Sunday, July 20, 2014

ለአዲስቱ ኢትዮጵያ! የጋራ እንቅስቃሴና!

ለአዲስቱ ኢትዮጵያ የጋራ እንቅስቃሲ የሃገራችንን የተወሳሰበ ችግር በጋራ ሁላችንም ተንቀሳቅስን መፍትሂ ልንፈጥርበት የሚያስችለን መንገድ ይመስላል ይህንንም ለማለት ያበረታታኝ በተለያየ ግዜ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ እንቅስቃሴ ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ በጽሁፍ ስለድርጅታቸው አላማና እንቅስቃሴ የሚሰጡትን መረጃ መሰረት በማድረግና የኢትዮጵያ ህዝብ ለጋራ ጥቅሙ አንድነት፤ ከመቼም ግዜ በላይ ማበር፤ እንድለበት አበክረው በተደጋጋሚ የሚሰጡትን መገልጫ መሰረት በማድረግ ነው።

በበርካታ የብሄረሰብ ጥርቅም ሐገር ውስጥ፤ በብዙ ሚልዮን ህዝብ መሪት ላይ፤ የተመሰቃቀለ የፖለቲካ ስርአት ከነገሰ፤ ድህነት ድንቁርናና በሽታ የበላይ ይሆናሉ።


ድህነት በሽታና ድንቁርና የአንድን ሃገር ህዝብ በጠቅላላው የመንግስት ጥግኛ በማድረግ ከእለት ለእልት ኑሮው በላይ እንዳያስብና፤ ለመብቱ እንዳይቆረቆር፤ የሞተ ተስፋ ባለቤት አድርገው፤ የአቅሙን ልክ በማሳነስ፤ ከሞቱት በላይ ካሉት ሁሉ ደግሞ በታች እንደሆነ አርጎ እንዲያስብና የዝቅተኛ መንፈስ እስረኛ እንዲሆን ያደረጉታል።

በተለይ ድህነት ድንቁናና በሽታ የፈጠሩትን ችግር ፖለቲካ ብቻውን በፍጹም ሊፈታው አይችልም ምክንያቱም እንደዚህ ያለው ችግር ሊፈታ የሚችለው በአጠቃላይ የሃገሪቱ ዚጎች ተረባርበው ሁሉም በጋራ በየችሎታቸው በሚያደርጉት እንቅስቃሴ እንጂ የፖለቲካ እምነት በመቀያየር ወይንም የተቃዋሚ ፓርቲዎችን የይስሙላ ህብረት በመፍጠር አይደለም።

ይህም ማለት ፖለቲካ ፓርቲና ፖለቲከኛ የተለየ ፍልስፍናና የተለየ እምነተን መሰረት አድርገው ሃሳባቸውን የሚጋራ የህዝብ ክፍል በመፍጠር ህዝብን የመከፋፈል ባህሪ ስላላቸው፤ የፖለቲካ ፓርቲና ፖለቲካኞች ሀዝብን አንድ ያደርጋሉ ማለት ዘበት ነው፤ በፓርቲዎችም ህብረት የህዝብ አንድነት ይመጣል ማልት ከእባብ እንቁላል እርግብ እንደመጠበቅ ነው።

ስለዚህም ህዝብ የጋራ ጠላቱ ላይ በጋራ ካልዘመተ ጥቅሙን ለፖለቲካ ቁማር ጨዋታ አሳልፎ በመስጠት ለድህነትና ድንቁርና እንዲሁም ለበሽታ ይንበረከካል።

በሌላ በኩል ግን ህዝብ በጋራ ጥቅሙ አንድ ሲሆን ማንኛውም ፓርቲ ከሀገሪቱ ህዝብ የጋራ ጥቅም ውጪ ውልፍች ሊሉ አይችሉም። ምንም እንዃን ፓርቲዎች እንደአሸን ቢፈሉ የጋራ ጥቅሙን ከሚያስጠብቅ ህዝብ ፍላጎት ውጪ ከቶውንም ለማፈንገጥ አይሞክሩም፤ ከሞከሩም በቀላሉ ከጨዋታው ውጪ ይሆናሉ።

በጋራ የህዝብ እንቅስቃሴ የጋራ ጥቅምን በማስከበር የደሀውንም ሆነ የሀብታሙን፤ የተማረውንና ያልተማረውንም፤ የተለያዩ ብሄረሰቦችንና የተለያዩ ፖለቲካ ፓርቲዎች፤ ጠላት የሆኑትን ድህነት በሽታና ድንቁርናን በማሸነፍ ከተመሰቃቀለ የፖለቲካ ስርአት መውጣት ይቻላል።

ለዚህም መንገዱ ለፓርቲዎች አንድነት ስኬት አልባ ለሆነ ህብረት ግዜን በማባከንና ስሜትን በመጉዳት ሳይሆን ለጋራ ጥቅማችን አጋር በመሆን

ከአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ እንቅስቃሲ ጋር የህዝብ አንድነት መፍጠር አንዱ አማራጭ ሊሆን ይችላል።

ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ እንቅስቃሴም፤

የኢትዮጵያ ህዝብ በአንድነት ለጋራ ጥቅሙ የሚያደርገው እንቅስቃሴ ከሆነ፤ ይህም እንቅስቃሴ ግለሰብን ከጎሳና ከፓርቲ በመነጠል ሰው መሆን ብቻውን በቂና ከቡር መሆኑን በማስተማር በጋራ ለውጥ ሊያመጣ የሚችል ብቸኛ አማራጭ ሊሆን ይችላል የሚል እምነት አለኝ።

በአሁን ባለንበት ተጨባጭ ሁኔታ የኢትዮጵያኖች ሁሉ የጋራ ጥቅም ብለን ሳያከራክሩን የምንስማማባቸዉ ጉዳዮች እጅግ በጣም ብዙ ቢሆኑም ጥቂቶቹን ብንመለከት፤

ህብረት በጋራ ጥንካሪያችን ላይ፤ ትብብር የጋራ ችግራችንን ለማስወገድ፤ አንድነት በማህበራዊ ኑሮ መሰረታችን ህልውና ላይ፤ ርብርብ በሀገር የጋራ ጥቅም ላይ፤ ሁለተናዊ ተስፋ በመጭው ትውልድ ህይወት ላይ፤ በአጠቃላይ ለሰላም፤ ለብልጽግና፤ ለሰባዊ መብት መከበርና ለዲሞክራሲያዊ ስራት መፈጠር የጋራ የህዝብ እንቅስቃሴ እሁንም ወሳኝ ነው።

ለአዲሲቱ ኢትዮጵያ!

የጋራ እንቅስቃሴ! የፖለቲካ ፓርቲ ካልሆነ። በሀገሪቱ ውስጥና ውጭ ያሉትን ፖለቲካ ፓርቲዎች፤ እንዲሁም የግለሰቦችና፤ ብሄረሰቦች፤ መበት እያከበረ ነገር ግን ካጎሳና ከፖለቲካ እምነት በላይ የሁላችንንም ጉልብት የሚጠይቁትን የጋራ ጥቅሞቻችን ላይ በማተኮር የጋራ ሀላፌነት በመውሰድ እያንድ አንዳችን የየግል ድርሻችንን አስተዋጻ በማድረግ ለውጥ የምናይበት የጋራ እንቅስቃሴ መሆን ይችላል።

ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ ድህነት በሽታና ድንቁርና የፈጠረው የተመሰቃቀለ የፖለቲካ ስርአት የሰብአዊ መብት እንዲረገጥ፤ ዲሞክራሲ ትርጉም እንዲያጣ፤ ከፍተኛውን አስተዋጻኦ ማድረጋቸው እየታወቀ ነገር ግን እነኝህን ቀንደኛ የኢትዮጵያ ህዝብ ጠላት የሆኑትን ለማሸነፍ ሀላፌነቱን ለአለም አቀፍ ማህበረሰብ (ለባእድ) አሳልፈን ሰጥተናቸዋል።

በእነኝህ እጅግ በጣም ስር በሰደዱ ችግሮቻችን ላይ ህብረት መፍጠር የሚያስገኘው ውጤት ለአንዴና ለመጨረሻ በመንግስቱ ላይ ሙሉ ስልጣን ያለው ህዝብ ያዘጋጃል፤ ለጋራ ጥቅሙ ያልቆመን መንግስት የማይቀበል ህዝብ ይፈጥራል፤ በሰብአዊ መብት ረገድም የአንድ ግለሰብ መብት መረገጥን የሁሉም ሰው መብት መረገጥ መሆኑን የሚያምን ማህበረሰብ አካል ሊሆን ይችላል።

ለአዲሲቱ ኢትዮጵያ የጋራ እንቅስቃሴ

አላማውም ግቡም ሁላችንንም ብሚያስማሙን ጉዳዮች ላይ የጋራ አንድነት በመፍጠር ለመፍትሄ ከታች ወደላይ የሚጓዝ የህዝብ እንቅስቃሴ ከሆነ።

የህዝብ አንድነት በመፍጠር ጦርነትን ማስወገድ! የሰብአዊ መብተን ማስከበርና፤ የግለሰብ ነጽነትን ማረጋገጥ! ድንቁርናን በማሸነፍ ረሀብን ማጥፋትና በሽታን በማሸነፍ ለሁሉም እኩል የሆነች አዲሲቷን ኢትዮጵያ መፍጠር ይቻላል!!

እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይታደጋታል

No comments:

Post a Comment