Tuesday, September 29, 2015

መግለጫ ወይንስ መጋለጫ – የሞላ አስግዶም ኩብለላ (ይገረም አለሙ)

ይገረም አለሙ
ከአንድ ሳምንት ወሬ የማይዘለው የሞላ አስግዶም ኩብለላ ብዙ ነገሮችን አያሳየን ነው፡፡ ወያኔ የሞላ ኩብለላ የሱ የሥራ ውጤት እንደሆነ አሳያለሁ ብሎ “ በቅሎ ሽንቷን አጠራ ብላ ሀፍረቷን አሳየች” የሚባለውን አይነት ድርጊት ፈጸመ፡፡ ለነገሩ ወያኔ መቼ ሀፍረት ያውቅና፡፡ አቶ ሞላም የተሰጠው ስልጠና የአጭር ግዜ ሆኖበት ሽክ ብሎ የቀረበበትን ጋዜጣዊ መግለጫ የወያኔና የራሱ መጋለጫ አደረገው፡፡ የወያኔ የመረጃ ስራ በጉልበት አንጂ በእውቀት እንዳልሆነ የምናውቀውንም ይበልጥ አረጋገጠልን፡፡Mola Asgedom's defection
የቱንም ያህል ቢጩኹ፤የቻሉትን ያህልም ውሸት ቢደራርቱ እውነትን ማሸነፍ እንደማይቻል ወያኔዎች ብዙ ግዜ ሞከራው ከሽፎባቸው ያዩት ቢሆንም አንዴውኑ ከእውነት ጋር ተጣልተዋልና የህይወት መሰሶአቸውም ውሸት ሆኖአልና ከውሸት ሊላቀቁ አልቻሉም፡፡ ዛሬም እየዋሹ ብዙሀኑን ኢትዮጵያዊ በግድ ሊግትቱ ይዳዳቸዋል፡፡ ጥቂት አይናቸውን ለጆሮአቸው ያስገዙ ሰዎቻቸው ደግሞ እንዴት ብሎ መጠየቅ ለምን ብሎ ማመዛዘን የለም ብቻ ውሸቱን እየተቀበሉ ከበሮ ይደልቃሉ፡፡እውነቱ ሲጋለጥም ሌላ ውሸት ይፈበርካሉ እንጂ ለእውነት እጅ አይሰጡም፡፡

የሞላ አስገዶም ነገር!

በተስፋዬ ነጋ (ዋሽንግተ ዲሲ)
ኢቲቪ ስለትህዴን መክዳት የለፈለፈው፣ አቶ ሞላ ስለ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ ስለተቃዋሚዎቹ፣ የሻብያን ጦር “እየደመሰሱ” ስለመምጣት በግነት የተናገረው፣ ሌላው የትሄዴን ጊዜያዊ ሃላፊ ኮማንድር መኮንን ተስፋዬ ስለከዳው የትህዴን ጦር እና ስለውጊያው የተናገረው እና የተለያዩ ሌሎች አስተያየቶች ሰሞኑን በማህበራዊ ድህረገጾች ተለቀዋል፣ ኢትዮጵያውያን በነቂስ ተወያይተውባቸዋል። እኔም ውይይቱን መልሼ መድገም አልፈልግም፥ የእኔ አላማ የአቶ ሞላ አስገዶም በተለያዩ አካላትና ሁኔታዎች መዳፍ ስር ቢወድቅ ኖሮ በጥትቅ በሚታገሉ የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች፣ በኢትዮጵያ መንግስትና፣ በኤርትራ መንግስት ላይ የሚፈጥረው አዎንታዊና አሉታዊ ተፅዕኖዎች በአጭሩ መዳሰስ ነው።

የሰካራም እግርና የሞላ አስገዶም ምላስ

ቹቸቤ
ቹቸቤ ነኝ እንዴት ከረማችሁ? በዐል እንዴት ነበር? ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም አሉ የአገራችን ሰዎች። ዘንድሮ ከጉድም ጉደኛ ሰው ከወደ ሰሜን አቧራውን አጬሰውና የኔንም ቀልብ ሳበው። ኢካድፎች ይህንን ከሰማያዊ ፓርቲ ተዘረፈ የሚባለውን በልኩ ያልተሰፋ ሱፍ ግጥም አድርጎ ‘እኛ እኮ አንቻልም’ የሚለውን ሰውዬ አሳይታችሁን እኔንም ለሳቅና ለቅሶ ጋበችሁኝ። ሳቅሁኝ በሞላ ለጋሰራሽ ድራማ። አለቅስኩኝ ኢትዮጵያችን ሰው አጥታ ሞላ የስንትና ስንት ሺህ የነጻነት አርበኞች መሪ ነበር የሚለውን ሳስብ። ቢሆንም አቶ ተሰማ እሸቴ አንዳንድ አርበኛ የሚለውን ስም የማይመጥኑትን ለመግለጽ “እዩት ተመልከቱት የአምላክን ደግነት …. እንዴት ያስደስታል አርበኛ ሲጫወት” ብለው የተቀኙትን አስታውሼ እውነትም አር-በኛ ተጫወተብን አልኩኝ …. ሞልዬ ጎምላላዬን አይቼና ለመስማት ሞክሬ።

ፕሮፓጋዳ ዓይን ያወጣ ውሸት ማቅረብ አይደለም፣ የሚሰራ መሆን አለበት፣ ጎብልስና ወያኔ

ከቢላል አበጋዝ – ዋሽግቶን ዲሲ
የወያኔ ትልቁን “ኩዴታ” ጥምረት ውህደትን “በሾኬ የጣለበትን” የወሬ ጋጋታ እንግዲህ አለፍነው። ተመስገን። ሰማይ አልተደረመሰም። የወያኔ ቲቪ ሰዓት እላፊ ሰራ። በዳያስፖራ ያሉ የወያኔ አሽከሮች “የፍየል ወጠጤ” ዓይነት መልክት አስተጋቡ። ወያኔን አትንኩብን አሉ። የአንድን ሰው መክዳትን ድል አድርገው ሊያደናቁሩ ተሟሟቱ። አዲስ የተሻሻለች ህወሃትን የሚሹ ምሁራንም የቆሙበት በግልጥ ታየ። ሌሎችም ጥምረት ውህደቱን ተቹ። ህብረት እንፍጠር ያላችሁ ሳይገባችሁ ነው አሉ። የሞላ መክዳትት ወሬ ጥቂቶችን አናዞ እያለፈ ነው።መጭውን የወያኔ “የረቀቀ ስለላ ውጤት” እስክንሰማ እንጠብቃለን።የሞላ አስከዶም ተገቢው ጎራ መዘነቅ ወሬው ቶሎ ከሰመ::ከዚህ የሚያልፍ አይደለም።ግን መጥኔ ለአዲሳባ!

ትግሉ ለዴሞክራሲያዊ ስርአት ወይንስ ለምንይልክ ቤተ መንግሥት (ይገረም አለሙ)

ይገረም አለሙ
ፈጣሪ ዕድሜ ከጥንካሬ ጋር ያደላቸው በሀገር ጉዳይ የማይታክቱት ፕ/ር መስፍን ወልደ ማሪያም ሰሞኑን በምድረ አሜሪካ ነዋሪ ከሆኑ ኢትዮጵያውያን ጋር ያደረጉትን ውይይት ዘመነ ቴክኖሎጂ ምስጋን ይግባውና በያለንበት ሆነነን ተከታትለናል፡፡ ከውይይቱ ታዳሚዎቸች ከቀረቡ በርካታ ጥያቄዎች አንዱ በያ ትውልድ ላይ ጨከኑበት የሚል ነበር፡፡ ፕ/ር መስፍን ሲመልሱም አልጨከንኩበትም እውነቱን ነው የተናገርኩት አንዳንዶቹ እንደውም ተማሪዎቼ ነበሩና አነጋሬአቸዋለሁ፣ ፍላጎታቸው ለሀገርና ለሕዝብ ሳይሆን ሥልጣን ነበር ብለዋል፡፡
በዚሁ ሰሞን እጄ የገባው ባለ 96 ገጽ ሰነድ ውስጥ ፕ/ር የተናገሩትን የሚያረጋገጥ ከጉዳዩ ባለቤቶች አንዱ በሆነው የተነገረ አገኘሁ፡፡ ሰነዱ በእያንዳንዱ ገጽ ላይ“ በሀገርና ሕዝብ ደህንነት ጥበቃ ምኒስቴር የማዕከላዊ ምርመራ ድርጅት የወንጀል መዝገብ ቤት” የሚል ማኅተምና “ጥብቅ ምሥጢር” የሚል ማሳሰቢያ ያረፈበት ሲሆን ከኢህአፓ መሪዎች አንዱ የነበረው ብርሀነ መስቀል ረዳ በእስር ቤት የሰጠውን የምርመራ ቃል የያዘ ነው፡፡ ከአጀማመራቸው አንስቶ እስከ መንዝና መርሀ ቤት ቆይታው ይዘረዝራል፡፡

የተናገሩት ከሚጠፋ… (በኤፍሬም ማዴቦ – ከአርበኞች መንደር)

በኤፍሬም ማዴቦ
ባለፈዉ መጣጥፌ “ቃል የእምነት ዕዳ ነዉ” ብዬ ጀምሬ “ቃላችን አይለወጥ” ብዬ ነበር የተለየኋችሁ። አለምክንያት አልነበረም እንዲህ ያልኳችሁ፤ በአንድ በኩለ ቃል መከበርም መከፈልም ያለበት ዕዳ ስለሆነ በሌላ በኩል ደግሞ ቀትር ላይ የገባዉን ቃል ሳይመሽ እንደ ጴጥሮስ ሦስቴ የሚክድ ብዙ ቃላ አባይ ሰላለ ነዉ። አገሬን ከወያኔ አጸዳለሁ ብሎ ቃል የሚገባ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ዕዳ አለበት። ዕዳዉ ደግሞ ገንዘብ ወይም ንብረት አይደለም። ቃሉን መጠበቅ ወይም ቃሉን ማክበር ነዉ።Ephrem Madebo with Patriotic Ginbot 7 fighters
ደግሞም አንድ ሰዉ የተናገርዉን ቃል ሰብሮ የእምነት ባለዕዳ ከሚሆን ዕድሜ ልኩን የገንዘብ ባለዕዳ ቢሆን ይሻለዋል። የገንዘብ ዕዳ ቆይቶም ቢሆን ይከፈላል ወይም አበዳሪዉ ሊምረን ይችላል፤ የዕምነት ዕዳ ግን የማይሽር ጠባሳዉ እየቆረቆረን አብሮን ይኖራል እንጂ አይጠፋም። ማንም ሰዉ ለአገሬ ህይወቴን እሰጣለሁ ብሎ ቃል ሲገባ መሃላዉ ከህዝብና ከአገር ጋር ብቻ አይደለም፤ እንዳዉም የሰዉ ልጅ ቃል የሚገባዉ መጀመሪያ ከራሱ ጋር ነዉ። ለራሱ የገባዉን ቃል የማያከብርና ቃሌ ቃል ነዉ ብሎ የገዛ ራሱን የእምነት ዕዳ ያልከፈለ ሰዉ ለህዝብና ለአገር ቃል መግባት አይችልም።

ይቅርታ- የወያኔ ካርታ (ይገረም አለሙ)

ይገረም አለሙ
1437ኛው የኢድ አል አድኻ ( አረፋ) በአል በአዲስ አበባ ስታዲየም ሲከበር ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ አስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት በሽብር ወንጀል ተከሰው ከተፈረደባቸው የሙስሊሙ ማህበረሰብ ችግሮች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት መካከል ስድስቱ በቅርቡ የተለቀቁት በእነርሱ ጥያቄና ጥረት አንደሆነ፤ ጥያቄአቸው ምላሽ በማግኘቱና ጥረታቸው በመሳካቱ መደሰታቸውን ገልጸው ለመንግሥት ምሥጋና ማቅረባቸውን የጀርመን ድምጽ ራዲዮ ዘጋቢ ከስፍራው ባስተላላፈው ዘገባ አሰምጾናል፡፡ ወያኔ ግዜና ወቅት እየጠበቀ የሚጠቀምባት የፖለቲካ ቁማር መጫወቻ የይቅርታ ካርድ በሌላ መንገድና መልክ ተመዘዘች ማለት ነው፡፡

ሁለት የሶማሌ የጦር አውሮፕላኖችን መተው የጣሉት የቀድሞ አየር ኃይል ጀግና አረፉ

የኮለኔል ባጫ ሁንዴ የህይወት ታሪክ

ኮለኔል ባጫ ሁንዴ በአንቦ አካባቢ በጊንጪ ከተማ ተወለዱ ።በአምቦ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን እንዳጠናቀቁ በ1965 እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በኢትዮጵያ አየር ሃይል በአውሮፕላን ጥገና አገራቸውን ለማገልገል ተቀጥረው ስልጠናቸውን እንደጨረሱ ከክፍላቸው ያመጡት ውጤት የላቀ በመሆኑ እና የተዋጊ አውሮፕላን በራሪ ለመሆን ባሳዩት ከፍተኛ ፍላጎት ሙያው የሚጠይቀውን ማንኛውንም መስፈርት በማሟላት ወደ በረራ ትምህርት ቤት ገቡ።Colonel Bacha Debele
የሚፈለግባቸውን የበረራ ትምህርት እንደጨረሱ ወደ ተዋጊ ስኳድሮን በመመደብ የኤፍ 86 አውሮፕላን ሲበሩ ቆይተው የኢትዮጵያ አየር ሃይል F-5E የሚባል አዲስ አውሮፕላን ሲገዛ ወደ አሜሪካን አገር ተልከው በዚሁ አውሮፕላን ስልጠና በመውሰድ እና በማጠናቀቅ ወደ አገራቸው ተመልሰው በወቅቱ አገራችንን የወረሩትን የሱማሌ ወራሪዎች ጋር ፍልሚያ ውስጥ በመግባት በአየር ላይ ውጊያ ሁለት የሱማሌ ሚግ አውሮፕላኖችን መትተው የጣሉ ሲሆን በዚህም ላሳዩት ከፍተኛ ጀግንነት ከኢትዮጵያ መንግስት የጦር ሜዳ የላቀ ጀግንነት ሜዳይ ተሸላሚ ሆነዋል።

“የየጁ ደብተራ ቅኔው ሲጎልበት ቀረርቶ ሞላበት” (ስሜነህ ባዘዘው)

ስሜነህ ባዘዘው
በሻቢያ እርዳታ የሚደረግ ትግል በአፍንጫዬ ይውጣ የሚሉ ወገኖች ሃሳባቸውን በተለያየ መልክ ሲገልጹ ቆይተዋል፤ አብዛኞች የአመለካከት ልዩነታቸውን በሰለጠነ መልክ “በልዩነት” ይዘው የራሳቸውን ስራ እየሰሩ ነው። ይህ ደግሞ የብስለት ምልክት ነው።

ኑሮ በመፈክር (ጌቱ ኃይሉ)

ጌቱ ኃይሉ
አቶ ዠ 57 አመታቸው ነው። መተዳደሪያ አላቸው። እንዴት ያለ ሙያ!! ባሥራ ሰባት አመታቸው የጀመሩት። አርባ አመት ሙሉ ያለማቋረጥ እየሰሩ ያሉት። ሰዉ ከሥራው በመንግሥት ለውጥ፣ በሰበብ ባስባቡ ሲባረር እሳቸው ሥራ አላጡም። ሥራቸው? መፈክር አድምቆ መጻፍ።
መጀመሪያ በሁለት ቃላት ጀመሩ። በነጻ “ኢትዮጵያ ትቅደም!” ብለው አድምቀው ጻፉ። ከዚያ እየተከፈላቸው ደግሞ “ከቆራጡ መሪ ጋር ወደፊት !!” ብለው ቀጠሉ። ሰውየው ብቻቸውን ሲቀሩ። ወደ መጨረሻው ግድም ደግሞ “አብዮታዊት እናት ሃገር ወይም ሞት” ብለው ደጋግመው አድምቀው ጻፉ። “አብዮታዊት እናት ሃገር ወይም ዝምባብዌ!” ብለው አላፌዙም።

ለየት ባለመንገድ ደፈር ብሎ ስለማሰብ፣ ጉርብትናና በሰላም መኖር፣ በየኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል

ከቢላል አበጋዝ – ዋሽግቶን ዲሲ
ዛሬ ካለንበት ተነስተን ስናስብ ወያኔ ህወሃት ጋር ያለን ጠብ ሳይሆን ከወያኔ በኋላ በምን ሁኔታ የምትኖር አገርን እንሻለን የሚለው ጥያቄ ግዝፈት አለው።በኢትዮጵያም በኤርትራም ያለው ህዝብ ከወያኔም፤ከሻቢያም በላይ ነው።ያአንድ አገር እድል ከፖለቲካ ድርጅቶች ፤ከመሪዎችም በላይ ነው።የአካባቢውን ህዝቦች እጣ ፈንታ ስናስብ በወሰን ተገድበን እንዳይሆን ጥንታዊና በዙ መእዘን ያለው ትስስራችን አስበን ከስሜተኝነት ርቀን እንደ ችግር ፈችዎች እንድናስብ የግድ ይለናል። የኢትዮጵያና ኤርትራ ጉዳይ እንድንወያይበት በሚል ይህ ጽሁፍ ቀርቧል።

አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን ለአዲስ አመት ዋዜማ በላፍቶ ሊያዘጋጀው የነበረው ኮንሰርት በመሰረዙ

መስከረም ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን ለአዲስ አመት ዋዜማ በላፍቶ ሊያዘጋጀው የነበረው ኮንሰርት በመሰረዙ በአድናቂዎቹ ዘንድ የፈጠረው ቅሬታ ሳይረሳ ፣ አሁን ደግሞ ለመስቀል በአል ያዘጋጀው ኮንሰርት በድጋሚ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እንዳይካሄድ መከልከሉን የፎርቺን ሳምንታዊ ጋዜጣ ዘገባ ያመለክታል። የአዲስ አበባ መስተዳድር የካቢኔ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት አቶ ፈለቀ ነጋሽ የ አዲስ አመት ኮንሰርቱ የተሰረዘው በአስተባባሪዎቹ የፈቃድ ጥያቄ የቀረበው በአጭር ጊዜ ውስጥ ከመሆኑ አኳያ አስተዳደሩ ባጋጠመው የስራ መደራረብ ሳቢያ እንደሆነ ለጋዜጣው መግለጻቸው ይታወሳል፡፡

በኢትዮጵያ ታሪክ ጉዳይ ላይ ኢሕአዴግን እንዴት ማመን ይቻላል?! በዲ/ን ኒቆዲሞስ

ወንድማችን ዲ/ን ዳንኤል የኢትዮጵያችን ልዩ ቅርስ በኾነው የዘመን አቆጣጠራችንን በተመለከተ አንድ ጥያቄ አንስቶአል፡፡ ይኸውም የኢትዮጵያን የዘመን አቆጣጠር በተመለከተ ‹‹ጠቅላይ ሚ/ሩን እንመን ወይስ አርቲስቶቻችንን?!›› የሚል ጥያቄ አንስቶ አንድ ትዝብትና ማሳሰቢያ አከል ጽሑፍ አስነብቦናል፡፡ እኔ ግን እንዲህ እላለሁ በኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠርም ሆነ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ታሪክ ጉዳይ ላይ ኢሕዴግን/ክቡር ጠቅላይ ሚ/ሩን እንዳናምናቸው የሚያደርጉን አንዳንድ የታሪክ ሐቆች እንዳሉ ላንሣ፡፡
እስቲ እነዚህን ሐቆች በጥቂቱ ብቻ ለማየት እንሞከር፡፡ በመሠረቱ የአገሪቱን ታሪክ ወደ መቶ ዓመት አውርዶ ለሚተነትነው፣ ጥንታዊው የሆነው ፊደላችን፣ ሦስት ሺሕ ዘመንን ያስቆጠረውን የሥነ-መንግሥት ታሪክ ‹‹የአቢሲኒያውያን/የነፍጠኞች ቅኝ ገዢዎች ታሪክ›› አድርጎ የኢትዮጵያን ሕዝቦች ታሪክ በብሔር ብሔረሰቦች ማዕቀፍ ቀንብቦ ዳግም ለመፍጠር ለሚውተረተረው፤ አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የሚመሩት የኢሕአዴግ መንግሥት በምን ሞራልና ተጠየቅ፡- ‹‹ከአፍሪካ አገራት ሺሕ ዘመናትን ያስቆጠረ የራሳችን ፊደልና የዘመን አቆጣጠር ያለን ኩሩ ሕዝቦች …፡፡›› ተብሎ በአደባባይ ሊነግሩን እንደደፈሩ አይገባኝም፡፡ የታሪክ እውነት/ሐቅ ሲያሻን የምንደርበው እንዲያ ሲል ደግሞ አውልቀንና አሽቀንጥረን የምንጥለው የበረሃ ሽርጥ ኾነ እንዴ ጎበዝ …?! ይሄ በእውነት ያስተዛዝባል፡፡ ወይስ ደግሞ እንደው ሳንሰማ ኢሕአዴግ በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ ያለውን አቋም አስተካክሎ ይሆን እንዴ … እ…እ…እ… አይመስለኝም፡፡

አቶ ሞላ ለምን ደነበረ? ታሪኩ አባዳማ

ጄነራል ከማል ገልቹ ከበርካታ ወታደሮች ጋር ድንበር ጥሶ ወደ ኤርትራ ገባ ሲባል ሰማን። በዚህ የተነሳ የወያኔ ሰራዊት ለይቶለት የተናደ መስሎን በማግስቱ አንዳች የፖሊቲካ ለውጥ ለማየት የጓጓን ልንኖር እንችላለን – ጄት እና ስልታዊ የውትድርና ተዋጊ ሄሊኮፕተር ይዘው ወያኔን የከዱ መኮንኖች ዜና ሲሰማ አሁንም የድል ቀን ተቃረበ ብለን በቅንነት ደስታ የወረረን አንጠፋም።
በተቃራኒው ደግሞ አቶ ሞላ አስገዶም የደሚህት መሪ እጁን ለወያኔ ሰጠ ሲባል ትግሉ ተኮላሸ ብለን የደነገጥንም አንጠፋም …
በመሰረቱ ከነኝህ መልካም ሆነ ክፉ አጋጣሚዎች ልንማር የሚገባን ነገር ቢኖር የነፃነት ድል ባንድ ወይንም በሁለት ያልተጠበቁ ድንገተኛ ያቋም ለውጦች የሚጨበጥ ወይንም የሚዳከም ጉዳይ አለመሆኑን ብቻ ነው። እያንዳንዱ አጋጣሚ ግን ለትግሉ የይዘት ሳይሆን የአይነት ለውጥ በማከል ያጠናክረዋል። የህዝባዊ ትግል ድል አዝጋሚ ግን የማይቀር መሆኑን ጭምር አብሮ መቀበል ያሻል።

ሁለት የአሜሪካ ከፍተኛ የጦር አማካሪዎች ኤርትራ ገቡ።

በ 1960 ዎቹ አመተ ምህረት አካባቢ ወደ ቬትናም ሄዶ ሲያሰለጥን የነበረዉ የአሜሪካዉ ምርጥ እንዲሁም ኤኮ 31 በመባል የሚታወቀዉ ሐይል U.S. Army Special Forces and Echo 31 ኤርትራ መግባታቸዉ ታዉቋል በትናንትናዉ እለት ከኤርትራ ከፍተኛ ባለስልጣናትና ተቀማጭነታቸዉ በኤርትራ በሆኑ የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች ጋር በተለይም ከርበኞች ግንቦት 7 አመራሮች ጋ መክሯል የተባለዉ ይህዉ ቡድን አመጣጡ ተቃዋሚዎችን ለመርዳት ነዉ ሲሉ ምንጮቻችን ገልጸዋል።

Monday, September 14, 2015

የተደበቀው የህወሓት ማንነት ከደደቢት እስከ ቤተመንግስት – ክፍል 2 “ሳሞራ የኑስ በበረሃ በርካታ የህወሓት ታጋይ ሴቶችን ድፍሯል”


የተደበቀው የህወሓት ማንነት ከደደቢት እስከ ቤተመንግስት –  “ሳሞራ የኑስ በበረሃ በርካታ የህወሓት ታጋይ ሴቶችን ድፍሯል” (ክፍል 2)

መለስ ዜናዊ፣ ስብሀት ነጋ፣ ስዬ አብርሃ፣ ስዩም መስፍን፣ አባይ ፀሀዬ፣ ገብሩ አስራት፣ አለምሰገድ ገ/አምላክ፣ አውዓሎም ወልዱ፣ አረጋሽ አዳነ፣ አርከበ ዕቁባይ፣ ፃድቃን ገ/ተንሳይ፣ አበበ ተ/ኃይማኖት እና ክንፈ ገ/መደህን ለረጅም ጊዜ መቀሌ ላይ በመዶለት በኢትዮጵያና ህዝቦቿ ላይ አሲረው የበቀል፣ የዘረፋ፣ የመከፋፈል እና የረጅም ጊዜ የአፈና ስርዐት እቅድ ነድፈው ሰራዊታቸውን በባሌ ልከው እነሱ በቦሌ አዲስ አበባ ገቡ፡፡
TPLF 2
በአንድ ጃቸው መቀሌ ውስጥ ተጠፍጥፎ ተሰርቶ የተሳለ የበቀል ሰይፍ በሌላኛው እጃቸው የዘረኝነት ረጅም ዘንግ ጨብጠው አዲስ አበባ የገቡት የባንዳ ልጆች ስብስብ ሳይውሉ ሳያድሩ የጥፋት ተልዕኳአቸውን ዕቅድ አንድባንድ መተግበር ጀመሩ፡፡
የጥፋት ቡድኑ መሪ መለስ ዜናዊ “ከእናንተ ወርቅ ከሆናችሁት የትግራይ ህዝብ በመፈጠሬ እኳራለሁ፤ እንኳን ከእናንተ ተገኘን፤ እንኳን ይሄ ህዝብ የሌላ አልሆነ፤ እንኳን በሩቅ እያየን የምንቀናባችሁ አልሆናችሁ…” በማለት በአደባባይ ተናግሮ እሱም እንዳያቶቹ ኢትዮጵያዊነቱን ሽምጥጥ አድርጎ ካደ፡፡

የናትናኤል ፈለቀ ማስታወሻ – ጥቂት ስለ ማዕከላዊ (ከቂሊንጦ እስር ቤት)


ይህንን ጽሁፍ ስጽፍ ዓላማዬ ማዕከላዊ ያሉ ሥራቸውን አክብረው የኢትዮጵያውያንን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ የሚሰሩ ጥቂት ፖሊሶችን (ምናልባትም በአንድ እጅ ጣቶች ተቆጥረው የሚያልቁ መርማሪዎችን) ለማበረታታት አይደለም፡፡ ይህን ዓላማ በሌላ ጽሁፍ እመለስበት ይሆናል፡፡ ለነገሩ ሥራቸውን አክብረው የሚሰሩ ባለሙያ ፖሊሶች የኔ ማበረታታትን የሚፈልጉ አይደሉም፡፡ ያሉበት ደረጃ ላይ ለመድረስ በኃላፊነት ማሰብ የቻሉ ስለሆኑ፡፡
Nathaniel-Feleke-with-Kerry-625x370
ስለዚህ የዚህ ጽሁፍ ዓላማ በተቋሙ ውስጥ ኢትዮጵያ የምትተዳደርባቸውን ሕጎች ለማክበር (የተላለፉትን ለይቶ ለማስቀመጥና በስህተት የተጠረጠሩትን ነጻ ለማውጣት) ሳይሆን የአገዛዙን ዕድሜ ለማርዘም የሚሰሩትን አብዛኞቹን ሙያቸውን የማያከብሩ ፖሊሶች ‹‹ምርመራ›› ሴራቸውን እንዴት እንደሚፈትሉ ለማሳየት፣ ቢያንስ ሌላ ስልት እስኪፈጥሩ ድረስ በሀገሪቷ ጉዳይ ያገባናል የሚሉ ኢትዮጵያውያን አንዴ በተቋሙ ውስጥ ከገቡ በኋላ ሊገጥማቸው የሚችለውን የተንኮል መረብ ለማስረዳት እና ቀድሞ ለማዘጋጀት ያሰበ ነው፡፡

ሰበር ዜና፡ ታጋይ ዘመነ የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል አመራር ከአባይ ሚደያ ጋር አጭር ቆይታ አደረገ

ሰበር ዜና፡ ታጋይ ዘመነ የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል አመራር ከአባይ ሚደያ ጋር አጭር ቆይታ አደረገ።

አባይ ሚዲያ ከግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል የፖለቲካ ሃላፊ ከሆነው ታጋይ ዘመነ ካሴ ጋር የስልክ ውይይት አደረገ። ታጋይ ዘመነ ለአባይ ሚዲያ ሲናገሩ አቶ ኤልያስ ጋዜጠኛ ስለመሆኑም እና እንዴት እና በምን ሂሳብ ወደ ትግል አለም እንደገባም እንደማያውቁ ተናግረዋል።
ወጣቱ ታጋይ ዘመነ ለኢትዮጵያ ህዝብ ባስተላለፈው መልእክት አዲሱ አመት የሰላም እና የድል ዘመን እንዲሆን በመመኘት እና ወንድማችን ታጋይ አንዳርጋቸውን የከፈለውን መሰዋእትነት ከንቱ እንዳይሆን ህዝባዊ ሃይሉ እና ከሌሎች የነጻነት ሃይሎች ጋር እየተደረገ ያለው ሂደት መፋጠኑን በዚህ አመት የምናወራበት ሳይሆን ወደ ትጋበር ተሸጋግረን ወያኔን የምናበረክክበት ዘመን እንደሚሆን አትጠራጠሩ ሲል መልእክቱን አስተላልፉል።

አስመራ ተጉዘው የነበሩት ሁለቱ የኢሳት ጋዜጠኞች ስለ ሞላ አስገዶም መክዳት ምን አሉ?

በአዲስ ዓመት ዋዜማ ኢሳት ያሰማው ሰበር ዜና አነጋጋሪ ሆኗል:: ውህደት ተፈጸመ የሚለው ዜና 3 ሌሊት ሳያልፍ ይህ ዜና ብዙዎችን እያነጋገረ ነው:: ስለታጋይ ሞላ አስገዶም አስመራ ሄደው አግኝተውት የነበሩት ሁለቱ የኢሳት ጋዜጠኞች ፋሲል የኔዓለም እና መሳይ መኮንን ምን ይላሉ? ያንብቡት:: ፋሲል የኔዓለም ስለ ሞላ አስገዶም:- የደሚህቱ ሞላ አስገዶም መክዳቱን ስሰማ በእጅጉ ተገርሜአለሁ። ከቀናት በፊት ሞላ ፣ ሰው አክባሪ፣ ተግባቢና አገሩን የሚወድ ሰው መሆኑን ጽፌ ነበር። ኤርትራ በነበርኩበት ጊዜ ደጋግሜ አግኝቸዋለሁ ፣ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ጊዜ ወስደን ተነጋግረናል። እስከዛሬዋ ቀን ድረስ ስለሞላ የነበረኝ አመለካከት ቀደም ብዬ የገለጽኩት ነው። ስለእውነት እመሰክራለሁ፣ ኤርትራ በነበርኩበት ወቅት አንድም ቀን በሰላይነት እንድጠረጥረው ወይም በወያኔነት እንድፈርጀው የሚያደርግ ነገር አላነበብኩም። ከህወሃት ጋር የሚጋራቸው አቋሞች ቢኖሩም፣ በኢትዮጵያ አንድነት ላይ የማይናወጽ አቋም እንዳለው፣ ህወሃት ኢትዮጵያን ታሪክ አልባ በማድረጉ በጣም እንደሚያዝን ነግሮኛል። ከእርሱ ጋር የተግባባንበት የመጨረሻው ነጥብም ይህ ነበር- ህወሃት ኢትዮጵያን ከመበታተኑ በፊት እንድረስላት።

Wednesday, September 9, 2015

የፖለቲካ ለዉጥ ያስፈልገናል

ወያኔ ለኢትዮጵያ ህዝብ ያስተማረዉ ነገር ቢኖር ዘረኝነትን፡ሌብነትን፡ሙስናን፡ዉሸትን፡መስሎ መኖርን ወይም አድርባይነትንና ራስ ወዳድነትን ነዉ።ኢትዮጵያን አሁን ላይ እየመሯት ያሉት ከአብራኳ የወጡ ምሁራን ሳይሆኑ ከጫካ የመጡ ስለሀገርና ህዝብ ግድ የሌላቸው አውሬዎችና ፍርፋሪ ያጠገባቸዉ ካድሬዎች ናቸዉ፤የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሲስተም ተበላሽቷል፤አሁን ላይ ኢትዮጵያ የትግራይ ህዝብና አሽቃባጭ ካድሬ የሚስቅባትና የሚፈነጭባት ነገር ግን ሰፊዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ቀንና ማታ የሚያለቅስባት ለቅሶውን የሚያደምጥ መንግስት የሌለባት አገር ነች፤አሁን ላይ ኢትዮጵያ ማለት ደደብ የወያኔ ካድሬ የሚፈነጭባትና እንደፈለገ የሚያዝባት ነገር ግን ምሁር የማይከበርባትና የሚሰደድባት አገር ነች፤በምሁራን ፍልሰት ኢትዮጵያ ቀዳሚ አገር ሆናለች፤አሁን ላይ በኢትዮጵያ የትምህርት ጥራት ወድቋል፤የትምህርት ተቋሞች እየተመሩ ያሉት በምሁር ሳይሆን ለፖለቲካ ታማኝ በሆኑ ሰዎች ነዉ፤በየዓመቱ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ከዩኒቨርስቲ ተመርቀው ሲወጡ ጥሩ ስራ ማግኘት አይችሉም፣አሽቃባጭ ካድሬ ወይም ትግሬ ካልሆነ በስተቀር ሰርቶ መቀየር አስቸጋሪ ነዉ።

የአገራችን እውነተኛ ባለቤቶች ለመሆን ከምናደርገው ትግል ጎን ለጎን

የአገራችን እውነተኛ ባለቤቶች ለመሆን ከምናደርገው ትግል ጎን ለጎን፣ በስደት በምንኖርበት አገር ሁሉ ከሚደርስብን ጥቃት ራሳችንን ለመከላከል እጅ ለእጅ ተያይዘን መታገል ይኖርብናል። በደቡብ አፍሪካ የሚታየው አስቀያሚ ሁኔታ በሌሎች አገሮችም ሊከሰት እንደሚችል ልብ ልንል ይገባል። በተለይ የኢኮኖሚ ቀውስ በሚያጋጥምበት ወቅት ስደተኞች ሁሌም ኢላማ መሆናቸው አይቀርም። በስደት የሚገኙ ኢትዮጵያን ለህልውናቸው ሲሉ በየአካባቢያቸው እንዲሁም በአለም አቀፍ ደረጃ የሚሟገት ጠንካራ ማህበራትን መመስረት አለባቸው።

Somalia

"Somalia was once seen as a failed state, suffering from violence and lack of governance. But now hundreds of Ethiopians are moving to Somalia in search of a better life - although Somalia is a much poorer country. 
And while many of these migrants help boost the local economy, they face xenophobia and hostility from some locals who want to see them deported.

ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ የመስዋትነቱን ጣሪያ ከፍ አድርጎ ሰቀለው።

ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ የመስዋትነቱን ጣሪያ ከፍ አድርጎ ሰቀለው። ለአገር፣ ለፍትህ ፣ ለነጻነት፣ ለዲሞክራሲና ለሰብዓዊ መብት መስዋት መሆን ማለት እስከምን እንደሚደርስ አሳየን። ፕሮፌሰሩ ጣሪያውን ከፍ አድርጎ ቢሰቅለውም፣ እኛም ከቻልን እንደሱ ከጣሪያው ላይ ለመውጣት፣ ካልቻልን ደግሞ ከቆምንበት ውሃ ልክ ላይ ላለመውረድ እንጠንቀቅ፤ ከውሃ ልኩ የወረደም፣ ከወለሉ በታች ላለመቀበር ይጣር።

በፍትህ እንዲህ የተቀለደበት ዘመን ይኖር ይሆን?

ወንድሞቼ ዳንኤል፣ አብርሃም፣ የሽዋስና ሃብታሙ ይፈታሉ በመባሉ በጣም ደስ ብሎኛል። በመፈታታቸው ደስ እየተሰኝን የአገዛዙን ፖለቲካዊ ጨዋታ ማየቱም አይከፋም። ከዚህ ቀድም እንዳልኩት ነው፤ አገዛዙ እድሜውን የሚያራዝመው በሰላማዊ ትግል እና በትጥቅ ትግል መካከል ያለውን የሃሳብ ልዩነት በማራገብ ነው። ሰላማዊ ትግልን የሚያቀነቅኑ ሃይሎች እየጠነከሩ ሲመጡ፣ የትግሉን መሪዎች ያስርና ህዝቡ "ሰላማዊ ትግል አያዋጣንም" ብሎ ወደ ትጥቅ ትግል ፊቱን እንዲያዞር አድርጎ አደጋውን ይቀንሰዋል። የህዝቡ ትኩረት ወደ ትጥቅ ትግል ሲዞር ደግሞ፣ የታሰሩ ሰላማዊ ታጋዮችን ይፈታና የፖለቲካ ምህዳሩንም ትንሽ ከፈት አድርጎ " አዲስ የተስፋ ዳቦ" ይሰቅላል ። ህዝቡም እንደገና በሰላማዊ ትግል ተስፋ ያደርግና ትጥቅ ትግሉን ለመቀላቀል ልቡ ያመነታል- የታጋዩን ልብ እየከፋፈሉ የመግዛት ፖለቲካ ። የእነ አብርሃን መፈታት "ሃሳብን ከፋፍሎ በመግዛት የፖለቲካ ስልት " ካየነው ስሜት ይሰጣል።

መልካም የድል ዓመት።

አራቱ ንቅናቄዎች በዚህ ፍጥነት የጋራ ድርጅት ይመሰርታሉ ብዬ አላሰብኩም ነበር። ሁሉም የድርጅት አመራሮች ምስጋና ይገባቸዋል፤ ፕ/ር ብርሃኑ ትግሉ ስርዓት ይዞ በጥሩ አቅጣጫ እንዲጓዝ እያደረገው እንደሆነ በመስማቴ እንደ ወትሮው ኮርቸበታለሁ። የደሚት መሪ ሞላ አሰግዶም ትሁት፣ ሰው አክባሪ፣ ተግባቢና አገሩን በጣም የሚወድ ሰው ነው። መአዛው ጊጡም እንዲሁ ደግ፣ቅን፣ ሰው አክባሪና አገሩን የሚወድ ሰው ነው። የአማራን ድርጅት መሪ በአካል አላገኘሁትም፣ ምክትሉንና ጸሃፊውን አነጋግሪያቸዋለሁ፤ በተለይ ጸሃፊውን በቅርበት አውቀዋለሁ፣ ገና ትግሉን በረሃ ወርዶ ሳይቀላቀል በአገር ቤት ብዙ ታሪክ የሰራና መስዋትነት የከፈለ ወጣት ነው። የአፋሩ ኢብራሂም ሙሳም ሆነ ዶ/ር ኮንቴ አገራቸውን የሚወዱ አሪፍ መሪዎች ናቸው። በሁሉም ድርጅቶች ውስጥ፣ በጣም ብዙ አገር ወዳድ ታጋዮች አሉ፤ አዲሱ ድርጅት የእነዚህ ታጋዮች ሁሉ ውጤት ነውና እነሱም ክብር ይገባቸዋል።

አይ ኦነግ አላማ የሌለው

አይ ኦነግ አላማ የሌለው ስብስብ አንዳንድ ጊዜ ለምን ኦነግ 3 ሆነ ብዬ እራሴን ጠይቅና እናም ለራሴ ስመልስ እንወክለዋለን ወይም ነፃ እናወጣዋለን የሚሉትን የኦሮሞን እዝብ ስለማያውቁት ወይም እዝቡ አንቅሮ ስለተፋቸው/Rejected by the peoples / ይመስለኝና።
** ግን ለምን እዝቡ አንቅሮ ተፋቸው ስልና ምክንያቴን ሳስቀምጥ በእርግጥ የኦነግ መሪዎች ለስልጣን እንጂ ለእዝቡ ነፃነት ግድ እ
ንደሌላቸው እዝቡ ስላወቀ ነው የኦሮሞ እዝብ ስነ ልቦና ከቀሪው እዝብ ስነ ልቦና የሚለይ አይመስለኝም በዚህ የወያኔ 25 ክፉ አመታትን አብረን ኖረናል ይህ ለአንድነታችን ምስክር ነው ከዚህም በኋላ አብረን እንኖራለን።

አንዳንድ የኦሮሞ የፌስ ቡክ "አክቲቪስቶች"

አንዳንድ የኦሮሞ የፌስ ቡክ "አክቲቪስቶች" ግንቦት7 ኦነግን አፈረሰው እያሉ አዲስ ታሪክ መጻፍ ጀምረዋል። እነዚህ ሰዎች ግንቦት7ትን ሲወነጅሉ ኦነግን እያሳነሱት መሆኑ አልገባቸውም። እስኪ እግዜር ያሳያችሁ፣ የ40 ዓመቱን ጎልማሳ ድርጅት የ7 አመቱ ግንቦት 7 አፈረሰው ሲባል፣ ድክመቱ የማን ነው? አንድ የ40 ዓመት ጎልማሳን የ7 ዓመት ልጅ ደብድቦ ቢጥለው ፣ ሰውዬው 40 ዓመት ሙሉ ምን ይሰራ ነበር? ግንቦት7 ኦነግን አፍርሶት ከሆነ፣ ኦነግ ከመጀመሪያውም ድርጅት አልነበረም ማለት ነው፤ እንዲህ በቀላሉ የሚበታተን ድርጅት ከሆነም ኦነግ በስም እንጅ በገሃዱ ዓለም ያልነበረ ድርጅት ነበር ማለት ነው።

የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ የውስጥ አርበኞች በህወሓት አገዛዝ መከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት በመሰንዘር ለአንድ ሰዓት የዘለቀ ከባድ ውጊያ አድርገው ከፍተኛ ጉዳት አደረሱ፡፡

asee
የአርበኞች ግንቦት 7 የውስጥ አርበኞች ህወሓት “ክልል አንድ” እያለ በሚጠራው በጎንደር-ወልቃይት ደጃች ሜዳ ወረዳ አቤራ ቀበሌ ስልኪ ዳግባ በተባለው ቦታ ነሃሴ 23 2007 ዓ.ም በህወሓት መከላከያ ኃይል ላይ ድንገተኛ የተኩስ ውርጅብኝ በመክፈት ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ ወታደሮችን ገድለውና አቁስለው ድል ተቀዳጅተዋል፡፡

ህወኃት ፀገዴ ላይ ያካሄደው ስብሰባ ከሸፈ፣

የትግራይ ነፃነት ግንባር /ህወኃት/ ገና ከፅንስሱ ሲነሳ ለሙን የሰሜን ወሎን፣ ምዕራባዊ ጎንደርን እና ምዕራባዊ ጎጃምን በማካተት ታላቁን የትግራይ ሪፐብሊክ መመስረትግብ አድርጎ መመስረቱና ለዚህም አላማው ስኬት የቻለውን ሁሉ በማድረግ ላይ እንድሚገኝ የሚታወቅ ነገር ነው።
በተለይም በወልቃይት፣ ፀገዴና አርማጭሆ ያካሄደው መስፋፍት በአካባቢው ነዋሪ ህዝብ ላይ ትውልድ ይቅር የማይለው ግፍ ፈጽሟል፡ አሁንም የመስፋፋት ህልሙን እውን ለማድረግና ቀሪ የአማራን መሬት ለመቆጣጠር ያለማቁአረጥ ጥረት እያደረገ ነው። ከላይ በተጠቀሱት አካባቢወች የሚኖረውን የአማራን ህዝብ በማንበርከክ እኩይ ፍላጎቱን ለማስፈፀም ቀደም ሲል የጎንደር አስተዳደር ከተሞች በነበሩና አሁን በጉልበት ወደ ትግራይ በተወሰዱ ሁመራ፣ ማይካድራ፣ ማይፀብሬ፡ ዳንሻ፣ ማክሰኞ ገበያ/ ንጉስ ከተማ/ና ዲቪዥን የተባሉ ከተሞችን ማዕከል በማድረግ በአካባቢው የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆችን በተለይም ምልስ የህወኃት ወታደሮችን በመመልመል ከሃምሌ 2006 እስከ መስከረም 2007 ለሶስት ወር የዘለቀ በሁመራ ከተማ ለ120 ሰወች ልዩ የስለላና የአፈና ስልጠና የተሰጣቸው ሲሆን በፀለምት ዲቪዥን ከተማና በዳንሻ ከተማ በያንዳንዳቸው 1500 የሰው ሃይል ለፀጥታ ስራ በሚሊሻነት አሰልጥኗል።

“ወንድ ከወንድ፣ሴት ከሴት ጋር አላጋባም” ያሉ የህግ ሹም ወደ እስር ቤት ተወረወሩ

አንዳንዴ የዚህች አማሪካን ‘ገደብ የለሽ ‘ የሰብአዊ መብቶች ጎተራነቷን ለተመለከተ መገረሙ እና መበረገጉ አይቀረም። ለምሳሌ ንብረቴን፣ቤተሰቤን እና እራሴን እጠብቃለሁ ያለ አሜሪካዊ የጦር መሳሪያ ለመታጠቅ እንደ እኛ አገር የግድ የፓርቲ ሰው አሊያም የድሮ አብዮት ጠባቂ(ሰላም እና መረጋጋት አባል) መሆን የለበትም ።ከአቅራቢያው መደብር ጎራ ብሎ ከቀላል እስከ አውቶማቲክ የጦር መሳሪያ በቀላሉ መግዛት ይችላል። የጦር መሳሪያ ነገር ከተነሳ ዘንዳ አብዛኞቹ ፖሊሶቿ ተጠረጣሪን አድኖ ከመያዘ “አልሞ መተኮስ “ይቀደማቸዋል ይባላል።

የዞን9 ጦማርያን ጉዳይ በድጋሚ ለመስከረም 27 ተቀጠረ።

በነሶልያና ሽመልስ የክስ መዝገብ ለዛሬ በተደጋጋሚ የተላለፈው የብይን ጥበቃ በድጋሚ ዳኞች አልተሟሉም በሚል ሰበብ ለ37ተኛ ጊዜ ተቀጥሯል።
በዳኞች አለመሟላት የተነሳ ችሎቱን ማስቻል አልችልም ብለው በቢሮ ተከሳሾችን እና ጠበቆችን የጠሩት ዳኛ ዘሪሁን ብይኑ ቢሰራም ለማሳወቅ ሁሉም ዳኞች መገኘት ስላለባቸው ለመስከረም 27 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥተናል ብለዋል ።
ተለዋጭ ቀጠሮ ተከሳሾችን ቤተሰቦችን እና ውሳኔውን ሲጠብቁ የነበሩ ብዙ አጋሮችን በከፍተኛ ደረጃ ያስከፋ ነበር ።

የኢትዮጵያ አገር አድን በዴሞክራሲ የጋራ ንቅናቄ ምስረታ በማስምልከት የወጣ ድርጅታዊ መግለጫ

editorial of alliance
የኢትዮጵያ ህዝብ የኣገሩን ሉዓላዊነትና ኣንድነት ኣስከብሮ የኖረ ብቻ ሳይሆን ኣፍሪካውያን ወንድሞቹና እህቶቹ ከቀኝ ኣገዛዝ ነፃ እንዲወጡ የራሱ ኣስተዋፅኦ ያደረገ ጀግና ህዝብ ነው። ሆኖም ይህ ጀግና ህዝብ ከኣብራኩ በወጡ ገዢዎች ነፃነቱ ተገፎ፤ መብቶቹ ተረግጠው የመከራ ኑሮ እየገፋ ኣያሌ ዘመናት ኖZል። ይህ የመከራና የሰቆቃ ኑሮ ዛሬም ኣላበቃም፤ እንዲያውም “ከጭቆና ነፃ ኣወጣንህ” እያሉ የሚሳለቁበት ግፈኛ ገዢዎች የጫኑበት የስቃይ ቀንበር ተሸክሞ የውርደት ኑሮ እየኖረ ነው።

የትግራይ ነጻ አውጭ ድርጅት /ህወሃት በተለየ ሁኔታ በኤርትራ ላይ ዛቻ እያሰማ ነው።

-ኤኤፍፒ የአገሪቱን የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በመጥቀስ እንደዘገበው፣ የኢህአዴግ መንግስት በኤርትራ ላይ የሚያሰማው የጦርነት ዛቻና አገሪቱን እወራለሁ እያለ የሚያሰማው መግለጫ ጨምሯል። የትግራይ ነጻ አውጭ ድርጅት /ህወሃት በተለየ ሁኔታ በኤርትራ ላይ ዛቻ እያሰማ ነው።
በክረምቱ ወር ይሰማ የነበረው ፉከራ ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ተጠናክሮ መቀጠሉን የማስታወቂያ ሚኒስቴሩ ገልጿል። የህወሃት አገዛዝ ኤርትራን እንዲወር ከአሜሪካ ፈቃድ አግኝቻለሁ እያለ በመናገር ላይ መሆኑን የገለጸው የኤርትራ መንግስት፣ በተለይም ከኤርትራ ጋር ግንኙነት አላቸው ብሎ የሚጠረጥራቸውን ሃይሎች ለማሸማቀቅ እየጣረ መሆኑን ገልጿል።

‹‹ተንጠልጥሎ መቅረት እንደኢትዮጲያ !›› (አሌክስ አብርሃም)

freedom.jpg
አንዳንዴ ምን ይገርመኛል መሰላችሁ እኛ ኢትዮጲያዊያን ነገሮችን ሞቅ በማድረግና ወዲያው እርግፍ አድርጎ በመተው (በመርሳት) በሽታ የተለከፍን ይመስለኛል ….ለዛም ነው ታሪካችን በእንጥልጥል ፣ እውቀታችን በእንጥልጥል ፣ ስልጣኒያችን በእንጥልጥል ፣ፍቅራችን በእንጥልጥል ሁሉም ነገራችን በእንጥልጥል የሚቀረው !! …እንደኔ እንደኔ የፕሮፌሰር መስፍን የ‹‹መክሸፍ›› ቲዎሪ ከመክሸፍ ይልቅ ‹‹ተንጠልጥሎ መቅረት›› የሚለው ቃል በትክክል የሚገልፀው ይመስለኛል …መክሸፍ የተጀመረ ነገር ዳግም ላይመለስ ላያንሰራራ እንደገናም ከቆመበት ላይቀጥል መበላሸት መጨናገፍ መቆም ነው ትርጓሜው …እንደውም መክሸፍ እረፍት ነው !! በቃ አንድ ነገር ላይመለስ መኮላሸቱን አውቆ ከ ሀ ለመጀመር ሳያበረታታ አይቀርም ! ለመክሸፍማ አልታደልንም!

በሶርያ .የኢትዮጵያውያን ስደተኞች አቤቱታ.

” በጦርነት ውስጥ እያለን የዜግነት ማረጋገጫ አቅርቡ ተባልን “
* ” ማጣራት ካስፈለገ ከወጣን በኋላ ያጣራ !”
* ” በሊባኖስ ቤሩት ኢንበሰሲያችን አይተባበረንም !”
* ” የምንኖረው በኢትዮጵያ አምላክ ጥበቃ ብቻ ነው! “
የሻም ታሪካዊ ምድር ጥንታዊዋ ደማስቆስ ሶርያ በጦርነት አረንቋ ተዘፍቃ ትገኛለች ። በዚህችው ምድር በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በህገ ወጥ ደላሎች እየታለሉ ለስራ ይገባሉ ። ይህ ሁኔታ አሁን ድረስ መቀጠሉን ከሶርያ ደማስቆ የደረሰኝ ተጨባጭ መረጃ ያስረዳል ። ከደማስቀስ የደረሰኝን ይህንን መረጃ መሰረት አድርጌ በዚያው ስላሉ እንደ ጨው የተበተንን ዜጎች ጩኸት በዛሬው የማለዳ ወጌ የምለው አለኝ …

ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ከአስመራ ለመጀመሪያ ጊዜ ለጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ተናገሩ

ብረት አንስተው የሕወሓትን መንግስት እጥላለሁ ብለው አስመራ የዘመቱት ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ከአንድ ወር በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ጋር ቆይታ አድርገዋል:: ዶ/ር ብርሃኑ እርሳቸው ከዘመቱ በኋላ ሕዝብ እያወራው ስላለው ነገር ሲናገሩም “ጆሮ ሰጥቼ ስከታተለው አልነበረም” ብለዋል:: ሙሉውን ያድምጡት::

‹‹ከዳኞች ጋር ምንም ችግር የለብንም ከማን ጋር እንደተጣላን ገብቶናል›› በእስር ላይ ያሉ ጦማሪያን

‹‹አንድ ዳኛ ምንም ማድረግ አይችልም›› ዳኛ ዘሪሁን ደሳለኝ ‹‹ከዳኞች ጋር ምንም ችግር የለብንም ከማን ጋር እንደተጣላን ገብቶናል›› በእስር ላይ ያሉ ጦማሪያን በተጠረጠሩበት የሽብር ተግባር ወንጀል ክስ ከተመሠረተባቸው በኋላ የከሳሽ ዓቃቤ ሕግ የሰውና የሰነድ ማስረጃ ቀርቦባቸው ለብይን የተቀጠሩት አራት ጦማሪያን፣ ለአራተኛ ጊዜ ጳጉሜን 2 ቀን 2007 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ መሰጠቱን ተቃወሙ፡፡ ተከሳሾቹ ጦማሪያን ናትናኤል ፈለቀ፣ አቤል ዋበላ፣ አጥናፍ ብርሃኔና በፍቃዱ ኃይሉ ጳጉሜን 2 ቀን 2007 ዓ.ም. ብይን እንደሚሰጥ የጠበቁ ቢሆንም፣ ጉዳያቸው በሦስት ዳኞች የሚታይ ከመሆኑ አንፃር በዕለቱ አንድ ዳኛ አቶ ዘሪሁን ደሳለኝ ብቻ የተገኙ በመሆናቸው ብይኑ ሳይሰጥ ቀርቷል፡፡

ሰበር ዜና ህዝባዊ ወያኔ ሐርነት የሚመራዉ ጽንፈኛ ቡድን ድንጋጤ ላይ ወድቋል፤፤

asee
ህዝባዊ ወያኔ ሐርነት የሚመራዉ ጽንፈኛ ቡድን ድንጋጤ ላይ ወድቋል፤፤
ዛሬ ይህዉ ወንጀለኛ ቡድን በመከላከያ ሚኒስቴር በኩል የመከላከያ ሰራዊቱ አጠቃላይ አዛዦችን ባጠቃላይ አስቸኳይ ስብሰባ ጠርቷል። በተለይም የሰሜኑና የምስራቁ እዝ አዛዦች ላይ ትኩረት ያደረገዉ ይህዉ ድንገተኛ ጥሪ የጦርነት ነጋሪትን ለመጎሰም ይመስላል ይላሉ መረጃዉን የላኩልን ግለሰብ።