Wednesday, September 9, 2015

በሶርያ .የኢትዮጵያውያን ስደተኞች አቤቱታ.

” በጦርነት ውስጥ እያለን የዜግነት ማረጋገጫ አቅርቡ ተባልን “
* ” ማጣራት ካስፈለገ ከወጣን በኋላ ያጣራ !”
* ” በሊባኖስ ቤሩት ኢንበሰሲያችን አይተባበረንም !”
* ” የምንኖረው በኢትዮጵያ አምላክ ጥበቃ ብቻ ነው! “
የሻም ታሪካዊ ምድር ጥንታዊዋ ደማስቆስ ሶርያ በጦርነት አረንቋ ተዘፍቃ ትገኛለች ። በዚህችው ምድር በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በህገ ወጥ ደላሎች እየታለሉ ለስራ ይገባሉ ። ይህ ሁኔታ አሁን ድረስ መቀጠሉን ከሶርያ ደማስቆ የደረሰኝ ተጨባጭ መረጃ ያስረዳል ። ከደማስቀስ የደረሰኝን ይህንን መረጃ መሰረት አድርጌ በዚያው ስላሉ እንደ ጨው የተበተንን ዜጎች ጩኸት በዛሬው የማለዳ ወጌ የምለው አለኝ …

በሊባኖስ የኢተትዮጵያን ኢንባሲን በዜጎች ቅሬታ ዙሪያ ጠይቄያቸው ኢትዮጵያውያኑን እየረዳን ነው ቢሉም ኢትዮጵያውያኑ ግን በባለስልጣኑ ምላሽ አልተስማሙም !

ነቢዩ ሲራክ
ጳግሜ 3 ቀን 2007 ዓም

No comments:

Post a Comment