸኳይ እንዲዋሀዱ ጠየቀ፡፡ 
ብሔራዊ /ቤቱ ቅዳሜ ሚያዝያ 19 ቀን 2005 . ደረገው ስብሰባ ባስተላለፈው ውሳኔ መሰረት የአራት ፓርቲዎች ስብስብ የሆነው የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ላለፉት አራት ዓመታት አሳሳቢ በሆኑና በበርካታ ችግሮች ተተብትቦ የቆየ ቢሆንም ሀገራችንን ወደ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለማሸጋገር በተደረገው ትግል ውስጥ የተጫወተው ሚና እጅግ ከፍተኛ መሆኑን አረጋግጧል፡፡ ብሔራዊ /ቤቱ በሰየመው ገምጋሚ ኮሚቴ አማካኝነት የመድረክ አጠቃላይ ሁኔታ በስድስት ዋና ዋና ክፍሎች ተገምግሞ ሚያዝያ 19/2005 . ለብሔራዊ /ቤቱ በግምገማው ሪፖርት ውይይት ተካሂዶበታል፡፡ ከጠዋቱ 300 – 100 ሰዓት ስብሰባውን ያካሄደው የአንድነት ብሔራዊ /ቤት በዚሁ የግምገማ ሪፖርት ላይ ብቻ በመወያየት የመድረክ ጉዞ በውህደት እንዲጠናቀቅ ወስኗል፡፡