Wednesday, July 23, 2014

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያልተፈረደባቸውን ሰዎች በሚድያ ጥፋተኛ ማድረጋቸውን ተቃዋሚዎች ነቀፉ

69B94794-33D9-4BAE-A6C7-2AB0E841B85A_w640_r1_s
“በፍርድ ቤት ‘ጥፋተኛ’ ባልተባሉ ሰዎች ላይ በመገናኛ ብዙኃን የጥፋተኝነት አስተያየት መስጠት ተገቢ አይደለም” ሲሉ የተቃዋሚ ፓርቲዎች መሪዎች የጠቅላይ ሚኒስትሩን ንግግር ተቃውመዋል።
“በፍርድ ቤት ‘ጥፋተኛ’ ባልተባሉ ሰዎች ላይ በመገናኛ ብዙኃን የጥፋተኝነት አስተያየት መስጠት ተገቢ አይደለም” ሲሉ የተቃዋሚ ፓርቲዎች መሪዎች የጠቅላይ ሚኒስትሩን ንግግር ተቃውመዋል።

***ኩዲታ ግዜው ደርሷል***

መልካም አስተዳደር ለማስፈን የሚያስፈልገው የተራዘመ ትግል ሳይሆን ፈጣን ዕርምጃ ነው
ለመልካም አስተዳደር ችግሮች በተራዘመ ትግል መፍትሔ አመጣለሁ ሲል ዕድገቱን ቁሳዊ እያስመሰለው ነው፡፡ ለሰብዓዊ ጉዳዮች መወሰድ ያለበት ዕርምጃ በዘገየ ቁጥር ቁጣ ይቀሰቅሳል፡፡ ይህ ቁጣ ሲጋጋም አብዮት ያስከትላል፡፡ ይህ አብዮት ደግሞ ጠራርጎ ይወስዳል፡፡ አሁንም ይህንን ሐሳብ የሚያጠናክሩ በርካታ ምልክቶች አሉ፡፡ የዲሞክራሲያዊና የሰብዓዊ መብት ረገጣ፣ ዜጎች የመሰላቸውን ሐሳብ በነፃነት እንዳያንሸራሽሩ ማፈንና ተቃውሞን ፀጥ ለማሰኘት መንቀሳቀስ ብሶት እየፈጠሩ ናቸው፡፡ ሕጋዊ መንገዶች እየተዘጉ በሄዱ ቁጥር ሕገወጥነት ይንሰራፋል፡፡

Sunday, July 20, 2014

የለውጥ እንቅስቃሴ ጥሪ!

ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ ድርጅቶች፣ የሃይማኖትና የሲቪክ ተቋማት በሙሉ!

በአሁኑ ጊዜ በሰሜን አፍሪካና በሌሎች አገራት የሚካሄደውን ለውጥ እየተመለከትን እኛም ለአገራችን የማናስብበትና የህውሃት/ወያኔን የሚመስሉ ጨቋኝ አምባገነኖች ከሌሎች አገሮች እየተወገዱ እኛ ዝም ብለን የምንመለከትበት ምንም ምክንያት ሊኖር አይገባም፡፡ በእነዚህ የሰሜን አፍሪካ አገራት የኑሮ ውድነት፣ የነጻነት ዕጦት፣ ጭቆና፣ ግድያ፣ ሕገወጥነት ወዘተ ያንገፈገፈው ሕዝብ የደረሰበትን የምሬት ደረጃ የኢትዮጵያ ሕዝብ አልደረሰበትም ማለት ፈጽሞ አይቻልም፡፡ ምናልባትም ግፉ ከዚህ የበለጠ ሊሆን ይችላል፡፡

ግልፅ ደብዳቤ ለኢሳት (ESAT) ና ታዳሚዎች!!!አንተነህ ሽፈራው

‘የነገዋ ኢትዮጵያ በዛሬው ቅይት ትለካለች’:-
ወያኔ የየካቲት 1967 ዓ.ም አፈጣጠሩ፣ እድገቱ፣ አሁን እየሠራ ያለው ተግባሩ፣ ቀጣይ ዓላማውና እንዲሁም በ1997 ዓ.ም ምርጫ እርቃኑን የቀረው ዘረኛ የፖለቲካ መሠረቱና ኋላቀርነቱ ኢትዮጵያን መሠረት አድርገው ከተደራጁ ዴሞክራሲያዊ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ ቡድኖችና ከግለሰቦች ጋር ሳይቀር ለሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ስልጡን የፖለቲካ ሥርዓት ተገዥ ሆኖ ለሥልጣን ለመወዳደር ስለማይፈቅድለት ሕዝባችንን አረመኔ በሆነ ድርጊቱ በጠብ-መንጃ በገፍ ይገላል፣ የአገር ንብረት ይዘርፋል፤ አልፎ አልፎ ብቅ ብቅ ያሉ ጠንካራ ጋዜጠኞችም ከመጠን በላይ ስለሚያስፈሩት ያለአግባብ ለተደጋጋሚ ግዜ በእስር ፍዳቸውን አሳይቶአቸዋል፤ የሚወዷት አገራቸውን፣ ሕዝባቸውንና ቤት ንብረታቸውን ትተው ለስደት ዳርጓቸዋል፤ አሁንም ድረስ እልፍ አህላፍ የሕሊና እስረኞችና ጋዜጠኞች ቀድሞ በነበሩትና ወያኔ በከፈታቸው ተጨማሪ እስር ቤቶች በገፍ እየተንገላቱ ይገኛሉ::

ለአዲስቱ ኢትዮጵያ! የጋራ እንቅስቃሴና!

ለአዲስቱ ኢትዮጵያ የጋራ እንቅስቃሲ የሃገራችንን የተወሳሰበ ችግር በጋራ ሁላችንም ተንቀሳቅስን መፍትሂ ልንፈጥርበት የሚያስችለን መንገድ ይመስላል ይህንንም ለማለት ያበረታታኝ በተለያየ ግዜ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ እንቅስቃሴ ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ በጽሁፍ ስለድርጅታቸው አላማና እንቅስቃሴ የሚሰጡትን መረጃ መሰረት በማድረግና የኢትዮጵያ ህዝብ ለጋራ ጥቅሙ አንድነት፤ ከመቼም ግዜ በላይ ማበር፤ እንድለበት አበክረው በተደጋጋሚ የሚሰጡትን መገልጫ መሰረት በማድረግ ነው።

በበርካታ የብሄረሰብ ጥርቅም ሐገር ውስጥ፤ በብዙ ሚልዮን ህዝብ መሪት ላይ፤ የተመሰቃቀለ የፖለቲካ ስርአት ከነገሰ፤ ድህነት ድንቁርናና በሽታ የበላይ ይሆናሉ።

Friday, July 18, 2014

ችቦዉ ተለኩሷል የበለጠ ማቀጣጠሉ ወይም ማጥፋቱ የኛ ምርጫ ይሆናል !

አሁን በስልጣን ላይ ያለዉ የሕወሃት መንግስት ብቻ ሳይሆን ሌሎችም ሕዝብን በግፍ የሚገዙ አምባገነኖች ለስልጣናቸዉ ማራዘሚያ የሚጠቀሙበት ትላልቅ መሳሪያዎች ፍርሃትና ህዝብን መከፋፈል ነዉ።
ሕወሃት ስልጣን ከጨበጠ ከጅምሩ በኢትዮጵያ የዘረጋዉ ፖለቲካ በዘር ላይ የተመሰረተ ከፋፋይ ፖለቲካ ነዉ። ኢትዮጵያ የብዙ ብሄረሰብ አገር ናት። በታሪኳ የተሰሩ ብዙ ስህተቶችና በደሎች አሉ። በአንጻሩም ደግሞ ኢትዮጵያዉያን ከተለያዩ ቋንቋዎችና ክልሎች በሰላም በፍቅር ኖረዋል፣ ተዋደዋል፣ ተደባልቀዋል። በጋራ የዉጭ ወራሪ ኅይላትን መክተዋል።
የሕወሃት መንግስት ኢትዮጵያዉያን በጋራ የሰሩትን አጉልቶ አንድነትን ከማጠናከር ይልቅ ልዩነቶቻቸዉን አቻችለዉ ከዚህ በፊት በተሰሩት ስህተቶች ይቀር ተባብለዉና ካለፈዉ ትምህርት ቀስመዉ ፣ አንዱ የአንዱ ቋንቋ ባህል አክብሮና ተረዳድቶ እንዲኖር ከማድረግ ይልቅ እርስ በርስ ህዝቡን በመከፍፋፈል ወገን ከወገን ወንድም ከወንድም ማጣላቱን ስራቸዉ አድርገዋል። ጣሊያን አምስት አመት ኢትዮጵያን ወሮ በነበረ ጊዜ እንዳደረገዉ ትግሬ ፣ አማራ፣ ኦሮሞ፣ ሱማሌ እያሉ ሕዝቡን በዘር ሸነሸኑት።

ወያኔ አቶ አንዳርጋቸውን እንዴት ማፈን ቻለ? ኪሩቤል በቀለ

ወያኔ አቶ አንዳርጋቸውን እንዴት ማፈን ቻለ? ለዚህ ጥያቄ መልስ መስጠት ለግንቦት 7 ብቻ ሳይሆን ለሁላችንም የሞትና የሽረት ጥያቄ ነው:: በቂ ማስረጃ እስክሚሰበሰብ ድረስ አራት አቅጣቻዎችን መመርመር ያስፈልጋል::
1) ለሻቢያ ሁሉ ነገር ከራስ በላይ ነፋስ ነው:: ራሱ ሻቢያ በተዘዋዋሪ ለወያኔ የአቶ አንዳርጋቸውን የበረራ ሰዓታቸውን አሳልፎ ሊሰጥ ይችላል::ይህ እንግዲህ በኤርትራ ውስጥ የሚገኙ የግንቦት 7 መሪዎች ሁኔታውን በደንብ ሰለሚያውቁ ይህ ግምት ሊሆን ወይም ላይሆን እንደሚችል መጠቆም ይችላሉ:: ለምሳሌ ሻቢያም ሆነ በሻቢያ የሚታዘዘው ደሚት ስለ ግንቦት 7 ደስ ያላላቸው ነገር እንዳለ የታዘቡት ነገር አለ ወይ? ሌላም ሌላም የተፈጠሩ ክስተቶች ካሉ መገምገም ይኖርባቸዋል::

የውህደት እንቅስቃሴአችን በተሳካ ሁኔታ ቀጥሏል!! – ከመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) እና ከአንድንት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ከጉባኤ አዘጋጅ ኮሚቴ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

ለውህደቱ መሳካት ጥረት እና ድጋፍ እያደረጉ ላሉ ኢትዮጵያውያን ምስጋና እናቀርባለን!1እንደሚታወቀው የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) እና አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የቅድመ ውህደት ስምምነት ፊርማ ካኖሩ በኋላ ጠቅላላ ጉባኤ በመጥራት ውህደቱን ምሉዕ ለማድረግ የጋራ ኮሚቴ በማቋቋም እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ፡፡
ይሄው ውህደት አመቻች ኮሚቴ በስምምነት ሰነዱ በተቀመጠው መሰረት ለማጠናቀቅ ቀን ከሌሊት እየሰራ ሲሆን የሁለቱ አንጋፋ ፓርቲዎች ውህደት የተሳካ እንዲሆን ትንሽ ግዜ መጨመር አስፈላጊ ሆኖ አግኝቶታል፡፡ በተለይም ለውህደቱ መሳካት የሚያስፈልገው የገንዘብ መጠን ሰፊ በመሆኑ በሀገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ ደጋፊዎቻችን የአቅማቸውን ድጋፍ ለማድረግ በስምምነት ሰነዱ የተቀመጠው የውህደት ግዜ ላይ ሁለት ሳምንት መጨመር እንደሚያስፈልግ ታምኖበታል፡፡

ከእስሩም በላይ – “ሽብርተኝነት” – እስረኞቹ በሽብር መከሰሳቸውን አያውቁም

ጽዮን ግርማ
tsiongir@gmail.com
አንድ ዓመት ከአንድ ወር ኾኖታል፡፡ እስክንድር ነጋ ከታሰረ ከዐስራ ስምንት ወራት በኋላ ከባለቤቱ ከጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል እና ከልጁ ከናፍቆት በተጨማሪ ለመጀመሪያ ጊዜ ሌላ ሰው እንዲጠይቀው በሰኔ የመጀመሪያ ወር ላይ በ2005 ዓ.ም እንደተፈቀደለት ነው፡፡ በወቅቱም እስክንድርን ልጠይቀው ቃሊቲ ወደሚገኘው እስር ቤት አምርቼ ነበር፡፡
zone 9
ተገናኝተን ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላም እንዲህ አለኝ፤‹‹ሽብርተኛ አይደለኹም፤ሀገሬ በማንም እንድትሸበር አልፈልግም አልፈቅድምም እኔ የምፈልገው የሀገሬ ሕዝቦች በነጻነት የሚያስቡባትና የሚንቀሳቀሱባት ሰላማዊ ሀገር እንድትኾን ነው››፤እስክንድር ‹‹ሽብርተኛ›› አይደለምና ከእስሩም በላይ ያንገበገበው ‹‹አሸባሪ›› መባሉ ነበር፡፡
እስክንድር ‹‹ጋዜጠኛ›› ነው፡፡ እስክንድር ሲጽፍ ሀገሪቱ ላወጣችው ሕግ ራሱን አስገዝቶ፣በሀገሪቱ ሕግ ማዕቀፍ ሥር ራሱን ገድቦ ነው፡፡ ይህም ኾኖ ግን ሲጽፍ ሕግ ተጥሶ አደጋ ሊደርስበት እንደሚችል፣ሲጽፍ ሕግ ተጥሶ ሊታሰር እንደሚችል ያውቃል፡፡ ግን ደግሞ ቢታሰር በቀጫጭን መስመርም ቢኾን በሀገሪቱ ሕግ ተዳኝቶ ከእስር ሊለቀቅ እንደሚችል ያምን ነበር፡፡በዚህ እምነቱም የመጣበትን ለመቀበል ተዘጋጅቶ ሀገሩ ላይ ቁጭ ብሎ ይጽፋል፡፡

የዘር ማጥፋት ወንጀሎች በአማራ ሕዝብ ላይ በታሪክ ሂደት ውስጥ ከጥንት እስከ ዛሬ! (ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው)

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
amsalugkidan@gmail.com
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
ይሄንን ጽሑፍ ታች አምና ከጉራፈርዳና አካባቢው አማራ በመሆናቸው ምክንያት ብቻ ሕጋዊነታቸውን የሚያረጋግጡ ሰነዶችን ይዘው እያለ ሕጋዊ ሆነው የየክልሉ መንግሥት አውቋቸው በሥርዓቱ ግብር እየከፈሉ እየኖሩ የነበሩ ምስኪን ገበሬዎችን “ሕገ ወጥ ሰፋሪዎች”  በሚል ሕገ ወጥነታቸው አግባብነት ባለው የሕግ አካል (ፍርድቤት) ክስ ተመስርቶባቸው ሳይረጋገጥባቸው በጅምላ በግፍና በሕገ ወጥ መንገድ ንብረታቸውን ሁሉ ተወርሰው እንዲወጡ በተደረገ ጊዜ ጽፌው ለጥቂት መደበኛና ኢመደበኛ (Conventional and Social Media) ልኬው ነበር እስከማውቀው ድረስ ለሕዝብ ይፋ አድርገውት ያስነበቡት ወይም ያስደመጡት አልነበሩምና ሕዝብ ሊያውቃቸው የሚገባ በርካታ ቁምነገሮች ስላሉት እንዳያመልጣቹህ በማሰብ ወደ እናንተ አድርሸዋለሁ መልካም ንባብ፡፡

“አሸባሪ”ዎቹን ፍለጋ – ከተመስገን ደሳለኝ (ጋዜጠኛ)

 (የሽብር – ዘፍጥረት ፫)
    ….በሁለት ተከታታይ ጽሁፎች የሽብርተኝነትን አነሳስ እና የአልሸባብን አፈጣጠር በደምሳሳውም ቢሆን መቃኘታችን ይታወሳል፡፡ በዚህም የኢትዮጵያ ጦር ወደ ሶማሊያ መግባቱ ለምስራቅ አፍሪካው አደገኛ ቡድን መወለድ መንስኤ ስለመሆኑ ከተለያዩ የመረጃ ምንጮች እና ከሞቋዲሾ እስከ ኪስማዩ በደም ከተፃፈው የሠራዊቱ አባላት ገጠመኝ መረዳት ችለናል፤ ይህ ቡድን ዛሬ ከመንግስታዊ ተቋማት ይልቅ ንፁሀን ዜጐችን ዒላማ አድርጎ፣ የቀንዱን አገራት አካባቢ ወደ ሕግ-አልባ የጦር ቀጠናነት መለወጥ የሚያስችለውን ግዙፍ ኃይል አካብቶ አስፈሪ እየሆነ ስለመምጣቱ ማስተዋሉ አዳጋች አይደለም፡፡ ለርዕሰ-ጉዳያችንም መቋጫ የምናደርገው የኢትዮጵያ መንግስት ‹‹ሽብር››ን እንዴት ለፖለቲካዊ ዓላማ እንደሚጠቀምበትና እነማንን በ‹‹አሸባሪ››ነት  ፈርጆ በመወንጀልና በማሳደድ እኩይ ተግባር ላይ መጠመዱን በጨረፍታ መመልከት በመሆኑ ወደዛው እናልፋለን፡፡

Monday, July 14, 2014

ሰሞኑን ያካሄድኩት መጠነኛ ጥናት፤ የኢትዮዽያ ህዝብ በሁለት ይከፈላል ይላል - “አሸባሪ” የሆነና አሸባሪ ያልሆነ ተብሎ፡፡

ሰሞኑን ያካሄድኩት መጠነኛ ጥናት፤ የኢትዮዽያ ህዝብ በሁለት ይከፈላል ይላል - “አሸባሪ” የሆነና አሸባሪ ያልሆነ ተብሎ፡፡
የሀገሬ ጉዳይ ያገባኛል ፣ የሀገሬ የወደፊት እጣ ፋንታ ያሳስበኛል ፣ መንግስት በደመነፍስ የሚያስረውን ፣ የሚገርፈውን ፣ የሚገለውን እቃወማለው የምትል ከሆነ፤ አትጠራጠር አንተ “አሸባሪ” ነህ - ለሀገርና ለህዝብ የምታሰጋ፡፡ 
“አሸባሪ” የሚል ማዕረግ ተጎናፅፈህም በሰላም የምትቀመጥ እንዳይመስልህ፡፡ እንደ አንዳርጋቸው ፅጌ ፣ እንደ አብርሃ ደስታ ፣ እንደ ዞን ዘጠኞች ፣ እንደ እስክንድር ነጋ ፣ እንደ ርዮት አለሙ በተለጠፈብህ የአሸባሪ ታፔላ ወህኒ ትወርዳለህ - የሀገሬ ጉዳይ ይመለከተኛል ስላልክ ብቻ፡፡

***አናቱን የሚያሳክከውን እግሩን ብናክለት ሆነ ነገሩ***

***አናቱን የሚያሳክከውን እግሩን ብናክለት ሆነ ነገሩ***
ዛሬ በኢትዮጵያ ያሉት የሰላማዊ ተቃዋሚ ታጋዮችን torture እያደረገ ነው ያለው የወያኔ ጠቅላይ ሚኒስተሩ ሀይለማሪያም ደሳለኝ በአንድ ወቅት በሰጡት መግለጫ 99 የተለያዩ ፓርቲዎች አሉ በየሳምንቱ ሰላማዊ ሰልፍ እየወጣቹ ከምጨውብን ተደራጅታቹ ወጣቹ ብጮሁ ይሻላል ነው ያሉት ዛሬ በሰላማዊ ፓርቲ ውስጥ ያሉት አመራሮች አንበርክኮ በመግረፍ እና ሰላማዊ ሰልፍ አትወጡም በማለት የተለያዩ በደል ሲፈፅምባቸው እያየን ምንድነው የሚጠበቀው።
በግል ጥላቻ የተነሳ የተለያዩ አስተያየት ይሰጣል።አንዳንዱ ተቃዋሚዎች አመፅ እንዲመጣ ይፈልጋል እያሉ ሟርት የሚናገሩ ሰዎች አሉ ለዚህ ሁላ ተጠያቂው ወያኔ ነው ምክንያቱም የኢትዮጵያ ህዝብ በሰላም፣በፍትህ፣በዲሞክራሲ፣በህግ ህገ መንግስቱን አንተርሶ ጥያቄዎችን እያቀረበ መልስ ሳይሰጠው በየአደባባዩ በጥይት መደብደብ ፣መታሰር ፣መሰደድ ሆኗል መልሱ ስለዚህ አላፊነቱን መውሰድ ያለበት ወያኔ እንጂ ተቃዋሚው አይደለም።

Thursday, July 10, 2014

አንዳርጋቸው ኢትዮጵያዊ ነው !!! (በልጅግ ዓሊ)

በልጅግ ዓሊ
ወንድሙን ሲገሉት ፣ ወንድሙን ካልከፋው፣
ሱሬውን አምጡለት፣ ደሙ እንዲገለማው።

በጉን በጉ በላው በድዱ ጎትቶ ፣
ለማን አቤት ይሏል፣ ሰሚስ የት ተገኝቶ።

የሕዝብ ግጥም
አንዳርጋቸው በሁለት ወንጀለኛ መንግሥታት ትብብር ታፈነ፣ ተወሰደ ፣ ታሰረ ፣ ተሰቃየ።
ይህ አሳዛኝና የሚያበሳጭ ዜና ነው። በዚህ ቅጥፈት በሞላበት ዓለም ውስጥ ሕዝባቸውን በየቀኑ የሚያስሩ፣ የሚገድሉ፣ የሚያፍኑ መንግሥታት ቢተባበሩ ምንም የሚገርም ጉዳይ አይሆንም። አንዱ የሌላውን  እከክ ማከኩ የተለመደ ነው። ይህ የመጀመሪያ ሳይሆን የተደጋገመ የወያኔ ዘረኛ አገዛዝና የአካባቢው ወንጀለኛ መንግሥታት የተለመደ ወንጀል ነው። ወያኔ ገና ስልጣን ላይ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ፣ እንዲሁም ከዚያ በፊት ጀምሮ ያስራል ፣ ይገድላል ፣ ያሰቃያል።

“ ድንጋይ ቢቆሉት አይሆንም ቆሎ ”

ይድነቃቸው ከበደ
(ይድነቃቸው)
(ይድነቃቸው)
ሉቃ ም.14ከቁ.15-24 “በእግዚአብሔርመንግስት እንጀራ የሚበላ ብፁዕ ነው አለው፡፡እርሱም ግን አንድ ሰው ታለቅ እራት አዘጋጅቶ ብዙዎችን ጠራ፡፡በእራትም ሰዓት አሁን ተዘጋጅቷልና ኑ እንዲላቸው ባሪያውን ላከ ሁላቸውም በአንድነት ያማካኙ ጀመር ይላል፡፡” የሚገርመው የነዚህ ሰዎች ምክንያት ተራና የውሸት ምክንያት መሆኑ ነው “ ፊተኛው መሬት ገዝቻለው ወጥቼ ላየው በግድ ያስፈልገኛል” አለ፡፡ሰው መሬትን መርምሮ የሚያየው ከመግዛቱ በፊት እንጂ ከገዛ በኋላ ነው ? ሁለተኛውም “አምስት ጥማድ በሬዎችን ገዝቼአለው ልፈትናቸው እሄዳለሁ”አለ፡፡በሬን የሚገዛ ሰው በሬውን የሚፈትነው ቀንበር መሸከም መቻሉን አለመቻሉን አይቶ ማረጋገጥ ያለበት ከመግዛቱ በፊት ነው ወይስ በኋላ? በተጠቀሰው መጽሐፍ ቅዱስ ምዕራፍ ላይ ታሪኩ በሰፊ ይገኛል፡፡ ምክንያተኛ ሰው ሌላው ቀርቶ እግዚአብሔር ሲጠራው ይቸገራል፡፡
ምክንያት ለሰው ልጅ ለየትኛውም እንቅስቃሴ አስፈላጊ ከመሆኑም ባሻገር ተፈላጊም ጭምር ነው፡፡ምክንያት አያስፈልግም ከሚል መደምደሚያ የሚያደርስ የማናቸውም ሰው ክርክር ዉሃ የማይቋጥር ጉንጭ አልፋ ሙግትነው፡፡ለማድረግ ወይም ላለማድረግ የቀረበው አመክንዮ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም? ለማለት ምክንያታዊ አስተሳሰብን መሠረት በማድረግ መሞገት፣ ተመራጭ አሳብን ለማቅርበ እድል ይሰጣል፡፡

እኔ የማይገባኝ እንዴት 23 አመት ሙሉ ዜጎችን እያሰሩ ይቀጥላሉ ?

ግርማ ካሳ
ሃብታሙ አያሌው ፣ ዳንኤል ሺበሺ እና የሺዋስ ከበደ ወደ ማእከላዊ መዉረዳቸዉን የሚገለጽ ዜና ተመለከትኩ። በጣም አዝኛለሁ።
habtamu ayalew
ሃብታሙ አያሌው
ሃብታሙ አያሌው በአንድነት ፓርቲ ዉስጥ ትልቅ ሥራ እየሰራ ያለ፣ በቅርቡ ወዳጅ አባቷን ያጣችው እህታችን ባለቤት እና የአንዲት ቆንጅዬ ልጅ አባት ነው።የአንድነት ፓርቲ እና መኢአድ የቅድመ ዉህደት ስምምነት ፈርመው ፣ ዉህደቱን ለማስፈጸም ያቋቋሙት የጋራ ኮሚቴ ሰብሳቢ ነው። ያ ብቻ አይደለም የሚሊዮኖች ንቅናቄ ግብረ ኃይል ሰብሳቢ ሆኖ ሰርቷል ፣ አቶ ሃብታሙ።
ዳንኤል ሺበሺ የአንድነት ት ጉዳይ ሃላፊ ም/ሰብሳቢ ነው። የአንድነት ፓርቲ ድርጅታዊ መዋቀሩን በአገሩቷ ሁሉ ለማጠናከር እየሰራው ባለው ስራ፣ ወጣት ዳንኤል ሺበሺ ትልቅ ሚና የነበረው ወጣት አመራር ነው።
የሺዋስ አሰፋ የሰማያዊ ፓርቲ ምክር ቤት ም/ሰብሳቢ ነው። በቅርቡም ሰማያዊ ፓርቲ ለሰፍ ቅስቀሳ በሚያደርግበት ጊዜ ታግቶ ከሳምንት በላይ ውህኒ የተወረወረ ወጣት ነው።

Tuesday, July 8, 2014

ጊዜ የማይሠጥ ሀገራዊ ጥሪ አለብን! እስከመቼ ባለንበት እንረግጣለን?

ራሱን “የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር” ብሎ የሰየመው ፀረ-ኢትዮጵያ መንግሥት (ፀረ-ኢትዮጵያ መንግሥት)፤ ሀገራችንን ዕለት ከዕለት ወደ ባሰ አዘቅት እንድትገባ እየጎተታት ነው። የፖለቲካ ፍልስፍናውና የአስተዳደር መመሪያው የሀገራችንን ሕልውና በንጥልጥል ላይ እንዲቀመጥ ሌት ከቀን እየጣረ ነው። በአንፃሩ ደግሞ ለኢትዮጵያዊያንና ለኢትዮጵያ በመቆም፤ በተለያዩ ድርጅቶች ከፍተኛውን መስዋዕትነት በመክፈል፤ ከዚህ ፀረ-ኢትዮጵያ መንግሥት ጋር እየተዋደቁ ያሉ ታጋዮች አሉ። ይህ በዚህ ፀረ-ኢትዮጵያ መንግሥትና በኢትዮጵያ ሕዝብ መካከል እየተደረገ ያለው ግብግብ፤ ለረጅም ዘመን እንዳለ ሆኖ፤ ፀረ-ኢትዮጵያዊው መንግሥት የፈለገውን እያደረገ ያለበትና፤ በታጋዩ ወገን ያለው ክፍል ደግሞ ላለፉት ፳ ፫ ዓመታት ባለበት የሚረግጥበት ሁኔታ አልተለወጠም። ከጊዜ ወደ ጊዜ ይህ ፀረ-ኢትዮጵያ መንግሥት የሚጠናወተው ክፍል እየበዛ፤ በአሁኑ ሰዓት ሀገሪቱ ይኼው ፀረ-ኢትዮጵያ መንግሥት ሊቆጣጠረው በማይችልበት ቀውስ ውስጥ ልትገባ አዝምማለች።

አንዳርጋቸው ጽጌ የሕዳሴው ታጋይ

የአረቦች አሽከር የሱዳን ገረድ የሻብያ ፍጥረት የሆነው ድኩማኑ ዘረኛውና ሰውበላው የትግሬ ነጻ 
አውጪ ተብዬ የወንበዴ መንጋ ክብር የሌለው ቅጥረኛ ሞራል የሌለው ነውረኛ የበታችነት ስነልቦና 
ሕሊናቸውን የሰለበው በዚህ የሌባ ዘራፊዎችና ነብሰ ገዳዮች የሚዘወረው የወያኔ ቡድን ለግዜያዊ ጥቅምና ስልጣን የሃገርን ዳር ድንበር እንደ ሸቀጥ ሲቸረችር የኖረ ከአፍንጫቸው አርቀው ማየት የማይችሉት የዚህ ማፍያ ቡድን መሪዎች ከፀሐይ በታች ለጥቅምና ስልጣናቸው ሲሉ ማንኛውንም ነገር ላማድረግ የማይመለሱ ነውረኞች በመሆናቸው ሱሪያቸውን እንኳ ከማውለቅ ወደኋላ የማይሉ ርካሾች የማይመጥናቸውን ሕዝብና ልካቸው ያልሆነችውን ታላቅ ሃገር በታሪክ አጋጣሚ እነሆ እጃቸው ላይ ወድቃ ላለፉት 23 አመታት ሕዝባችንን እየገደሉ መሬታችንን እየሸጡ የህዝባችንን የኖረ አንድነቱን በሃውርታዊ ውህደቱን በውሸት የተለወሰ ታሪክ በመንዛት ለእርስ በእርስ መጫረስ ሲያመቻቹት ትውልዱን ሞራለ ሰባራ ስደተኛና ተስፋአልባ እንዲሆን በተቀነባበረ ዘዴ የዕምነት ተቋማትንና ነባሩን በጎ ባህል በመናድ ዋልጌና ዝርክርክ በማድረግ ለአገዛዛቸው እንዲመች ቀን ከሌት ከመድከማቸውም በላይ ፤ ይህንኑ የጥፋት ዘመቻ በማክሸፍ የህዝባችንን መብት ለማስከበር በየጊዜው የተነሱትን አያሌ ታጋዮችን የህይወት የአካልና የእስር ዋጋ እያሰከፈሉ በመሪር አገዛዝ ታጋዮችን ቢያንገላቱም አንዱ ሲወድቅ ሌላው እየተተካ ትግሉ በውስጥም በውጭም በመጠናከር ላይ ባለበት በአሁኑ ወቅት በዚህ ዘመን ከተፈጠሩት ታጋዮች በቁርጠኝነቱና በአላማ ጽናቱ ወደር የማይገኝለት ብርቱውና ጀግናው መንድማችን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በቅጥረኛ የየመን አፋኞች ከመንገድ ላይ በህገወጥ ሁኔታ ድንገት ጠልፈው የታጋዩን ወኔ ለመስለብ ትግሉን በማኮላሸት ለደጋፊዎቻቸው አይበገሬነታቸውንና ሁሉበኩሉሄ መሆናቸውን ለማሳየት በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር ለቅጥረኛ አፋኞቹ በመክፈል ደጋፊዎቻቸውን ጮቤ ሲያስረግጡ መላውን ሃገር ወዳድ ኢትዮጽያዊ ሃዘን ድንጋጤና ቁጭት ላይ እንዲወድቅ አድርገውታል። 

Monday, July 7, 2014

ሕወሓት ሪከርድ በመስበር ቄሱን በሽብር ወንጀል ከሰሰች

ሕወሓት ሪከርድ በመስበር ቄሱን በሽብር ወንጀል ከሰሰች

  • 1413
    Share
አብርሃ ደስታ ከመቀሌ እንደዘገበው፦
Abrha Desta
ቀሲስ ብርሃነ ቆባዕ (ከእግሪሓሪባ) በሽብር ተጠርጥረው (ከነ አደይ አልጋነሽ ጋ) ዛሬ ሰኞ ሰኔ 30, 2006 ዓም በፖሊስ ታሰሩ። ቀሲስ ብርሃነ እያረሱ እያሉ ነው በአራት ፖሊሶችና ስድስት ምልሻዎች ተከበው ከእርሻ ማሳ ታስረው ፖሊስ ጣብያ የገቡ። የነ ቀሺ ብርሃነ ጉዳይ ሽብር የሚል ነው። ህወሓት የኦርቶዶክስ ሀይማኖት አባት በሽብር በመክሰስ ሪከርድ ሰብራለች። ወይስ ቀስን በሽብር የከሰሰች ሌላ ሀገር አለች?
ጉድ ብዪ ሀገሬ ቄሱም፣ ሐጂውም፣ ኡስታዙም አሸባሪ ነው።

Ethiopia: Fears for Safety of Returned Opposition Leader

Yemen Unlawfully Deported Andargachew Tsige, Concerns over Possible Mistreatment
JULY 7, 2014
HRW.svg(London) – An exiled Ethiopian opposition leader unlawfully deported by Yemen back to Ethiopia is at risk of mistreatment including torture. Andargachew Tsige is secretary-general of Ginbot 7, a banned Ethiopian opposition organization, and was convicted and sentenced to death in absentia in separate trials in Ethiopia in 2009 and 2012.

The current whereabouts of Andargachew, a British national, is unknown, raising concerns for his safety. The Ethiopian government should take all necessary steps to ensure Andargachew’s safety and his right to a fair trial. Many individuals arrested in politically related cases in Ethiopia are detained in Addis Ababa’s Maekelawi prison. In an October 2013 report, Human Rights Watch documented the use of torture by authorities against detainees in Maekelawi, including members of opposition political parties and organizations, as well as journalists.

ከግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የተሰጠ ልዩ መግለጫና ተግባሪዊ የመጀመሪያ እርከን የትግል ጥሪ

ሁላችንም አንዳርጋቸው ጽጌዎች ነን!!!
ሰኔ 29 ቀን 2006 ዓም
Ginbot_7_Logo_Lበየጊዜው እየከረረና እየመረረ የመጣው ትግላችን “ሁላችንአንዳርጋቸው ጽጌዎች ነን” ወደ ተባለ አዲስ ምዕራፍ ተሸጋግሯል። ይህ ጽሁፍ የዚህን የትግል ምዕራፍ ምንነትና ይዘት በአጭሩ ያብራራል። በዚህ ጽሁፍ ላይ የሰፈሩት ዓረፍተ ነገሮች ተነበው የሚታለፉ ሳይሆን በተግባር የሚተረጎሙ ሥራዎች ናቸው።
አንዳርጋቸው ጽጌን መሆንማለት ምን ማለት ነው? አንዳርጋቸው ጽጌ ለፍትህ፣ ለነፃነት፣ ለዲሞክራሲና ለእኩልነት በጀግንነት የቆመ፤ ትግሉ የሚጠይቀውን መስዋዕትነት ሁሉ ሲከፍል የነበረና አሁንም እየከፈለ ያለ መሪያችን ነው። አንዳርጋቸው ጽጌን መሆን ማለት ልክ እንደሱ ትሁት ሆኖም ግን ቆራጥ፤ ሆደ ሰፊ በዚያው ልክ ደግሞ መራር፤ አስተዋይና ብልህ ሆኖም ተግባር ተኮር መሆን ማለት ነው። አንዳርጋቸው ጽጌን መሆን ማለት ወያኔን ለማስወገድ መደረግ የሚገባውን እርምጃ ለመውሰድ የተዘጋጀ ሰው መሆን ማለት ነው። አንዳርጋቸው ጽጌን መሆን ማለት ለአገርና ለትውልድ ቤዛ መሆን ማለት ነው።

የካምብሪጅ ጠበቆች ቡድን ከእንግሊዝ ውጪ ጉዳይ ባለስልጣናት ጋር ነገ በአንዳርጋቸው ዙሪያ ይሰበሰባል። እንግሊዝ ከፍተኛ የሚኒስቴሮች ቡድን ከማስጠንቀቂያ ጋርወደ አዲስ አበባ ትልካለች ።

 አንድአርጋቸው ቴዲ አፍሮ ወይንም ብርቱካን ሚደቅሳ አይደለም !!!

573C78C ወያኔዎች አንዳርጋቸውን አስረው የፖለቲክ ትርፍ የሚያገኙ መስሏቸዋል። አንዳርጋቸው ሳይታሰር ከሚፈጥረው ተጽእኖ ይልቅ ታስሮ የሚፈጥረው ተጽእኖ ቀላል አይደለም ፡ በውጪ ከሚታገለው ኤጥፍ በላይ በወህኒ በሚከፍለው መስዋትነት በወያኔ ላይ ትልቅ ተጽእኖ ይፈጥራል። አንዳርጋቸውን በማሰራቸው የሚጸጸቱበት ቀን ሩቅ አይደለም ። ወያኔ ዝም ያለው የህዝብ ቁጣ በመፍርት ስኢሆን በሚስጥር የተብተኑ ደህንነቶች የሕዝቡን ትኩሳት እየለኩ መሆኑን ታውቅውል፤ ሃይለማርያም ደሳለንም ሆነ ሌሎች የወያኔ ባለስልጣናት የ አንዳርጋቸውን መታፈን የሰሙት ከግንቦት ስባት መግለጫ መሆኑ ተረጋግጧል። የወያኔ ድህረ ገጾች ላለፍት2 ሳምንታት ዝምታን መርጠዋል፡ ይህ የሚያመለክተው ወይኒ በራስ መተምመኑን ምን ያህል እንዳጣ ነው፡ ይህ ማለት ፕሮፌሰር አስራትን የያዙበት ግዜ አይነት አይደለም ዘመኑ አሁን የበሰለ ነው ሲሉ መረጃውን ያመጡት ተናግረዋል።

አዋጅ አዋጅ !!!………..ልብ ያለዉ ልብ ይበል ጆሮ ያለዉ ይስማ !! የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል

ዋጅ አዋጅ !!!
ልብ ያለህ ልብ በል ጆሮ ያለህ ስማ !!
G7የግንቦት7 ህዝባዊ ሃይል የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን በየመን መታገት አስመልክቶ አጭር መግለጫ ማውጣቱ ይታወቃል::በመግለጫችን የመን ታጋዩን ልታግት የምትችልበት የጸጉር ስንጣቂ የምታክል ምክንያት እንደሌላት ሊኖራትም እንደማይችል ስለሆነም ታጋዩ ባስቸኳይ እንዲለቀቅ በተደጋጋሚ ጠይቀን፣ ይህ ሳይሆን ቀርቶ የነጻነት ታጋዩ ለፋሽስቱ የወያኔ ቡድን ተላልፎ ቢሰጥ የመን የማይሰረዝ ታሪካዊ ስህተት የምትሰራ መሆኑን ህዝባዊ ሃይላችንም የበቀል እርምጃዎችን እንደሚወስድ አሳውቀን ወያኔም ምናልባት ትግሉን አስቆማለሁ በሚል የሞኝ ስሌት ያደረገው ከሆነ ድርጊቱ ትግሉን በዕልህ እና በበቀል አጅቦ ከመውሰድ እና ከማፋጠን የዘለለ ትልቁ የሃሳብ አባት አንዳርጋቸው በሃገሪቱ ሰማይ ላይ የለቀቀውን የኢትዮጵያዊነት ጸረ ወያኔ መንፈስ አስሮ አሰቃይቶ፣ገሎ ማስቆም እንደማይችል አሳስበን አስገንዝበን ነበር:: መግለጫችን የተጻፈበት ቀለም ሳይደርቅ ግን የየመን መንግስት እንደሰጋነው ትልቁን የቁርጥ ቀን ልጅ ለወያኔ አሳልፎ መስጠቱን አውቀናል::