Monday, July 14, 2014

ሰሞኑን ያካሄድኩት መጠነኛ ጥናት፤ የኢትዮዽያ ህዝብ በሁለት ይከፈላል ይላል - “አሸባሪ” የሆነና አሸባሪ ያልሆነ ተብሎ፡፡

የሀገሬ ጉዳይ ያገባኛል ፣ የሀገሬ የወደፊት እጣ ፋንታ ያሳስበኛል ፣ መንግስት በደመነፍስ የሚያስረውን ፣ የሚገርፈውን ፣ የሚገለውን እቃወማለው የምትል ከሆነ፤ አትጠራጠር አንተ “አሸባሪ” ነህ - ለሀገርና ለህዝብ የምታሰጋ፡፡ 
“አሸባሪ” የሚል ማዕረግ ተጎናፅፈህም በሰላም የምትቀመጥ እንዳይመስልህ፡፡ እንደ አንዳርጋቸው ፅጌ ፣ እንደ አብርሃ ደስታ ፣ እንደ ዞን ዘጠኞች ፣ እንደ እስክንድር ነጋ ፣ እንደ ርዮት አለሙ በተለጠፈብህ የአሸባሪ ታፔላ ወህኒ ትወርዳለህ - የሀገሬ ጉዳይ ይመለከተኛል ስላልክ ብቻ፡፡

ከሀገሬ ጉዳይ ይልቅ የሆዴ ነገር ያሳስበኛል የምትል ከሆነ ፣ ህሊናህን አንባገነኖች በሚወረውሩት ፍርፋሪ የለወጥክ ከሆነ ፣ ሙስናን የሚጠየፍ ልብ ከሌለህ ፣ በቴሌቭዥን መስኮት “ነጭ ውሸት” ዋሽትክ በሰላም የምትተኛ ከሆነ፤ እውነቱን ልንገርህ አንተ ከአሸባሪ ደም ነፅተሀል፡፡ ለዚ አኩሪ ተግባርህም.. የገንዘብ ፣ የማዕረግ ፣ ነፃ የትምህርት እድሎች የመሳሰሉትን ትጎናፀፋለህ፡፡ አልፎም ተርፎም “የክብር ዶክትሬት” ሊሰጥህ ይችላል - አንተ ብቻ 'አሸባሪ' ላለመባል ህሊናህን ሽጥ እንጂ!!

No comments:

Post a Comment