Wednesday, September 9, 2015

ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ የመስዋትነቱን ጣሪያ ከፍ አድርጎ ሰቀለው።

ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ የመስዋትነቱን ጣሪያ ከፍ አድርጎ ሰቀለው። ለአገር፣ ለፍትህ ፣ ለነጻነት፣ ለዲሞክራሲና ለሰብዓዊ መብት መስዋት መሆን ማለት እስከምን እንደሚደርስ አሳየን። ፕሮፌሰሩ ጣሪያውን ከፍ አድርጎ ቢሰቅለውም፣ እኛም ከቻልን እንደሱ ከጣሪያው ላይ ለመውጣት፣ ካልቻልን ደግሞ ከቆምንበት ውሃ ልክ ላይ ላለመውረድ እንጠንቀቅ፤ ከውሃ ልኩ የወረደም፣ ከወለሉ በታች ላለመቀበር ይጣር።

ይሄ ትግል የምር መሆኑ ሲነገራቸው ያልሰሙ አንዳንድ ሰዎች፣ ዛሬ በሚያዩት እየተደናገጡ፣ ትናንት የተናገሩት ከዛሬው ጋር እየተጣረሰባቸው ሲቸገሩ እያየን ነው። ጠንካሮችንና መስዋትነት በመክፈል ላይ ያሉትን በመሳደብ የራሳቸውን ድክመት ለመሸፈን ሲታትሩ እየታዘብን ነው። ቆርጠው ለነጻነት የሚታገሉ ሰዎችን የሚዘልፉ ሰዎች፣ የውስጥ ህመም ያለባቸው ሰዎች ናቸው። የህመማቸው መንስኤም ካለመቻል፣ ከመሸነፍ፣ ከመርህ አልባነትና የህይወትን ግብ ካለማወቅ የሚመጣ ነው። ፍሬድሪክ ኒቼ ይመስለኛል " He who has a why to live can bear almost anyhow " ያለው። የህይወትን ግብ ማወቅ ፣ ፈተናን ለመቋቋም ብቻ ሳይሆን ከሚዋዥቅ አቋምም ያድናል። አሸናፊም ጨዋም ያደርጋል።

No comments:

Post a Comment