Wednesday, September 9, 2015

የፖለቲካ ለዉጥ ያስፈልገናል

ወያኔ ለኢትዮጵያ ህዝብ ያስተማረዉ ነገር ቢኖር ዘረኝነትን፡ሌብነትን፡ሙስናን፡ዉሸትን፡መስሎ መኖርን ወይም አድርባይነትንና ራስ ወዳድነትን ነዉ።ኢትዮጵያን አሁን ላይ እየመሯት ያሉት ከአብራኳ የወጡ ምሁራን ሳይሆኑ ከጫካ የመጡ ስለሀገርና ህዝብ ግድ የሌላቸው አውሬዎችና ፍርፋሪ ያጠገባቸዉ ካድሬዎች ናቸዉ፤የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሲስተም ተበላሽቷል፤አሁን ላይ ኢትዮጵያ የትግራይ ህዝብና አሽቃባጭ ካድሬ የሚስቅባትና የሚፈነጭባት ነገር ግን ሰፊዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ቀንና ማታ የሚያለቅስባት ለቅሶውን የሚያደምጥ መንግስት የሌለባት አገር ነች፤አሁን ላይ ኢትዮጵያ ማለት ደደብ የወያኔ ካድሬ የሚፈነጭባትና እንደፈለገ የሚያዝባት ነገር ግን ምሁር የማይከበርባትና የሚሰደድባት አገር ነች፤በምሁራን ፍልሰት ኢትዮጵያ ቀዳሚ አገር ሆናለች፤አሁን ላይ በኢትዮጵያ የትምህርት ጥራት ወድቋል፤የትምህርት ተቋሞች እየተመሩ ያሉት በምሁር ሳይሆን ለፖለቲካ ታማኝ በሆኑ ሰዎች ነዉ፤በየዓመቱ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ከዩኒቨርስቲ ተመርቀው ሲወጡ ጥሩ ስራ ማግኘት አይችሉም፣አሽቃባጭ ካድሬ ወይም ትግሬ ካልሆነ በስተቀር ሰርቶ መቀየር አስቸጋሪ ነዉ።
ከሃያ አራት አመት በፊት ባዶ እግራቸውን ከጫካ የመጡ ወያኔዎችና በሰፊው ህዝብ ስምና በብሄር ስም የሚነግዱ አሽቃባጭ ካድሬዎች በዘረፉት ገንዘብ ሚሊዮነሮች ሆነዉ ዘና ብለዉ ሲኖሩ ሰፊዉ የኢትዮጵያ ህዝብ በኑሮ ዉድነት በጣም እየማቀቀ ነዉ ።ትግሬና ካድሬ ብቻ ዘና ብለዉ በፍቅርና በደስታ እየኖሩ ሰፊዉ የኢትዮጵያዉያ ህዝብ የበይ ተመልካች ሆኖ እስከመቸ ይቀጥላል?በነገራችን ላይ የኢትዮጵያ ህዝብ ጎዳና ላይ መኖር የጀመረው ናዚ ወያኔ ስልጣን ላይ ከተቆናጠጠ በኋላ ነዉ፤እድገት ማለት የኢኮኖሚክስ ምሁራን በቀላሉ ሲተረጉሙት በአንድ ማህበረሰብ ውስጥ የሚኖሩ ቤተሰቦች መልካም ኑሮ ለመኖር የሚያስፈልጋቸውን ቀለብ ከአምና ዘንድሮ በቀላሉ ማግኘት ሲችሉና ይህም ቀጣይነት ሲኖረዉ ነው ይህ ግን በኢትዮጵያ ፈፅሞ የለም።ሁለት ድጅት፡11 % ምናምን ገለመሌ እየተባለ በየሚድያዉ የሚደሰኮርለት እድገት ፍፁም ውሸትና በመሬት የሌለ ነው፡፡በዘመነ ወያኔ የኢኮኖሚ እድገት፡ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍል፡የፖለቲካ ነፃነትና የትምህርት ጥራት የለም።በዘመነ ወያኔ በፈጣን ሁኔታ እያደጉ ያሉት ዘረኝነት፡ስደት፡ሙስና፡የሃብት ብክነት፡ኑሮ ዉድነት፡ሽርሙጥና፡ስግብግብነት፡ሌብነት፡ክህደት፡አስመሳይነት፡ራስወዳድነት፡አፈና፡እስራት፡የመብት ጥሰት፡ኢፍትሃዊነት፡የሃሰት ምስክር፡ረሃብና ድርቅ ናቸዉ።

No comments:

Post a Comment